Let's Save Orthodoxy and humanity( ሰብእናንና ኦርቶዶክሳዊነትን እንታደግ)!!⁉️


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


ሰብእናንና የመንፈስ ልዕልናን ካዳበሩ ቤተሰቦች ጋር በመተባበር በሰብእናና በኦርቶዶክሳዊነት ላይ የሚፈጸምን(የተፈጸመን) ሥርዓታዊ፣መዋቅራዊ፣ሕጋዊ፣መናፍስታዊ፣ስነልቦናዊ ..ጥቃቶችንና አጥቂዎችን እንዲሁም ከጥቃት የመዳኛ መንገዶችን(መፍትሔ) የሚመለከትበት ቻናል ነው::

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


"...ድህነትን ጥጋብ፣ማፍረስን ግንባታ የምትል ፣ከተማን በማብለጭለጭ ድሀን የምታሰቃይ ሆይ!
በህልም ዓለም ኑሮ አየኖርክ ፣በድሀ ስቃይ የምትደሰት በማለት ኃጢአቷን ይገልጥባታል.."ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ


"...የአሁኗ ነነዌ የኢትዮጵያ መሪዎች መረጠነ ከሚሉት ሕዝብ ጋር ጦርነት ከፍተው፣አታሸንፉንም እያሉ የአስከሬን ክምር ያሳዩናል ይሄንን እውነት መደበቅ አይቻልም..."ብጹዕ አቡነ ጴጥሮስ




"አንዲት ዓረፍተ ነገር ስለ ነገራቸው ብቻ፤ሁሉን ነገር ተዉት"

ከነነዌ ሰዎች በላይ የከፉ ማን ነበር? ከነነዌ ሰዎች በላይ ግራውንና ቀኙን የማያውቅ ማን ነበር? ምንም እንኳን ድንጋይ ጠርበው ዕንጨት ቆርጠው የሚያመልኩ አሕዛብ ቢኾኑም፣ ምንም እንኳን ስለ ሀልወተ እግዚአብሔር ምንም ባያውቁም፣
ምንም እንኳን ስለ ፈሪሐ እግዚአብሔር ከማንም ነቢይ ባይማሩም ዮናስ መጥቶ አንዲት አረፍተ ነገር ስለ ነገራቸው ብቻ በሦስት ቀን ውስጥ ኹሉንም ተዉት፡፡ ዘማዊው ንጹሕ ኾነ፡፡ ስግብግቡ ለጋሽ ኾነ፡፡ ቁጡውና ተሳዳቢው መራቂ ኾነ፡፡ ሰነፉ ሰው ለጦም ለጸሎት ብርቱ ኾነ፡፡ ከክፋታቸውም አንዱን ወይም ኹለቱን ብቻ የተዉት አይደሉም፤ ኹሉንም ተዉት እንጂ፡፡ ምንም እንኳን የበደላቸው ጽዋ ሞልቶ መንበረ ጸባዖትን ለቁጣ የቀሰቀሰ የነበረ ቢኾንም ተመለሱ፡፡ ሲመለሱም እግዚአብሔር በቁጣ ሳይኾን በምሕረት ዓይን አያቸው፡፡ ያደርግባቸው ዘንድ በተናገረው ክፉ ነገር ተጸጸተ፡፡ ተወዳጆች ሆይ! የነነዌ ሰዎች ምንም አሕዛብ ቢኾኑም በሦስት ቀን ውስጥ ብቻ እንዲኽ ማራኪየኾነ ንስሐን ከገቡ፥ እጅግ ብዙ ዘመናትን ተምረን ያልተለወጥን እኛው ክርስቲያኖች እንደምን ይፈረድብን ይኾን?”
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

መልካም ጾም


..ለግለሰብ ነው የምንፋጀው፣መጽሐፍ ላይ ተመስርተን እንደ ኦርቶዶክስ ማሰብ ካቆምን ብዙ ዓመታችን ነው፤ይሄ የእግር ኳስ ባህል ነው ላገባው ማጨብጨብ የገባበት ላይ መሳቅ(ማሾፍ) ወደ ኦርቶዶክሳዊ ጸባይ እንመለስ..."መ/ር ፋንታሁን ዋቄ

