4-3-3 World News


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


ይህ የእርሶ፣ የአንተ፣ የአንቺ፣ የእናንተ፣ የኛ የሁላችንም ድምጽ ነው! ለሃሳብ አስተያየት ለመስጠት @atsbaha12 ይጠቀሙ

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ™ dan repost
Розыгрыш 10 подписок Telegram Premium сроком на 6 oy
Условия участия:
  • В розыгрыше участвуют все подписчики
  • Необходимо быть подписчиком 5 kanal
  • Конец розыгрыша: 24.11.2024 22:00


የከተማ አውቶቡስ ትራንስፖርት አገልግሎት እስከ ምሽት 4 ሰዓት ተራዘመ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በእጅጉ እየፈተኑ ከሚገኙ ጉዳዮች መካከል አንዱ የትራንስፖርት እጥረት መሆኑ ይታወቃል፡፡ መንግስት የትራንስፖርት እጥረቱን ለመፍታት የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ በተደጋጋሚ የሚገልጹት ጉዳይ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አዉቶቡስ ድርጅት በከተማዋ የሚስተዋለውን የትራንስፖርት እጥረት ለመፍታት የአገልግሎት አሰጣጡን እስከ ምሽት 4 ሰዓት እንዲራዘም ማድረጉን የድርጅቱ የኢንተለጀንስ ትራንስፓርት ሲስተምና ኦፕሬሽን አገልግሎት ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰብስባቸዉ መንግስቴ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ 7/24 የሚል እቀድ መያዙን የተናገሩት አቶ ሰብስባቸው ለጊዜው በምሽት የሚያጋጥመውን የትራንስፖርት እጥረት ለመፍታት ጎሮ እና መገናኛ ሙሉ በሙሉ እስከ ምሽት 4 ሰዓት አገልግሎቱ እየተሰጠ ነው ብለዋል፡፡

በትላንትናው ዕለትም የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 4ተኛ ዓመት አንደኛ መደበኛ ስብሰባ የሩብ አመት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ የከተማ አውቶቡስ ትራንስፓርት አገልግሎት ሰዓት ስለመራዘሙ ይፋ የተደረገ ሲሆን ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ የሸገርና አንበሳ አዉቶብስ ተብለዉ በተናጠል የነበሩት ተቋማት የአዲስ አበባ ከተማ አዉቶብስ ድርጅት በሚል በአንድ ላይ መቀናጀታቸዉ ይታወሳል፡፡

(መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 )

@Ethionews433 @Ethionews433


ኢትዮ ቴሌኮም የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ህትመት አገልግሎት መስጠት ጀመረ

ኩባንያችን የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂን እውን ለማድረግ የሚያስችሉ ዘርፈ-ብዙ የመሠረተልማት ማስፋፊያ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ ይህንን ስትራቴጂ እውን ለማድረግ ከሚያስፈልጉ አስቻይ ሲስተሞች ውስጥ አንዱ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ሲሆን፣ ለአካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ከፍተኛ ቁልፍ ሚና ያለው መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት በሀገር አቀፍ ደረጃ እስከ 2018 ዓ.ም ድረስ 90 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች ለማዳረስ በመደረግ ላይ ያለውን መጠነ ሰፊ ጥረት በመደገፍ የብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ ለማድረግ የመመዝገቢያ መሳሪያዎችን በመግዛት፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የአገልግሎት ማዕከላቱን በመጠቀም እና የሰው ኃይል በማሰልጠን የምዝገባ ስራ በስፋት በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡

አገልግሎት ደህንነቱ አስተማማኝ፣ ደረጃውን የጠበቀ እና ጥራት ያለው ካርድ በቀላሉ ለማቅረብ የሚያስችል ሲሆን ደንበኞች በቴሌብር ሱፐርአፕ ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ የካርድ ህትመት መተግበሪያ ወይም በድረገጽ https://teleprint.fayda.et/ በመግባት፣ የፋይዳ ተለዋጭ ቁጥር (FAN) በማስገባት፣ በአጭር ጽሑፍ የሚላከውን የማረጋገጫ መለያ ኮድ በማስገባት፣ የአገልግሎት ፍጥነት፣ ካርድ የመረከቢያ ቀን እና ቦታ እንደፍላጎታቸው መምረጥ ይችላሉ፡፡
የአገልግሎት ክፍያን በተመለከተ ደንበኞች በተለያየ የህትመት ማድረሻ ፍጥነት አማራጮች (delivery time) ማለትም ለመደበኛ በ7 የሥራ ቀናት (345 ብር)፣ ለፕሪሚየም በ2 የስራ ቀናት (600 ብር) እና ለኤክስፕረስ አስቸኳይ (800 ብር) በቀላሉ በቴሌብር በመፈጸም አገልግሎቱን ማግኘት የሚችሉ ይሆናል፡፡

