EBSTV NEWS


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


Welcome to EBS TV NEWS Telegram! We have daily news brief, interesting videos and breaking news updates, Sport. Don’t forget to share it with your friends.
https://t.me/ebstvworldwide
Inbox - @EbswhatsnewBot

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


በአንድ ጊዜ እስከ 10ሺህ ሰዎችን እንደሚያስተናግድ የተነገረለት የአዲስ አበባ ኮንቬንሽ ማእከል በትላንትናው እለት ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ በተገኙበት በደማቅ ስነስርአት ተመርቆ ተከፍቷል።

ይህ 40 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈና 10 የህንፃ ብሎኮችን የያዘ ማእከል ከህንፃዎቹ ውጪ ባለው ቦታ እስከ 50 ሺህ ሰው መስሰብ የሚችል የኤግዚቢሽን ቦታንም ጭምር መያዙ ነው የተነገረው።

ይህን ግዙፍ ማእከል ባማረ መልኩ ጨረስነው እንጂ እኛ አልጀመርነውም ሲሉ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ከረጅም አመታት በኋላ ትኩረት አግኝቶ  እንዲጠናቀቅ የተደረገው ወዳልጠቀሱት አንድ አገር  ተጉዘው ተመሳሳይ ማእከልን ከጎበኙ በኋላ መሆኑን ጠቅሰዋል።

8 መካከለኛና 2 ትልልቅ የስብሰባ አዳራሾችን ይዟል የተባለው ማዕከሉ ባለ 5 ኮከብ ዘመናዊ ሆቴልን ጨምሮ 2 የገበያ ማእከላትና አንፊ ቴአትር እንዲሁም የውሀ ፓርክን ያካተተ ነው ተብሏል።

በአንድ ጊዜ እስከ 2ሺ ተሽከርካሪዎችን የማስተናገድ አቅም እንዳለው የተነገረለት ይህ ማዕከል በቀጥታ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር የሚያገናኘው የመንገድ መሰረተ ልማት እየተዘረጋለት መሆኑም ተጠቁሟል።

በዚሁ ጊዜም  የዚህ ማእከል 96 በመቶ ድርሸ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባለቤትነት ስር እንደሆነ የተጠቆመ ሲሆን ቀሪው 4 በመቶ በፌዴራል መንግስት የልማት ድርጅቶች ና በግሉ ዘርፍ የተያዘ መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል።

ዘገባው የአቤል አበበ ነው።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


በወንዶቹ  ታደሰ ታከለ 2:03.23 በሆነ ጊዜ ቀዳሚ ሆኖ ሲገባ ደሬሳ ገለታ 2:03.51  በሆነ ሰዓት ኬንያዊውን ቪንሰንት ኪፕኬሞይን 2:04.00 በማስከተል በሁለተኛነት አጠናቅቋል። ሌላኛው ኢትዮጵያዊ ሙሉጌታ ኡማ በ2:05.46 በአምስተኛነት ጨርሷል።

በሴቶቹ  ለአሸናፊነቱ ቅድሚያ ግምት አግኝታ የነበረችው ሱቱሜ አሰፋ እንደተጠበቀችው አሸንፋለች  ርቀቱን ለመጨረስ የፈጀባት ጊዜም 2:16.31 ነው። ኬንያዊቷ ዊንፍሪዳህ ሞራ (2:16.56) እና ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት ሀዊ ፈይሳ (2:17.00) ደግሞ ተከትለዋት ገብተዋል። ጎይቶቶም ገ/ስላሴ (2:20.25) እና ደጊቱ አዝመራው (2:20.26) 7ኛ እና 8ኛ ሆነው ጨርሰዋል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


አድዋ የጥቁር ህዝቦች ኩራት!

እንኳን ለ129ኛው የጥቁር ህዝቦች ድል ለሆነው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረችሁ!