@tunbi_media


"በሰላሌ(ግራር ጃርሶ ወረዳ)ለከተራ ወጥተው በኦነግ ሸኔ የታገቱ 11 ካህናት እስከአሁን አልተለቀቁም። "ዲ/ን ዮሴፍ

በዓሉ በድምቀት ተከብሯል በሚል መዝገቡ ከተዘጋ ሰንብቷል

@tunbi_media


"እስካሁን ያልተደፈረውን ምሥጢረ ቅዳሴ፣ውስጠ ይዘቱን ለመቀየር እየሰሩ ያሉ አሉ"👆
እኛስ ምን አናድርግ 👂
ሙሉ መርሀ ግብሩን በቱንቢ

@tunbi_media




በሰሜን ሸዋ ዞንኤፍራታናግድም ወረዳ አገዛዙ በፈፀመው የድሮን ጥቃት የ4 ንፁኃኖች ሕይወት አልፏል!

በዛሬው ዕለት ከሌሊቱ 11:00 ሰዓት ገደማ በኤፍራታና ግድም ዘንቦ ቀበሌ በሰነዘረው የድሮን ጥቃት እናት ከእነ ልጇ ጨምሮ 4 ሲቪሊያን ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን ከ20 በላይ የቀንድና የጋማ ከብቶች ላይ ጉዳትና ውድመት አድርሷል።

መረጃው የፋኖ አበበ ሙላቱ ነው!


" ገንዘቡን፣ ሃይማኖቱንና ነፍሱን አጣ"

በእጁ ያቆረባቸውን ልጆቹን በሰይፍ የገደለው ፎላ እና ፍጻሜው

ሰማዕቷ ቅድስት ጤቅላ፡- ጤቅላ ማለት ‹‹ልጅ፣ ለግላጋ›› ማለት ነው፡፡ ቅድስት ጤቅላና ከእርሷ ጋር የነበሩ አራት ደናግል ጥር 30 ቀን ፎላ በሚባል ኃጥእ ቄስ እጅ ሰማዕትነታቸውን ፈጸሙ፡፡ ይህም ፎላ የተባለ ቄስ በአመጽ የሰበሰበው ብዙ ገንዘብ እንዳለው በከሃዲው መኰንን ዘንድ ነገሩበት፡፡ ስለዚህም መኮንኑ ገንዘቡን ሁሉ እንዲወርሱ አዘዘ፡፡ ፎላም ወደ መኰንኑ ዘንድ በመሄድ ገንዘቡን ይመልስለት ዘንድ ቢለምነው እምቢ አለው፡፡ ከሃዲው መኰንንም ስለ እነቅድስት ጤቅላ የምግባር የሃይማኖታቸውን ዜናቸውን በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ እንዲያመጧቸው አዘዘና አስመጣቸው፡፡ ጌታችንን አስክዶ እምነታቸው አውጥቶ ለጣዖት እንዲገዙ ግድ አላቸው፡፡ እነርሱ ግን በእምነታቸው በጸኑ ጊዜ መኰንኑ ፎላንን ጠርቶ ‹‹እነዚህ ደናግል ለፀሐይ ይሰግዱ ዘንድ እነርሱን ብትሸግልልኝ ገንዘብህን መልሼ እሰጥሃለሁ›› አለው፡፡ ፎላንም እነ ቅድስት ጤቅላን ይሸነግላቸው ጀመረ፡፡ ደናግሉም ‹‹አንተ የሰይጣን ልጅ የክብር ባለቤት ክርስቶስን እንክደው ዘንድ እንዴት ትፈትነናለህ? አንተ ቀድሞ መምህራችን የነበርክ ስትሆን›› ብለው ዘለፉት፡፡
መኰንኑም ይህን ቃላቸውን ከአንደበታቸው በሰማ ጊዜ በጅራፍ ጽኑ ግርፋትን አስገረፋቸው፡፡ እነዚህ ቅዱሳት ደናግል ግን ስለ ጌታችን ይመሰክሩ ነበር እንጂ ምንም አልፈሩም ነበር፡፡ መኰንኑም ፎላንን ‹‹የበከተ ብትበላ ደምንም ብትጠጣ ገንዘብህን እመልስልሃለሁ›› ባለው ጊዜ እንዳለው አደረገ፡፡ ዳግመኛም ‹‹እነዚህን ደናግል ብትገድላቸው ገንዘብህን እመልስልሃለሁ›› አለው፡፡ ፎላም ይህን በሰማ ጊዜ እንደ አስቆሮቱ ይሁዳ ልቡ በገንዘብ ፍቅር ተነድፏልና ልቡናውን አጽንቶ ቅዱሳት ደናግሉን ሊገድላቸው ሄደ፡፡ እነርሱም እንዲህ አሉት፡- ‹‹ከሃዲ ሆይ የመድኃኒታችንን የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን በእጅህ ታቀብለን አልነበረምን? ስለ ገንዘብ ፍቅር ብለህ እኛን የክርስቶስን በጎች ልታርድ መጣህን?›› እያሉ በገሠጹት ጊዜ ሰልፍ እንደተማረ አርበኛ ሰው ሆኖ በሰይፍ ራስ ራሶቻቸውን ቆረጣቸው፡፡ መኰንኑም የፎላንን ብላሽነትና ድንቁርናውን አይቶ ወዲያው በሰይፍ ገደለው፡፡ ፎላም ገንዘቡን፣ ሃይማኖቱንና ነፍሱን አጣ፡፡ የእነዚህም ቅዱሳት ደናግል ስማቸው መሪ የሆነቻቸው ጤቅላ፣ ማርያ፣ ማርታ፣ አመታ፣ አበያ ሲሆን ጥር 30 ቀን ሰማዕትነታቸውን በድል ፈጽመው የክብር አክሊልን ተቀዳጅተዋል፡፡ የሰማዕታቱ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!ስንክሳር ዘጥር 30


