أبـُـــــــــو مـــَـــاحــِــــي الـــــسَــــــلَــــفــــــي الأثـــــــــري الحــبــشــي


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ለውድ የዚ ቻናል ኣባላት የተዘጋጀ👇👇
🌹የተለያዩ አጫጭር የሆኑ ዱሩሶችን📖📖
🌹አዳዲስ ዜናወችን
🌹ዳዕዋወች🔔🔔💡
🌹ኢስላማዊ ትምህርቶች
🌹እና ወርቃማ ምክሮች
↪ የተለያዩ ፋኢዳና
🌹 ፅሁፎችን pdf ያገኛሉ 🌷🌷
ሀሳብ አስተያየት ካለወዎት በቦት ሀሳብ መስጫ ላይ ይስጡን !!

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔻🔻🔻🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔻

🔗تسجيلا المعراج الإسلامية السلفية في الحبشة

🔗يسرها أن تقدم لكم هذه المادة 🎙

🔎وهي عبارة عن محاضرة🔗

🔴 ከመስጂደል አቅሷ ሪልስቴት ዴሴ


👉ከ አል ሚዕራጅ ስቲድዮ


🔴 بعنوان عن  الإستقامة على دين الله



🔴👉 በአላህ ድን ላይ ቀጥ ስለማለት


🔴 በሚል ርእስ የተዘጋጀ ሙሃደራ

🔴👉ሸዋል 07


🔴👉1⃣4⃣4⃣6⃣ሂጅሪ


👈بأستاذنا أبي حذيفة سعيد /ወረኢሉ حفظه الله تعالى


👉በ ወንድማማችን አቡ ሁዘይፋ ሠኢድ ወረኢሉ አላህ ይጠብቀው

የሰለፍዮች ልሳን የሆነውን ጦሳማዶን ይጠቀሙ
♦️https://t.me/AbuNibrase_and_Namuse

🔇https://t.me/AbuNibrase_and_Namuse

؛


🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔻🔻🔻🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔻

🔗تسجيلا المعراج الإسلامية السلفية في الحبشة

🔗يسرها أن تقدم لكم هذه المادة 🎙

🔎وهي عبارة عن محاضرة🔗

🔴 ከመስጂደል አቅሷ ሪልስቴት - ዴሴ


👉ከ አል ሚዕራጅ ስቲድዮ


🔴 بعنوان : - عن الأخوة في الله



🔴👉   ወንድማማችነትን በተመለከተ


🔴 በሚል ርእስ የተዘጋጀ ሙሃደራ

🔴👉ሸዋል 07


🔴👉1⃣4⃣4⃣6⃣ሂጅሪ


👈بأستاذنا أبي عبدالله حسن /ልጓማ حفظه الله تعالى


👉በወንዲማችን አቡ አብዲላህ ሀሰን ልጓማ አላህ ይጠብቀው



የሰለፍዮች ልሳን የሆነውን ጦሳማዶን ይጠቀሙ !!


♦️https://t.me/AbuNibrase_and_Namuse

🔇https://t.me/AbuNibrase_and_Namuse

؛


Forward from: 👌🔷 ነህው ማለት የዕውቀት ሁሉ ፋስ ነው..።
ዳዕዋ


ተጀመረ


ተጀመረ

ተጀመረ


ወንድማችን አቡ አብዲሠላም ኢድሪስ ከላላ


👌 👉 አንድ ሠው በሆነ አጋጣሚ ከመኖሪያው ስፍራ ራቅ ብሎ ሲወጣ ልጆቹ ሚስቱ ቤተሠቦች ብሎም ገንዘብ ይናፍቀዋል !!
-------------------
እኔ ደግሞ በሆነ አጋጣሚ ከወንድሞቸ ነጠል ብየ አንድ ሳምንት የማይሞላ ጊዜን ብርቅ በናፍቆት እንግብግብ የሚያደርጉኝ በመንሃጃቸው ጥንክር ብለው ችግሩንም መከራውንም ዋጥ አድርገው ጧት ማታ ስለ ድናቸው የሚጨነቁት እንቁ ሠለፍይ ወንድሞቼ ናቸው !!
------------------
👌 👉 ዛሬ ወንድሞቸን በሪል ስቴት በመስጅደል አቅሷ ሙሉት ብለው ሳያቸውና ለዳዕዋ ያላቸውን ኢቅባል ስመለከት እንባየም መጣ ደስታም ዋጥ አደረገኝ !!

በየትም ቦታ ያሉ ሠለፍዮች ንፍቅቅቅ ይሉኛል ግን የደሴዎቹ ደግኖች ደግሞ ትለያላችሁ !!!


ወንድማችሁ አቡ ማሂ ........

https://t.me/Abumahiasselefi/6592




ምክር (በሸይኽ ሳሊህ አልፈውዛን)
- (ሱንዮች) አትበታተኑ
-ጥፋት ካለ ተመካከሩ
-ራስ በራሲችሁ ህሜትን ራቁ (የወንድማችሁን ስጋ አትብሉ



አስተንትን ወዳጄ አስተዉል

https://t.me/c/2381400367/1665


=============================

👌 👈 قال عبدالله بن المبارك: "صاحب البدعة على وجهه الظلمة، وإن ادَّهن كل يوم ثلاثين مرة".
=======================≠========

💫 👉 ትርጉሟን ......... ሞክሯት ........

https://t.me/Abumahiasselefi/6587


Forward from: 👌🔷 ነህው ማለት የዕውቀት ሁሉ ፋስ ነው..።
ዳዕዋ

ተጀመረ

ተጀመረ

ተጀመረ

ኡስታዝ አቡ ሀቢባ ሸይኽ በድሩ ገብተዋል


= 🔺A 🔺=  ከፊል  ዑለሞች  ነብይ  ከተላከ በኋላ  ዑዝር  የለም  ዑዝሩ  ነብይ  እስከሚላክ ብቻ  ነበረ  ይሉና  ይህችን  አንቀፅ  ያነባሉ ....
  "" وَمَا كُنَّا مُعَذِّبِينَ حَتَّى نَبْعَثَ رَسُولًا ""
ነብይ  ደግሞ  ልኳል ።  ስለዚህ  ነብይ  በመላኩ  ብቻ   ሁሉም   ሁጃ   እንደቆመባቸው  ይቆጠራልና  ዑዝር  የለም  ይላሉ  ...።


🔺B🔺=ከፊሎቹ   ዑለሞች  ደግሞ   በመጥፎ  ዑለሞቻቸው  ሹቡሐ  የገባባቸውና  ሐቅ  የተደበቀባቸው  አጥማሚዎች  ያጠመሟቸው  በደንብ  ሊደርሳቸው  ይገባል  ።  ምንም  ካልደረሳቸው   ዑዝር  ቢል  ጀህል  አላቸው  ይላሉ   ።  ምንም  አይነት  አስተማሪ  ሳይኖረው  ሽርክ የሚሰራ  ሰው  ወይም  አድስ  ሰለምቴ  ከሆነ  ይህ  አካል  እስከሚደርሰው  ዑዝር  አለው  ይላሉ  ።  ካላወቀ  ሽርክ  ቢሰራም  ዑዝር   አለው  ይላሉ  ።  ይሔ መዝሐብ  እነ  ሸይኽ  ሙሐመድ  ኢብን  ዓብዱል  ወሐብ  የሔዱበት  ነው  ይላሉ ።  ይህቺ  አገላለፅ  ናት  ለሰው  እንደጭቃ  እያዳለጠችው  ያለችው  ይህቺ  ናት  ።  ከልብህ  ተገንዘበውማ  ....  