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


የቀድሞ የማንችስተር ዩናይትድ የፊት መስመር ተጫዋች ማርከስ ራሽፎርድ የአስቶንቪላ ቆይታ ቋሚ እንዲሆን ታቅዷል፡፡

እንግሊዛዊው አጥቂ ከተቀዛቀዘ የማንችስተር ዩናይትድ ቆይታ በኋላ ባሳለፍነው ጥር በውሰት ውል ወደቪላዎቹ ቤት ማቅናቱ አይዘነጋም፡፡

አሁን ላይ ታድያ የቀድሞ ክለቡ እና ረሽፎርድ የውል ስምምነቱን ወደቋሚነት በመቀየር ዙሪያ ነገሮችን እያጤኑ መሆኑን ዘገባዎች አመላክተዋል፡፡

በዩናይትድ ዘንድ የክንፍ ተጫዋቹ በክረምት ሊመለስ ይችላል የሚል እምነት የነበረ ቢሆንም የረሽፎርድ ፍላጎት በኡናይ ኤምሪ ስር ቆይታውን መቀጠል መሆኑን ተከትሎ በሁለቱም ወገኖች በኩል ተመሳሳይ አቋም ተይዟል ተብሏል፡፡

ተጫዋቹ ከጋደኞቹ ጋር በነበረው ምክክር በቪላ ቤት የቀደመ ሂደቱን ለማግኘት እና ዳግም የሀገሩን መለያ ማጥለቅ እንደሚችል እምነት ማሳደሩን እንደነገራቸውም ለማወቅ ተችሏል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


ለ129ኛው የዓድዋ ድል በዓል እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት !

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ የካቲት 23 ቀን 2017  የሚከበረውን የ129ኛው የዐድዋ ድል በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ  ብለዋል !!

በዚህ  መልዕክትታቸውም

👉 የዐድዋ ጦርነት ለሰላምና ለጦርነት በሚዋጉ ኃይሎች መካከል የተደረገ ጦርነት መሆኑንና  የዐድዋ ድል ለሰው ልጅ ሉላዊ ዕሴቶች ያለንን ዋጋ ያሳየንበት ነው በማለት ገልፀዋል።

👉 በምርኮኛ አያያዛችን፣ ከተዋጉን ጋር መልሰን ለሰላማዊ ውይይት በመቀመጣችን፣ ለዘላቂ ሰላም በመሥራታችን፣
እናቶቻችንንና አባቶቻችንን በድል አድራጊነታቸው ብቻ ሳይሆን ለሰው ልጅ ዕሴቶች በከፈሉት ዋጋ እናመሰግናቸዋለን በማለትም ምስጋናቸውን አድርሰዋል።

የመልዕክታቸው ሙሉ ቃል እነሆ✍️


አድዋ የጥቁር ህዝቦች ኩራት!

እንኳን ለ129ኛው የጥቁር ህዝቦች ድል ለሆነው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረችሁ!

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል እራሱን ለማጠናከር ሲል በመጪው ክረምት  ተጫዋቾቹን ሊሸጥ እንደሚችል ተነግሯል፡፡

የሊጉ ተፎካካሪ በስብስቡ መሳሳትና መሰል ምክንያቶች የተነሳ በሊጉ የሚጠበቀውን ያህል በበቂ ሁኔታ ለዋንጫ እየተፎካከረ አይገኝም፡፡

አሰልጣኝ ማይክል አርቴታም በተለይም የቡድኑን የፊት መስመር ችግር ለመቅረፍ ሲል በመጪው ክረምት ወሳኝ ዝውውሮችን ለማድረግ ማቀዱ ተነግሯል፡፡

ከዛ ጋር ተያይዞም    ሊአንድሮ ትሮሳርድን አሊያም ደግሞ ጋብሬል ማርቲኔሊኒን አይነት ኮከቦቹን በክረምት የዝውውር መስኮት ለሽያጭ ለማቅረብ ሊገደድ እንደሚችል ተሰምቷል፡፡

ለቡድን ግንባታ በሚል ለገበያ የሚወጡት ተጫዋቾች መዳረሻቸው የሳውዲ አረቢያ ሊግ ሊሆን እንደሚችል ግምት ተቀምጧል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


🏃20ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር በትግራይ ክልል በዓድዋ ከተማ ዛሬ ረፋድ በድምቀት ተካሂዷል ።

በኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር ኢትዮ ኤሌክትሪክ በቀዳሚነት ሲያጠናቅቅ ሸገር ከተማ በሁለተኝነት እንዲሁም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል።

በውድድሩም አትሌት ያለምዘርፍ የኃላው ከኢትዮ ኤሌክትሪክ በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ፤  አትሌት እጅጋየሁ ታዬ ከሸገር ከተማ  ሁለተኛ፣ እንዲሁም አትሌት አሳየች አይቸው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሶስተኛ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል ።

በውድድሩ አሸናፊ ለሆኑ የቡድን አትሌቶች የሜዳልያና የገንዘብ ሽልማት የተበረከት ሲሆን፤ በቡድን አሸናፊ ለሆኑ ክለቦች ደግሞ የዋንጫ ሽልማት ተበርክቷል።


በ20ኛው የኢትዮጵያ ማራቶን ሪሌ ውድድር በአለም አትሌቲክስ ደረጃ ኮርስ የወሰዱ 60 ዳኞች ውድድሩን መርተዋል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews










የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህክምና ሳይንስ ትምህርት ቤት ለ52ኛ ጊዜ ያሠለጠናቸውን የህክምና ተማሪዎች አስመርቋል።

ዛሬ የተመረቁት ሃኪሞች  118  ወንዶችና 69 ሴቶች ሲሆኑ በአጠቃላይ 197 የህክምና ዶክተሮች ተመርቀዋል።

በዚሁ የምርቃ መርሃ ግብር ላይ የትምህርት ሚኒስቴርና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቻንስለር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንዲሁም የጤና ሚኒስቴር       
ዶ/ር መቅደስ ዳባና የአዲስ ዩኒቨርሲቲ ተባባቂ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌና የክብር እንግዶች ተገኝተዋል።

የክብር እንጋዳው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ተመራቂ ሀኪሞች  የሀገሪቱን የጤና ስርዓትና  የኢኮኖሚ ደረጃ ለማሻሻል በሀገር ውስጥ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።

በተመሳሳይ  የጤና ሚኒስቴሯ ደክተር መቅደስ ዳባ ተመራቂ ሃኪሞች በታማኝነትና በርህራሄ   ሕብረተሰቡን  ዝቅ ብለው እንዲያገለግሉ ጥሪ አቅርበዋል።

መረጃው የፍስሐ ደሳለኝ ነው

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከዩክሬኑ አቻቸው ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ጋር በትላንትናው እለት በነጩ ኦቫል ኦፊስ ዘለፋ ጭምር የተቀላቀለበት በኃይለ ቃል የተሞላ ውይይት  አድርገዋል።

ቢቢሲን ጨምሮ አለምአቀፍ ሚዲያዎች በቀጥታ ስርጭት እያስተላለፉት በነበረው የሁለቱ ፕሬዝዳንቶች ንግግር ዮክሬን በአሜሪካ ዘንድ የነበራትን የእናንትና ልጅ ቅርርብ የፈነገለው ይመስላል።

ትራምፕና ምክትላቸው ጄዲ ቫንስ ዜሌንስኪን "አክብሮት የጎደለው ፣ አሜሪካን ያላከበረ'' ሲሉ ሀይለ ቃል በተሞላበት ቁጣ የተናገሯቸው ሲሆን  "በሦስተኛው የዓለም ጦርነት ቁማር እየተጫወትክ። ነው" ሲሉ እጃቸውን እያወራጩ ወርፈዋቸዋል።

ሁነቱ  ሰርግና ምላሽ የሆነላት ሩሲያ የዮክሬኑን መሪ  እያብጠለጠለችው ትገኛለች። የሩሲያ የቀድሞ ፕሬዝዳንትና የሩሲያ የፀጥታ ምክር ቤት ምክትል ኃላፊ ዲሜትሪ ሜድቬድቭ፤ ክስተቱን “ተሳዳቢው አሳማ በኦቫል ቢሮ ውስጥ ትክክለኛውን ጥፊ ተቀበለ” ሲሉ ተሳልቀውባቸዋል።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ በበኩሏ፤ “ፕሬዝዳንት ትራምፕና ምክትላቸው ቫንስ ዘሌንስኪን ከመምታት መቆጠባቸው ተአምር ነበር” ብለዋል።

