Zemedkun Bekele (ዘመዴ)


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


• ደርሻለሁ… እናንተስ…?

"…በሉ ገባ ገባ በሉና ነጭ ነጯን እንጋት።


እየሄዳችሁ…🚶‍♂‍➡️🚶‍➡️

"…ወደ ቲክቶክ መንደራችን እየሄዳችሁ ጠብቁኝ… መጣሁ…

• አላችሁ አይደል…?


ግደለኝ አልኩህ… እኮ
ከጎጃም አልወጣም
ከጮቄም አልወርድም።

"…ጎንደር፣ ጎጃም፣ ሸዋና ወሎ በስንት ድካም አንድነት ፈጠሩ። ጊዜያዊ አመራርና መሪም መርጠው መደቡ። የፈለገ ይምጣ ብለው ነበር ይሄን የወሰኑት።

"…የጎጃሙ ወኪል አስረስ መዓረይ ግን በዘመነ መመረጥ አልተደሰተም። በጎን በእነ አዝማሪዋ አልማዝ ባለጭራዋ፣ በእነ ሒዊየ ብርሃኑ፣ በእነ ሰጣርጌ፣ በእነ አማኑኤል አብነት ዘመነን እያሰደበ፣ ስኳዱም፣ እነ ባናና፣ እነ ሰሌ ባለ ሃውልቱ፣ እነ ሚኪ ጠሽ፣ እነ እሸቱ ገጠሬው፣ ከግምባሩም እነ ጃል ሃብታሙ ሳይቀር ዘመነን እየሞለጩት፣ እያዋረዱት ቆዩ። ጎጄ አልገባውም ነበር።

"…ወሎ፣ ሸዋ፣ ጎንደር አንድነቱ ይፈረም እንጂ ብለው ቢወተውቱ አስረስ ወገቤን እያለ አዛጋቸው። ተስፋ ቆርጠው ተዉት። አስረስ በደወለልኝ ጊዜ እኔም ምን አስበህ ነው ብዬ ስጠይቀው "በሻለቃ ዝናቡና ጓደኞቹ" አሳብቦ ለማለፍ ሞከረ። በጎን ግን ከፋፍዴን፣ ከእነ እስክንድር ጋር እየተደራደረ ቆየ። አንድነቱን አዘግይቶ፣ የራሱን የፖለቲካ ካፒታል ገንብቶ፣ "በቃ ዘመነ እና እስክንድር አያስፈልጉም" የሚል መንፈስ ዘርቶ እሱ ሊመረጥ ነበር ዕቅዱ። ግን ተበላ። እኔን ጣለበት። አፉ ውስጥ የገባውን የተንኮል ሥልጣን ቀማሁት።

"…ዛሬ ጎጃም ሦስቱንም ቢለምን፣ ቢወጣ ቢወርድ ወፍ የለም። የዘመነን የመሪነት ዕድል አስረስ አስበላው። ዛሬ ጎንደሬው እስክንድር ከሥልጣን ተነሣ ቢባልም የአፄ ቴዎድሮስ ምትክ ያሉት ጌታ አስራደ ወይም ጎጃሜ እንዳይቀየም ማስረሻ ይመረጣል። ከዚያ በአባይ ሸለቆ በኩል እነ አስረስ ከአሕፋድ ጋር ተጣምረው እነ ዝናቡና ዘመነን በአየር ላይ ያንሳፍፋሉ።

"…አስቀድሜ የነገርኳችሁ ነው የሆነው። በጦማር የምለው ካልገባችሁ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ቲክቶክ ላይ በዲስኩር በሚገባ አስረዳችኋለሁ።

• ዘመዴ ነኝ ከጮቄ ተራራ…

16.9k 0 0 118 752

Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
አበደን አያስጥሉህም…

"…በነገራችን ላይ ዛሬ ማታ በተለመደው ሰዓት ምሽት ላይ ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር በቲክቶክ መንደራችን ይኖረናል። ለማስታወስ ነው። ነገር ግን ሌላ ሌላውን ትተን፣ የግብፅን ቤተ ክርስቲያን ቅርሻት በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለማቀርሸት መንደፋደፉን፣ በገድል፣ በድርሳናት፣ አጠቃላይ በአዋልድ መጻሕፍት፣ በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ላይ ማላገጡን ሳንረሳ…

1ኛ፦ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋው ወራት አብን አምልኳል። ካረገም በኋላ አሁን አብን ያመልካል።
2ኛ፦ለኢየሱስ ከተዋሕዶ በኋላ አብ አምላኩ ነው።
3ኛ፦"ለሥግው ቃል አንድ ፈቃድ እንዳለው ነገር ግን የሥጋ ፈቃድ ለመለኮት ፈቃድ ለዘላለም ሲገዛ ይኖራል።
4ኛ፦"ቃል የተዋሐደው የጎሠቆለ ሰውነትን ነው"
5ኛ፦"ቃል የተዋሐደው ሥጋ ስላልተለወጠ አሁንም ያንሳል ይህ በማለት ምንታዌነትን፣ በማስተማር እስላሞችን ጭምር ጮቤ ስታስረግጥ ከአርዮስ፣ ከእነ ንስጥሮስ የከፋ ምንፍቅናን ስትዘራ ከርመህ "ለምን ባይ ጠያቂ ሲመጣ የቲክቶሎጂ ውጤት የሆኑ ብረት ገፊ፣ ወደል ወደል ጠብደል ጎረምሳ አደራጅተህ እነሱ ስር ብትወሸቅም አትድንም።

"…በጫጫታ፣ በግርግር፣ በሴራ የምትፈርስ ቤተ ክርስቲያን የለችም። በኦርቶዶክስ አባቶች ፕሮፋይል ለፕሮቴስታንት መናፍቃን ለተሃድሶ ጋለሞቶች ጩኸት ጆሮ አንሰጥም። ትመነጠራለህ፣ ትበጠራለህ፣ እርቃንህን ትቀራለህ።

"…ብዙ ሳያቸው ሉጢ የሚመስሉኝ ሰዎች በነገረ መለኮት ላይ በጣም ድፍረት ያበዛሉ። አንዴ እንደረከሱ ስለሚሳማቸው ሌላውን ለማርከስ ቅሽሽ አይላቸውም። "ስለዲያቆን" ሐዋዝ መመለስ፣ አሰግድ ሲናገር ሐዋዝ አንድ የከፋ ኃጢአት ልምምድ ላይ እንዳለና ሊጸልይለት እንደሚፈልግ ሲናገር ሰምቼዋለሁ። በጋሻው፣ ትዝታው ለምን እንደ ጰነጠጡ ሌላው ባያውቅ የምናውቅ እናውቃለን። ሜካፓሞችንም እናውቃለን።

• እኔማ አልፋታችሁም…

25.5k 0 17 306 1.2k

"…ሰው በምድር ላይ ከተቀመጠ፥ ከዱሮ ዘመን ጀምሮ፥ የኃጢአተኛ ፉከራ አጭር መሆኑን የዝንጉዎችም ደስታ ቅጽበት መሆኑን አታውቁምን? ከፍታው ወደ ሰማይ ቢወጣ፥ ራሱም እስከ ደመና ቢደርስ፥ እንደ ፋንድያ ለዘላለም ይጠፋል፤ ያዩትም፡— ወዴት ነው? ይላሉ። እንደ ሕልም ይበርራል፥ እርሱም አይገኝም፤ እንደ ሌሊትም ራእይ ይሰደዳል። ያየችውም ዓይን ዳግመኛ አታየውም፤ ስፍራውም ከእንግዲህ ወዲህ አይመለከተውም። …ክፋት በአፉ ውስጥ ቢጣፍጥ፥ ከምላሱም በታች ቢሰውረው፥ ቢጠብቀውም ባይተወውም፥ በጕሮሮውም ቢይዘው፥ መብሉ በአንጀቱ ውስጥ ይገላበጣል፤ እንደ እፉኝትም ሐሞት በውስጡ ይሆናል።

"…የዋጠውን ሀብት ይተፋዋል፤ እግዚአብሔርም ከሆዱ ውስጥ ያወጣዋል። የእፉኝትን መርዝ ይጠባል፤ የእባብም ምላስ ይገድለዋል። የማሩንና የቅቤውን ፈሳሽ ወንዞቹንም አይመለከትም። የድካሙን ፍሬ ሳይውጠው ይመልሰዋል፤ እንደ ንግዱም ትርፍ አይደሰትም። ድሀውን አስጨንቆአል፥ ትቶታልም፤ ያልሠራውንም ቤት በዝብዞአል።