ልብ  በሉ  ከላይ  ዑለሞቹ  የተወዛገቡበት  ዑዝር  የቅጣቱን  ነው  እንጂ   ሽርክ  ሰሪውን  ሙስሊም  ወይም  ሙሽሪክ  ስለማለት  አይደለም ። ማሳያው   ሸይኹ  ቀጥለው  እንድህ  አሉ ።  የሁለተተኛዎቹ  ዑለሞች  ዑዝር  አለው  ማለታቸው  ሙስሊም  ነው  ማለታቸው  አይደለም  ...በዱንያማ  ሙዓመላ  የሚደረገው  እንደሙሽሪክ  ነው  አሉ  ...ስለዚህ  የዑለሞቹ  የዑዝር  ቢል  ጀህል  ውዝግብ  ስለመቀጣትና  አለመቀጣት  እንጂ  ሽርክ  የሚሰራው  ሰው  ሙስሊም  እንበለው  ሙሽሪክ  ስለሚለው  አይደለም  ።  ምክናየቱም  መጀመሪያ  ዑዝር  የለውም  ያሉት  ደምድመዋል  ጨርሰዋል  ። የሁለተኞቹ  ዑዝር  የሚሰጡት  ግን  ዑዝር  አለው  ይሉና  ዱንያ  ላይ  ግን  እንደሙሽሪክ  ሙዓመላ  ይደረጋል  ማለትም  አይሰገድበትም  አይወርስም  አይወረስም  ማለታቸው  እንደሆነ  ሸይኹ  በደንብ   አብራርተዋል  ።  ይህም  መዝሐብ  የሁለቱ  ኢማሞች  የብን  ተይሚያና  የሙሐመድ  ብን  ዓብዱል  ወሐብ  መዝሐብ  እንደሆነ  ገልፀዋል  ። 

👌አጭሩን   ሳያውቅ  ሽርክ  የሚሰራው  ሰውዬ ዑዝር  ይሰጠዋል  ማለት  ሙስሊም  ነው  ሳይሆን  ሳይደርሰው  አይቀጣም  ነው ።  ስለዚህ  የዑለሞቹ  ኺላፍ  ቅጣቱን  በተመለከተ  እንጂ  ሽርክ  ሰሪው  ሙሽሪክ  ነው  አይ  ሙስሊም  ነው  በሚለው  ነጥብ  ላይ   አይደለም  ።  ሽርክ  የሚሰራ  ሙሽሪክ  ለመባሉ  መጀመሪያ   ኺላፍ  የለም   ።  ይሔኛው  ኺላፍ  እንደደረሰው  ተቆጥሮ   ይቀጣል  አይቀጣም  ነው   ።   በቃ  ባጭሩ  ዑለሞቹ  በየትኛውም  ቦታ  ዑዝር  ይሰጠዋል  ሲሉህ ሳያውቅ  አይቀጣም  እንጅ  ሰውዬውን  ሽርክ  ቢሰራም  ሙስሊም  እንበለው  ማለታቸው  አይደለም  ። የኛም  መዝሐብ  ሁለተኞቹ  የሔዱበት  ዑዝር  ቢል_ጀህል  አለ  የሚለው  ነው  ።

👌 ይሔ  ድምፅ  የዑለሞቹ  መሠረታዊ  መነሻ  ሙህከሙና  የተረዘረ  ስለሆነ  አንብቡት  ። የዑለሞቹን  ተእሲላት  ሳይረዱ  ዑዝር  አለው  ሲሏቸው  ሮጠው  ያሰልሙልካል  ።   ሸይኹ  ከበቂ  በላይ  አብራርተውታል   ሰማይ  ከላይ  ነው  መሬት  ከታች  ነው  አይነት  ገለፃ  ገልፀውልካል  ። ለመወዛገብ  የፈለገ  መወዛገብ  መብቱ  ነው  ። ግን  በመሻይኾቻችን  ላይ  እየተለጠፋችሁ  የቅጣቱን  ዑዝር   እያመጣችሁ  አትወለካከፉብን ።


👌አረብያ  የሚገባህ  መስማት  የምትችል ድምፁን   ስማው  አዳምጥ  ... ድምፁ  የማይገባህ  ወደ ፅሁፍ  የተቀየረውን  አንብብ  ...  የሙነወር  ልጅ  አያጃጅልህ  እሱ   ጋዜጠኛ  እንጂ  የቀራ  ሰው  አይደለም  ...❗️


👌 قال شيخنا  العلامة النحرير الشيخ عبد العزيز الراجحي حفظه الله ورعاه وأطال عمره في طاعته وعبادته


السؤال:

 هل يعذر من يطوف بالقبر أو يفعل شيئا من وسائل الشرك بالجهل، أي: إذا كان جاهلا أن ما يعمله شركا، أرجو التفصيل؟

الجواب:

هذا فيه قولان للعلماء، بعد بعثة الرسول عليه الصلاة والسلام  هم أهل الفترات قبل بعثة الرسول عليه الصلاة والسلام  هؤلاء فيهم كلام لأهل العلم، أنهم يمتحنون، لكن بعد بعثة النبي -صلى الله عليه وسلم-، وبعد نزول القرآن، الله تعالى يقول:َ (وما كُنَّا مُعَذِّبِينَ حَتَّى نَبْعَثَ رَسُولًا) 
الله بعث الرسول وأنزل القرآن، فهل يعذر المشرك إذا لبس عليه كأن يطوف بالقبور ويدعوها من دون الله، ويذبح لها، لكن لبس عليه علماء الشرك فصار مغطى عليه الحق ، ولا يبصر الحق ولا يعلمه بسبب  تلبيس علماء السوء، الذين يلبسون عليه، ويحسنون له الشرك.


قال بعض العلماء: إنه يعذر في هذه الحالة، ولكن يعامل في الدنيا معاملة المشركين، لا يغسل، ولا يصلى عليه، ولا يدفن مع المسلمين في مقابرهم، وفي الآخرة أمره إلى الله، حكمه حكم أهل الفترات، وهذا هو الذي ذهب إليه الشيخ محمد بن عبد الوهاب رحمه الله قال: لا نكفر أحدا حتى تقوم عليه الحجة, و قال آخرون من أهل العلم: إنه لا يعذر أحدٌ بعد بعثة الرسول عليه الصلاة والسلام  لأن الله يقول: (وما كُنَّا مُعَذِّبِينَ حَتَّى نَبْعَثَ رَسُولًا)  وقد بعث الرسول، وأنزل القرآن، والقرآن يتلى والنصوص واضحة في بيان الشرك والتحذير منه، فلا يعذرون هما قولان لأهل العلم، ذكرهما شيخ الإسلام ابن تيمية وغيره، وعلى كل حال من يقول إنه يعذر، يقول: في الدنيا يعامل معاملة المشركين بمعنى أنه لا يغسل، ولا يصلى عليه، ولا يدفن مع المسلمين في مقابرهم، ولا يتصدق عنه، ولا يحج عنه، ولا يدعى له بالمغفرة والرحمة، أما في الآخرة فأمره إلى الله.

----------🔺     🔺--------


🔺🔺  አዳምጧት 🔺🔺


👌https://t.me/Al_menjeniq_R/332

-------
👌https://t.me/Al_menjeniq_R/332


👌 ቆይ  ማነው  ይህንን  ጋዜጠኛ  ድንገት  ቆንጥጦ  የቀሰቀሰው  በሸይኻችን  ላይ  እየተቀደደኮ  ነው  ... ሸይኹ  እንደ  ሙስጦፋ  አይደሉም  ዑዝር  ይሰጣሉ   አለና  አስቂኝ  ድምፅ  አያይዞ  ለቀቀ   ...❗️
🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻

👌 ብዙው  የዑለሞቹ  ንግግር  ጀምዒዮች ሳይረዱት  የሚያንከራትቱት  የተወዛገበና  የዑለሞቹን  መነሻና  የአገላለፅ  መርህን  ያላገናዘበ  የድንጋጤ  ሩጫ  ነው   ።   ነጥቡ  ካልገባችሁ  ረጋ  ብላችሁ  አንብቡ  የተክፊሪ  እያላችሁ  መንጋዎቻችሁን  ጅቡ  መጣልህ  ማስፈራሪያ  ከምትነግሯቸው  ሰብስባችሁ  አንብቡም  አዳምጡም  ።  ባለማንበባችሁኮ  ነው  ሜዳው  ዳገት  ሰፊው   ቅርቃር  የመሰላችሁ  ...።
-----
👌  የሚገርመው  ጋዜጠኛው  የሙነወር  ልጅ  የኔ  ወደ  ታላቁ  ሸይኽ  ዓብዱል  ዓዚዝ  አራ_ጂሒጋ  መሔዴ  አንጀቱን  ብልልልልት   አድርጎታል  ።  ፈነቀለው  አልቻለም አንገበገበው  ሸህ  ሙስጠፋ  የዓብዱል _ዓዚዝ  አል_ራጂሒ  ተማሪ  እየተባለ  ሊጭበረበር  ነውኮ  አለ  ።  ከቀራሁባቸው  ብትተረተርም  ተማሪያቸው  ነኝ  በትልልቅ  መሻይኾች  ላይ  ብዙ  አጥፊዎች  ቀርተዋል  እያልክ  ራስህን  አጥናና...❗️
---
👌 በቃ  አንተም   ያልቀራሐውን  ዓቂዳን  ያክል  ነጥብ  በግምት  ከምታቀራ  ለተወሰኑ  ወራቶች  እንኳ  ውጣና  እስኪ  በቃልቻ  ላይ  ሶርፉንም  ነህውንም  ሐድሱንም  ዓቂዳውንም  ትንሽ  ትንሽ  ሞካክር  ...።  ጦሐውያን  በግምት  ዋሲጥያን  በግምት  ኪታቡ  ተውሒድ  በግምት  ኧረ  ይደብራል  ።  ሰዎች  ህዝብ  ቆጠራ  እንኳ  ጥንቃቄ  ይፈልጋል  እንኳን  ዓቂዳ  የሚታመንበት  ...❗️