ዋቄ ገጽ dan repost
አሁን በኦርቶዶክስና አማራ ላይ የሚካሂደው ዘር የማጥፋት ፕሮጄክት አሁን ያለበት ደረጃ የደረስው በርዥም ዘመን የውስጥ ሤራና የክፉዎችና የተወሳሰበ ድርጊትና ፕሮፓጋንዳ ነው። መልካም ሰብእና ያላቸው ብዙሃን በዝምታ በመዋጣቸው ቤተ ክህነቱ ሳይቀር በክርስቶስ ስም ተሰይመው ለሆዳቸውና ለጎጣቸው ባርያ የሆኑ የበላይነት አገኙ።
አሁን ጊዜው መልካሞችና እውነተኞች፣ ከጥላቻና ከቅጥፈት ነጻ የሆኑ በዙኃን ሰዎች ተነስተው የሚሠሩብት ዘመን ነው!!

ከቂት ደቂቃዎቸ ብኋላ ረምብል ላይ ቪዲዮ በዚህ ሊንክ ተመልከቱ። ኦሮምኛና ትግርኛ የምትችሉ ትርጉም ሥሩና ለደነዘዘው፣ በዓላትና ጫጫታ ለተጠመዱት ንቃት ፍጠሩላቸውና ወደ ተግባራዊ ተጋድሎ እንዲጀመሩ እርዷቸው። https://rumble.com/v6i85qd-393410821.html


የአፍሪካ መሪዎች ሰው ነን ትላላችሁ?

ዶናልድ ትራምፕ ለአፍሪካውያን መሪዎች ያስተላለፉት መልእክት።

👉🏿 ከ50 ዓመታት የአህጉሪቷ የነጻነት ጉዞ በኋላ፣ ለህዝባችው አስፈላጊውን መሠረተ ልማት ካላሟላችው ሰው ነን ብላችው ታስባላችው?


👉🏿በወርቅ፣ በአልማዝ፣ በነዳጅ፣ በዩራኒየም፣ በብረት፣ በማዕድን፣ በብር፣ በማግኒዥየም፣ በነሐስ፣ በጋዝ የተፈጥሮ ሃብቶቻችው ላይ ተቀምጣችው፣ ህዝባችው በረሃብ፣ በትምህርት አለመዳረስ፣ በጤና አገልግሎት እጦት፣ ሲሞት፣ ሰው ነን ብላችው ታምናላችው?

👉🏿በስልጣን ላይ ቆይታችው፣የራሳችሁን  ዜጎች ለመግደል ከውጭ የጦር መሣሪያዎችን ስታስገቡ፣ ሰው ነን ብላችው ታስባላችው?