"…ከብረት መሣርያም ይሸሻል፥ የናስም ቀስት ይወጋዋል። እርሱም ይመዝዘዋል፥ ከሥጋውም ይወጣል፤ ከሐሞቱም ብልጭ ብሎ ይሠርጻል፤ ፍርሃትም ይወድቅበታል። ጨለማ ሁሉ ስለ ከበረው ዕቃ ተዘጋጅቶአል፤ በሰው አፍ እፍ የማትባል እሳት ትበላዋለች፤ በድንኳኑ ውስጥ የቀረው ይጨነቅባታል። ሰማይ ኃጢአቱን ይገልጥበታል፥ ምድርም ትነሣበታለች። የቤቱም ባለጠግነት ይሄዳል፤ በቍጣው ቀን እንደ ፈሳሽ ውኃ ያልፋል። ከእግዚአብሔር ዘንድ የበደለኛ ሰው እድል ፈንታ፥ ከእግዚአብሔርም የተመደበ ርስቱ ይህ ነው።  ኢዮ 20፥ 4-29

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

31.5k 0 10 1.4k 1.3k

Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
“…ዘመዴ ሚዲያ ከነ ነጭ ነጯ ከዘመዴ ጋር እየመጣ ነው።

39.2k 0 31 516 2.3k

በዚህም ነገር እንወያይ…

"…ጠንካራው፣ ግዙፉ፣ ሕዝባዊ የነበረው የዐማራ ፋኖ በጎጃም እንዲደበዝዝ፣ ጎጃም ከሌላው የዐማራ ግዛት በተለየ መልኩ የብአዴን ሚሊሻና አድማ ብተና፣ እንዲሁም በብራኑ ጁላ ሽንኩርቴ ሠራዊት መጫወቻ እንዲሆን ተደርጓል። ከጎንደር፣ ከወሎና ከሸዋ ወንድሞቹም ኅብረት እንዲለዩ ተደርገዋል። ይሄ ብቻ አይደለም። የዐማራ ፋኖ በጎጃም የአውሮጳ አክቲቪስቷ አልማዜም ዐማራ እንዲያሸንፍ ከተፈለገ ይሄን ይቀበል የሚል ሓሳብ አቅርባለች።

፩ኛ፦ ዐማራ ግብረ ሰዶማዊነትን መቃወም የለበትም። ይሄን በመቃወሙ ምክንያት ነጮቹ ይከፋቸዋል። እንደ ትግሬና እንደ ኦሮሞ ነፃ አውጪዎች መሆን አለበት በምትለው ሓሳብ ላይ እንወያይ።

፪ኛ፦ ዐማራ የዓድዋን የድል በዓል በነጮች ፊት ማክበር የለበትም። ዐማራ አድዋን ሲያከብር የተሸነፉት ነጮች ይከፋቸዋል፣ ይናደዳሉ። ስለዚህ ጮጋ ይበል ነው የሚሉት ፍሮፌሰሯ።

፫ኛ፦ ነገሥታቱም ቢሆን አሮጌና ሽማግሌዎች ተብለው በፍሮፌሰሯ ተሰድበዋል።

"…የእኔ ጥያቄ የዐማራ ፋኖ በጎጃም የዚህች ጋለሞታን ሓሳብ ይገዛል ብዬ አላምንም። ነገር ግን የዐማራ ፋኖ በጎጃምን መሳሳት፣ ያን ገናና ስም መቀበር፣ መሸፈን ስናይ፣ ደግሞም በዚህች ጋለሞታ ዙሪያ የተኮለኮሉትን ጢም አልቦ ሴት ወይዘሮ የመሰሉ፣ እነ እስማኤል ዳውድ ኢድሪስ፣ እነ አማኑኤል አብነት፣ እነ ከፍያለ ጌቱ፣ እነ ሰጣርጌን ወዘተ ስንመለከት ብንጠረጥር የሚፈረድብን አይመስለኝም። በጎጃም የኦርቶዶክሳውያንን መረሸን ስንመለከትም ስጋት ጥርጣሬአችን ይጨምራል።

•እንወያይ… ዐማራ በዚህ ልክ መሰደብ አለበት ወይ? ዐማራ በዚህ ልክ የግድ ከባህል ከሃይማኖቱ ውጪ በግድ መቀበል አለበት ወይ? ተወያዩ።

• በተለይ የጎጃም ዐማሮች ሓሳብ ስጡበት። ይሔን የአክቲቪስታችሁን ሓሳብ እንዴት አያችሁት? ተንፒሱ…✍

• ዘመዴ ነኝ ከጮቄ።

41.8k 1 26 316 1.4k

ችግርማ አለው…

"…ሰፋ ያለ ሱሪ፣ ታይት አድርጋችሁ ወደ ቅዱስ ቁርባን ቅረቡ። ጥፍር ቀለም፣ ዊግ፣ አርቴፍሻል ጥፍር፣ ቀለማ ቀለም ተቀብታችሁ ወደ ቅዱስ ቁርባን ቅረቡ አላለም ይሄ የግብፅ ቅጥረኛ የሰው ስልባቦት። የፕሮቴስታንት ቸርች እኮ አይደለችም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን።

"…ይሄ ልክ አይደለም ስትለው አኬ ሰልባቦት ሳይሆን መንጋው ግርር ብሎ ውይ አኬን አትንካብኝ ይለሃል። እኔም ጭንብል ገፋፊ ነኝ። ከነከስኩ ነከስኩ ነው። በሃገርና በሃይማኖቴ ድርድር አላውቅም። ስትፈልግ በአናትህ ተትከላታለህ እንጂ በህይወት እያለሁ አንድም ጨምላቃ ዕድልና ቦታ አልሰጠውም።

"…ለባለጌ ትሁት ምናምን መሆን አያስፈልገኝም። ለባለጌ፣ ለአስመሳይ፣ ለቀጣፊ፣ ለአጭቤ መናፍቅ ወርጄ ነው የማናግረው። ለዚህ ኮተታም የምን መቅለስለስ ነው። ለዚህ ራሱን ከሲኖዶስ በላይ አድርጎ ለሚቆጥር ሰው የምን መቅለስለስ ነው።

• ቲክቶሎጂያም ሁላ… ቀለምህን ነው የምሀፈው።

40.2k 0 104 254 1.4k

"…አባቴ ነጠላ መልበስ ብቻውን በቂ አይደለም። ትተፋታለህ። መርዟን ትተፋታለህ። ይሄን ልጅ ስትቆጡት ሦስት አካላት ይጮሁባችኋል።

፩ኛ፦ ተሃድሶ መናፍቃን
፪ኛ፦ በልጻጊ መናፍቃን
፫ኛ፦ የጃንደረባው ትውልድ አባላት።

"…እኔ በደንብ ነው የማውቃቸው። በጆሮ አቀማመጣቸው፣ በአፍንጫቸው፣ በረጅምና ጥቁር ምላሳቸው፣ በአጭቤ ዓይናቸው ነው የምለያቸው። የቲክቶሎጂውንም፣ የቲኦሎጂውንም ትውልድ አሳምረን ነው የምናውቀው።

"…ደፋር… ምንም አደባባይ ላይ ተው የሚል ተቆርቋሪ አካል ቢጠፋ፣ በቃ ቢጠፋ ሰው ባይኖር እንኳ እንዲህ በቀላሉ የምታማስለው ቤት አይደለም ቤተ ተዋሕዶ። ጭበጫባ የሰቀለውን ጭበጨባው ሲቀር ቀስስ ብሎ ይወርዳታል። የእነ ቲቲ፣ የእነ ቤቲ፣ የእነ ሳሚ፣ የእነ ሚኪ ድጋፍ ከቲክቶክና ከፌስቡክ ዘልሎ ወንዝ አያሻግርም።

"…ደግሞ እኮ አኬን አትናገረው ይበላልኛላ…😂 እወቅጠው። ሊበላ…? መጣሁ…

39.8k 0 12 255 1.4k

Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
"…በሉ ለ318 ቱ ሊሞላ 1 ሰው ነው የቀረው። አሱም ቆይቶ ይሞላል። አሳሳቢም አይደለም።

"…አሁን ግን ሳይመሽብን በጊዜ ወደ ሰሞኑ አጀንዳዎች እንመለከትና ወደ ጭምል ገፈፋዬ ልግባ። እንደፈረደብኝ የአዳሜንና የሔዋኔን የበግ ለምድ ልገፍፈው ነኝ።

"…እኔ ትንሽ መብረቅ ነው ብልጭ የማደርገው። እናንተ ስትፈልጉ በበፓውዛ መብራት አልያም በጠራራ ፀሐይ ፈልጉአቸው። ተመራምራችሁ ድረሱባቸው።

"…እኔ አዕምሮአችሁ ላይ እሠራለሁ። እናንተ ስትነሡ፣ ስትተኙም፣ ስትራመዱም፣ ስትቀመጡም አንሰላስሉት፣ ነገርየውን አላምጡት፣ አውጡት አውርዱት፣ አላምጣችሁ ስትጨርሱ ዋጡት ወይ ትፉት።

"…ተግባባን አይደል? ለእናንተ ቀድሞ የሚታየው ቆንጆ ነገር ለእኔ ካልታየኝስ? ለእናንተ የታየው መጥፎ ነገር ለእኔ ካልታየኝስ። ቆይቶ ልትደርሱበት፣ ልንደርስበት መጀመሪያ ከምንጣላ ብንመራመርበት ምን ይለናል?