👌ደዕዋውም  ቂርአቱም  በግምት  የሆነው  የድፓርትመንቱ  ተፅኖ  ይመስላል  ።  ሔሞ ሬክተስና  ሖሞ  ሐቢለስ  እድሚያቸውም  አቋማቸውም  የሚነገረው  በግምት  ነው   ።  ሉሲን  እንኳ  ከሶስት  ሚሊዮን  በላይ  ቆይታለች  ይሉክና  የሞተችውም ከፊሎቹ   ከዛፍ  ላይ  ወድቃ  ነው ብለው ሲገምቱ  ከፊሎቹ  ደግሞ  አይ  ባውሬ  ተበልታ  ነው  የሚሉ  ገማቾች  ናቸው  ።  እንደዚህ  አይነቶቹ  ድኑን  ተረከቡና  ግምት  በግምት  አደረጉልህ  .. ጀምዒያም  በግምት  ዑዝር  ቢልጀህልም  በግምት  .... አይ  የሙነወር  ልጅ  ትላልቅ  ዑለሞች  ያልተሸከሙትን  ዶክተሮች  ያልያዙትን  ወንበር  ይዞ  ።  በቂርአት  በተለይ  በነህና  ሐድስ  የበታችነት  ስለሚሰማው  አሳዶ  ነው   የሚተቸው  ....❗️

👌 እኔ  ግራምህን  ተረዳ  ነው  የምልህ  ። አንተኮ  ድንገት  ሳታውቀው   ፅሁፍህን  አይተው  ኡስታዝ  ኡስታዝ  አሉህ  ሳትደርስ  ደረስክና  ከመድረስ  ተደናቀፍክ ። ያልደረስክበትን  ወንበር  ተንጠራርተህ  ተሰቀልክበትና  አሁን  ማን  ይውረድልህና  ይቅራ  ... ለቀንድ  ሳትበቃ  በንቦሳነትህ  ቀንድ  አበቀልክና  ገና  ራስህና  አንገትህ  ሳይጠነክር  ቀንድ  ስላበቀልክ  ብቻ  ለመዋጋት  አቧራ  ትጭር  ጀመርክ  ታው  ይቅርብህ  ያልነው  ገና  ቀንዳም  እንቦሳ  እንደሆንክ  ስላየንህ  ነበር  ።  በየቦታው  እየገባህ  አታቡካ  ዝቅ  ብለህ  ቅራ   ምክሬ  ነው  እንጂ  አንተ  ሰለፍያ  ላይ  ቅንጣት  ተፅእኖ   የለህም   ...  አዋጅህም  የብድ  አዋጅ   ነው  ...

-----

👌 ወንድሞች   ኢብን  ሙነወር  ከስጋት  ተነስቶ  ነው  "  በቀድመህ  አጠልሽ""  መርህ  ዘመቻውን  የከፈተው  ።  የሙነወር  ልጅ  ስላላወቀና  ስላልገባው  እንጂ   ዘመቻው  ጅብ  ከሔዴ  ውሻ  ጮኸ  ነው  አርፍደካል  በሉት  ... በአሁኑ  ሰዓት  ህዝቡ  ተገንዝቦ  ወጣቶቹ  ገብቷቸው  አንብበው  የመሻይኽን  ድምፅ  ሰብስበው  ጀምዕ  አድርገው  ከጨረሱ  በኋላ  ብልህ  የሚመስለው  ሞኛሞኙ  ከረፈደ  አይናሩን   እየጠራረገ   ኧረ  ዑዝር  አለ  እያለ  ሲለፈልፍ  ትንሽም   ቢሆን   አሳቀኝ ...። ሸሁ  አንተ  የኛ  ጀግና  አንተ  ከሌለህ  ሜዳው  ባዶ  ነው  ሙስጠፋን  አንጨፍጭፍልን  እያሉ  የሚገፋፉትና  ጎሽ  የኛ  ኡስታዝ  እያሉ  የሚያጨበጭቡለት  የኢርጃእ  ዛር  ያለባቸው  አቶና  ወይዘሮ  ድንገት  ጃስ  ብለውት  ነው  የተወዛገበው    ። 

👌እንደ ኳስ  ደጋፊ  ያልሆንክ  የአይንህ  ባለቤት  የጆሮህ  እረኛ  የአዕምሮህ  ባለቤት የሆንክ ... ማለትም  በራስህ  ማየት  የምትችል  መስማትና  ማሰብ  የምትችል  ነፃ  ሰው  የዑለሞቹን  አገላለፅ  ለብቻህ  ሆነህ  ሳትወሳወስ   ከልብ  ሆነህ  አዎ  ገለል  ብለህ  ስማቸው  ....❗️ ከዚያ  ስትጠላም  ስትፈርጅም  ያምርብካል  ....


🔺 የገረሙኝ  ሁለቱ  ነጥቦች 🔺
🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻
-----

👌 ""  ዶሮ  ብታልም  ጥሬዋን  ""  ያስቀየመችው  የጀምዒያው  ጉዳይ  ነው  ። ዞሮ  ዞሮ  ማረጊያ  በጀምዒያ  አበድዖ  ይልካል  ።   የሚገርመው  አባ  ውዴው  የሙነወር  ልጅ   ሸይኻችንን  ይህችን  የቆሸሸች  ጀምዒያውን  ማስጌጫ  ሊያደርጋቸው  ይፈልጋል ...።

👌🔻 አንደኛው 🔻የሚገርመው  ወደ  ጃሚዓ ራጂሒ   መስጅድ  ስንገባ  በሩ  አካባቢ  ጀምዒየቱል _ኸይሪያ  የሚል  ታፔላ  የተለጠፈበት  የየቲሞችና  የአቅመ  ደካሞች  መረዳጃ  ጀምዒያ  አለ  ።  ነገር  ግን   የራሷ  ዳዒ  የላትም  የራሷ  አባልም  የላትም  ከጧኢፋ  አትገናኝም   የዘካን   ገንዘብ   ተቀብለው  ለሚስኪን  ያደርሳሉ  ለመሳጅዶች  መልካምን  ያደርጋሉ  አለቀ  ደቀቀ  ... ይሔንን  ራሱን  ባንቀበለውም  አያስፈልግም   በሰለፎች  ጊዜ  የለችም  ብንልም  ።  ሐበሻ  እንዳለችው  ጀምዒያ  ግን  አይደለችም  በፍፁም አይገናኙምም   ።  የናንተኮ  የራሷ  ዳዒ  የራሷ  ጀማዓ  ያላት  ቡድን  ናት  ።  ባጭሩ  ቅንጅት  ወይም  እናት  ፓርቲ  እንደሚባለው   ሱና  ፓርቲ  ናጅያ  ፓርቲ  ማለት  ናት   ።  ዑለሞቹ  ይህችን  የናንተን  የሽርክ  ቀፎና  የቢድዓ  ገንዳ  የሆነችዋን  ታላላቆቹ  ፈቀዱልን  ብትለኝ  የምሰማህ  ይመስልካል ...❓ 
ዑለሞቹ  የፈቀዷት ጀምዒያ  ሐበሻ  ካለችውጋ  ፍፁም  ይለያያሉ  አልኩህ  ።  የናንተኮ  ድሞክራሲ  አምጣ  የወለደቻት  የማሶኒያ  የልጅልጅ  ናት  ።

👌🔻ሁለተኛው🔻 ዑዝር_ቢል_ጀህልን  በተመለከተ  የሚነገረው የሸይኹን  አገላለፅና  አካሔድ  በደንብ  ተረዱ ...
👌 አሁንም  ሸይኻችን  ሸይኽ ራጂሒ  አል_ዑዝር  ቢልጀህልን  በተመለከተ  የሰጡት  ማብራሪያ  እንደ ሸይኻቸው  እንደ  ኢማም  ኢብን  ባዝ  አይነት  ነው  ።  የሚገርመው  ሸይኽና  ተማሪ  ይወራረሳሉና  አገላለፃቸው  ራሱ  አንድ  አይነት  ነው  ።  እኛ  ንግግራቸውን  ሰብስበን  ስለቃኘነውና  ሸይኹንም  በአካልም  ስለሰማናቸው  እንድሁም  ነጥቡ  ግልፅ  ስለሆነ  በናንተ  ወከባ  አይበርደንም  አይሞቀንም  ። ስማ
አል  ዑዝር  ቢል  ጀህልን  በተመለከተ  ሸይኻችን  ገለፃቸው  የማያሻማ  ግልፅ  ነው  ።  እሳቸውም  እንደ  ሸይኻቸው  ኢማም  ኢብን  ባዝ  ዑዝር  ቢልጀህልን  ዑለሞች  በሁለት  ተከፍለውበታል  ብለው  ይጀምራሉ  ..እንዳትቸኩልና  ኺላፍይ  ነው  እንዳትል  ተከተለኝማ  ...  እንካ  ....