👉🏿የገዛ ዜጎቻችሁን እንደውሻ ስታንገላቱና ስትገድሉ፣ ማን ዜጎቻችሁን እንዲያከብር  ትጠብቃላችው?

👉🏿በራሳችው  አገር ላይ ቀማኛና ሌባ በመሆናችው ፣ የሃገራችሁን  ሀብቶች ሁሉ በመስረቅ፣ አብዛኞቹ ዜጋዎቻችው በስደትና በድህነት ውስጥ እንዲያልፉ ስታረጉ፣ የሰው ልጆ ነን ብላችው ታስባላችው?

ከ ፌስቡክ የተገኘ


ዋቄ ገጽ dan repost
የቀሲስ አስተራየ ጽጌ መልእክቶች

https://t.me/kesisasteraye


ቤተ ክርስቲያን ተቀርጸን የምንወጣበት ተቋም ናት
(ለወላጆች እና ለአሳዳጊዎች)

በልጅነት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተቀርጸን ስናድግ እጅግ መልካም ነው። ጅማሮ በመልካም ቦታ ከሆነ አዎን ፍጻሜውም ያማረ ይሆናል። መጨረሻው የሚያምረው መጀመርያው ያማረ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረገ ነው። ልጆቻችንን ወደ ቤተ ክርስቲያን የምንልከው ደግሞ መልካም ሰዎች እንዲወጣቸው ብቻ ሳይሆን ቅዱሳንን እንዲሆኑ ነው።

ልጆች በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሰጥቶ ማሳደግ ለቤተ ክርስቲያን ፍቅር እንዲኖራቸውና ለሃይማኖታቸው ባዕድ እንዳይሆኑ ያደርጋል። ቅዳሴው ሰዐታቱን ኪዳኑን በልጅነት ካልታወቀ ዕድሜ ከገፋ በኋላ የሚመጣ ንዝላልነት እና ስንፍና ለቤተ ክርስቲያን እና ስርዐቷ ባዕድ ያደርጋልና ከልጅነት የተኮተኮተ ፍቅረ እግዚአብሔር በወጣትነት በጎልማሳነት ያፈራል። በእሮግናም ክብር ይሆናል።

ልጆች እንዴት ወደ ቤተ ክርስቲያን ይሄዳሉ
ነገር ግን ልጄን እንዴት ወደ ቤተ ክርስቲያን ዝም ብዬ እልካለው የሚል የወላጆች ፍርሃት አለ። እንደ እውነቱ ልጅን በፍርሃት ማሳደግ ከምንም አያድነውም። በዓለም ከስንት ነገር ጠብቀንስ ይቻላል። ባይሆን ልጅ በእምነት ሲያድግ መልካም ነው። እግዚአብሔርን በማመን ያደገ ልጅ ጠንካራ የሚጠቅመውን እና የሚጎዳውን የሚያውቅ በመንፈሳዊ ህይወቱም ብርቱ ዘወትር የሚያድግ ይሆናል። ፍርሃት ሳይሆን እምነት ልጅን ጤናማ አድርጎ ያሳድጋል። ልጆች መንፈሳዊ እንዲሆኑ የሚደረግ የወላጆች ትጋት ወላጆችንም መንፈሳዊ ያደርጋል። የአንድ ሀገር ነባራዊ ሁኔታ ለመረዳት ህጻናቶቿን ላይ እየሆነ ያለውን መመልከት ነው።