የመታወቂያ ህትመቱ አገልግሎቱ ዘመናችን በደረሰበት የመጨረሻ የህትመት ቴክኖሎጂ በላቀ የህትመት ጥራት ደረጃ የሚከናወን ሲሆን፣ በቀላሉ የማይጫጫር፣ ቀለሙ የማይለቅ እና ሳይበላሽ እስከ 10 አመታት የሚደርስ የአገልግሎት እድሜ ያለው ነው፡፡
የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ አገልግሎቶችን ለዜጎች ለማቅረብ፣ የላቀ የደንበኞች አገልግሎት ተሞክሮን እውን ለማድረግ፣ የሥራ ፈጠራን ለማበረታታት፣ የኢ-ኮሜርስን ግብይት ለማሳለጥ፣ የፋይናንስ አካታችነትን የሚጨምሩ የአነስተኛ ብድር አገልግሎቶችን ያለዋስትና ለማቅረብ፣ የክሬዲት ግብይት ለማስፋፋት፣ የብድር ምጣኔ (credit score) ለማሻሻል እንዲሁም የዜጎችን የአኗኗር ዘይቤ የሚያዘምኑ እና ቢዝነስን የሚያቀላጥፉ የዲጂታል አገልግሎቶችን ለማቅረብ ያስችላል፡፡

@Ethionews433 @Ethionews433




በ6 አመትውስጥ በኢትዮጵያ  ከ1 ሚሊየን በላይ ቤቶች ተገንብተዋል ተባለ

በኢትዮጵያ ከለውጡ በኋላ  ባሉት ስድስት አመታት ከአንድ ሚሊየን በላይ ቤቶች መገንባታቸውን መንግስት ገለፀ።

የኢትዮጵያን ያለፈውን የኢኮኖሚ ሁኔታ እና የአሁኑ የኢኮኖሚ ደረጃ እየተገመገመ ባለበት ወቅት የቤት ችግርን ለመፍታት ከአንድ ሚሊየን በላይ ቤቶች ተገንብተዋል ተብሏል።

የፕላን እና ልማት ሚኒስትሯ ዶር ፍፁም አሰፋ ባቀረቡት ንግግር ላይ ጣቢያችን እንደሰማው በ18 አመት ውስጥ ወደ 400 መቶ ሺ ኮንዶሚኒየም ብቻ መገንባታቸውን ያስታወሱ ሲሆን፤

በስድስት አመት ውስጥ ግን  ከግሉ ዘርፍ ጋር በቅንጅት በመሆን ከ1 ሚሊየን በላይ ቤቶች ተገንብተዋል ብለዋል።

በዚህም ወደ 71 ሺ የሚጠጉት ቤቶች ግንባታቸው የተደረገው በመንግስት ድጋፍ መሆኑን ገልፀው የተቀረው ግን በግሉ ዘርፍ ትብብር ነው ይለዋል።

የቤቶቹ የግንባታ  እድገት የታየውም በግሉ ዘርፍ ጥምረት መሆኑም ተገልጿል።

@Ethionews433 @Ethionews433


መርካቶ የእሳት አደጋ መነሳቱ እየተገለፀ ይገኛል።

@Ethionews433 @Ethionews433


በቀብር ስፍራ በመገኘት የቲክቶክ ቪዲዮ ሲሰሩ የቆዩ ወጣቶች በፖሊስ ተያዙ...