• ተመልሼ እመጣለሁ።

38.5k 1 41 67 1.1k

ለማሳወቅ ያህል…

• መልእክቱ የተለጠፈው ለ287 ሺ ሰው ነው።
• የሚፈለገው 6 ሰው ነው።
• መልእክቱን ያነበበው 6ሺ 9 መቶ ሰው ነው።
• እስከ አሁን የመጣው 4 ሰው ነው።
• የሚቀረው 2 ሰው ነው።
• 3 ወንዶች እና 1 ሴት ተመዝገበዋል። በተለይ አንደኛው ከሀገረ እንግሊዝ ለዘመዴ ሚዲያ በእጅጉ የሚያስፈልግ ባለሙያ ነው።

"…በዚህ ልጥፍ ላይ ልጥፉ ባያስቅም 7 ሰዎች ግን በሳቅ 😁 ገልፍጠው ፍርፍር ሲበሉ ታይተዋል። የሚስቁትስ እሺ ይሁን ማሽላ እያረረም ይስቃል እንበል የሚገርመኝ በዚሁ ልጥፍ ላይ 7 😡 ብው ብለው የተናደዱቱ ሰዎች ናቸው። ኧረ ቀስ ቀስ ኦንዲሜና ኢቶቼ። ቀስ ቀስ በሉ ስኳር፣ ልብድካም፣ ደምግፊት የሚባል ነገር እኮ አለ። ቀስ። ከሁሉ ከሁሉ የሚያስቁኝ ደግሞ አሉ ጠዋት ጠዋት እንደምን አደራችሁ ስል ልክ እንደ ሰላምታ እነርሱም ሳያቋርጡ ጠዋት ጠዋት ተነሥተው 😡 ብው የሚሉ። ምን ዓይነቶቹ አጋንንታም ናቸው ባካቹ።

• በጣም ነው እንዴ የማበሳጫቸው?

37.1k 0 6 35 1.1k

ከወጋችን በፊት…6 ሰው ይፈለጋል።

"…ዘመዴ ሚዲያ ለሚፈልጋቸው 300 ሠራዊተ ጌዴዎን ዘ-ኢትዮጵያ መሥራች አባላት ምልመላ ጥሪ አድርጎ ነበር። በተደረገው ጥሪ መሠረትም 300 ሠራዊተ ጌዴዎን በሰዓታት ውስጥ በፍጥነት ተመዝግበዋል። በዚህ መሃል ግን ከ300ው በተጨማሪ 12 ሰዎች ቁጥራቸው ከ300 ው ሠራዊት ሆኖ በትርፍ በተጠባባቂ ተመዝግበውም ነበር። ነገር ግን ይህን ያዩ ንስር ዓይኖች "…ዘመዴ 312 ሠራዊተ ጌዴዎን ከምትሆኑ ሦስት መቶው እንዳለ ሁኖ አሥራ ሁለቱ ላይ ስድስት ጨምራችሁ 318 ብትሆኑ በብዙ ነገር ምስጢር ይገጥማል።" የሚል ሃሳብ አቀረቡ። እኔም ሓሳቡን ገዛሁት።

"…ስለዚህ 300 ሠራዊተ ጌዴዎን ቢሉ ወይም ሠለስቱ ምዕት ለ318ቱ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን መታሰቢያቸው ይሆናል ማለት ነው።" ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና።" ማቴ 18፥20። ለ318ቱ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ዘመን በኒቂያ ለመሰብሰባቸው ዋነኛው ምክንያት የአርዮስ የክህደት ትምህርት ነበር። በመጀመሪያ ደጋግመው በቃል መከሩት፣ አስተማሩት እምቢ ብሎ በክህደቱ ሲጸና አልመለስም ሲል ጉባኤ ሠርተው አወገዙት። ለዩት።

"…ኋላም ሠለስቱ ምዕት ከጉባኤ ኒቂያ በኋላ ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን በሚገባ አደራጁ። ጸሎተ ሃይማኖትን ለመንግሥቱም ፍፃሜ የለውም እስከሚለው ድረስ ጽፈው ዐወጁ። በስማቸው የሚጠራም ሥርዓተ ቅዳሴ አዘጋጁ። እንዲያው በየሰበባ አስባቡ፣ በየምክንያቱ የቀደሙ አባቶችን እናስታውስ፣ እነዘክራቸው ብዬ እንጂ የእኛ ስብስብ እንደ ኒቅያ ጉባኤ አባቶች ያለ ስብስብ ነው ማለት አይደለም። አይሆንምም። በረከታቸው እንዲያድርብን ግን ሠለስቱ ምዕትን ከሠራዊተ ጌዴዎን ጋር ብናስታውስ ምን ይለናል? ምንም። በሉ 6 ሰዎች አለሁ በሉን። ሠራዊቱንም ተቀላቀሉ።

• ፍጠኑ።

37.3k 0 7 64 1.2k

መልካም…

"…ዛሬም በኢትዮጵያ ጎጃም ጮቄ ተራራ ላይ ነው ያለሁት። ቅዳሜ ከሰዓታችንን እኔ ከጮቄ እናንተ ደግሞ ካላችሁበት ሥፍራ ሆናችሁ አጫጭር ውይይቶችን በማድረግ፣ ጥቂት ነቆራዎችንም በማከል፣ ያለበዙ ምክሮች፣ አስፈላጊ ናቸው ብዬ ያመንኳቸውን መልእክቶች ወደ እናንተ በማድረስ አብረን እናሳልፋለን።

"…የዛሬው ግጥም እና መሰንቆ አዝማሪም የለውም። የጮቄ ብርድ በካቲካላ፣ በድንች፣ ጾሙ እስኪገባ በጎጃም ጮማ እየተከላከልኩ እቆያለሁ። ጮቄ ላይ ሆኜ፣ ጎጃም ሙሉውን፣ ጎንደር፣ ትግራይ፣ ወሎና ሸዋም ወለል ብለው ነው የሚታዩኝ። ከዚያም አልፎ ወለጋ፣ ተሻግሮ ጅማ ጌራ ወረዳ ድረስ የሚሆነው ሁሉ ይታየኛል። ጮቄን የመሰለ ሥፍራ ማግኘት መታደል ነው።

"…የእናንተም ተሳትፎ ወሳኝ ነው። ዝም ጭጭ ብሎ ነገር የለም። ብቻዬን ማውራትም የለብኝም። በጨዋ ደንብ ተሳተፉ። እንወያያለን። በደንብ ነው የምንወያየው። ጥያቄ ካለ መልሱ። ሓሳብ ስጡ። አትፍሩ፣ አትቅለስለሱ።

"…ከጎጃም አልወጣም። ከጮቄም አልወርድም። አላችሁ አይደል? ልቀጥል?


“…ሰላምና ደኅንነት ነው ሲሉ ያን ጊዜ ምጥ እርጕዝን እንደሚይዛት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል ከቶም አያመልጡም። 1ኛ ተሰ 5፥3

• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?

• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ ‼

40.6k 0 6 1.4k 1.3k

መልካም…

"…የዛሬ ወር ከምናምን ወደ ጎጃም ምድር ስገባ የዐማራ ፋኖ በጎጃም ሊጠፋ የደረሰ ነጥብ አክሎ ነበር የሚታየው። ያ ግዙፍ፣ የጀግና ዐማሮች ስብስብ፣ ያ የጀግናው በላይ ዘለቀ ልጆች ተቋም ተውጦ ሊዋጥ የደረሰ ተቋም ነበር።

"…ስኳድ፣ ኦሮሙማው፣ ሸንጎ፣ ወያኔና ሸአቢያ፣ ግንቦቴ፣ ፋፍህዴን፣ አሕፋድ ወዘተ የዐፋጎን አመንምነውት ነበር። በድፍረት ጎጃም መግባቴን ተከትሎም በተለይ አዝማሪዋ ለተቋሙ አስባ ሳይሆን 16 የጎጃም ዐማራ ወጣቶችን አስይዛ፣ 13ቱን አስረሽና ሦስቱ አምልጠው ሁለቱ በድጋሚ ተይዘው አንደኛው ልጅ መትረፉን መዘገቤን ተከትሎ በመደንገጧ ነበር ጨርቋን ጥላ አብዳ ሁሉንም ያሳበደቻቸው። ለእኔ ግን ተናግሮ አናጋሪ እፈልግ ስለነበር እንደልቤ ለመሆን ረድቶኛል።

"…መረጃ ቲቪን አሸብረው፣ አስጨንቀው አጣብቂኝ ውስጥ ከትተው እየዬ ቢሉም ሊያስቆሙኝ አልቻሉም። ደግነቱ መሬት ላይ ያለውም ኃይል፣ በውጭ ያለውም የጎጃም ዐማራ የእኔን ግግም ማለትና እየቆየ ሁኔታውንም ሲረዳ ወደ መሬትም በመደወል እውነታውን በማረጋገጡ የዐማራ ፋኖ በጎጃምን ከውድቀት ታድገውታል።

