ኢትዮ ቤስት ዜና 🇪🇹🇪🇹🇪🇹


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


🇪🇹🇪🇹🇪🇹ስለ እናት ሀገራችን ኢትዮጵያ ቀን በቀን የሚወጡ ዜናዎችን እና እንዲሁም አለም አቀፍ መረጃዎችን ወደ እናንተ እናደርሳለን 🙏ሰላምና ፍቅር ለእናት ሀገራችን ይሁን❤
👉 ለማንኛውም አስተያየት እና ጥቆማ @Gebrel or @Wizbeki7 ያናግሩን።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri




🛜wifi password 🔑 መለመን ቀረ!!
App ለማግኘት ከታች  WIFI PASSWORD HACKER ሚለውን ይንኩ




❗ባይናንስ በናይጄሪያ የ81 ቢሊዮን ዶላር ክስ ቀረበበት❗

የናይጄሪያ የፌደራል የሀገር ውስጥ ገቢ አገልግሎት የክሪፕቶከረንሲ መገበያያ በሆነው ባይናንስ ላይ የኢኮኖሚ ኪሳራ አድርሷል በማለት
በአቡጃ በሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ክስ መስርቶበታል።
የናይጄሪያ ኢኮኖሚ ላይ ባደረሰው ኪሳራ 79.5 ቢልዮን ዶላር እንዲከፍል እንዲሁም በ2022 እና 2023 ያልተከፈለ 2 ቢሊዮን ዶላር ውዘፍ የታክስ እዳ ባለመክፈል ነው ባይናንስ ክሱ የተመሰረተበት።
ያለ ህጋዊ ፈቃድ የክሪፕቶከረንሲ ልውውጥ ሲያካሄድ እንደነበር እና በዚህም ያልተፈቀደ የፋይናንስ አገልግሎትን መስጠት እና የውጭ ምንዛሬን በማካሄድ ብሎም በበርካታ ህጎችን መጣስም የክሱ አካል ሆኗል።
ባይናንስ ከ382 ሺህ በላይ ተጠቃሚዎች ይዞ ከ21 ቢሊዮን ዶላር በላይ ግብይት በማካሄድ 35.4 ሚሊዮን ዶላር የተጣራ ትርፍ በ2023 አስመዝግቧል።
ባይናንስ በናይጄሪያ ውስጥ ከ6 ዓመት በላይ ያለ ህጋዊ ምዝገባ እና ፈቃድ ሲሰራ እንደነበርም ስፑትኒክ ዘግቧል።


❗ግልፅ ያልሆነ ሰሌዳ ለጥፈው በሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ❗

የታጠፈ የደበዘዘ የተፋፋቀ እና በአጠቃላይ ለዕይታ ግልፅ ያልሆነ ሰሌዳ ለጥፈው በሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡


በአዲስ አበባ ከተማ በየጊዜው እየተባባሰ ለመጣው የመንገድ ትራፊክ አደጋ ልዩ ልዩ የደምብ መተላለፍ ጥፋቶች እንደ ምክንያትነት የሚገለጹ ቢሆንም ለእይታ ግልፅ ያልሆኑ የተሽከርካሪ ሰሌዳዎች መበራከት ለአደጋ ብቻ ሳይሆን የወንጀል ስጋት እየሆኑ መምጣታቸውን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በተያዘው በጀት ዓመት በስድስት ወራት ውስጥ በተለያዩ የደምብ መተላለፍ ጥፋቶች ከአንድ ሚሊየን ሁለት መቶ ዘጠና ሦስት ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች በትራፊክ ፖሊስ አባላት ብቻ እርምጃ የተወሰደባቸው ሲሆን በጥር ወር 2017 ዓ/ም ብቻ ለዕይታ ግልፅ ያልሆነ ሰሌዳ ለጥፈው በሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ላይ በተደረገ ቁጥጥር ከ2 ሺ 1 መቶ በላይ አሽከርካሪዎች እርምጃ ተወስዶባቸዋል፡፡

በየጊዜው የታጠፈ የደበዘዘ እና የተፋፋቀ ሰሌዳ ለጥፈው በሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ ቢሆንም በሚፈለገው ደረጃ ችግሩን መቅረፍ እንዳልተቻለ ያስታወቀው ፖሊስ ችግሩን ለመፍታት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ጠንካራ የቁጥጥርና የክትትል ስርዓትን በመፍጠር ህጋዊ እርምጃዎችን መውሰድ እንደሚገባ ታምኖበታል።