ዜለንስኪ የሰለም ስምምነት ለመፈረም ዋስትና ያስፈልገናል ቢሉም፤ ትራምፕ "ለመደራደሪያ የሚሆን አቅም እና ሥልጣን የለህም" በማለት አቋርጠዋቸው ያለህ አማራጭ ስምምነቱን መፈረም ነው ካልሆነ አሜሪካ ከዚህ ትወጣለች” ሲሉም ተናግረዋል።

ይህንም ተከትሎ ፕሬዚዳንት ዜለንስኪ ዋይት ሀውስን ጥለው የወጡ ሲሆን ሁለቱ መሪዎች ሊያደርጉት የነበረው ጋዜጣዊ መግለጫም ተሰርዟል፡፡

ሁለቱ ፕሬዝዳንቶች በጋዜጠኞች ፊት ያደረጉት ኃይለ ቃል የተሞላበት ንግግር የአለምን ትኩረት ስቦ አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል።

#EBS
#EBSTVNEWS


የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የወልቂጤ ከተማ እግር ኳስ ክለብ ክሊፍተን ሜይሶ አይሲ የተባለ ተጫዋችን በተመለከተ የተላለፈበትን ውሳኔ ተፈጻሚ ባለማድረጉ ቅጣት አስተላልፎበታል።

ክለቡ ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርግ በተደጋጋሚ ቢገለፅም ተግባራዊ አለማድረጉን ተከትሎ የፊፋ የህግ ፖርታል የነጥብ ቅነሳ እንዲደረግበት ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ትዕዛዝ አስተላለፏል።

በዚህም መሰረት ወልቂጤ ከተማ እየተወዳደረበት በሚገኘው የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ከሰበሰበው ነጥብ ላይ የስድስት (6) ነጥብ ቅነሳ ውሳኔ ተላልፎበታል።

በያዝነው አመት ከፋይናንስ ደንብ ጥሰት ጋር በተያያዝ ከፕሪሚየር ሊግ ወደ ከፍተኛ ሊግ ውድድር የወረደው ክለቡም ሁለተኛ ቅጣቱን በያዝነው አመት ለማስተናገድ ተገዷል።

በከፍተኛ ሊጉ በምድብ ሀ እየተወዳደረ የሚገኘው ወልቂጤ ከተማ በሊጉ በ15 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ነበር።

የነጥብ ቅነሳውን ተከትሎም ክትፎዎቹ አሁን ላይ በውድድሩ 9 ነጥብ ይዘው 11ኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገደዋል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


ዛሬ የካቲት 22 የሚደረጉ ጨዋታዎች

⚽በእንግሊዝ ኤፍኤ ካፕ
09:15  ክርስቲያል ፓላስ ከ ሚልዋል
09:15 ፕሬስተን ከ በርንሌይ
12:00 በርንማውዝ ከ ወልቭስ
02:45 ማንችስተር ሲቲ ከ ፕሌይማውዝ 

⚽በስፓኒሽ  ላሊጋ
10:00  ጅሮና ከ ሴልታ ቪጎ
12:15  ራዮ ቫልካኖ ከ ሴቪያ
02:30  ሪያል ቤቲስ ከ ሪያል ማድሪድ
05:00 አትሌቲኮ ማድሪድ ከ አትሌቲክ ቢልባዎ

⚽በጣሊያን ሴሪ ኣ
11:00 አታላንታ ከ ቬንዚያ
02:00 ናፖሊ ከ ኢንተር
04:45 ዩድንዜ ከ ፓርማ

⚽በጀርመን ቡንደስሊጋ
11:30 ቦቸም ከ ሆፈናየም
11:30 ሀይደናየም ከ ሞንቼግላድባህ
11:30  አርቢ ሌፕዝንግ ከ ሜንዝ
11:30  ሴንት ፓውሊ ከ ዶርትሙንድ
11:30 ወርደር ብሬመን ከ ወልቭስበርግ
04:30 ፍራንክፈርት ከ ባየር ሌቨርኩሰን

