Фильтр публикаций


በወንጀል መከላከል ተግባር በርካታ ተግባራት መከናዎናቸውን ፖሊስ ገለፀ።

በክልሉ ከተፈጠረው የፀጥታ ችግር በኋላ ይፈፀሙ የነበሩ በርካታ የወንጀል ተግባራት አሁን ላይ መሻሻል ማሳየታቸውን በባህርዳር ከተማ አስተዳደር የ1ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል መከላከል ክፍል ኀላፊ ረዳት ኢንስፔክተር መኮንን እንየው ተናግረዋል።

የፀጥታ ችግሩን ተንተርሶ ይፈፀሙ የነበሩ የእገታ፣ስርቆት፣ተኩስና ፍንዳታዎች፣ዝርፊያና ንጥቂያ፣የመንገድ መዝጋት፣የስራ መዝጋትና መሰል ድርጊቶች ማህበረሰባችንን እረፍት የነሱ ድርጊቶች ነበሩ ያሉት ረዳት ኢንስፔክተር መኮንን አሁን ላይ ከማህበረሰቡ ጋር በተደረገ ግልፅና ንቁ ተግባቦት ችግሮቹን በከፍተኛ ደረጃ ለመቀነስ ችለናል ብለዋል።

ፖሊስ የማህበረሰቡን ሰላም ለማስጠበቅ ከማህበረሰቡ ጋር በመነጋገር የተለያዩ የብሎክ አደረጃጀቶችን በመፍጠር አካባቢን የመጠበቅ ስራ እየተሰራ ነው።

ኃላፊው አክለውም ወንጀሎች የሚፈፀሙት ማህበረሰቡ ውስጥ በሚኖሩ አካላት የሚጎዱትም ማህበረሰቡን መሆኑ የተረዳው የከተማችን ነዋሪ ወንጀለኛን በማጋለጥም ሆነ በመከላከል ለፀጥታ ኀይሉ ድጋፍ እያደረገ ነው።በዚህም ወንጀልና ወንጀለኛን የቀነስንበት ጊዜ ላይ ነን ብለዋል።

የእገታና ንጥቂያ ወንጀሎች እንዲቀንሱም ከፀጥታ ኀይሉ ጥረት በተጨማሪ የአካባቢ ጥበቃ፣የሰፈር የውስጥ ለውስጥ አጥርና የማህበረሰቡ ንቁ ተሳትፎ ትልቁን ድርሻ ይይዛል ነው ያሉት ረዳት ኢንስፔክተር መኮንን እንየው።

የማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ተግባር ወደስራ ገብቶ ወንጀልን ከዚህ የበለጠ ለመቆጣጠር ሁሉም የማህበረሰብ ከድጋፍ ለፀጥታ ኀይሉ ጋር ንቁና ጤናማ የሆነ ግንኙነት ሊኖው ይገባልም ሲሉ ኀላፊው መልዕክት አስተላልፈዋል።


የግለሰቦችን የቴሌግራም አድራሻ በተለያዬ ዘዴ በመጥለፍ በስማቸው ሲያጭበረብር የነበረው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሏል።

በኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር በተደጋጋሚ ከተለያዩ ግለሰቦች ገንዘብ የሚያጭበረብሩ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር እያዋለ ለህግ እያቀረበ የሚገኘው የከተማው ፖሊስ ከሰሞኑ የግለሰቦችን የቴሌግራም አካውንትን በመጥለፍ የተቸገረ በማስመሰል ገንዘብ ጠይቆ በማስላክ ለግል ጥቅሙ ሊያውል የነበረው ተጠርጣሪ ሰፎኒያስ አደም ጥላሁ የተባለ ወጣትን በከተማ አስተዳደሩ የቢራሮ ክፍለ ከተማ ፖሊስ በቁጥጥር ስር አውሏል።