በቀጨኔ ወረዳ 4 ቀጨኔ ዘላቂ ማረፊያ በሚባለው የቀብር ቦታ በመገኘት ሙዚቃ በመክፈት የቲክቶክ ቪዲዮ እየሰሩ ሲለቁ የነበሩ ወጣቶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት ወጣቶች መካከል አንዱ ድርጊቱን የፈፀምነው ተመልካችን ለማዝናናት ብለን ነበር ተጠያቂ እንደሚያደርግ ባለማወቃችን ስህተት ፈፅመናል ብሏል።

ድርጊታቸው በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ አንቀጽ 493 የሙታንን ሰላም እና ክብር መንካት በሚል እንደሚያስጠይቅ ከዚህ ቀደም መምህር፣ ጠበቃና የህግ አማካሪ አበባየሁ ጌታ መረጃን አጋርቶ ነበር ።

@Ethionews433
@Ethionews433


የዲኤንኤን ምርመራ በኢትዮጵያ ተጀመረ

ዛሬ የፌዴራል ፖሊስ የፎሬንሲክ ምርመራ እና የምርምር የልህቀት ማዕከልን መርቀናል። ከአንድ አመት ተኩል በፊት እንደ ሀገር የዲኤንኤ ምርመራ ሲያስፈልግ ወደ ውጭ ይላክ ከነበረበት ዛሬ ላይ ኢትዮጵያ ከዲኤንኤ ጋር የተያያዙ ችግሮች ሲገጥማት በራሷ መስራት ብቻ ሳይሆን የጎረቤት ሀገራት ጭምር ሊገለገሉበት የሚችል ተቋም ገንብተናል። ይህ በጸጥታ እና ደህንነት ዘርፍ ባለፉት አመታት የሰራናቸው የሪፎርም ስራዎች ውጤት ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)

@Ethionews433 @Ethionews433


የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ የተንጠላጠለ ወጣት በ5 ዞኖች ለኃይል መቋረጥ ምክኒያት መሆኑ ተሰማ

በከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶ ላይ የተንጠላጠለ ወጣት በ5 ዞኖች ኃይል እንዲቋረጥ ማድረጉን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ኦፕሬሽን ዘርፍ አስታውቋል፡፡

በዘርፉ የደቡብ ሁለት ሪጅን እንደገለፀው፤ ወጣቱ ትላንት ከቀኑ 8:00 ጀምሮ ከወላይታ ሶዶ ወደ ሳውላ በሚሄደው ከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ወጥቶ አልወርድም ማለቱን ገልጿል፡፡

በዚህም በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሚገኙ ጎፋ ዞን፣ አሪ ዞን፣ ባስኬቶ ዞን እና ኦሞ ዞን ሙሉ በሙሉ እንዲሁም ጋሞ ዞን በከፊል ከሦስት ሰዓታት በላይ ኃይል ተቋርጦ መቆየቱ ተነግሯል፡፡

በምን ምክንያት የኃይል ማስተላለፊያ መስመሩ ላይ እንደወጣ ያልታወቀው ወጣት በአካባቢው ሽማግሌዎችና የመስተዳደር አካላት ቢለመንም ለመውረድ ግን አስቸግሮ እንደነበር መምሪያው ገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ባለሙያዎች ኃይል በማቋረጥ ወጣቱ ሳይጎዳ በገመድ አስረው በማውረድ ህይወቱን መታደግ መቻላቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች የሚያስተላልፉት የቮልቴጅ መጠን ከፍተኛ በመሆኑ ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መምሪያው አሳስቧል፡፡

@Ethionews433 @Ethionews433


በወላይታ ሶዶ የ15 ዓመት ታዳጊዋን ለአምስት ሆነው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀሙ ተከሳሾ በጽኑ እስራት ተቀጡ

በወላይታ ሶዶ ለአምስት ሆነው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦች በጽኑ እስራት መቀጣታቸውን የወረዳው ፍ/ቤት አስታውቋል ።ተከሳሾቹ በቁጥር አምስት ሲሆኑ ጉርዛ ጉቡላ፣ጉቴ ጴጥሮስ፣ሙርቴ ሙኩሎ፣ወጣት ጩምቡሎ ጩጩሞ እና ወጣት ካፍቴ ኢዮና የተባሉ ናቸው፡፡