⚽በፈረንሳይ ሊግ ኣ
01:00  ሴንት ኢቴን ከ ኒስ
03:00 ሌንስ ከ ሌ ሃቬር
05:05 ፒኤስጂ ከ ሊል

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


በየሁለት ዓመቱ ፈተና ወስደው እንዲመረጡ ባስቀመጠው መመርያ መሰረት ምዝገባ ላከናወኑ ኮሚሽነሮች የፅሑፍ፣ የቴክኖሎጂ እና ቃለ መጠይቅን ያካተተ ፈተና በዛሬው ዕለት  ተሰጥቷል።

በአጠቃላይ 7 ኮሚሽነሮች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን በወንዶች ሁለት በሴቶች ሁለት በድምሩ አራት ኮሚሽነሮች ማለፍ ችለዋል።

በዚህም በወንዶች  ልዑልሰገድ በጋሻው እና  ሰሎሞን ገብረሥላሴ ፈተናውን ሲያልፉ በሴቶች  ጌራወርቅ ከተማ እና  ተስፋነሽ ወረታ በተመሳሳይ አመርቂ ውጤት አምጥተው ተመርጠዋል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


የኢትዮጵያ  እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሊግ ካምፓኒውን ውሳኔ አገደ

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አክስዮን ማህበር ያሳለፈውን ውሳኔ ማገዱን ይፋ አድርጓል።

አራት ክለቦች እና ሰባት ተጨዋቾች የይግባኝ አቤቱታ ማስገባታቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ውሳኔውን በይደር እንዲቆይ ውሳኔ አሳልፏል።

ፌዴሬሽኑ የቅጣት ውሳኔውን እና የቀረበውን አቤቱታ መርምሮ ውሳኔ ለማሳለፍ ጊዜ በማስፈለጉ ምክንያትም

የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አክስዮን ማህበር ያሳለፈው ውሳኔ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ መርምሮ ተገቢውን ውሳኔ እስኪሰጥ ሳይፈፀም ታግዶ እንዲቆይ ትህዛዝ ተሰጥቷል።

ከዚህ በተጨማሪም አክስዮን ማህበሩ ተጨዋቾች እና ክለቦችን ለመቅጣት ያስቻለውን ሰነድ ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፅህፈት ቤት በአምስት ቀናት ውስጥ እንዲያቀርብ ታዟል።

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews


129ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል በመጭው እሁድ የካቲት 23 ፒያሳ አካባቢ በሚገኘው የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ይከበራል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

🚦🚥በቸርችል ጎዳና በቴዎድሮስ አደባባይ ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ባንኮ ዲሮማ መብራት

🚦🚥ከአራት ኪሎ በራስ መኮንን ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ራስ መኮንን ድልድይ

🚦🚥ከመነን አካባቢ እና የካቲት 12 ሆስፒታል በአፍንጮ በር ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ አፍንጮ በር

🚦🚥ከእሪ በከንቱ በኤሌክትሪክ ህንፃ ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ደጎል አደባባይ

🚦🚥ከአዲሱ ገበያ በሰሜን ሆቴል ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ሰሜን መብራት

🚦🚥ከመርካቶ በአቡነ ጴጥሮስ ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ደጃዝማች ሀብተጊዮርጊስ ድልድይ

🚦🚥ከእንቁላል ፋብሪካ በቅዱስ ዮሐንስ ቤተክርስቲያን ወደ አድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ዮሐንስ መብራት የሚወስዱት መንገዶች ከየካቲት 22 ቀን 2017 ዓ/ም ከምሽቱ 6፡00 ሠዓት ጀምሮ እስከ የካቲት 23 ቀን 2017 ዓ/ም ከቀኑ 7፡00 ሠዓት ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ ስለሚሆኑ አሽከርካሪዎች ይህንን ተገንዝበው አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ እና የትራፊክ ፖሊሶች የሚጠቁሟቸውን አማራጭ አቅጣጫዎችን በመጠቀም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ፖሊስ አስታውቋል፡፡


👉ህብረተሰቡም ማንኛውም አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ በ 011-1-11-01-11 ወይም በነፃ ስልክ መስመር 991 መጠቀም የሚቻል መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews

20 last posts shown.