👌👉 ወንድሜ አባ ዩስራ 👈 👌
---------------
አላህ አድሎሃል ስንኝን መደርደር
ቀጥቅጠህ ውቀጠው እስከሚደናበር
ግረፈው በጅራፍ ስትፈልግ በአለጋ
አላወቀም እሡ ሲገባ አልጋ በአልጋ
ሳያውቀው በርግጎ ከዝንጀሮ መንጋ
መቀጥቀጥ ጀምሯል ተኝቶ ላይነጋ
የሙነወሩ ልጆ ገብቶ አንበሶች መጋጋ
-------------
ምነው ብትመክሩት አጃሪ በጎቹ
ተነጥሎ ሲሄድ ከዝንጀሮዎቹ
ዘው ውሎ ሲገባ ከአበሳዎቹ
ይገርፉት ይዘዋል እነዛ ጀግኖቹ
----------------
ከጀግኖቹ መሃል አንዱ አቡ ዩስራ ነው
አላህ አድሎታል ለሂዝብይ ጅራፍ ነው
ይገርፋል በጅራፍ ሲሻውም ባለንጋ
አድፍጠህ አትቀርም የሂዝብዩ መንጋ
ብዕሩም የፋፋ ነው ያሳጣሃል ዋጋ
----------------




ከወንድምህ አቡ ማሂ አብደልከሪም .......


👌 👉 https://t.me/Abumahiasselefi/6582


Forward from: 🇪🇹🇪🇹ከሸዋ ሰማይስር ሚዳና መራኛ የሰለፍዮች ቻናል🇪🇹🇪🇹
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
🎙_አባ-ውዴም ባቅሙ_🎙_


📄ከስንኞቹ

_እንኳን በሽጉጤ በነጅድዮች ፋና
_ባንተ አፍ አይነሳም ይቀርሀል ገና



🎤🎧በወዳጃችሁ አቡ_ዩስራ_ሙራድ


🕌በጦሳ ማዶ ተገጠመች

لا نسمحــ ــحذفــــــ  الرابطــــــــــــــــــــــ. 
👇                👇                 👇

🔗
https://t.me/alqariabuyusra

,    👍         💯        💪        🌹


👌 👉 መልስ በሉና እንደገና አድምጧት እስኪ -----------


👆👆    هذا بلاغ للناس   👆👆
ጀምዕያ ማለት ምን ማለት ነው❓
የጀምዕያ መሰረት ምንድን ነው❓
ማን ነው ጀምዕያን የመሰረተው❓
ወደ እስልምና ያስገባት ማን ነው❓
ጀምዕዮች እነ ማን ናቸው❓
የጀምዕዮች አካሄድ ምንድን ነው❓
ጀምዕዮች ሚንጠለጠሉባቸው ሹብሀዎችስ ምን ምን ናቸው ሚሰጣቸው ምላሽስ❓
ኡለሞች ስለ ጀምዕያ ምን ብለዋል❓
👆እነዚህና ሌሎችም ወሳኝ ነጥቦች በሰፊው ተዳሰዋል።

ጀምዕያ ከየት ወደ የት ከፍል 1

https://t.me/Abumahiasselefi/1197

ጀምዕያ ከየት ወደ የት ክፍል 2👇

https://t.me/Abumahiasselefi/1198

ጀምዕያ ከየት ወደ የት ክፍል 3👇

https://t.me/Abumahiasselefi/1199

ጀምዕያ ከየት ወደ የት ክፍል 4👇

https://t.me/Abumahiasselefi/1200

ጀምዕያ ከየት ወደ የት ክፍል 5👇

https://t.me/Abumahiasselefi/1201

ጀምዕያ ከየት ወደ የት ክፍል 6👇

https://t.me/Abumahiasselefi/1202

ኡለሞች ስለ ጀምዕያ ምን ይላሉ👇

https://t.me/Abumahiasselefi/1203


ተሳዳቢዎች ጀምዕዮች ናቸው ወይንስ ሰለፍዮች👇

https://t.me/Abumahiasselefi/1204

ጀምዕዮች በሰለፍዮች ላይ ሚቀጥፏቸው ቅጥፈቶች👇

https://t.me/Abumahiasselefi/1205

ጀምዕያ ሀረካ ቢላ በረካ ክፍል 1👇


https://t.me/Abumahiasselefi/1206



ጀምዕያ ሀረካ ቢላ በረካ ክፍል 2👇


https://t.me/Abumahiasselefi/1207



👆ይህ ነው ሀቂቃውን ለፈለገ‼️

በየ fb ፔጅ እና የዋትስ አፕ ግሩፕ ምስኪን ሙስሊሞችን ሰብስባቹ የምታጃጅሉ የጀምዕያ ኡስታዞች ባጠቃላይ ይመለከታችኋል።

ልጆቹ ልቀቋቸው ሀቅን ይማሩበት


#ሀቅ በሀቅነቱ ሊከተሉት የሚገባ እንጂ እኔ ቀድሜ ያገኘሁትን አለቅም የሚባል አይደለም።


ሀቅ ከማንም ይምጣ ከማን መቀበል እና ለሀቅ መሸነፍ ጀግንነት ብልህነት እንጂ ደካማነት አይደለም‼


https://t.me/Abumahiasselefi/1208


👌 ኢብኑ ሙነወር ሰሞኑን ኡስታዝ አቡ ኒብራስ ላይ እና ከሱጋ ባሉ ወንድሞች ላይ ስለተናገረው የተሳሳተ ንግግር የተሰጠ አጠር ያለች መልስ ።

👌 ... በወንድማቸው አቡ ኻሊድ ኡስማን ቢን ዩሱፍ .... حفظه الله تعالى

32 ደቂቃ ብቻ ።

=======


🔺https://t.me/Al_menjeniq_R/330

-----
🔺https://t.me/Al_menjeniq_R/330


Forward from: 👌 ደዕዋ ሰለፍያ ጃማ/ደጎሎ
ውሸት የሚባለው ምን አይነት ነው...❓

----

ያልተደረገን በግምት ከምትተች የተደረገውን የራሳችሁን የተጨማለቀ አካሔድ አስተካክል....
من كان بيته من زجاجة لايرمي الناس بالحجارة
ቤቱ የመስታወት የሆነ ሰው ሰዎች ላይ ድንጋ አይወረውርምና ....

ጋዜጠኛው እንደሚለው ሙስጠፋን ኢኽዋንዮች አግዘውት ነው ሱዑድ የሔደው ። ስለዚህ ወደነሱ ወደዚያው ወደተነሳበት ሊሔድ ነው እያለ ከሚዘባርቅ ... እውነት ኢኽዋንን እንደዚህና በዚህ ልክ ሊሸሹት እንደሚገባ ከተረዳህና መንሐጅህ ካሳሳህ ለምን የደሴ የጀምዒያ ፈረሰ የሆኑትን የራስህ ጀመዓዎች ሙሐመድ መኪንን, ሸይክ ሰዒድ, ሸክ ሐሰን ቃዲውን, አንተ ኢኽዋን ከምትላቸውጋ የዑለማ ምክር ቤት ለምን መሰረቱ ...❓ የራስህ ጀማዓዎች ተቀባዮችህ የወሎ ዳዒዎችህ አማክረውህ ከኢኽዋን ተዘፍቀው ልብህ እያወቀ ለምን ባላዬ ባልሰማ ዝም አልካቸው ...❓ . ነው ደዕዋ አብሮ ማስኬድ ችግር የለውም ችግሩ ምሳ ማብላት ነው ...❓ ወይ ዘንድሮ ...❗️

ጀምዒያ ከሚፈቅዱትጋ ሊቀራ ሔደ አለ

ሰውዬው ጃሒል እንደሆነ የዑለሞቹን ከሌሎቹ የማይለይ ሐዚል ደካማ እንጭጭ ስለሆነ ጥያቄውም ግልፅ ስለሆነ እዚህ ነጥብ ላይ መቆየት ወደ ሰማይ መተኮስ ስለሆነ አልተኩስም ::

كتبه أخوكم أبو الناموس الأثري وفقه الله تعالى ..