"…በዛሬው የፎቶ ምስሌ ላይ ባለፈው ጊዜ ነጥብ ያሳከልኩትን የዐፋጎን ሎጎ ዛሬ ትንሽ ጎላ ለማድረግ ተገድጃለሁ። አሁን መሬት ላይ እየተናበቡ ነው። ሌባውና ባንዳው እየተለየ ነው። መሞት ቀርቷል። በቀጣይ ደግሞ የተዋጡት የጎጃም ዐማሮችና በሓሳብ አሸንፈው ከወሎ፣ ከጎንደርና ከሸዋ ወንድሞቻቸው ጋር አንድነትን ይፈጥራሉ ብዬ አምናለሁ።

"…ለውጥማ አለ። ስንዴው ከግርዱ፣ ብርሃን ከጨለማው፣ ጀግናው ከባንዳው፣ ፍጥጥ ብሎ እየተለየ ነው። እኔም እነ መዓረይን፣ አበጀ በለውን፣ ዘውዳለምን፣ እነ ጥላሁን አበጀን፣ ሁለቱን ፓስተሮች ልክ ሳላስገባ ከጎጃም አልወጣም፣ ከጮቄም አልወርድም። ምንአባህ እንደምታመጣ አያለሁ።

• ሓሳብ ስጡበት…✍✍✍

42.6k 1 16 149 1.8k

👆④ ✍✍✍

"…የጎጃሙ አገው ሸንጎ፣ የጎንደሩ ስኳድ፣ ከወሎው እና ከሸዋው የእስክንደር ቡድን ጋር ተናበው ነው የሚሠሩት። ምንአልባትም አሁን ከጃዋር መሀመድ ጋር በለስ ከቀናን አብረን ወደ ሥልጣን እንመጣለን ብለው የሚያስቡ ሁላ አልጠፉም። አዳዲስ አጀንዳ ተፈብርኮ ለሕዝብ በመሥጠት ሻአቢያ፣ ስልጤ፣ ትግሬና ኦሮሞ፣ ስኳድና የአገው ሸንጎ መከራ እየበሉ ነው። የሰሞኑ የአረብ ሀገር የዐማራ እገታና የኦሮሞ እገታ ሁሉንም ፀረ ዐማራ ኃይሎች አንድ ላይ አሰባስቦአቸዋል። የኦሮሞ ወኪሎቹ እነ ጂጂ ኪያ ከጀርመን፣ እነ ሚኪ ጠሽ ስኳድ የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላዎቹ ከጀርመን፣ እነ ጃል ሀብታሙ በሻ ከአማሪካ፣ እነ ስልጤ ኦሮሞ አገው ሙባረክ ከአዲስ አበባ፣ እነ ሲቪል ዋር ቀስቃሾቹ አጀንዳ የጠረረባቸው የሂዊ ወኪሎቹ አኪላና ዘርሽ ከአማሪካ፣ እነ ስኳድ ባናና፣ ዐማራ ዛሬ፣ የኒ ማኛ፣ ኪያ፣ ሄለን ባለ ግዙፍ መ*መጫዋ፣ እነ ጋሽ ቤታ፣ ኧረ ምን ቅጡ። ከሞጣና ከብሪጅ ስቶን በቀር ሌሎቹ በሙሉ ዋይዋይ ሲሉ ነው የከረሙት። ስለዚህ ነገ በሰፊው እንወያያለን። የጠረረውን የቲክቶክ ተመልካች በጥቅሴ እየነዱ አመጡት።

"…በዓረብ ምድር የአጋች ታጋቹን ድራማ ሻአቢያ፣ የወያኔ ኤጀንቶቹ ዋን አዋራዎች፣ ከጎንደር ስኳድ፣ ከጎጃሙ አገው ሸንጎና፣ ከኦሮሞው ኦነግ ጋር እንዴት አድርገው ፒፕሉን ፊንታ እንደሠሩት እያየሁ በሳቅ ፍርፍር አምሮች ትናንት ስበላ ነው የዋልኩት። እሱን ነገ እመለስበታለሁ። ስልጤ ሙባረክ እንኳን ከአቅሙ የዐማራውን የሳይበር መንጋ እንዲህ ይንዳው? ጉድ እኮ ነው። 😂 እሱን ነገ በሰፊው እንመለስበታለሁ። በርእሰ አንቀጹ ላይ ጠቀስ አርጌው ግን አልፌአለሁ።

"…የጎጃሙ ኃይል አክቲቪስቶች መሪ ፍሮፌሶር አዝማሪት አልማዝ ዳኛቸው ዘውዴ መገርሳም ፈረንጆቹ ደስ እንዲላቸው ዐማራም እንደ ትግሬና ኦሮሞ ታጋዮች ሠልጥኖ ግብረ ሰዶማዊነትን መቀበል አለበት የሚል ኃሳብ አፍልቀው መወያያ ሆነዋል። አስረስ መዓረይ የቀደሙ አባቶች ያወረሱን ፋኖነት የለም ብሎ በፌስቡኩ በገለፀ ማግሥት አፈቀላጤው አልማዝ ባለጭራዋም ነገሥታቱን አሮጌና ሽማግሌ እያለች መዝልፏ አነጋጋሪ ሆኗል። የእኔ ጎጃም መግባት፣ ዘንዶው አንገት ላይ መቆሜም በዐማራ ፋኖ በጎጃም የሌለ የተደበቀ መርዙን እያስተፋሁት ነው። እነ ጥልሚያኮስ አማኑኤል አብነትም እንቅልፍ አጥተው ስለ እኔ በሥጋ ቆራጩ በኩል እየደረሱልኝ ነው። ቆሜም እያጨበጨብኩላቸው ነው። ኑሩልኝ። እንዳትደክሙ። በርቱም በሉልኝ። 😁 እንደ ድሮው በየሰዓቱ ቲክቶክ ቤት ከፍቶ ግቡ ግቡ ላጥረገርገው ነው ማለት ቀርቷል። አሁን ገንዘብ ማግኛው የቲክቶክ እገታ ነው። ምስኪን ዐማራ በሻአቢያ፣ በኦሮሞና በሸንጎ በስኳድ ይታገታል፣ ከዚያ ለማስለቀቂያ እነ ዘርሽ፣ እነ አኪላ ይቀፍላሉ። ተጠቃቅሰው አጠቡት ይሄን ምስኪን ዐማራ።

• ለማሸነፍ ብቸኛው መፍትሄ የዐማራ አንድነት ብቻ ነው። ሌላ የለም። 

• ዘመዴ ሚዲያ እየመጣ ነው…!

• የባንዳና የሾተላይ መርዝ ይሽራል
• የባንዳና የሾተላይ እሾህም ይነቀላል
• የዐማራ ፋኖ በጎጃምም ከሕመሙ ይፈወሳል
• ዐማራም እንደ ሕዝብ ድል ያደርጋል።

~ • ይደፈርሳል… ግን ደግሞ ይጠራል…✊

•••

ሻሎም…!  ሰላም…!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
የካቲት 7/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።


👆③ ✍✍✍

"…እስከ ፍኖተ ሰላም ባለው የፋኖ ቀረጥ መቆሙን፣ በምትኩ የብአዴን ካድሬ የዘረፋና ሕዝብ የማማረር ሥራውን እንደጀመረ አይቻለሁ። አሁን የዐማራ ፋኖ አንድነት በመዝገየቱ ብአዴን ልቡ አብጧል። ወይ እንደ ጎንደር ከተማ ለሚሊሻ በወር በወር ከውኃ ቆጣሪ ጋር 500 አምስት መቶ ብር ቢያስከፍል ይሻለው ነበር። ዘመዴ በጣም ያሳቀኘ ነገር ነው በጎንደር ከውኃ ቆጣሪ  ጋር 500 አምስት መቶ ብር የሚሊሻ ደሞዝ መከፈሉ። ጎንደር እንደምታውቀው ውኃ በወር አንድ ጊዜ ለዚያውም ሌሊት እንደጅብ ጠብቀው በጀሪካ ውኃ ይቀዳሉ። በዓለም ላይ ብቸኞቹ ውኃ ሳይጠጣ የውኃ ቆጣሪ ቢል የሚከፍል ልዩ ሕዝብ የጎንደር ከተማ ነዋሪ ነበር። አሁን ደግሞ የውኃ ቆጣሪ መቶ ብርም ይቁጠር አንድ ሺ ተጨማሪ የግዴታ የሚሊሻ ደሞዝ 500 አምስት መቶ ብር መክፈል አለባቸው። ግዴታ ነው። አንድ ሰው የውኃ ወርሃዊ ቆጣሪው 150 ብር ቢቆጥር የሚሊሻ 500 ብር ጨምሮበት 650 አድርጎ ይከፍላታል።1,000 ሺ ብር የውኃ ቆጣሪ የቆጠረበት ሰው ደግሞ የሚሊሻ 500 መቶ ብር ጨምሮ 1,500 ብር አድርጎ በተለያዬ ደረሰኝ ይከፍላታል። ይሄ ሁሉ ለምን ሆነ ያልን እንደሆነ የፋኖ አንድ አለመሆን ያመጣው ጣጣ ነው። አለቀ።