የቢራሮ ክፍለ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር መሀመድ ይማም እንዳሉት ከሰሞኑ አንድ የግል ተበዳይ የቅርብ ቤተሰቡ የሆነች ልጅ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንዳለችና ገንዘብ እንደሚያስፈልጋት በቴሌግራም አድራሻዋ 340 ሽህ ጠየቀችው ያለውን180 ሺህ ብር ከላከ በኋላ ሲያጣራ አድራሻዋ መጠለፍ ተረጋገጠ ብለዋል። በዚህ መነሻነት ፖሊስ ተከታትሎ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ መሆኑን ገልፀው አሁን አሁን በቴክኖሎጂ የተደገፈ የማጭበርበር ስራዎች እየጨመሩ መሆናቸውን አንስተዋል።

ወንጀል ፈፃሚዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ሂደት ማህበረሰቡ ላደረገላቸው ጥቆማ ያመሰገኑት ም/ኢንስፔክር መሀመድ ይማም ወደ ፊትም ከፖሊስ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።


የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፈ እሸቱ የሱፍ(ዶ/ር) በክልሉ የፀጥታ ኀይል የ6 ወር የስራ አፈፃፀምና የሪፎርም ስራዎች ዙሪያ የማጠቃለያ ሀሳብ በሰጡበት ወቅት ያነሷቸው አንኳር ነጥቦች፦

👉 የክልሉ የፀጥታ ኀይል ከመከላከያ ሰራዊትና ከፌደራል የፀጥታ ኀይሎች ጋር በመሆን በግማሽ ዓመቱ ውስጥ ጥቃቅን ክፍተቶች የነበሩ ቢሆንም በአመዛኙ ጥሩ ውጤቶችን አስመዝግቧል።

👉ለፀጥታ ኀይላችን አስፈላጊውን እና ተገቢውን የሎጀስቲክ አቅርቦትና የጥቅማጥቅም ጉዳይ ከግምት ውስጥ በማስገባት ለማሟላት ጥረቶች ተደርገዋል እየተደረጉም ይገኛሉ።

👉በየደረጃው ላሉ የፀጥታ አካላት በሰራዊቱ ውስጥ ያሉ ድክመቶችን እንዲያርሙ እና ጥንካሬዎችን እንዲያጠናክሩ ውይይቱ የሚቀጥል ይሆናል።

👉የተሳካ የህግ ማስከበር እንዲኖር በትብብር መስራት ይጠበቅብናል።

👉በሰላማዊ መንገድ እጂ የሰጡ ታጣቂዎችን ወደ ተሀድሶ ማሰልጠኛ ለማስገባት ልዩ ትኩረት ማድረግ አለብን።

👉በኦፕሬሽን ወቅት የሚያዙ ግለሰቦችን ሰብዓዊ መብት ባከበረ መልኩ ተገቢው ምርመራ ሊደረግ ይገባል።


"በውስጣችን ያለን ችግር ነቅሶ በማውጣት የተጠናከረ ሰራዊት መገንባት ለነገ የህግ ማስከበር ተልዕኳችን መሰረት ነው።"የአብክመ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደስየ ደጀን

ሰራዊቱ በሎጀስቲክም ሆነ በአቅም የተጠናከረ እንዲሆን አስፈላጊው ተግባር እየተከናወነ ነው ያሉት ኮሚሽነር ደስየ ደጀን በመካከላችን የሚስተዋሉ ትንንሽ ችግሮችን በመፍታት ለዘላቂ ግዳጅ መዘጋጀት ይገባል ብለዋል።

በግማሽ ዓመቱ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች የተከናወኑ የህግ ማስከበር ስራዎች ጥሩ ውጤት የተመዘገበባቸው ናቸው፤ይሁን እንጂ የሚቀሩ ተግባራት ስላሉ በጠላት ስር የሚገኙ አካባቢዎችን ሙሉ ለሙሉ ነፃ ለማድረግ የእርስ በርስ ከቅንጂትን ከቆራጥነት ጋር አጣምሮ በመርህ ተግባራዊ በማድረግ መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ አሳስበዋል።