====


https://t.me/Al_menjeniq_R



https://t.me/Al_menjeniq_R


Forward from: 👌 ደዕዋ ሰለፍያ ጃማ/ደጎሎ
👉👉 እስኪ ንገረኝ ይሔንን ሁሉ እሽክርክሪቶሽ መገለባበጥ እንበለው ወይስ ለሐቅ ተገዥነት እንበለው ...❓ከደሊልጋ መዞር ወይስ ከስሜትጋ መሽከርከር የትኛውን ሰጠከው ...❓ የሙነወር ልጅ ኢኽዋንን የሚቃወም ኢኽዋኒ ሱሩሪ ለመሆኑ ምንም ጥርጣሬ የለብንም ። ከኢኽዋንነት ወደ አክራሪ ጀምዒይነት ከዚያም አድጎ ተመንድጎ መ) ሁሉም መንሐጅን ተሸክሞ የሚዞር አገር አቀፍ የተምይዕ አውቶቡስ ሆነ ። እሺ ይሔ ሐቅን ሲያገኙ ማሻሻል ነው ወይስ መንሸራተት መከረባበት ምን እንበለው ሸሁ ...❓
ነው የናንተ መገለባበጥ መስተካከል ወይም ደሊል በዞረበት መዞር ለኛ ሲሆን ደግሞ መንሸራተት ነው የሚባለው ..❓

---

👉በተለይ በአገራችን ተጨባጭ ሁሉም ሰው አንተን ጨምሮ እያንዳንዱ ሰው ከሆነ መንሐጅ የመጣ ነው ወይ ሱፍይ ነበር ወይ ኢኽዋን ነበር ስለዚህ ይህ መሆኑ እየታወቀ የድሮውን ተውበት የተደረገበትን እየመዘዙ የሸግግሩንና ከሌላ መንሐጅ የመመለሱን ቁጥር የማብዛት ወይም የማስፋት ዘመቻ መክፈት ተንጋሎ መሽናት ነው ። ምክናየቱም የጫሌ ጎረቤት ሆነህ አድገህ እንደ ሶሐባ ልጅ በዓቂዳ ነው የተወለድኩት ካላበድክ በስተቀር ይህንን አትልም ።

👉ጋዜጠኛው ያወባሩትና ለዚህ ድፍረት ያበቁት የቲክቶክ ተማሪዎች ናቸው :: በቅጥ እንኳ ቁርአን ያልቀራው የሙነወር ልጅ ሒስትሪን ተምሮ በነ ሔሞሬክተስ ታሪክ ተመርቆ በመላምት በድፍረት ያለ አንድ ሸይኽ ከሱፍይም በለው ከኢኽዋን አንድ አስተማሪ ሳይኖረው መንሐጅን ያክል ነጥብ በራሱ እያነበበ መፈትፈቱ ከባድ ነገር ነው ።

👉 ይህ ጋዜጠኛ :- ብዙ አቅሙ የማይፈቅድለት በሆኑ ነጥቦች እየገባ ሲያቦካና ሲያጨማልቅ አየዋለሁ እናም በድፍረት ገብቶ አማረኛ የበለጣቸውን ብዙ ሚስኪኖችን የተምይዕ ቅሬው አባል አድርጓቸዋል ። ጀምዒያን ዑለሞች ፈቅደዋታለሰ ብሎ መፅሐፍ ፃፈ ደህና አርጎ ቸበቸበ ሸጠ ቤቱንም ገዛ ። ዛሬ ላይ ስትቀጠቀጥበትና ኦክሲጅኑ ሊቋረጥ አደጋ ላይ ሲወድቅ መንደፋደፍ ጀመረ ። ባጭሩ ሰውየው በትኩረት ለተመለከተው የሰዎችን ሙቀትና ግለት እየተከታተለ መፅፍ የሚፅፍ ሆድ አደር ሰው ነው ።

ኢብን ሙነወርን ካያችሁት እንደ ሙሐመድ አወል መንዙማ እንደሙዓዝ ነሽዳ የሰውን ስሜት በተለይ ረመዷንን እየተከተሉ መንዙማና ነሽዳ እንደሚቸበችቡ ሁሉ እሱም እንደነሱው ኺላፍ መቀጣጠሉን ይመለከትና መፅሐፍ በመፃፍ ወደ ገበያ ይመጣል ..። ይሔም የሙነወር ልጅም የሚሸጥበትን ጊዜ እያዬ መፅሐፍ በመፃፍና በመሸጥ ጥቅሙን ያስከበረ ምርጥ የመሐይማን ዳዒ ነው ። አሁንም አል_ዑዝር ቢል ጀህልን ፅፎ ለመቸብቸብ ወደ ኋላ አይልም ፤ ጋዜጠኛው እንደጠርሙስ ሆድ እንጂ አዕምሮ የሌለው ቀላል ሰው ነው ., ስለዚ ሰውየው አይጠግብም ። ይሔንን ነገር ነግሬህም ነበር ። ባጭሩ ይሔ የብን ሙነወር የተምይዕ በሽታ የሐሰን ታጁ የወጣትነቱ በሽታ ነበር ። ካለማወቁ የተነሳ በኢኽዋን ቤት ተወሽቆ ኢኽዋንን ያወግዛል ::

----

👌 አጫጭር መልስ 👌
🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻

👉ስሙ ጀማል ወርቄ ነበር ቀየረው አለ ። አይ መወዛገብ ...❗️ ስሜ ደረሳ ሆኜ ጀማል ነበር ወርቄ የሰፈራችን ስም ነበር ። መታወቂያም ሆነ ማንኛውም ዶክሜንቴ ግን በሙስጠፋ ነው ። ስሜን መቀየሬን ሳይሆን ሸርዓዊ ብይኑን መናገር ይቀል ነበር ይህንን ጉዳይ ደግሞ አብራርቸዋለሁ ። አባቴም እናቴም ዘመዶቼም ሁሉም ጀማልን ረስተውታል .. ወንጀል የሚሆነው ሁለት መተዋወቂያ ሁለት እጣ እየቀያየርኩ ባጭበረብርበት ሐጢያት ይሆን ነበር ፤ እንደዚህ ደግሞ አላደረኩም ...❗️ ይሔ ምኑ ያስወቅሳል...❓ ስንት ስሙን የቀየረ አለ ...❓

👉 ከኢኽዋን ምሳ ተገባብዞ ጀምዒያ ስጡኝ ብሎ ጠይቋል አለ ..
سبحان الله ከየት አመጣከው ...❓
ተመልከቱ አራት ማእዘን ውሸት ሲዋሽ ...

"" وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَآَنُ قَوْمٍ عَلَى أَلَّا تَعْدِلُوا اعْدِلُوا هُوَ أَقْرَبُ لِلتَّقْوَى وَاتَّقُوا اللَّهَ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ "" ٨ المائدة
ኧረ አትቀደድ ፍትህ መለኮታዊ ትዕዛዝ ነውኮ ። ሙብተድዕ ነው ብለህ መጥላት ትችል ይሆናል ነገር ግን መዋሸት በፍፁም አይፈቀድልህም :: መጅሊስ ሔዶ መስጅድ ጠየቀ ከየመሳጅ አታባሩን አለ :: አዎ መጅሊስ የሙስሊሞች ተቋም እስከሆነ መሳጅዶቻችንን ታስተደድራላችሁ አለ የመሳሰሉትን ብሏል ብትል እንኳ እውነት ነው ..ጀምዒያ ስጡኝ አለ ብለህ መዘባረቅህ ግን ይገርማል :: ይህንን ጥቁር ውሸት ትዘባርቃለህ ...❓ አይቀፍህም ሞትኮ አለብህ ቀብር አለብህኮ ነው እኛላይ መዋሸት ጭራሽ ወንጀል አይመስላችሁም ልበል ...❓ ጋዜጠኛው እስኪ በመረጃ ንገረኝ እስኪ ልቶብት በልማ ...❗️

የሙነወር ልጅ ንደተኛ ነው በትንሽ ነገር ቱግ የሚል ብስጩ አጭበርባሪ እንደሆነ ጠንቅቄ አውቃለሁ ። ውሸታም ስለሆነና ለድን ሳይሆ ከጥቅሙጋ የሚሔድ ተራ ሰው የመፅሐፍ ነጋዴ በመሆኑ ምክናየት .." ባህርዳር ሐራ መርሳ ኮቻ የነበሩት መፅሐፍ ሸማቾቹ ትተውት ተጠርገው ወደለተሞ የሔዱ እንዳሉ ሁሉ ብዙ እህቶችም የጀምዒያ ቢድዓ በቃን ብለው ትተዋቸው ወደኛ ሲመጡበት የኑሯቸው የግልኮስ ገመድ ሲቀደድ ብዙም ጥቅም ሲያጡ ጋዜጠኛው ሳሩንም ቅጠሉንም አፈሩንም ወረወረብን ...በቃ ተባነነኮ አሁንማ ተግባብተን ....❗️

----
👉 ሱዑድ ሲሔድ ያመቻቹለት ኢኽዋንዮች ናቸው አለ .... ጉድኮ ነው አለ ....