"…ይሄን የሕዝብ ሰቆቃና በደል፣ ጭፍጨፋ ለማስቆም ሦስት ብቸኛ አማራጮች ናቸው ያሉት። ከዚህ በቀር ፋኖ ከእነዚህ አማራጮች ውጪ ቢፈርጥ፣ ቢዘል፣ ቢነሣ፣ ቢቀመጥ፣ ቢወጣ፣ ቢወርድ አያሸንፍም። አረመኔው አቢይ አሕመድ እንዳለው ሺ ዓመት ቢዋጉ አያሸንፉም። ስለዚህ ለማሸነፍ የግድ

፩ኛ፦ አንድ መሆን አለባቸው።
፪ኛ፦ አንድ መሆን አለባቸው።
፫ኛ፦ አንድ መሆን አለባቸው።

"…ያለ አንድነት ማሸነፍን እርሱት። በስግብግብነት፣ በጠልፎ መጣል ማሸነፍ ብሎ ነገር የለም። በሴራ፣ በብልጠት፣ በአፈ ጮሌነት፣ በባንዳነት ማሸነፍ ብሎ ነገር የለም። እናም የዐማራ ሕዝብ ከጎንደር የፖለቲካ ቅማንት ከትግሬው ዲቃላ ስኳድ፣ ከጎጃሙ የፖለቲካው አገው ሸንጎ፣ ከቫይረስ ብአዴንና ወያኔ፣ ከመናፍቁ ብልፅግና ቫይረስ የጸዳ ዐማራዊ አንድነት በቶሎ ካላመጣ ዐማራው ይደቃል። ሞቱ እንኳ አሁን አሁን ሰው ማሳዘኑ ቀርቷል። የሚደነግጥ፣ ሰልፍ የሚወጣ ሰው እንኳ የለም። ወሬ ብቻ ሆኖ አርፏል። ይሄን መራር፣ ነገር ግን የሚፈውስ ኪኒን መዋጥ የግድ ነው። ዶሮ ማታ፣ ዶሮ ማታ እያልክ የኮሶውን መድኀኒት ካልዋጥቅ ፈውስ የለም። እንደናፈቀህ ይቀራል። ደፋር የዐማራ ጋዜጠኛ፣ አክቲቪስት ያስፈልጋል። ተመዝነው፣ ቀለው የተገኙ በሙሉ ከፋኖ አመራርነት ገለል ተደርገው በአዲስ አመራር መተካት አለባቸው። በውሸት፣ በሐሰት፣ በማጭበርበር እስከዛሬ ያሉትን በሥር ነቀል ለውጥ ገለል ማድረግ ካልተቻለ ማሸነፍን እርሱት። ለተቋም መመሪያ የማይገዙ፣ በየቲክቶኩ ሲቀደዱ የሚኖሩ አንዱም ወሬያቸው ያን ግዙፍ ተቋም የማይመጥን፣ በአረቄ መንፈስ ያሻቸውን ወጥተው የሚያቀረሹ ገለል ተደርገው ምራቅ የዋጡ ቁጥብ የሥራ ሰዎች ቦታውን ይያዙ። የሞባይል ሌባ እንዴት የዐማራ ፋኖ ወኪል ይሆናል? ነውር ነው።

"…ይሄ ፍፁም ዐማራዊ አንድነት የዐማራ ሕዝብ ብቻ በጉጉት የሚጠብቀው አይደለም። የሁሉም ነፃነት ፈላጊ ኢትዮጵያዊ ሁላ ፍላጎት ነው። አሁንማ በደቡብ ያሉ አንዳንድ ወጣቶች የፋኖን ሁኔታ ገምግመው፣ ገምግመው ሲያበቁ በፋኖ ላይ የሚያሾፍ የቲክቶክ ቪድዮ መልቀው ጀምረዋል። ሰሜን ሸዋ የሚሰለጥነው ሚሊሻ መከላከያን ነው የሚያስንቀው። ባህርዳር ብአዴን እግሩን ተክሏል። ጎንደር ከተማ ድሮ በቅርብ ርቀት የነበረው ፋኖ አሁን ጎንደር ከተማ ራሱ እንደ ጨረቃ ርቃበታለች። ደብረ ብርሃን ዙሪያ የነበረው ፋኖ አሁን ይኑር ይበተን አይታወቅም። አራት ኪሎ ሲጠበቅ የነበረው የጎጃሙ ግዙፍ የፋኖ ጦር አሁን የክልሉ የገጠር ከተሞች ይናፍቁት ይዘዋል። በፊት መከላከያውን እንደ ከብት እየነዳ ምርኮ ያስቆጥር የነበረው ጎጃም አሁን ወርዶ ሁለት ሽማግሌ ሚኒሻዎች ከነ ቆመህ ጠብቀኛቸው ማረኩ ብሎ እልልል በሉ ምእመናን ለማስባል ይላላጣል። ያ ሁላ የአስረስ መዓረይ ድንፋታ አሁን እንደ ቀዘቀዘ ሽሮ ልኩ ገብቷል። ያ ሁላ የእነ ጥላሁን አበጀ ከጎጃም አልፎ ወለጋና ደቡብ ኢትዮጵያ ድረስ ገብቶ ዜና ሲሠራ የነበረ መንጋ አሁን ሸበል በረንታ የሆነች ቀበሌ ተወሽቆ ይለፈልፋል። እነዚህን አውርቶአደር ፀረ አንደነት የብአዴንና የወያኔ ጎጤዎች በሥርነቀል ለውጥ ቀይሮ አዲስ አስተሳሰብ፣ አዲስ ራእይ፣ አዲስ ተስፋ የሚያስጨብጡ ዐማሮች ካልመጡ እርሱት። 

"…ልብ በሉ ደቡብ ጎንደር ከጋይንት እስከ ባህርዳር ያለውን የመኪና መስመር ብትመለከቱ የምድር ሲኦል ከሆነ ዓመታት ተቆጥሯል። በዚያ መስመር ሹፌሮች ይታገታሉ። በዚያ መስመር ስታልፍ በአካል፣ በሰውነት ትንሽ ወፈር ካልክ አለቀልህ። ትንሽ ወረት አለው የተባለ ሁሉ እየተጠና ይታገታል። ተራ ሙያተኛ ሳይቀር ይታገታል። ያሻው ጎረምሳ ከመኪና ውረድ ብሎ በጥፊ ይልሃል (ጥፊ ቀላሉ ነው)። በጥቅሉ መስመሩ ሲኦል ነው። ይሄ በማን በማን ይፈጸማል የሚለውን በሁለት መንገድ ፈጻሚዎቹን እንመልከት።

1ኛ፦ አንደኛው የወንጀሉ ፈጻሚዎች መንግሥት የሚደግፋቸውና ትጥቅ የሚያሟላላቸው በዋናነት በዞን አስተዳዳሪው አቶ ጥላሁን ደጀን ትእዛዝ የሚንቀሳቀሱ የፋኖ ኃይሎች ሲሆኑ፣ እኒህ የፋኖ ኃይሎች ከተማ ውስጥም እየገቡ ባለሀብቶችን፣ ከእነጥላሁን ደጀን ቡድን ያልሆኑ ካቢኔዎችን፣ የሥራ ሂደቶችንና፣ ለእነ ጥላሁን ደጀን የሚያዙትን ሁሉ እሺ ብለው አሠራር፣ መመሪያ እያሉ አንፈጽምም የሚሉ ሙያተኞችን ጭምር አፍነው ይወስዳሉ። መከላከያ ተብየው ደግም 1 ኪሜ ከማይሞላ ርቀት ላይ ሁኖ ከመንግሥት ፋኖዎች ጋር እየተያዩ የሚዘርፉ ናቸው። በቀደም እንዲያውም እነዚህን የመንግሥት ፋኖዎች ትክልለኛው፣ ኦርጂናሉ ፋኖ እርምጃ ወስዶባቸው ዜናው ተሰራጭቷል።