ኮሚሽነር ደስየ አክለውም ሙያና ኃላፊነታችንን የሚመጥን ተግባር በመፈጸም ህዝባችን የሰላምና ልማት ተጠቃሚ ይሆን ዘንድ የህግ ማስከበር ተግባራችንን በተገቢው መንገድ መወጣት በየደረጃው የሚገኙ አመራርና አባላት ድርሻ ነው ብለዋል።

የሎጀስቲክ፣የስነ ምግባርና መሰል ችግሮች በአባላቱ ውስጥ የሚስተዋሉ ዋና ዋና ችግሮች መሆናቸው ከተወያዮቹ የተነሱ ሲሆን እነዚህንና የመሳሰሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የታቻላቸውን እያደረጉ እንደሚገኙም ነው ኮሚሽነር ደስየ በምላሻቸው የገለፁት።


ወደ ሠረግ ሲሄዱ በተፈጠረ የትራፊክ አደጋ ጉዳት ደርሷል።

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ድሬ ቀበሌ ከተባለ ቦታ በጥር 18/2017 ዓ.ሞ አ/አ ታርጋ-03 -75745 የሆነ የጭነት መኪና ለሰርግ የሚሄዱ ሰወችን ጭኖ ከምንጃር ወደ ድሬ ቀበሌ እየሄደ እያለ ከቀኑ 8:00 ላይ ተሽከርካሪው በመገልበጡ አንድ ሰው ሲሞት 05 ሠው ላይ ከባድ ጉዳት 11 ሠው ላይ ቀላል ጉዳት በትራፊክ አደጋ በመድረሱ ከባድ ጉዳት የደረሠባቸው በአረርቲ ሆስፒታል አየታከሙ መሆናቸውን የወረዳው ፖሊስ መረጃውን አድርሶናል።
ጥር ወር የሠረግና የበዓል ወቅት ከመሆኑ በተጨማሪ አርሶ አደሩ ምርት ሠብስቦ የሚሸጥበት ወደ ተለያዩ ቦታ የሚንቀሳቀስበት ዘመድና ወዳጅ የሚጠይቅበት በመሆኑ የትራፊክ ፍሠቱም የሚባዛበት የጭነትም የህዝብ ተሽከርካሪዎች ላይ አላግባብ ሠው የሚጫንበት ነው።
በዚህ ምክንያት አደጋወች ከመቼውም ጊዜ በቁጥር ጨምረዋል ተበራክቷል በሠውና በንብረት ላይ ከወትሮው በተለየ አሠቃቂና አሰከፊ አደጋዎች ደረሰዋል። በአደጋዎቹ ምክንያት የብዙ ሠው ህይወት መጥፍት የሠው አካል መጉደል የንብረት ወድመት ደርሷል።

የአደጋወቹ መንስኤ የአሽከርካሪዎች የጥንቃቄ ጉድለትና ሀላፊነትን በአግባቡ አለመወጣት መዘናጋት በመሆኑ ሌሎች አሽከርካሪዎች ከተፈፀሙ አደጋወች ትምህርት በመውሠድ አስከፊ አደጋ እንዳይደረስ በመጠንቅና በማሽከርከር አደጋን በመከላከል የሠው ህይወትና ንብረትን ልንታደግና ልንጠብቅ ይገባል።

መረጃው፦ከሠሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የኮሚኒኬሽንና ሚዲያ ኀላፊ ነው።


ኮሩ የሰላም አማራጭ ባልተቀበሉ ፅንፈኞች ላይ እርምጃ ወስዷል።

አማራ ፖሊስ፦ጥር 18/2017 ዓ.ም

በሰሜን ጎጃም ዞን የምስራቅ ዕዝ ኮር ሰሞኑን ባደረገው ስምሪት የሰላም አማራጭ አልቀበልም ባሉ የፅንፈኛው ታጣቂዎች ላይ እርምጃ በመውሰድ በርካቶችን ሙት በማድረግ ትጥቆችንና ሎጅስቲክሳዊ ማቴሪያሎችን መማረክ ችሏል።