በቅርቡ ተግባራዊ በሆነው ደምብ ቁጥር 557/2016 መሰረት ለዕይታ ግልፅ ያልሆነ ሰሌዳ ለጥፈው በሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ላይ ጥፋቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሆነ 1ሺ 5 መቶ ብር የሚያስቀጣ ደምብ መተላለፍ መሆኑን ተደንግጓል፡፡


"የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሁሉም ተማሪዎች በተማሩበት ስርዓተ ትምህርት ይዘት ይዘጋጃል፡፡" - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2017 ዓ.ም ተፈታኝ ተማሪዎች ከ9ኛ-10ኛ በነባሩ ስርዓተ ትምህርት፣ ከ11ኛ-12ኛ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት እንዲሁም ለስርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ በናሙናነት ተመርጠው የተሳተፉ ትምህርት ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች 10ኛ ከፍልን በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የተማሩ መሆናቸውን አገልግሎቱ ገልጿል፡፡

በአማራ ክልል በፀጥታ ችግር ምክንያት በ2016 ዓ.ም ሳይፈተኑ የቀሩና የ11ኛ ክፍልን በነባሩ ስርዓተ ትምህርት የተማሩ ትምህርት ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች በ2017 ዓ.ም የሚፈተኑም አሉ፡፡

በመሆኑም የ2017 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና "ከላይ የተገለፁትን ነባራዊ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ባስገባና ሁሉንም ተፈታኝ ተማሪዎች በማከለ መንገድ ስታንዳርዱን፣ ደህንነቱንና ሚስጢራዊነቱን ጠብቆ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል" ብሏል አገልግሎቱ።

የፈተና ዝግጅቱ ምን ያካትታል?

➫ ከ9ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከነባሩ ስርዓተ ትምህርት፣
➫ ከ10ኛ ክፍል በነባሩ እና በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ተመሳሳይ ይዘቶች፣
➫ ከ11ኛ ከፍል በነባሩ እና በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ተመሳሳይ ይዘቶች፣
➫ ከ12ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሰረት የሚዘጋጅ ይሆናል።

የኢኮኖሚክስ የትምህርት ዓይነት በስርዓተ ትምህርቱ አዲስ የተጀመረ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በ12ኛ ክፍል ይዘት ላይ ብቻ ተመስርቶ ይዘጋጃል ተብሏል።


❗ ሒልተን በአዳማ እና ድሬዳዋ ደብል ትሪ ሆቴሎችን ለመክፈት ከብራይተን ሆቴሎች ጋር ስምምነት ተፈራረመ። ❗

ሂልተን ከብራይተን ሆቴሎች እና ቢዝነስ ኃ.የተ.የግ.ማ. በአዳማ እና በድሬዳዋ ከተማ "የመጀመሪያዎቹ አለም አቀፍ ብራንድ ያላቸው ሆቴሎች" በማለት የገለፀውን ሁለት DoubleTree በሂልተን ሆቴሎች ለመክፈት ነው የተስማማው።

ሆቴሎቹ እ.ኤ.አ. በ 2028 ይከፈታሉ ተብሎ የሚጠበቀው የሂልተን ሰፊ የማስፋፊያ እቅድ አካል ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ሒልተን አዲስ አበባ ጨምሮ DoubleTree by ሂልተን አዲስ አበባ ኤርፖርት ለመክፈት ማቀዱ ተሰምቷል።


Telegram መክፈል ጀምሯል እስካሁን አልሰማችሁም?

✅ JOIN ✅ የሚለውን ንኩ አና በቀላሉ ገንዘብ ይስሩ 🫶🫶


Profile picture dan repost
🚨✅ ቤቲንግ መበላት ላማረራችሁ ጥሩ TIP የምታገኙበት ቻናል ተከፍቷል አሁኑኑ ተቀላቀሉ👇

https://t.me/+7ZOmNi9fCxg2ZDc0
https://t.me/+7ZOmNi9fCxg2ZDc0


Promotion k dan repost
💔 ️የተወለዱበትን ወር ቶሎ ይምረጡ እና በ Zodiac ሳይንስ ስለራስዎ በደንብ  ይወቁ 😍😍😍 የፍቅር ሁኔታዎንም ይጠቁማል