ግለሰቦቹ በወላይታ ዞን በዑባ ደብረ ፀሐይ ወረዳ ሻላ ጽጾ ትፌ ቀበሌ ክልል ውስጥ ልዩ ሥሙ ጽጾ ንዑስ ተብሎ በሚጠራበት አካባቢ ከምሽቱ 2:00 ሰዓት አካባቢ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል መፈፀባቸው ተገልፆል፡፡ የግል ተበዳይ የሆነችው በየነች ሞርካ የተባለች የ15 ዓመት ታዳጊ ስትሆን የጓደኛዋ ሠርግ ቤት ሄዳ ስትመለስ ተከሳሾች ሆን ብለው በቡድን ተደራጅተው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል እንደፈፀሙባት የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ኢንስፔክተር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

ተከሳሾቹን ፖሊስ በቁጥጥር ስር በማዋል በሰውና በህክምና ሰነድ ማስረጃ አደራጅቶ ለአቃቤ ህግ ያቀርባል፡፡አቃቤ ህግም ከፖሊስ የደረሰውን የምርመራ መዝገብ መነሻ በማድረግ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ክስ በመመስረት ፍ/ቤት ያቀርባል።

በዚህም መሰረት የወረዳዉ ፍርድ ቤት ህዳር 4 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት በእያንዳንዳቸው ተከሳሾች ላይ በ14 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ፍ/ቤት ውሳኔ ማስተላለፉን ኢንስፔክተር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል

@Ethionews433 @Ethionews433


በአንድ ወር የሚዘንብ ዝናብ መጠንን በአንድ ሰዓት ባስተናገደችው ስፔን ሺዎች ተፈናቀሉ

በአንድ ወር የሚዘንብ ዝናብ መጠንን በአንድ ሰዓት ባስተናገደችው ስፔን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿ ተፈናቅለዋል፡፡

ከሁለት ሳምንታት በፊት በስፔን ቫሌንሺያ ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ የበርካታ ሰዎች ሕይወት ማለፉ ይታወሳል፡፡

በዛሬው ዕለትም ሀገሪቱ በአንድ ወር የሚዘንብ ዝናብ መጠንን በአንድ ሰዓት በማስተናገዷ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቿ መፈናቀላቸው ተሰምቷል፡፡

በሀገሪቱ ማላጋ አካባቢ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎች ሲፈናቀሉ ከ1 ሺህ በላይ ቤቶች ደግሞ በጎርፉ አደጋ ከጥቅም ውጭ መሆናቸውን በአንዳሉሺያ የጎርፍ አደጋ ፕላን ዳይሬክተር አንቶኒዮ ሳንዝ አስታውቀዋል።

አሁንም ከባድ ዝናብ እስከ ምሽት ድረስ ከማላጋና ግራናዳ እስከ ቫሌንሲያ እና ታራጎና ሊቀጥል እንደሚችል መመላከቱን ሲኤንኤን ዘግቧል።(ኤፍ ቢ ሲ)

@Ethionews433 @Ethionews433


ታዋቂው የሰብአዊ መብት ተሟጋች የኢራንን መንግሥት በመቃወም ራሱን አጠፋ

አራት የኢራን የፖለቲካ እስረኞች እስከ ረቡዕ ምሽት ከእስር ካልተለቀቁ ራሱን እንደሚያጠፋ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ አስታውቆ የነበረው ታዋቂው ኢራናዊ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ኪያኖሽ ሳንጃሪ፤ የኢራንን መንግሥት በመቃወም ራሱን ማጥፋቱን ቢቢሲ ዘገበ፡፡

“አንድ ቀን ኢራናውያን ነቅተው ባርነትን ያሸንፋሉ” ሲል ራሱን ከማጥፋቱ በፊት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ መጻፉ ተነግሯል፡፡

የኢራንን መንግሥት አጥብቆ በመተቸት የሚታወቀው ኪያኖሽ ሳንጃሪ ለዴሞክራሲ ሲታገል የቆየ ሲሆን፤ ከመሞቱ በፊት “ማንም ሰው ሐሳቡን በመግለጹ ምክንያት መታሰር የለበትም። መቃወም የሁሉም ኢራናውያን መብት ነው” ብሏል።

ታዋቂው ታጋይ የኢራን መንግሥት እንዲፈታቸው የጠየቃቸው አራቱም ፖለቲከኞች የታሰሩት የ22 ዓመቷ ማሳ አሚኒ መገደሏን ተከትሎ፣ የተነሳውን ሕዝባዊ ተቃውሞ በመደገፋቸውና በመሳተፋቸው ነበር።