የፅንፈኛው አባላት በጎጅ ቆለላ ወረዳ በዋሽራ ቀበሌ አካባቢ በአራት አቅጣጫ የመሪያቸውን ደም ለመመለስ አስበው ትንኮሳ ቢሞክሩም ሰራዊታችን ባደረገው ፀረ-ማጥቃት እርምጃ በአራቱም አቅጣጫ የመጣውን ፅንፈኛ ሃይል መደምሰስ መቻሉን የምስራቅ ዕዝ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል አለሜ ታደለ ገልፀዋል፡፡

ኮሩ በሰሜን ጎጃም ዞንና ባህር ዳር ዙሪያ ግንደሎሚ፣ ጎንጂ ቆለላ ወረዳ ዋሽራ ቀበሌ ባደረጉት ስምሪት 41 የፅንፈኛው አባላትን በመደምሰስ፣ 30 ክላሽ፣ 21 ኋላ ቀር መሳሪያ፣ 02 የእጅ ቦምብ፣ 05 ትጥቅና የተለያዩ ወታደራዊ አልባሳት መማረክ ተችሏል።

ዘገባው-የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነው።


የ 85 ኛው የአገው ፈረሰኞች ማህበር ክብረ በዓል በሰላም እንዲከበር በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራ መደረጉን የአዊ ብሄረሰብ አሰተዳደር ፖሊስ መምሪያ ኮማንደር እሱባለው መኮነን አስታወቁ።

ጥር 23/2017 ዓ.ም ከበዓል ጋር በተያያዘ ሊፈጠሩ የሚችሉ ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ተገቢ የሆነ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የብሄረሰብ አስተዳደር ዞኑ ፖሊስ መምሪያ ኀላፊ ተናግረዋል።
የአገው ህዝብ ለሰላም ተባባሪ ነው የሚሉት ሀላፊው አሁንም በዓልን ምክንያት በማድረግ የሚከሰቱ ጥቃቅን ወንጀሎችን ህብረተሰቡ ከፀጥታ ሀይሉ ጋር ተቀናጅቶ በመስራት እንዲከላከል ጥሪ አቅርበዋል።
በበዓላት ወቅት፣የስርቆት፣የማጭበርበርና ሌሎችም ወንጀሎች እንዳይፈፀሙ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን ይህንን ክልከላ በመተላለፍ ወንጀል ከተፈፀመ ምርመራውን በተገቢው መንገድ የሚያጣራ የምርመራ ቡድን የተቋቋመ መሆኑን ገልፀዋል ።
ወንጀልን ለመከላከል ከፍተኛውን ድርሻ የሚወስደው የማህበረሰቡ ተሳትፎ እንደሆነ የጠቆሙት ሀላፊው በማነኛውም ቦታ ፀጉረ ልውጦችን ሲያገኝ ለፀጥታ መዋቅሩ መረጃ በመስጠትና በመጠቆም የህግ የበላይነት መከበር የዘወትር ትብብርዎን ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።

በየትኛውም አካባቢ 85ኛው የአገው ፈረሰኞች በዓል ወጉንና ባህሉን ጠብቆ በሰላማዊ መንገድ ማህበረሰቡ እንዲያከናውን ያነሱት ሀላፊው ማህበረሰቡ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ 85ኛው የአገው ፈረሰኞች በዓል እንዲያሳልፍ መልዕክት አስተላልፈዋል።
መረጃ፦የአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ፖሊስ ሚዲያና ኮሚኒኬሽን ዋና ክፍል ነው።


በሰራባ የስልጠና ማዕከል የመንግሥትን የሠላም ጥሪ ተቀብለው የተሃድሶ ስልጠና ሲሠለጥኑ የቆዩ ታጣቂዎች ተመረቁ።

አማራ ፖሊስ ፦ጥር 18/2017 ዓ.ም
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ በሰራባ የስልጠና ማዕከል የመንግሥትን የሠላም ጥሪ የተቀበሉ ከ1 ሽህ 490 በላይ ታጥቀው በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ወደ ተሃድሶ ስልጠና መግባታቸው ይታወሳል። ስልጠናውን በማጠናቀቅም ተመርቀዋል።