2ኛ፦ በፋኖ መዋቅር ውስጥ ያሉት ናቸው። በግልጽ እንድታውቁት በሆነ ክፍለ ጦር ስር ነኝ ይልና ሥራው ግን ዘረፋ ነው። ሰው ያግታል። ለክፍለ ጦሮቹ አመራር የዘረፈውን ያካፍላል። ኅብረተሰቡ በእነ እገሌ ተዘረፍን እያለ ለፋኖዎቹ አመራር ሲጠቁም እነሱማ የመንግሥት ተላላኪዎ ናቸው። ከእኛ ወገን አይደሉም እያለ የፋኖ አመራሩ ዝም ይላል። የድርሻው ስለሚሰጠው አይናገርም። አይተነፍስም። ሌላው ተዋጊ ጫማና ልብስ የሚቀይርበት አጥቶ፣ ጥይት አልቆበት ባዶ ከዝና ይዞ መከራ እያየ እነሱ 24 ሰዓት ይጠጣሉ፣ ለሴት ጭምር ይከፍላሉ። ይሄው ነው ሀቁ። በተለይ በተለይ ከጋይንት እስከ ባህርዳር ያለው መስመር የምድር ሲኦል ነው የሆነው። ከዋሸሁ እኔ ልቀጣ። ደውሉ ቤተሰብ ያላችሁ። ጠይቁ። …👇③ ✍✍✍


👆② ✍✍✍ …

"…ከዚያ በተራው መከላከያ በሚኒሻና በዐድማ ብተናው እየተመራ ፋኖዎቹ በቁጥጥራቸው ስር አድርገው ባቆዩአት ከተማ፣ ወይ ወረዳ ይገባል። ሰተት ብሎ ነው የሚገባው። ከዚያ በፊት ግን በዐማራ አክቲቪስቶች ሰበር ዜና ይሠራል። የዐማራ ፋኖ በእንትን እዚህና እዚህ ቦታ እየተናነቀ፣ የጁላን ሠራዊት እየደመሰሰ ነው። ሆስፒታሎች በቁስለኛ ተሞልተዋል፣ አሸባሪው አገዛዝ ገሚሱ ፈርጥጦ የተቀረው ሬሳውን በዚህን ያህል መኪኖች ጭኖ ተመልሷል የሚል ዜና ይለቃሉ። ማኅበራዊ ሚዲያው ይጥለቀለቃል። እውነታው ግን እሱ አይደለም። የአገዛዙ ጥምር ኃይሎች ከተማውን ይቆጣጠራሉ። ከዚያስ? ከዚያማ በተራቸው የበቀል ዱላ ማሳራፍ ይጀምራሉ። ፋኖዎቹ በከተማዋ ውስጥ በነበሩ ጊዜ ከፋኖዎቹ ጋር ጤናማ ግኑኝነት የነበራቸው በሙሉ አለቀላቸው። ተለቅመው ተራ በተራ ይረሸናሉ። ይጨፈጨፋሉ። ልክ እንደ ፋኖዎቹ መከላከያውም ገንዘብ ስብሰባ ይጀምራል። እምቢ፣ የለኝም ያለውን አንተማ ፋኖ ነህ፣ የፋኖ አደራጅ ነህ ተብሎ ይገደላል። ወይ ሀብት ንብረቱን ይወረሳል። እነዚያ የዝንጀሮ ባል ከምን አያስጥሌዎች ለዚህኛው አረመኔ አሳልፈው ሰጥተውት ለመከራ ዳርገውት እነሱ ሌላ ከተማ ሰፍረው ተመሳሳይ ሥራና ተግባር ይፈጽማሉ። ተመልከቱ ምስኪኑ ዐማራ፣ ንፁሑ ሕዝብ በፋኖም፣ በአገዛዙ ጥምር ኃይሎችም በየተራ ይደቅቃሉ። በፋኖ የአስተዳደር ሳምንት ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች መከላከያ ሲመጣ ዋነኛው ተበቃይ ሆነው ይገኛሉ። መከላከያው ሲወጣ ደግሞ በመከላከያ ተጎድተው የነበሩ ዐማሮች በተራቸው ከፋኖው ጊዜአዊ አስተዳደር ጋር ሆነው ቂምበቀላቸውን ይወጣሉ። በመሃል ዐማራ ርስ በርሱ ተፋጀ፣ አለቀ።

"…ለዚህ መፍትሄው ምንድነው ያልን እንደሆነ መጀመሪያው አንድነት ነው። ከዚያስ? ከዚያማ ወታደራዊ ዲሲፕሊን። ወታደራዊ ሥልጠና ነው። እንደ አስረስ መዓረይ ክላሽ ይዞ ፎቶ እየተነሡ የዐማራን አንድነት ጀግና ጀግና እየተጫወቱ አፈር ከደቼ ማብላት ሳይሆን ለዚህ ከከተማ፣ ከትምህርት ቤት ግርር ብሎ ጫካ ለገባ ወጣት ልክ እንደ ሳሚ ባለድል ፋኖዎች ነገ ሀገርን እንደሚረከቡ አምነው እውነተኛ የወታደር ባህሪን መላበስ ነው ያለባቸው። ከጎጃም ከእነ አስረስ፣ ከሸዋ ከእነ መከታው፣ ከወሎ ከእነ ሙሀባው፣ ሲሳይ ሳተናው፣ ከጎንደር ከእነ ጌታ አስራደ በቀር ቲክቶክ ላይ ተጥዶ፣ ትዊተር ስፔስ ተጥዶ፣ ዩቲዩብና ፌስቡክ ላይ ተጥዶ የሚውል የፋኖ አደረጃጀት ሰምታችኋል? አይታችኋል? ድሮን እንደማይመታቸው፣ በአይፒ አድሬሳቸው ጥቃት እንደማይደርስባቸው ዐውቀው ከመሳይ መኮንን፣ ከሞገስ ኦሮምቲቲ፣ ከወያኔ አፈቀላጤዎቹ ጋዜጠኞች ጋር አፍ ሲካፈቱ የሚውሉ ሌሎች አደረጃጀቶች መኖራቸውን አላውቅም። ባርች የእስክንድርና የመከታው፣ እነ ማርሸት ከአዝማሪዋ ጋር፣ ሌሎችም እንዲሁ ነው የሚታዩት። ጭራሽ ከሞጣ ጋር ጌም ሁላ ይጫወታሉ። ታብታብ አድርጉኝም ብለው ይማጸናሉ። የቁስ ሰቀቀናቸው ያልለቀቃቸው፣ የዐማራ ፋኖ ትግል ሳይገባቸው ጫካ የገቡትን እነዚህን ይዘህ አታሸንፍም። ለዚህ ሁሉ መፍትሄው ወታደራዊ ዲሲፒሊን ይኑር። ጓደኞቻቸው ክላሽ ይዘው ፎቶ ስለተነሡ ያንን ዓይቶ እኔም እንደነሱ ልሁን ብሎ ለሾው ጫካ የገባው ሁሉ በአስቸኳይ ይጠርነፍ። ያለበለዚያ መከራ ሰቆቃው ይቀጥላል።

"…እኔ እንደዚህ ብዬ የምጽፈው እውነት ለዚህ ለፌስቡክ አርበኛ፣ ለአስመሳይ፣ ቀጣፊ፣ ሂሊኮፍተር በድንጋይ መትቼ ጣልኩ ለሚል ቀጣፊ አልመቸውም። ይሄ በፋኖ ስም ፋኖነትን መጦሪያው፣ እንጀራው ላደረገው አውርቶ አደር አልመችም። ይሄ ሳይተኩስ ወሬ፣ ሳይገድል ጎፈሬውን አሳምሮ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ለሚጎሻመረው አስመሳይ አልመችም። ጦርነቱ ካለቀ ምን በልቼ አድራለሁ፣ አሁን ቶሎ ቶሎ ልዝረፍ ብሎ ለዘረፋ የገባ ይሄን የእኔን ሲያነብ አይመቸውም። በሃሰት ዜና፣ በሕዝብ ሰቆቃና መከራ ላይክና ሼር የሚሰበስብ፣ ሳንቲም የሚለቃቅም ሆድአደር የእኔ መራር እውነት አይመቸውም። ይጠንነዋል። ያንጎፋልለዋል። ይጎፈንነዋል። በጭራሽ እኔ አልመቸውም። ለፋኖ የተላከ ብር ኡጋንዳ በዶላር፣ ወደ ካናዳና ወደ አሜሪካ ጭምር ለሚያሸሽ ወንበዴ የወንበዴ ልጅ የእኔ ጦማር አይመቸውም። ተመቸው አልተመቸው ግን እውነቱ ይሄው ነው። በወሬ የለም ፍሬ። ትታያለህ፣ ትመዘናለህ፣ ከዚያ ቀለህ ስትገኝ ትዋረዳታለህ። አለቀ።