@Ethionews433 @Ethionews433


በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት ላይ ስርቆት የፈፀሙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ካዛንቺስ አካባቢ 550 ሺ ብር የሚገመት የኤሌክትሪክ መስመር ላይ ስርቆት ያደረሱ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች በኮሪደር ልማት ሥራ ምክንያት ተቆፍረው የተቀመጡ 200 ሜትር የሚደርስ የኤሌክትሪክ መስመሮችን ቆራርጠው ለግል ጥቅማቸው ያዋሉ ሲሆን ተቋሙ ከአዲስ አበባ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ጋር ባደረገው ከፍተኛ ርብርብ መያዛቸው ተጠቅሷል፡፡

በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ ስርቆት መፈፀም በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት አውታሮች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 464/97 መሰረት ከ5 ዓመት እስከ 20 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት ቅጣት ያስጠይቃል፡፡

በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ አመት ብቻ ከ2 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶች ላይ የስርቆት ወንጀል መፈፀሙ የሚታወስ ነው፡፡

(የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት)

@Ethionews433 @Ethionews433


ፕሬዚዳንት ኤርዶኻን ሀገራቸው ከእስራኤል ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማቋረጧን ገለጹ

ቱርክ ከእስራኤል ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ማቋረጧን የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን አስታወቁ፡፡

ፕሬዚዳንቱ በሰጡት መግለጫ÷ የቱርክ ሪፐብሊክ ለረጅም ጊዜ ከእስራኤል ጋር ንግግር እንዳልነበረው አስታወሰው፤ አሁን ላይ ዲፕለማሲያዊ ግንኙነቱ ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል ብለዋል፡፡

የጋዛ እና የሊባኖስን ጦርነት ስታወግዝ የቆየችው ቱርክ፤ በመካከለኛው ምስራቅ የተኩስ አቁም እስከሚደረግ ድረስ ከእስራኤል ጋር ንግግር እንደማይኖራት ማመልከታቸውን ስፑትኒክ እና ቲ አር ቲ ወርልድ ዘግበዋል፡፡

ቀደም ሲል በጋዛ የሚካሄደውን ጦርነት ተከትሎ ከእስራኤል ጋር ያላትን የወጪ እና ገቢ ንግድ ያቋረጠችው ቱርክ፤ ከእስራኤል ጋር በሚደረጉ ሌሎች የንግድ ልውውጦች ላይም ማዕቀብ መጣሏ ይታወሳል።

@Ethionews433 @Ethionews433


ትራምፕ ቢሊየነሩን መስክን ሾሙ....

ሹመቱ ለትራምፕ እንዲመረጡ በርካታ ቢሊዮን ዶላሮች ፈሰስ ያደረገው መስክን የበለጠ ተጽእኖ እንዲኖረው የሚያደርግ ነው ተብሏል

ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ቢሊየነሩ ኢለን መስክ አዲስ በሚቋቋመው ተቋም ሚና እንዲኖረው በትናንትናው እለት ሾመውታል።

ሹመቱ ለትራምፕ እንዲመረጡ በርካታ ቢሊዮን ዶላሮች ፈሰስ ያደረገው መስክን የበለጠ ተጽእኖ እንዲኖረው የሚያደርግ ነው ተብሏል።

መስክ እና የቀድሞው የሪፐብሊካን ፕሬዝደንታዊ እጩ ቪቬክ ራማስዋሚ ትራምፕ የተጓተተውን የመንግስት አሰራርን በማሳጠር ቀልጣፋ አሰራር እንዲኖር ያስችላል ያሉትን አዲስ የተቋቋመውን 'ዲፓርትመንት ኦፍ ገቭርመን ኢፊሸንሲ' ወይም የውጤማነት ቢሮ ይመራሉ።

ትራምፕ ባወጡት መግለጫ መስክ እና ራሜስዋሚ "የእኔ አስተዳደር የመንግስት ቢሮክራሲ እንዲያፈርስ፣ ብዙ መመሪያዎችን እንዲቀንስ፣ ብክነትን እንዲቀንስ እና የፌደራል ኤጀንሲዎችን መዋቅር እንዲያስተካክል መንገድ ይጠርጋሉ" ብለዋል።