ሰልጣኞቹ ከአንድ ዓመት በላይ በተሻገረው የአማራ ክልል ግጭት ሰባዊ ቀውስና ቁሳዊ ውድመት መድረሱን ጠቅሰው ፤ በድርጊቱም መፀፀታቸውን ተናግረዋል።

የተፈጠረው ግጭት የአማራን ሕዝብ የማይገባ ዋጋ አስከፍሎታል የሚሉት የተሃድሶ ሰልጣኝ ተመራቂዎቹ የአማራ ሕዝብ የሰላም ረፍት እንዲያገኝ የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።

የተበደለውን ሕዝብ ለመካስና ሠላምን ለማረጋገጥ እንሠራለን ብለዋል።

በምረቃው የተገኙት የሀገር ሽማግሌዎችም የሰላም ጥሪን የተቀበሉ ወጣቶች በሰራባ የስልጠና ማዕከል የተሃድሶ ስልጠና ወስደው በመመረቅ ወደ ሠላምና ልማት መመለሳቸው የሚበረታታና ለሌሎች ትምህርት የሚሰጥ ነው ብለዋል።

በስልጠና ማዕከሉ ለተሃድሶ ሰልጣኞች አስፈላጊው አቅርቦት ሲከናወን መቆየቱን ያነሱት የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ ምክትል ኃላፊና የስልጠና ማዕከሉ አስተባባሪ ነጋ ብርሃኑ ስልጠናው የሠልጣኞችን አቅም ለመገንባት ያስቻለ መሆኑን ገልጸዋል።

የርእሰ መሥተዳደር ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊና የሰራባ ስልጠና ማዕከል አስተባባሪ አበባው አምባዬ የመንግሥትን የሠላም ጥሪ የተቀበሉ ታጣቂዎች የተሃድሶ ስልጠናቸውን በአግባቡ መውሰዳቸውን ገልጸዋል።

አስተባባሪው ሠልጣኞች የክልሉን ሕዝብና መንግሥት መካስ የሚያስችል ተግባር ለመከወን መዘጋጀታቸውንና ለዚህም መተማመን ላይ መደረሱን አስገንዝበዋል።

#አሚኮ


የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው በቡርቃ የተሃድሶ ማዕከል ስልጠና የወሰዱ ታጣቂዎች ተመረቁ።

አማራ ፖሊስ፦ጥር 18/2017 ዓ.ም

የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው በቡርቃ የተሃድሶ ማዕከል ስልጠና ሲወስዱ የቆዩት ታጣቂዎች በተሳሳተ መንገድ የበደልነውን ማኅበረሰብ ለመካስ ተዘጋጅተናል ብለዋል።

በክልሉ ከአንድ ዓመት በላይ በዘለቀው ግጭት ታጥቀው ወደ ጫካ የገቡ ታጣቂዎች ወደ ሰላም እንዲመጡ ሕዝብ እና መንግሥት ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ ሲያቀርቡ ቆይተዋል። በተለያዩ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ በርካታ ታጣቂዎችም የሰላም ጥሪውን ተቀብለው ወደ ተሃድሶ ማዕከላት መግባታቸው ይታወሳል።

በአማራ ክልል ከሰሜን ወሎ፣ ከደቡብ ወሎ፣ ከሰሜን ሸዋ፣ ከዋግ ኽምራ ብሔረሰብ እና ከኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩት ታጣቂዎች በቡርቃ የተሃድሶ ማሰልጠኛ ማዕከል በመግባት ስልጠናቸውን አጠናቅቀው ተመርቀዋል።

ታጣቂዎቹ የአማራን ሕዝብ ጥያቄዎች ለማስመለስ በሚል ወደ ጫካ መግባታቸውን ጠቅሰው የተከተሉት መንገድ ግን የተሳሳተ እንደ ነበር አመላክተዋል። በትጥቅ ትግሉ ምክንያት የመጀመሪያው ተጎጂ የክልሉ ሕዝብ በመኾኑ የሰላም መንገድን እንደመረጡም ተናግረዋል።