👉 ይገርማችኋል የኔን ኢቃማ የገዙት አረብ አገር ያሉ ከፊል ወንድምና እህቶች በውስጥ ለውስጥ በራሳቸው ተነሳሽነት ተመካክረው ተስማምተው ወደ ሱዑድ ይምጣና ይቅራ በማለት ከጨረሱ በኋላ ሰማሁ ሳልለምን ማስተዋወቂያ ሳልሰራ በራሳቸው ፍቃድ በሚያደርጉት እንቢ አልልም ብዬ ፕሮሰሱን ጀማርኩ ጥሩ እድል ነው ከዑለሞችምጋ የመገናኘት እድል ይኖረኛል የሚል ጉጉት አደረብኝና ወደ ዑለሞች መጣሁ ። የኢቃማውን የከፈሉት የተወሰኑ ወንድም እህቶች ናቸው ብያለሁ ። ኢኽዋን ድንቡሎ አላገዘኝም እንኳን እጃቸው ሊኖርበት ቀርቶ ወደ ሱዐድያ እንደምሔድም አያውቁም ነበር ። እውነታው ይህ ሁኖ እያለ የግድ የኛን ነገር ከኢኽዋንጋ ለማገናኘት መጋጋጥና አራት ማዕዘን ውሸት መዋሸት የትም አያደርስም ። ኢኽዋንን ከኛጋ ለማገናኘት የውሸት መረብ መዘርጋት ምስራቅንና ምእራብን አንድ ላይ መጨፍለቅ ነው ። ይሔ ውሸት ወይም ቱልቱላነት ካልሆነ


Forward from: 👌 ደዕዋ ሰለፍያ ጃማ/ደጎሎ
ልብ በሉ ይሔንን ተረት የሰጡት ከዚህ በፊት ቢስቲማ ሔደው ሙስጠፋ የመስጅዱ ኮሚቴዎች ከቢስቲማ መስጅድ አባረውት በመንደር ውስጥ ሲከታተሉት ሚስት አግብቶ አገኙት እያሉ የባጥ የቆጡን ያወሩ መዋሸት እንኳ ከማይችሉ ፋራ ኡስታዞች ይዞ ዛሬም ይተረተራል ። ሸሁ ቂያማ አለብህ ቀብርም አለብህ ያንተ ውሸት እንደማንኛውም ተራ ውሸት አይደለም በመሻይኽ እጥረት ባንተ በጃሒሉ ስር የወደቁ 97K ሺ ሚስኪኖች አሉ ዋሽተህ አታስዋሻቸው

። ካድማስ አድማስ በሚያዳርሰው ቻናልህ ተቀደህ በቀብር ውስጥ ጉንጭህ ከሚቀደድ ረጋ ብለህ አስበህ መረጃ ያለበትን ብትናገር ላንተም ለኛም ለመንጋዎችህም ጠቃሚ ይሆን ነበር ..።

عن سمرة بن جندب "" أَمَّا الَّذِي رَأَيْتَهُ يُشَقُّ شِدْقُهُ فَكَذَّابٌ يُحَدِّثُ بِالْكَذْبَةِ، فَتُحْمَلُ عَنْهُ حَتَّى تَبْلُغَ الْآفَاقَ فَيُصْنَعُ بِهِ إِلَى يَوْمِ الْقِيَامَةِ." البخاري

👉ለመሆኑ ያ ፍትሐዊይ ነው የምትለው ብዕርህ የት ሔዴ ..ነው ስትቆጣ ስትበሳጭ ስትመቀኝ እንድህ ያደርግካል..❓
___

👉ስማኝማ ይህንን ሁሉ የቃሚ ቂሷ ከምትዘባርቅ አረጋግጠህ መረጃ ይዘህ ሐጢያትና ስህተት ያልከውን በመረጃ አስደግፈህ ብትመክረን ብትተቸን ምናልባትም ከተሳሳትን የሒዳያ ሰበብ ልትሆነን ትችል ነበር ። ነገር ግን ስሜትህን ለማርካት እንድሁም ንደትህንና ቁጭትህን ለመወጣት ወይም ያመረቀዘ ቂምህን አጋጣሚ ጠብቀህ ለመበቀል ብቻ መፃፍህ አንተንም ሆነ መንጋዎችህን ይጎዳል እንጂ መሬት ላይ ጠብ የሚል ነገር የለም ። ደግሞም ንግርህ ድፍረት እንጂ ኢኽላስም አይኖረውም ። አልሰማ አልክ እንጂ እኛማ ገና ከጧቱ ነግረንህ ነበር ብዕርህ ሆድ እንጂ አይንና ጆሮ የለውም ። ብዕርህ ህሌናም የለውም ። ከጧት ጀምሮ ብዕርህ ይቀፈናል ። የአማረኛ አሰካኩና ቅኝቱ ራሱ ከሐሰን ታጁ መፅሐፍ የተቀዳ ደረቅ የቃላት ስብስብ እንጂ መረጃ ቀርቶ ለዛ የለውም ።

ጋዜጠኛው ሆይ ልብ በልማ ...
🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻

👉 አሉ ተብሎ ሁክም አዘል ረድ አይፃፍም ። በሰው ላይ ሁክም ወይም ብይንም አይሰጥም ። ያውም ከምናውቃቸው ከቀጣፊዎችህ ይዘህ ይህንን ቃርቃር የሚል ፍልስፍናህን መለቅለቅህ ደግሞ ውስጥህ ምን ያክል እንደተጎዳ ያሳብቅብካል እንጂ ሌላ በመሬት ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም ። ቆይ ለመሆኑ ያ ወሰጥያ የሚደሰኩረው አስመሳይ ብዕርህ ምነው ዛሬ ማረጋገጥ ቀርቶ ማስመሰል እንኳ ተሳነው..❓
ድሮውንም በአሉ ወሬ የሚገነባ ዘገባ ከመላምትነት አይዘልም ።
---

እስኪ ስለመገለባበጥ
🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻
👉 ጋዜጠኛው የሙነወር ልጅ ሆይ :- ቆይ አንተ በልጅነትህ ከነቤተሰብህ የጫሌን ጋቻ ስትማፀን አደክ ያንን ትተህ በግዜው ወሐብያ ወደሚባለው በተማሪነት ዘመንህ ተገለበጥክ ...ከዚያ ደሴ በሰይድ ቁጥብ እየተነታረካችሁ ከኢኽዋን የሚነታረክ መንሐጁን የማያውቅ መንጋ ሆናችሁ ። ዩኒቨርሲቲ ገብተህ ሒስትሪህን ተምረህ ስትወጣ ደግሞ የጠጣህ ጀምዒይ ሆንክና ፅሁፍ ጀመርክ ከብን መስዑድ ወይም ከመርከዙ ሰዎችጋ ጋብቻ ፈፅመህ አብረህ መጓዝ ጀመርክ ።

👉አብነት የነበረችዋ የብን መስዑድ መርከዝ ጫጉላህ እንደነበረች ጠንቅቄ አውቃለሁ ። ቆየት አልክና በፅሁፍህ የሸወድካቸውና የቀራህ የመሰላቸው ገልቱ ተማሪዎችን ማጠራቀምህን ስታውቅ ከሳዳት ገጠማችሁና የመርከዙን ሰዎች ጭፍጨፋ ጀመርክ ። ብዙም ሳትቆይ በአረብ አገርና በዩኒቨርሲቲ ባሉት ጨቅላዎችህ ተሸለለልህ አንተም አንበሳ አንበሳ ሰራህ መፅሐፍ ፃፍክ ሸጥክ አጋጣሚ ገበያውን ተጠቀምክና ኑሮህን ቀየርክ ። ከዚያ ከለተሞጋ ስትጋጩ የትናንትናዎቹን ሰዎች ተንሸራተህ የሙሐመደል ኢማምን ኢባናን አንብበህ ቅዝቅዝ አልክና እንደገና የኋላ ማርሽ በማስገባት በስንት አመት የወጣሃውን የመንሐጅ አቀበት እንደገና ተመልሰክ ቁልቁለቱን ሳምንታት ባልጨረሰው ፍጥነትህ ወረድከው ። ይሔንን ቅዱስ ኺላፍ እንበለው ...❓ ወይስ ቅዱስ አክሮባት እንበለው ...❓