"…ከመሬት የምሰማውን ደግሞ ልጻፍላችሁ። "…ዘመዴ እውነት ለመናገር አንተ ጎጃምን ከጎበኘህ በኋላ በጎጃም ፋኖዎች ላይ መሻሻል ታይቷል። አሁን ፋኖ ሲያሻሽል የድሮ ጥጋቡ የተመለሰበት ብአዴን ነው። ለምሳሌ እኔ ሰምኑን ሥራዬ ብዬ የጎጃምን መስመር ለማየት ከባሕር ዳር መሸንቲ፣ መርአዊ፣ ቢኮሎ፣ ዱርቤቴ፣ ዳንግላ አዲስ ቅዳም፣ ኮሶበር፣ ከሳ፣ ቲሊሊ፣ ቡሬ፣ ማንኩሳ፣ ፍኖተ ሰላም ድረስ በመኪና ሂጃለሁ። ከባሕር ዳር ፍኖተ ሰላም እስክንደርስ ድረስ በመሀል ያሉትን ከተሞች እንድታውቃቸውና የት ላይ ችግር እንዳለ ላስረዳህ ፈልጌ ነው። እናም እኔ ባየሁት መሠረት ከዚህ ቀደም ከባህር ዳር ደጀን ድረስ ፋኖ የማይቀርጥበት ቦታ አልነበረም። አሁን ግን ከባሕር ዳር ፍኖተ ሰላም እስክገባ ድረስ የፋኖ ቀረጥ የለም። ቆሟል። አሁን በምትኩ ሕዝብን ከወረዳ እስከ ከተማ ድረስ ምርርርርር ያደረጉት እጥፍ እጥፍ ውሻ ሆነው ተደራጅተው የተነሡት በየዞንና ወረዳ ከተምችና የገጠር ቀበሌዎች ድረስ የብአዴን ካድሬዎች፣ ሚሊሻና አድማ ብተናውን ይዘው የማያስከፍሉትን ጠይቀኝ። ለድሀ ድሀ እርዳታ፣ ለጤና መድን፣ ለምናምን የማይጠይቁት ገንዘብ የለም። የለኝም ያለ ነጋዴ ከኮንቴነር እስከ ጉልት ገበያ ያለ ቀጥል ወደ መከላከያ ካምፕ ነው ሚባል። ይታሰራል። አፍንጫውን ተይዞ ተገዶም ይከፍላታል። በምትኩ ግን በመንገድ ላይ ባሉ ኬላዎች ላይ በሙሉ ፋኖ መቅረጥ አቁሟል።

"… አሁን በምትኩ ሹፌሮችን የመንግሥት ገቢዎች ደረሰኝ ይዘው ከከተማ መውጫና መግቢያ ላይ ያስከፍሏቸዋል። ከከተማ ወጣ እንዳሉ ከዚህ ቀደም ፋኖ ይቀርጥባቸው ከነበሩበት ኬላዎች ላይ ሚኒሻ ያስከፍላል። ለሚኒሻ ከፍለህ እንዳለፍህ መከላከያው ያስከፍልሃል። ለመላከያ ከፍለህ 10 ሜትር ሳትጓዝ አድማ ብተና አስቁሞ ያስከፍልሀል። ጉድ ጉድ ነው የምትለው። በዚህ ደረጃ ሹፌርን ማማረር በቃ ሹፌር ኧረ ብር ጨርሻለሁ ከዚህ እስከዚህ ከፍዬ ካለ ምን አባክ ውረድ። ይሄኔ ፋኖ ቢጠይቅህ ሳትከራከር በሞባይል ባንኪንግ አስልከህ ትከፍል ነበር። በማለት ሹፌሮችን የመንግሥት ኃይሎች ካድሬ ሚሊሻ አድማ ብተናና መከላከያ ተናበው አሳራቸውን እያበሏቸው ነው። የጎጃም ፋኖ እማ እኔ እንዳዬሁት በዚህኛው ከባሕር ዳር መርአዊ ዳንግላ ቡሬ ፍኖተ ሠላም ድረስ መመሪያ ተላልፏል። አንድም ፋኖ መንገድ ላይ ኬላ ዘርግቶ ቁሞ እንዳይቀርጥ ተብሎ ተወስኗል ብለው አሁን አይቀርጡም። በዚህ ትችትህን ሰምተው የጎጃምን ፋኖ አማራሪ ቀረጥን በማስቀረቱ አንተም በሚዲያ ልታመሰግናቸው ይገባል። ይሄን የምነግርህ ዘመዴ በዓይኔ ስላየሁ ነው ያሉኝ ወዳጄ ናቸው።…👇 ② ✍✍✍


"ርእሰ አንቀጽ"

"…አሳዛኝ‼️… በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ቱመት ቀበሌ 23 ሰላማዊ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በጅምላ ተጨፍጭፈዋል። አብዛኞቹ ለቀን እና ለጉልበት ሥራ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ሲሆን የተወሰኑት ደግሞ የአካባቢው ተወላጅ የሆኑ ነጋዴዎች ናቸው። ከቤት ተወስደው በወላጆቻቸው ፊት የተረሸኑ መኖራቸውን ለማወቅ ተችሏል። ይሄ አሰቃቂ ጭፍጨፋ የተፈጸመው የካቲት 6/2017 ዓም በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ነው። 17 የሚሆኑት አስክሬኖች በጅምላና በተናጠል በከተማዋ ነዋሪዎች ተቀብረዋል። ስድስት አስክሬኖች እስከ ምሽት ድረስ ሳይነሱ መንገድ ላይ ወድቀው ይታዩ ነበር ሲሉ የዓይን እማኞች ተናግረዋል። በእሳት የተቃጠሉ አስክሬኖች መመልከታቸውን የዓይን እማኞቹ ጨምረው አስረድተዋል።

"…ይሄ ዜና ትናንት በዐማራ ፔጆች ላይ ያነበብኩትና ያስቀረሁት ዜና ነው። 23 ሰላማዊ ዜጋዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በጅምላ ተጨፍጭፈዋል ነው የሚለው ዜናው። ዜናው ሲሠራ እንኳ እንዴት እንደሚፈሩ ተመልከቱ። ጎንደር ውስጥ የተጨፈጨፉ ዐማሮችን ዐማራ ሞተ ማለት፣ ተገደለ፣ ተጨፈጨፈ ማለት የማን ሥራ ነው? ይህን ዜና የዘገቡት ጋዜጠኞች ወይ ኢዜማ ናቸው። ግንቦት 7 ናቸው። አልያም የእስክንድር ነጋ አሕፋድ፣ የአርበኛ ደረጀ በላይ ጠቅላይ ግዛት ናቸው። አብዛኞቹ ለቀን እና ለጉልበት ሥራ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ሲሆን የተወሰኑት ደግሞ የአካባቢው ተወላጅ የሆኑ ነጋዴዎች ናቸው። ከቤት ተወስደው በወላጆቻቸው ፊት የተረሸኑ መኖራቸውን ለማወቅ ተችሏል፣ በእሳትም ተቃጥለው የሞቱ አሉ ነው የሚለው ዘጋቢው። ይሄ አረመኔያዊ ድርጊት የተፈጸመው የት ነው? ኢትዮጵያ ውስጥ። ማነው የፈጸመው? አገዛዙ። የት ነው የተፈጸመው? ምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ቱመት ቀበሌ ውስጥ፣ ስንት ሰዎች ተጨፈጨፉ? 23 ሰላማዊ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ በጅምላ ተጨፍጭፈዋል። ነገዳቸው ከወዴት ነው። ኢትዮጵያውያን ናቸው ይልልሃል ዐማራው ራሱ ዜናውን ሲሠራ።

"…ይሄ ነገር የተፈጸመው ኦሮሚያ ውስጥ ኦሮሞ ላይ፣ ትግራይ ውስጥ ትግሬ ላይ ቢፈጸም ራሱ ይሄን ዜና የሚዘግቡት እነ በለጠ ካሣ መኮንን ዜጎች ሞቱ፣ ተጨፈጨፉ አይሉም። ኢትዮጵያ ውስጥ ሰው ሲጨፈጨፍ ዜጋ የሚሆነው ዐማራው ብቻ ነው። በቁሙ ያጣውን፣ የተነፈገውን የኢትዮጵያዊነት ክብርና መብት የሚያገኘው ከሞተ በኋላ ነው። ዐማራ በፖለቲከኞቹ ዘንድ የለም። ዐማራ መኖሩ የሚታወቀው ሊገድሉት፣ ሊያጸዱት፣ ሊያጠፉት ሲፈልጉ ብቻ ነው። ዐማሮች የት ናቸው? ብለው ይጠይቃሉ። ይገድሉታል፣ ይዘርፉታል፣ ያፈናቅሉታል፣ ከዚያ ዜናው ሲሠራ ዜጎች ሞቱ፣ ተገደሉ፣ ጥቃት ደረሰባቸው፣ ተፈናቀሉ ተብሎ ይሠራል። በሰፈር ጸብ ተጣልተው ጉዳት የደረሰበት አንድ ኦሮሞ ከተጎዳ ግን ዓለሙ ሁሉ ድብልቅልቁ ነው የሚወጣው። በጣም ገራሚ ጉዳይ ነው።