አዲሱ ዲፓርትመንት የሪፐብሊካን የረጅም ጊዜ ህልም እንደሆነ እና "ከመንግስት ውጭ ሆኖ ምክር እና መመሪያ እንደሚሰጥ" የገለጹት ትራምፕ የመስክ እና የራማስዋሚ ሹመት የሴኔት ይሁንታ የማያስፈልገው ይፋዊ ያልሆነ ሹመት መሆኑን አመላክተዋል።  መስክም በትራምፕ ከተሰጠው ኃላፊነት በተጨማሪ የግዙፍ ማህበራዊ ሚዲያ ኤክስ፣ የቴስላ እና የስፔስ ኤክስ ኃላፊ ሆኖ እንዲቀጥል ያስችለዋል  ተብሏል።

ፕራምፕ እንዳሉት አዲሱ ዲፓርትመንት "መጠነሰፊ የመዋቅር ለውጥ ለማፋጠን እና የቢዝነስ አስራርን ለመፍጠር" ከኃይትሀውስ እና ከበጀት ቢሮ ጋር ይሰራል።

ስራው የአሜሪካ ነጻነት በታወጀበት 250ኛ አመት መታበሲያ እለት ሐምሌ 2026 ይጠናቀቃል ተብሏል።

በፎርብስ መጽሄት የአለም ቁጥር አንድ ሀብታም ደረጃን የተቆናጠጠው መስክ ኩባንያዎቹ በትራምፕ ድል ምክንያት በተሻለ ሁኔታ እንዲታዩ ለማድረግ እየሰራ ነው።

መስክ ለትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ሚሊዮን የሚቆጠር ዶላር ከመስጠት ባለፈ በአደባባይ አብሯቸው በመታየት ድጋፉን ገልጿል። 

መስክ በመንግስት ስራ መሳተፉ እንደ አርቴፊሻል ኢንተሊጀንስ እና ክሪፕቶከረንሲ ያሉት ኩባንያዎቹ የገበያ ዋጋ እንዲጨምር ሊረዳው ይችላል።

ዶናልድ ትራምፕ የዲሞክራቷን እጩ ካማላ ሀሪስን በማሸነፍ በድጋሚ ወደ ኃይት ሀውስ መግባት ችላዋል። ትራምፕ ለኃይት ሀውስ ኃላፊነት ጨምሮ ለበርካታ የመንግስት የስልጣን ቦታዎች አጋሮቻቸውን እየሾሙ እና እያጩ ይገኛሉ።[አል አይን]

@Ethionews433 @Ethionews433


አቢሲኒያ ባንክ መግለጫ ሰጥቷል

ዛሬ ህዳር 3 ቀን 2017 ዓ.ም. በሲስተም መቛረጥ ምክንያት ለደረሰባችሁ መጉላላት ታላቅ ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡ የዲጅታል ባንክ አገልግሎቶቻችንን ጨምሮ ሁሉንም አማራጮች ስራ ለማስጀመር ከፍተኛ ርብርብ እያደረግን ሲሆን ላሳያችሁን ትዕግስትና ድጋፍ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን ።

አቢሲንያ ባንክ!

@Ethionews433 @Ethionews433


ከ294 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

የጉምሩክ ኮሚሽን ከጥቅምት 22 እስከ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 279.7 ሚሊዮን ብር የገቢ የኮንትሮባንድ እቃዎች እና 14. 8 ሚሊዮን ብር የወጭ፤ በድምሩ 294.5 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግንባታ እቃዎች፣ ቡና፣ ጥራጥሬ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች ፣ መድኃኒት፣ የምግብ ዘይት ፣ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች እና የወጭ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የገቢ እና የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ጅግጅጋ፣ ድሬድዋ እና ሞያሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ ሲይዙ በቅደም ተከተላቸውም 86 ሚሊዮን፣ 61 ሚሊዮን እና 52 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎችን መያዝ ችለዋል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ እና በበረራ የተያዙ ሲሆን የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 14 ተጠርጣሪ ግለሰቦች እና 7 ተሽከርካሪዎችም በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

(ጉምሩክ ኮሚሽን)

@Ethionews433 @Ethionews433

17 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.