💯 ትክክል የሆነ  ✅




❤️❤️ለእዚች እናት ❤️❤️
10000 Like ያንሳታል❤️❤️


ቤስት ስፖርት በኢትዮጵያ ™🇪🇹🇪🇹🇪🇹 dan repost
ዛሬ የሚደረጉ ጨዋታዎች

🇪🇺በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ 

02:45 |🇩🇪 ዶርትሙንድ ከ ስፖርቲንግ ሊዝበን 🇵🇹
[Agg: ❸-0]
05:00 |🇫🇷 ፒኤስጂ ከ ብረስት 🇫🇷
[Agg:❸-0]
05:00 |🇳🇱 ፒኤስቪ ከ ጁቬንቱስ 🇮🇹
[Agg:➊-➋]
05:00 |🇪🇸 ሪያል ማድሪድ ከ ማንችስተር ሲቲ🇬🇧
[Agg:❸-➋]
🇬🇧 በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ

04:30 |🇬🇧 አስቶን ቪላ ከ ሊቨርፑል 🇬🇧

SHARE @BHBESTFOOTBALL
SHARE @BHBESTFOOTBALL


ቤስት ስፖርት በኢትዮጵያ ™🇪🇹🇪🇹🇪🇹 dan repost
🇪🇺ትላንት የተደረጉ የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ጨዋታዎች

🇮🇹ኤሲ ሚላን 1-1 ፌይኖርድ 🇳🇱
[Agg : ➊-➋]

🇮🇹አታላንታ 1-3 ክለብ ብሩጅ 🇧🇪
[Agg : ➋-❺]

🇩🇪ባየር ሙኒክ 1-1 ሴልቲክ 🏴󠁧󠁢󠁳󠁣󠁴󠁿
     [Agg : ❸-➋]

🇵🇹ቤኔፊካ 3-3 ሞናኮ 🇫🇷
[Agg : ➍-❸]

የተቆጠሩ ጎሎችን ለመመልከት

@BH_bestgoal

SHARE @BHBESTFOOTBALL
SHARE @BHBESTFOOTBALL


🚨ጠ/ሚ አብይ ለህውሃት 50ኛ አመት ያስተላለፉት መልእክት


ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ፣ አኹንም የፖለቲካ ልዩነቶችን በኃይል የመፍታት ፍላጎት ጎልቶ እንደቀጠለ መኾኑን ዛሬ የሚከበረውን የሕወሓት 50ኛ ዓመት በዓል አስመልክተው በትግርኛ ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል።

ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ በመፍታት፣ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው በመመለስና ኢኮኖሚያዊ ማገገምና ማኅበራዊ መረጋጋትን ማረጋገጥ እንዲሁም ፍትሕ እንዲሠፍን መስራት እንደሚያስፈልግም ዐቢይ አሳስበዋል።

የየካቲት 11 ትሩፋት ማንኛውም ልዩነቶች በድርድር የሚፈቱበት መኾኑን እንደገና መረዳት ያስፈልጋል ያሉት ዐቢይ፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግን ልዩነቶችን ለመፍታት የተመረጡ የግጭት መንገዶች ከየካቲት 11 ዓላማዎች ያፈነገጡ መኾናቸውን አውስተዋል።

ዐቢይ አያይዘውም፣ ኾኖም ብዙ ዋጋ ከተከፈለ በኋላም ቢኾን ወደ ውይይት መመለሳችን የሚበረታታ ርምጃ ነው ብለዋል።


የተባበሩት መንግሥታት የዘላቂ ልማት መፍትሔ ጥምረት (SDSN) የአፍሪካ ማዕከል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከፍቷል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተከፈተው የጥምረቱ ማዕከል የጥናትና ምርምር ሥራዎችን በማከናወን ለፖሊሲ አውጪዎች ግብዓት የሚሆኑ ሳይንሳዊ መፍትሔዎችን ያቀርባል ተብሏል።

የማዕከሉ መከፈት ተጨማሪ አቅም እንደሚፈጥር እና በትብብር ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄዎችን ለመቅረፅ የራሱን አበርክቶ እንደሚወጣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተ/ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡


የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕሮፈሰር ፀጋዬ ቱኬ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ከቀረበባቸው ሁለት ክሶች በነፃ ተሰናበቱ።

የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፈሰር ፀጋዬ ቱኬ የሕግ ጠበቃቸው አቶ ገብረመድህን ተክሌ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሀዋሳ ማዕከል ከቀረበባቸው ከባድ የሙስና ወንጀል እና በሕገወጥ መንገድ የተገኘን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ መጠቀም በሚል የቀረበባቸዉን ሁለት ክሶች ላለፉት አንድ ዓመት ሲከታተሉ ቆይዋል።

በዛሬዉ ዕለት በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሐዋሳና አከባቢዋ ማዕከል በነፃ መሰናበታቸውን ጠበቃቸው ተናግረዋል።

ከቀድሞ የሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ረ/ፕሮፈሰር ፀጋዬ ቱኬ በተጨማሪ ተመሳሳይ ክስ ተመሰርቶባቸዉ የነበሩት የቀድሞ የሲዳማ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበራ አሬራም በነፃ መሰናበታቸውን ጠበቃ ገብረመድህን ተክሌ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስታውቀዋል።


🚨" በሃይማኖት አባቶች የተጀመረው የሽምግል እና የእርቅ እንዲሁም የካቲት 11 በጋራ የማክበር እንቅስቃሴ አልተሳካም አሉ " የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ።

ፕሬዜዳንቱ ለእርቅ እና ሽምግልና አለመሳካት " ቡድን " ሲሉ የጠሩትን አካል ተጠያቂ አድርገዋል።

ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ባወጡት መግለጫ " መንግስት የማያውቀው ርችት በመተኮስ የሚያጋጥም ችግር ካለ ተጠያቂው ቡድኑ ነው " ብለዋል።

አላስፈላጊ የአመፅ እንቅስቃሴዎች እየታዩ መሆናቸው የገለፁት ፕሬዜዳንቱ ፤ ህዝቡ አከባቢውን በልዩ ሁኔታ በመጠበቅ በዓሉ እንዲያከብር አሳስበዋል። 

ከቀናት በፊት ለእርቅና ሽምግልና ፍቃደኛ መሆናቸው በትግራይ የሃይማኖት አባቶች መግለጫ የተሰጠባቸው ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳና የህወሓት ሊቀ-መንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) በትናንቱ የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እጅ ለእጅ ሲጨባበጡ የሚያሳይ ፎቶ መለቀቁ ብዙዎች አስደስቶ ነበር።


ኮካ ኮላ ወደ ሩሲያ ገበያ ለመመለስ እንዳቀደ እና በቀድሞዎቹ ፋብሪካዎቹ ላይ ድጋሚ ማምረት እንደሚጀምር ተዘግቧል

ኩባንያው ቀድሞውንም ወደ ገበያ ለመግባት እና ከሩሲያ ብራንዶች ጋር ለመወዳደር ስልቶችን እየተወያየ ነበር ተብሏል።

Source RT


❗ብሔራዊ ባንክ የዋጋ ግሽበት ቀንሷል ቢልም ተቃራኒ ሪፖርት መውጣቱ ተገለጸ❗

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የሀገሪቱ የዋጋ ግሽበት በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱን ባወጣው የእስታትስቲክስ ሪፖርት ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ይህም በባለፈው አመት ጥር ወር ከነበረበት 29.4 በመቶ ወደ 15.5 በመቶ ዝቅ ያለ ሲሆን ይህም 13.9 በመቶ ማሽቆልቆሉን የሚያመለክት መሆኑን ገልጾ ነበር፡፡

እንዲሁም የምግብ ግሽበት በ16.6 በመቶ እና በምግብ ነክ ያልሆኑ የዋጋ ግሽበት በ10.2 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል ተብሏል።

ይሁን እንጂ ትሬዲን ኢኮኖሚክስ ተደረገ ባለው ጥናት ከብሄራዊ ባንክ ሪፖርት ጋር ተቃራኒ የሆነ ቁጥር መመዝገቡን ገልጿል።

በመሆኑም የኢትዮጵያ አመታዊ የዋጋ ግሽፈት 17 በመቶ እንደሆነ ያስታወቀ ሲሆን የብሄራዊ ባንክ ካወጣው ቁጥር ጭማሪ የሚያሳይ ነው፡፡

ሁለቱም ሪፖርቶች የቁጥር ልዩነት ቢኖራቸውም የዋጋ ግሽበት እንደ አጠቃላይ ከነበረበት መቀነሱን አመላክተዋል፡፡

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.