ልጆች እንዴት ይደጉ
ሀገራችንን ስንመለከት ደግሞ በእውነት እግዚአብሔር ካልሆነ በማን መታመን ይቻላል? ልጆቻችንን ጠንቅቀው በሃይማኖት እንዲያድጉ የንባብ የጸሎት የምጽዋትን ፍቅር በልባቸው እንኮትኩትባቸው። ለሰው መራራትን ለሕገ እግዚአብሔር ያለ ቀናኢነት በልጅነት ካልተሰራ በኋላ አይመጣም። ቢመጣ ብዙ ያለፋል። ስለዚህ እንዲህ እናሳድርግ
፠ ልጆቻችንን በአደራ ለአብነት መምህራን ወስደን እንስጥ ዘወትርም እንከታተል
፠ ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ ቀጥታ እንከታተል
፠ ከትምህርት ሰዓት ውጪ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚያሳልፉትን ጊዜ እንቆጣጠር
፠ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሚያፈሩትን ጓደኛ እንመልከት
፠ ቤተክርስቲያንን እንደ መዋያ ሳይሆን ሕይወት ይመለከቷት ዘንድ መንፈሳዊ አቅጣጫ እንስጥ
፠ ከሥርዐተ አምልኮት ከቅዳሴ እንዳይርቁ ክትትል እናድርግ
፠ ሚዲያን ስልክን ለመንፈሳዊ አገልግሎት እንዲጠቀሙ እናስለምድ
፠ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ እና የቅዱሳንን ህይወት ማወቅ ከልጅነት ይተረክላቸው
፠ ቅዱሳንን አርአያ እንዲያደርጉ ከቅዱሳን ጋር ቤተሰብ እናድርጋቸው።
፠ ካህናት ማናገር እና ንስሐሃም ይለማመዱ
፠ ከቤተ ክርስቲያን ውጪ ባለው ማንነታቸው እና በቤተክርስቲያን ውስጥ በሚቀረጸው መካከል ተስማሚነት ላይ አተኩረን እንስራ።


እምየ ተዋህዶ Emye Tewahedo dan repost
Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ኦሮሚያ ውስጥ የጠፋ መስሎ ተዳፍኖ ውስጥ ለውስጥ እየተስፋፋ ያለው እሳት

ህገወጡ ''የጳጳሳት'' ቡድን በአደባባይ መውጣት ባይችሉም የቤት ለቤት አገልግሎት እየሰጡ ነው

ጳጳስ ሳይሆኑ የዋሁን ምዕመን ቤት ድረስ እየሄዱ አገልግሎት ሲሰጡ ዝም ማለት ደግሞ በሃይማኖት ሽፋን ምዕመኑን ማዘረፍ ነው ።

ገና ብዙ ዋጋ ሚያስከፍል ጉዳይ ከፊታችን አለ


(ዘ-ሐበሻ ዜና) | "የተከሰስኩት የመንግሥትን ብልሹ አሠራር በማጋለጤ ነው:: በእስር ላይ የምገኘው የወንጀል ድርጊትን የሚያቋቁም የሕግ መተላለፍ ስለፈጸምኩ አይደለም። ለእስር የተዳረግኩትት የገዢውን ፓርቲ እና የመንግሥት አሠራሮችን እንዲሁም የአመራሮችን ብልሹነት እና ዘረፋ በመታገሌ እና በማጋለጤ ነው። በምክር ቤቱ በመንግሥት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢነት በነበረኝ ኃላፊነት የሠራሁት የማጋለጥ ሥራ ነው ለእስር የዳረገኝ። በዚህ ኃላፊነቴ ተደጋጋሚ የአመራር ብልሹነት ያሳዩ አካላት ላይ የወንጀል እና የፍትሐ ብሔር ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ፣ ክስ እንዲመሠረት ፍትሕ ሚኒስቴርን አዝዤ ነበር። በምክር ቤት አባልነቴም፣ እንደ ቋሚ ሰብሳቢነቴም የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የፋይናንስ ግልጸኝነት እና ሕጋዊነትን እንዲከተሉ እና እንዲያረጋግጡ ጠይቄ ነበር። እነዚህን ጥያቄዎች እንዳልጠይቅ አንዳንድ አመራሮች በግል በኢመደበኛ ሁኔታ ሊያግባቡኝ ሞክረዋል። ይህን ባለመቀበሌ በዚህ ሳቢያ ለእስር ተዳርጌያለሁ"
- አቶ ክርስቲያን ታደለ ዛሬ በችሎት የዕምነት ክህደት ቃላቸውን ሲሰጡ ከተናገሩት
ሙሉውን ከዜናችን ላይ መመልከት ይቻላል።


#በባንዳነት በትልቁ የተመዘገቡት ደጃዝማች ጉግሳ ኃይለሥላሴ እና ራስ ኃይሉ ተክለሃይማኖት

frim Ethiopian hisory and tourism

መዝግብ
ለሀገር እጥፊ ቡድን በዘመቻ እና በዝምታ የተሰለፋችሁ
ከምዕመን እስከ ሀይማኖት መሪ፤
ከሚሊሻ እስከ ጦር አዝማች፤
ትውልድ እና ታሪክ በዚህ መልኩ ይዘክራችኋል