👉ወንድሞችዬ ባጭሩ ጋዜጠኛው መብስልም ይበለው ከፈለገ መስለሐ መፍሰዳ ማየት ይበለው ስለ ኢብን መስዑዶችና ስለ ኢኽዋንዮች ትራሱን አበጃጅቶ ለሽ ብሎ ተኝቷል አልፎ አልፎ እንደነማማ አሽሙሩን ጣል እያደረገ እየኖረ ነው ። አዎ ትገርሚኛለሁ እያለ ባሽሙር ሲለቀልቅ የነበረው ንደተኛው ጋዜጠኛ ዛሬ ዝም ብሏል ። ይሔ በቻናሉ ላይ በለዘብተኝነት የሰበሰበው በተለያዬ ባራት አቅጣጫ የሚያስብ የተለያየ መንጋ ነው ።

👉 ጋዜጠኛውኮ ሲናደድ ሲገነፍል የሚፅፈውን አያውቀውም :- ሸሁ ስትናደድ አትፃፍ ብየውም ነበር :: አስታውሳለሁ አንድ ጊዜ የህየል_ሐጁሪን በመተቸት የሸይኽ ረቢዕን በየህያ ላይ የተናገሩትን የህያ ውሸታም ነው ያሉበትን ንግግር ተርጉሞ በመልቀቅ የህየል_ሐጁሪን በአስቀያሚ ገለፃ ወረፈው ። ሰለፍያ ከደማጅ የምትመጣ ሰልባጅ አይደለችም እያለ ሲበጠረቅም ቆዬ ... የሐጁሪ መንጋዎች እያለ ሲፅፍም ከቆየ በኋላ ዛሬ ላይ እንደገና ያለምንም ተውበት አክሮባት ሰርቶ በእኛ እልህ ወይም ዑዝር ቢል _ጀህል ስላገናኛቸውና እንደ አዝማሪ አየር ንብረቱን እያዬ ስለሚጓዝና እንደ አስለቃሽ የሰውን የማዘኛ ስስ ብልት እያዬ ማስለቀስና ማላቀስ ሙያው ስለሆነ ይህንን ሙያ ስለተካነበት በነሱ ለመወደስ ብሎ ሸይክ የህያ ታላቅ የየመን ዓሊም ነው አላህ ይጠብቀው እያለ በሚገርም ሁኔታ አሽቃበጠ ።

ይህ ሁሉ እንደላሊባ ወይም እንደ አዝማሪ ሲያሽቃብጥ ለመሆኑ ቅንጣት ጥርጣሬ የለንም ። የሚገርመው "" ሳይጠይቁ ያመኑ ብፁዓዊያን ናቸው "" የሚለው ተረት የሚገልፃቸው ተማሪዎቹ ወይም እንደ ሱለይማን ጅኖች ታዛዥ የሆኑት መንጋዎቹ ቢያንስ የትናንትናውን ተውበት አድርግ እንጅ ኡስታዝ አይሉትም ።

👉 ለመሆኑ ጋዜጠኛው እንደዚህ መከረባበቱ ምራቅ እየዋጠ መሆኑ ነው ወይስ የእውቀት አድማሱ እየሰፋ ነው ..❓ በሚገርምና በሚያደናግር ሁኔታ መንሐጁን እብድ የበላው በሶ ያስመሰለ ብቸኛው ብርቅዬ እንሰሳ እሱን አየሁ ። እኛ ግን ከጀምዒያም ይሁን ከሌላ መንሐጅ ስንወጣ በግልፅ ተውበት ነው :: ባጭሩ የዑለማ ኺላፍ አለበት እያለ እያመጣ መንሐጃቸውን መ)ሁሉም አድርጎታል ። ባለንበት ተጠጨባጭ ከዚያ ሁሉ ጉዞው በመቀጠል አሁን ላይ የቀለጠና ሱፐር ማርኬት የሆነውን የሙመይዓ መዝሐብ እስከ እግር ጥፍሩ ተዘፈቆበታል ..። እሺ ይሔስ ቅዱስ መገለባበጥ ነው የሚባለው ..❓


Forward from: 👌 ደዕዋ ሰለፍያ ጃማ/ደጎሎ
👉ቀረዷዊን የሚተቸው ታዳጊው ቀረዷዊ ምን እንድህ አንጨረጨረው...❓
🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻

ሌባ እያለ የሚሮጥን ሌባና ውሸትን የሚተች ውሸታምን በደንብ ተጠንቀቃቸው ...


👌ቀረዷዊን ለመምሰልም ሆነ ለመተቸት እንድሁም የቀረዷዊን መንሐጅ ለመተወንም ሆነ ለመዋጋት የተወሰነም ቢሆን በስሱ እውቀት ያስፈልጋል ። ስለዚህም ቀረዷዊይን በትክክል ካለማወቅ የተነሳ ነው በአገራችን ላይ ቀረዷዊን የሚያወግዙ ብዙ ቀረዷዊዎች የተፈጠሩት ። መንሐጃቸውን እንደቀረዷዊ ለጥጠው አስፍተው አላልተው አቅልጠው ሁሉንም ነጥብ ኺላፍ አለበት እያሉ ኺላፍያ የሚል የማለዘቢያ ባዝሊኒ የሚቀቡ ብዙ ቀረዷዊዎች ተፈልፍለዋል ። ይግባህ ወንድም ዓለም በመሐይምነት ተውጠህ የቀረዷዊን መንሐጅ በእልህ ሰክረህ በምቀኝነት ተቃጥለህ የምትተውነው ከሆነ ስንት አይነት ሰው እንደምትሆን አስተውል በቃ ባጭሩ መንሐጅህ ሱፐር ማርኬት ይሆናል ። የሙነወር ልጅና ቢጤዎቹ የቀረዷዊን ነጃሳ የመንሐጅ ሌጦ ወስደው በነብኑ ባዝ በነ ፈውዛን ቀለም ቀብተው አሰማምረው የመንሐጅ ነጃሳ ሌዘር ጃኬት አድርገው የሚያመጡ የተምይዕ ፋብሪካዎች ወይም የነጠሩ ሙመይዓዎች ናቸው ።

-----
👌 ራስ ሳይጠና ጉተና እንደሚባለው የሙነወር ልጅ የሐሰን ታጁን ያክል እንኳ ቂርአት ያልቀመሰ በሁሉም ሸሪዓ ነክ ዕውቀት ምንም አይነት ግንዛቤ የሌላው ጥርብ መሐይም ነው ። ይህ ሰው ሌላው ቀርቶ የሱፍይም ሆነ የኢኽዋን ሸይኽ የማይታወቅለት ጥራዝ ነጠቅ ሰው ነው ። ሰውዬው ሸይኽ አልባ በጎግል ጡጦ ያደገ ሁሉም ትክክል የሚመስለው አንድ ወጥ መንሐጅ የሌለው ጋጠ ወጥ ፀሐፊ የሆነው በዚሁ በእውቀት እጥረት ነው ። ለዚህ ነው ልጓም የሌለውን ሆዳምና በሒዝብያነት የዶለዶመ ብዕሩን በማሾል ምንም አይነት ተጨባጭና መሰረት የሌለው ተረታ ተረቱን ለቅልቆ ያየነው ።
----
👉 እኛ እንደምናውቀው የሙነወር ልጅ የታሪክ ተማሪ እንጂ በቅጥ እንኳ እንደገጠር ልጅነቱ ቂርአት የቀመሰ አይደለም ። መሐይምት ያጀገነው ደፋር ፀሐፊ ነው :: እኛ ለሰዎች የምናስገነዝበው ነገር ቢኖር የያዝነው መንሐጅ ወይም ነጥብ የፊቅህም ከተባለ በዑለሞች እንጂ "" ሔሞ ኢሬክተስና ሖሞ ሐቢለስ""ን ባጠና ተራ የአካዳሚክ ተማሪ እረኛ በሌላቸው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቀለም በቀመሱ የቲክቶክ ቆማሪዎች የተሾመን መሐይምን የምንሰማበት ትርፍ ጆሮ የለንም ።
----
👌ተምይዕን ወሰጢያ ስድብን ጥንካሬ የሚያስመስለው ይህ ተራ ጋዜጠኛ ትናንትና ሐሰን ታጁ በልጅነቱ በታመመበት የእናምቦርቅቅ በሽታ ተለክፎ ይሔው ዛሬ ያልጋ ቁራኛ ሆኗል ። የህመሙ መነሻ ሰፋ አርገን እናስብ ቦርቀቅ አርገን እንመልከት የዑለማ ኺላፍ ያለበትን ነጥብ አንገፋፋበት አንተም በኪታብህ እኔም በኪታቤ አትንካኝ አልንካህ ከነካኸኝ ጫፍና ጫፍ የረገጠ እልካለሁ እያለ የሚያስፈራራ ጅልም መሐይምም ነው ። ይህ የጎግል ተማሪ ሒደቶቹን ሁሉ ስትከታተሉ የምታገኙት የምትደርሱበት ነጥብ ዑለማ ከተኻለፈበት እሱጋ የፊቅህ መስአላ ብሎ እንደሚያስበው ትደርስበታለህ ። ይህ ደግሞ የነጋሽ ሰብስቤ ቋሚ በሽታ ነው ። ዛሬ በጀምዒያ ኢብን ባዝን ተጋፈጥ ፈውዛንን ተጋፈጥ እያለ ሲደመር ዑለማ የተጋጨበትን ወላእ በራእ አታሸክመው የሚል ሙሉ ድምዳሜ ላይ ከደረሰ ነገ ኢስቲዋእን በተመለከተ ነወውይን ተጋፈጥ መውሊድን በተመለከተ አቡ ሻማን ተጋፈጥ ላለማለቱ ዋስትና የለንም ። የጎግል የተምይይዕ መሻይኾችን እየሰማ ችሎታ የሌለው የባህል ወጌሻ ሆኖልካል ።