በስልጠና ቆይታችንም የሕዝብ ጥያቄ በዚህ ሁኔታ እንደማይመለስ ተገንዝበናል ብለዋል። በቀጣይ እስከዛሬ የበደልነውን ማኅበረሰብ ለመካስ ተዘጋጅተናል ያሉት ታጣቂዎቹ የክልሉ መንግሥት ስልጠናውን በማመቻቸት ላደረገላቸው ድጋፍም አመስግነዋል።

የአማራ ክልል ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኀላፊ ደጀኔ ልመንህ የክልሉን መንግሥት እና ሕዝብ የሰላም ጥሪ ተከትሎ በርካታ ታጣቂዎች ወደ ስልጠና ማዕከል እንዲገቡ እየተደረገ መኾኑን ገልጸዋል።

ስልጠናውን ያጠናቀቁ የቀድሞ ታጣቂዎችም በቀጣይ ወደ ማኅበረሰቡ ሲቀላቀሉ የሰላም አምባሳደር ኾነው እንዲሰሩ የሚደረግ መኾኑን ያነሱት ምክትል ቢሮ ኀላፊው በጫካ የሚገኙ ሌሎች የታጠቁ ወገኖችም የሰላም አማራጭን እንዲቀበሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በስልጠናው ማጠቃለያ መርሐ ግብር ላይ የተገኙት በሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል አሰፋ ቸኮል በበኩላቸው ሰላምን መምረጥ የታላቅነት መገለጫ መኾኑን ጠቁመዋል።

ሌተናል ጄኔራል አሰፋ ቸኮል በጫካ የሚገኙ ሌሎች ታጣቂዎችም የሰላምን መንገድ መርጠው ለሕዝብ እፎይታ እንዲሰሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
#አሚኮ


የፍትሕ ተቋማት የመንግሥትን እና የሕዝብን ጥቅም ማስከበር ይጠበቅባቸዋል።

አማራ ፖሊስ፦ጥር 18/2017 ዓ.ም
የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የግማሽ በጀት ዓመቱን የመደበኛ እና የትራንስፎርሜሽን እቅድ አፈጻጸም የፍትሕ አካላት በተገኙበት ግምገማዊ የውይይት መድረክ በደብረ ብርሃን ከተማ እያካሄደ ይገኛል፡፡

በመድረኩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ኀላፊ ብርሃኑ ጎሽም የፍትሕ ተቋማት የመንግሥትን እና የሕዝብን ጥቅም ለማስከበር መሥራት ዋና ተግባራቸዉ ሊኾን እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በክልሉ በተፈጠረዉ የሰላም እጦት ሳቢያ በሕግ ቁጥጥር ስር የሚገኙ ተጠርጣሪዎች ላይ የመርማሪ ቡድን በማዋቀር እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

ያለአግባብ የመንግሥትን ሀብትን ያባከኑ እና የሕዝብ ጥቅምን የተጋፉ አካላት ላይም በሕግ ተጠያቂ እንዲኾኑ የማድረግ ሥራ መሠራቱንም አንስተዋል፡፡

ለአብነት በሕገወጥ መንገድ በቤት ማኅበር በደላሎች የተደራጁ እና መሬት ያለአግባብ በጥቅም አሳልፈዉ የሰጡ አካላት ላይ ሕጋዊ ርምጃ መወሰዱን ጠቅሰዋል፡፡
#አሚኮ


በአብክመ ፖሊስ ኮሚሽን ተቋማዊ የሪፎርም ዳሰሳ ጥናትና ፍኖተ ካርታ ሰነድ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ተካሄደ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን እንደተቋም የተለያዩ ተቋማዊ የሪፎርም ተግባራትን ያከናወነ ሲሆን በእነዚህና በነበረረው የህግ ማስከበር ተግባራት ዙሪያ የየዞኖቹ የመደበኛና የአድማ መከላከል ፖሊስ አመራሮች በተገኙበት ውይይት ተደርጓል።