የቀጠለ👆👇
ጊዜው አልረፈደም እንዲስተካከል እንጠይቃለን። ካልተስተካከለ የእርስ በእርስ የአገልጋዮች ዕልቂት እንደሚፈጠር አስረግጨ መናገር እፈልጋለሁ። የአጥማቂው ጀሌዎች ሐሳብና ዕውቀት የሌላቸው መሆኑን ስንቶችን የአካል ጉዳተኛ እንዳደረጉ ሕይወት እንዳጠፉ የሚያውቅ ያውቀዋል። ዛሬም ያንን ሲደግሙትና አጥቢዎችን በጉልበት ሲወሩት ዝም የምንልበት ምክንያት አይኖርም።
እነ መምህር ገብረ መድኅን ዋጋ ከፍለው ሰጥ ያሰኙትንና ከምዕራብ ጎጃምና ከሌሎች ሀገረ ስብከቶች እንዳይንቀሳቀሱ ያደረጉትን ጉድ እናንተ በማን አለብኝነት ነፍስ ስትዘሩባቸው ማንም ዝም አይልም። ጦርነት ላይ ላለ ሕዝብ ሌላ ጦርነት አንፈልግም። ግን አይ ካላቸው አሁን ድሮ አይደለምና ዋጋ ትከፍላላችሁ።
ማኅበረ በኩራት ማለት የሐሳዊ መሲሕ መንገድ ጠራጊዎች ቡድን ነው።

ይድረስ
ለባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ሥራ አስኪያጅ
የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት
Mahibere Kidusan - ማኅበረ ቅዱሳን ባሕር ዳር ማእከል
  ቤተ ክርስትያን ስትወረር ቁመን አናይም


እስከዛሬ ድረስ ለዓመታት ዋጋ እየከፈልሁ ያለሁት በአጥማቂው ዮሐንስ ምክንያት ነው። ከምወደው መሥሪያ ቤትም የተፈናቀልሁት በእሱ ጀሌዎች እንግርግሪያ ነው። ግን ባንተ ስሜት ልክ የሚጓዝ መሪ ከሌለህ ሁለመናህም ይወረስብሃል። ይኸው ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጀምሮ እስከ ባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ድረስ ወረሩን። የመጨረሻውን ጦርነት አድርገን ግልብጥ ብለን መጥተን ሀገረ ስብከት የምትሉትን እንበትነዋለን። ብፁዕ አአቡነ አብርሃም ሆይ ከእርስዎ ጋር ስለ አጥማቂያን ገመና ከማስረጃ ጀምሮ አውርተን ነበርና እኔ በግሌ እንደሚያስተካከሉት ተስፋ ነበረኝ። ስለ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን፣ ስለ ንዋዕያተ ቅድሳት ዝግጅትና ሽያጭ፣ ስለ አእምሯዊ ንብረት፣ አጠቅላይ መንፈሳዊ ሕትመቶች ማእከላዊ ሆነው እንዲታተሙና ሌሎች ጉዳዮችም ጭምር አውርተን በእርስዎ የሥራ አስኪያጅነት ዘመን እንደሚስተካከሉ ተስፋ ነበረኝ። ግን ብፁዕነትዎ የተለወጠ ነገር የለም ይባሱን ይኸው ሀገረ ስብከት ላይ ሃይማኖተኛ መሳይ ከሃይማኖቱ መንገድ ውጭ ለሚንቀሳቀሱ ጎረምሶች ዕውቅና ሰጥተው እሾህ እንዲተከል አመቻችተዋል ወይም በቀጥትታ ፈቅደዋል ወይም በዝምታ አልፈዋል።


ኢትዮ ቱንቢ ሚዲያ Ethio Tunbi (Official) dan repost
#በተለይ_ለኢትዮጵያውያን #የነፃ_ተሳፋሪነት_ጽንሰ_ሐሳብ #Free_Rider_Theory #የምንፈልገው_ሀገራዊ_ሁኔታ_ቁልፍ_ጉዳይ #በያሬድ_ኃይለመስቀልhttps://youtu.be/wfjZKbYHQG4?si=_5W_1Mb_CM1eSG5T

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.