👉እኛ እያልን ያለነው ዑለሞች የተኻለፉበት ሁሉ ኢጅቲሐድይ ወይም የፊቅህ መስአላ ነው ማለት አይደለም ፤ ምክናየቱም ተኻልፈውበት ኢጅቲሐድይ ያልሆነ ብዙ ነጥብ አለና ። ስለዚህ ነጥቦችን ሁሉ የሚገባቸውን ድግሪያቸውን እንስጣቸው እያልን ነው ። የፊቅሁን በፊቅህ የዓቂዳውን እንደ ደረጃው እንመልከታቸው ። እኛ ነጥቦችን የማይሸከሙትን አሸክመናቸው አናውቅም ያሸከምናቸውም ካሉ በመረጃ ጥቀሷቸውና እኛም እንቶብት ።

👉 የሙነወር ልጅ በሰለፍዮች ዘንድ ህመሙ ግልፅ ነው ። ያችን የገቢ ምንጭ የመፅሐፍ መሸጫ ኮንቲየነር ያደረጋትን ጀምዒያውን በጥቂቱም ቢሆን አፍርሰንበት ባትጠፋም የረድን ዝናብ እንዳትመክት አድርገንበታል ። ለዚህ የገቢ ምንጭነቷ አሽቆልቁላበታለች የድሮው ገቢ ዛሬ ላይ የለም ። በሆዱ በኑሮው መጣንበት ሰለፍዮችም ጠበጠቡት ለተሞዎችም አስተፉት ለዚህም ነው እስካሁን በውስጡ ቂም እንዳመረቀዘ የቆየው ። አጋጣሚ እየጠበቀልን ቆይቶ ዛሬ ላይ እንደ በረሐ እባብ ከአሸዋው ራሱን ብቅ አደረገ .....።

""" ወደ ዋናው ሐሳቤ ""
🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻

👉 ጋዜጠኛው ለመዋሸት ስለፈለገ ውሸት የምትለዋን ቃል ደጋግሞ አወገዛት :: ለመታዘብም ይግቡ ለመማር 97K "" ዘጠና ሰባት ሺ "" ይህ ጋዜጠኛ የሚበልጣቸው ከሱ እውቀትን የሚፈልጉ በዚህ ጃሒል ቀጭን ገመድ የሚጎተቱ እንደበቀቀን ያለውን የሚሉ ለምን ብለው የማይጠይቁ ሲያለቅስ የሚያለቅሱ አያሌ ብርቅዬ እንሰሳዎች አሉት ። ሙነወርንና ሳዳትን እነዚህን ሁለት መሐይሞች እንደ አዋቂ በዚህ ልክ የሚከተላቸው መኖሩን ሳይ ይገርመኛል ። ይህ የሚያሳየው የሰውን የእውቀት አድማስ መስፋት ሳይሆን የሚያሳየው ኢትዮ ውስጥ ሰው እጅግ መብዛቱንና በቀላል ወጥመድ የሚያዝ ብዙ መሐይም መኖሩን ነው ። ከሽንኩርት ይልቅ ሰው መርከሱንም ያሳያል :: የሚገርመው የሙነውር ልጅ በዚህ ሰፊ በረቱ ላይ የለጠፈውን ወንድሞች ልከውልኝ አየሁት ገረመኝ .. በዚህ ልክ መቀደድና መወዛገብ ምንጩ የማይታወቅ የግምት ወሬ ወይም በውሸታምነታቸው ከታወቁ ዳዒዎቻቸው ይዞ ሳያረጋግጥ እንደወረደ መለቅለቁ ገረመኝ . ለማንኛውም ጥቂቶቹን እንያቸው...:-
----

....የጋዜጠኛው ከፊል ትችቶች ...
🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻🔻

----
👉ይዋሻል አሉ ሲያወሩት እንዳይክዳቸው ሪከርድ ያደርጉታል አሉ ።
👉ሰዑዲ የሸኙትና ያገዙት ኢኽዋንዮች ናቸው አሉ ።
👉ከኢኽዋንዮችጋ ደሴ ተሰባስቦ ጀምዒያ ስጡኝ ብሎ ነበር አሉ ።
👉 ስሙ ጀማል ወርቄ ነበር አሉ ..
👉 ዑዝር ቢል ጀህል ኺላፍያ ነው ይል ነበር አሉ ...
ነበር አሉ ....
ነበር አሉ ....
አድርጎ ነበር አሉ ....


👌 👉 የባጢል ባለቤት አንድን ነገር ከተሳሳተ ያንኛውን ስህተቱን ተውበት አድርጎ ከመመለስ ይልቅ ሌላን ውሸትን በመጨመር ከበፊተኛው የባሠን ውሸት ይዞልህ ይመጣል !!

👌 👉 የሙነወር ልጅ በባለፈው በሸይኻችን አቡ ኒብራስ ላይ መዋሸቱ አልበቃው ብሎ ዛሬ ደግሞ ወደ ሸይኽ አብደለዓዚዝ ራጅሂ ላይም መዘዘዋወሩን ቀጥሏል ነገ ደግሞ ወደ ሷሊህ አል ፈውዛን መሸጋገሩ አይቀርም !!

👌 👈 قال ابن القيم  رحمه الله تعلى : - من عرض عليه حق فرده فلم يقبله عوقب بفساد قلبه وعقله ورأيه .  [ مفتاح دار السعادة ١/ ١٦٠ ]
 
ታላቁ የኢስላም ሊቅ ኢብኑል ቀይም አል ጀውዚይ እንዲህ ይላሉ :-  ሀቅ መቶለት ሀቅን አልቀበልም ብሎ ሀቆን የመለሠ  አካል ና ሀቅን ያልተቀበለ  ልቡ አቅሉ ና አመለካከቱ በመበላሸት ይፈተናል ::


👌 👉 ልክ የሙነወርን ልጅ ይመስል ሀቅ እንደ ፀሃይ ፍንትው ብሎ እየታየ ሀቅን አልቀበልም በማለቱ የተነሳ የሚናገረውን ና የሚፅፈውን ነገር እስከማያውቅና ከዚህ ንግግሬ ጀርባ ምን ይመጣብኛል ብሎ እንዳያስብ አድርጎታል !!!

ሙሉ ዝርዝሩን በሠፊው እመለስበታለሁ !!
=============================

اللهم احعل قلمي حق وصدق ورشد  وناصر لدينك وقامع لأهل الباطل وجزأة في الكلمة النافعة  لايعرف المجاملة في الدين ولا تلاعب بعقول المسليمين .

--------------------------آمين ------------------------


أخوكم الصغير الفقير إلى عفو ربه أبي  ماحي عبد الكريم بن حسن  وفقه الله لما يحبه ويرصاه .
💫 👉
https://t.me/Abumahiasselefi/6572

🔸 👈  لا أسمح لأحـد حذف  الرابط  🔸 👉

🚫👉 ሊንክ እዲቆረጥ አልፈቀድንም ‼

20 last posts shown.