በህግ ማስከበርና በመደበኛ ተግባራት የተከናወኑ ተግባራትን አስመልክቶ መነሻ ሰነድ ያቀረቡት የአብክመ ፖሊስ ኮሚሽን ዕቅድና ዝግጅት መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ምክትል ኮማንደር ዘመን ዩሐንስ እንደተናገሩት ባለፈው ግማሽ ዓመት ውስጥ ከመደበኛ ተግባራዊ ጎን ለጎን በመስዕዋትነት የታጀበ በርካታ የህግ ማስከበር ተከናውነዋል፤ጥሩ ውጤትም ተመዝቦባቸዋል ብለዋል።

በመደበኛ የፖሊስ ተግባራትም ከወቅቱ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ ጫናዎች ቢኖሩም የተሻሉ ስራዎች ተሰርተዋል።በተለይም በወንጀል ምርመራ ስራ ላይ ከበፊቱ በበለጠ ሁኔታ በርካታ የምርመራ መዝገቦች መመዝገባቸውን ነው ሰነዱ ያመላከተው።

በህግ ማስከበር ረገድም የህዝብ ለህዝብ ውይይትና የፅንፈኛውን ሴል በመጣጠስ በኩል የተከናወኑ የኦፕሬሽን ስራ አመርቂ ውጤት ታይቶበታል ነው ያሉት ምክትል ኮማንደር ዘመን ዩሐንስ።


የአማራ ክልል ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ባለፉት 6 ወራት ውስጥ በተከናወኑ የህግ ማስከበር አፈፃፀም ዙሪያ ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጋር ግምገማ አካሂዷል።
በክልሉ ውስጥ የተቀሰቀሰውን የእርስ በርስ ግጭት ለማርገብ ብሎም ለመከላከል በተለይም ባለፉት 6 ወራት ውስጥ በክልሉ የፀጥታ ኃይል የተከናወኑ የህግ ማስከበር ተግባራት ዙሪያ መነሻ ሰነድ በማዘጋጀት ነው ግምገማው የተካሄደው።

ሰነዱን ያቀረቡት የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ በሪሁን መንግሥቱ እንደገለፁት ክልላዊ የፀጥታ ችግሮችን በክልላዊ የፀጥታ ኃይል ለመቅረፍ እንዲቻል በየደረጃው የክልሉን ሚሊሻ፣ሰላም አስከባሪ፣አድማ መከላከል ፖሊስ እና መደበኛ ፖሊስን ኀይል የማጠናከር እና የማብቃት ስራዎች በሰፊው ተሰርተዋል ብለዋል።

በዚህም ባሳለፍነው ግማሽ ዓመት በፀጥታ ኀይላችን ላይ የሚስተዋሉ የቆራጥነትና መሰል ክፍተቶች የነበሩ ቢሆንም ከውስጥና ከውጭ በሚያጋጥሙ የጠላት ኃይል ላይ ትልቅ ኪሳራ በማድረስ ጥሩ ስኬት የተመዘገበበት ነበር ያሉት ኃላፊው ከኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት ጎን ለጎን የክልሉ የፀጥታ ኀይል አይነተኛ ሚና ተጫውቷል ነው ያሉት።

ሰላምና ልማትን ለማደናቀፍ ለክልላችን ህዝብ የተቆርቋሪነት ማሊያ ለባሽ በተግባር ግን የወገኑ የስቃይ ምንጭ የሆነውን ፅንፈኛ ኃይል ላይም በተሰራ ቅንጅታዊ የኦፕሬሽን ስራ ተጨባጭ ውጤት መመዝገቡንም ነው አቶ በሪሁን መንግስቱ ያቀቡት ሰነድ የሚያስረዳው።

ባለፉት 6 ወራት ውስጥም ከተከናወኑ ስኬታማ የህግ ማስከበር ስራዎች ውስጥም የመንግስት የሰላም በር አትራፊና አዋጭ መንገድ እንደነበር በመግለፅ የጠላት ሴሎችን በመበጣጠስ ረገድም ቀላል የማይባል ውጤት ተመዝግቧል።



Показано 13 последних публикаций.