"…ዐማራ አንድ ካልሆነ ሞቱ፣ ጭፍጨፋው፣ ውድመቱ ይቀጥላል። በወለጋ፣ በአሩሲ፣ በባሌና በሀረር፣ በጅማ ይሰማ ይታይ ይፈጸም የነበረው እልቂት ጭፈጨፋ ከደጃፉ ከገባ ቆየ። ከቀዬው ከገባ ቆየ። ከደጁ የደረሰውን ጠላት በሕዝባዊ ንቅናቄ ገትቶ ዓለሙን ሁሉ አስደንግጦ፣ አስገርሞም የነበረውን ሕዝባዊ የትግል ንቅናቄ ተማርን፣ ፊደል ቆጠርን፣ ታዋቂና ዐዋቂ ነን የሚሉ፣ አፈ ጮሌ ባንዳ ነጋዴዎች መጥተው ትግሉን ጠልፈው ሽባ አደረጉት። በሕዝቡ መነሣሣትና መነቃቃት ላይ ቀዝቃዛ ውኃ በረዶ ቸለሱበት። አኮላሹት። ከአገዛዙ ጋር እየተናበቡ፣ እየተመጋገቡ ዐማራን መዐዓት አወረዱበት። እነርሱ አይርባቸው፣ አይጠማቸው፣ አይበርዳቸው ሕዝቡን ግን ፍዳውን አበሉት። መከራውን አረዘሙበት። ያለ አንድነት፣ ያለ ኅብረት እንደማያሸንፉ እያወቁት አንድነቱን በታተኑት። ተስገበገቡ። ተሻሙም። ተንሰፈሰፉ። በዚህ ምክንያት በዐማራ ክልል ወንድ የተባለ፣ ገበሬ ይሁን የቀን ሠራተኛ እንደ እባብ በተገኘበት አናቱን ይቀጠቀጣል። ይጨፈጨፋል። እደግመዋለሁ አንድነቱን የሚያፈርሰውን የአገዛዙን ደላሎች፣ ፋኖ ውስጥ ያሉ ጉዳይ አስፈጻሚዎች ጫፋቸውን አይነካቸውም፣ አጠገባቸውም አይደርስም። እነርሱ ምንም አይሆኑም፣ የሚጎዳው ተራው ምስኪኑ ዐማራው ነው።

"…ፋኖ አንድ ከተማ ይቆጣጠራል። ወዲያው የመንግሥት ሰዎች ናቸው የሚላቸውን በሙሉ ይበቀላል። ይረሽናል፣ ወይም ዘመድና ገንዘብ ያለው ሰው ከሆነ ደግሞ መረሸኑ ቀርቶለት በከባድ የገንዘብ መቀጮ ይቀጣል። ከተማዋን የተቆጣጠሩት ፋኖዎች ወታደራዊ ዲሲፕሊን ስለሌላቸው፣ አብዛኛዎቹም በከምፕ የተጠረነፉም ስላልሆነ፣ በቀጣይ ምን እናድርግ ብለው እቅድ አውጥተው አይንቀሳቀሱም። ለሽ፣ ለጥ ነው የሚሉት። መዋቅር የመሥራት፣ መንግሥት የመሆን ሕልም ያላቸው ሁላ አይመስልም። እንዳይርባቸው፣ እንዳይጠማቸው ብቻ በማሰብ ትኩረት የሚያደርጉትና ለአፍታም የማይዘነጉት የማይረሱትም ነገር ሳንቲም ከማኅበረሰቡ ላይ መሰብሰብ ብቻ ነው። ለዲሽቃ መግዣ፣ ለብሬን መግዣ እያሉ ይሰበስባሉ። ሕዝቡም ያለ የሌለውን አውጥቶ ይሰጣል። ብሬኑም፣ ጥይቱም ይገዛል። ነፃ አውጪዎቹም ተዘልለው ይቀመጣሉ። ከረንቦላ፣ ፑል፣ ጆተኔ ይጫወታሉ። ቢንጎ ቤት ይውላሉ። የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁላ ይመለከታሉ። ይጠጣሉ፣ ይሰክራሉ፣ ይማግጣሉም። አርደው ሲበሉ፣ ሲጠጡም ይከርማሉ።

"…ይመሻል፣ ይነጋል። በሆነ ቀን መከላከያ ተብዬው በታጥቦ አይጠሬው ሚሊሻና በፀረ ዐማራው ዐድማ ብተና እየተመራ ወደዚያ በፋኖ ቁጥጥር ስር ወዳለች ወረዳ፣ ወይ ከተማ ያመራል። ገና መከላከያው መምጣቱ እንደተሰማ ከሕዝቡ በፊት እግሬ አውጪኝ ብሎ የሚፈረጥጠው ይሄው ኮሮምቦላ ሲጫወት የከረመው ኃይል ነው። በሕዝቡ ገንዘብ ከመከላከያ ላይ የተገዛው ብሬን ዲሽቃም አብሮ ይሰደዳል። እንደ አርበኛ ዘመነ ካሴ አይነቶቹ የጦር መሪዎች ደግሞ መከላከያ ጠላት ሲመጣባችሁ አትተኩሱበት፣ ሩጡ፣ ሽሹ ብለው መመሪያ ስላወረዱ እንኳንም ዘንቦብሽ እንዲሁም ጤዛ ተሆነው ዓላማ የሌለው ፀረ ዐማራ ፋኖ ቀነኒሳን፣ ሁሴን ቦልትን አስንቆ ይፈረጥጣል። በዚህ መሃል ኧረ እንዋጋቸው፣ እንደምስሳቸው፣ በጣም ቀላል እኮ ናቸው የሚል ሓሳብ የሚያነሣ ደፋር የዐማራ ፋኖ ካለ አለቀለት። ወይ ይገደላል፣ አልያም በከባድ ጥቁር መዝገብ ውስጥ ስሙ ይሰፍራል። ነገርየው እንዲህ ነው እየሆነ ያለው።…👇 ① ✍✍✍


መልካም…

"…ዛሬም ጎጃም ጮቄ ተራራ ልይ ነኝ። በጎጃም እና በደቡብ ጎንደር አካባቢ የሚታየኝን ውርውር እና ግርግር ነው እየጻፍኩላችሁ የነበረው። በጎጃም ለውጥም ስጋትም እያየሁ ነው። ሁለቱንም ጽፌላችኋለሁ።

"…በዓረብ ምድር የአጋች ታጋቹን ድራማ ሻአቢያ፣ የወያኔ ኤጀንቶቹ ዋን አዋራዎች፣ ከጎንደር ስኳድ፣ ከጎጃሙ አገው ሸንጎና፣ ከኦሮሞው ኦነግ ጋር እንዴት አድርገው ፒፕሉን ፊንታ እንደሠሩት እያየሁ በሳቅ ፍርፍር አምሮች ትናንት ስበላ ነው የዋልኩት። እሱን ነገ እመለስበታለሁ። ስልጤ ሙባረክ እንኳን ከአቅሙ የዐማራውን የሳይበር መንጋ እንዲህ ይንዳው? ጉድ እኮ ነው። 😂 እሱን ነገ በሰፊው እንመለስበታለሁ። በርእሰ አንቀጹ ላይ ጠቀስ አርጌው ግን አልፌአለሁ።

"…የጎጃሙ ኃይል አክቲቪስቶች መሪ ፍሮፌሶር አዝማሪት አልማዝ ዳኛቸው ዘውዴ መገርሳም ፈረንጆቹ ደስ እንዲላቸው ዐማራም እንደ ትግሬና ኦሮሞ ታጋዮች ግብረ ሰዶማዊነትን መቀበል አለበት የሚል ኃሳብ አፍልቀዋል። አስረስ የቀደሙ አባቶች ያወረሱን ፋኖነት የለም ሲል አፈቀላጤው ደግሞ ነገሥታቱን አሮጌና ሽማግሌ እያለች መዝልፏ ተይዟል። ጎጃም መግባቴ፣ ዘንዶው አንገት ላይ መቆሜ የሌለ የተደበቀ መርዙን እያስተፋሁት ነው። እነ ጥልሚያኮስ አማኑኤል አብነትም እንቅልፍ አጥተው ስለ እኔ በሥጋ ቆራጩ በኩል እየደረሱልኝ ነው። ቆሜም እያጨበጨብኩላቸው ነው። ኑሩልኝ። እንዳትደክሙ። በርቱ። 😁

"…ይሄን እንደ ኮሶ፣ መቅመቆ፣ ግራዋ፣ ሬት የመረረ፣ እንደ ቃሪያ በሚጥሚጣ ዳጣ የሚያቃጥል፣ የሚያንዘረዝር ፍጥጥ ያለ እውነት የሆነ ርእሰ አንቀጽ ለማንበብ፣ አንብባችሁም ለመወያየት ዝግጁ ናችሁ…?

"…እስቲ አንደ መቶ ጓደኞቼ አዎ ዘመዴ ዝግጁ ነነ ብላችሁ ቀውጡት። 😂

39.9k 0 11 219 1.3k
Показано 20 последних публикаций.