🌹✨ሀዘል ሀቢብ✨🌹✍ለትልቁ ሠውም ሆነ ለሶሐቦችም ከባድ በነበረው ዘመቻ ላይ ዘይነልዉጁድን ﷺ ለመከላከል ከጎናቸው ጦርነትን መካፈልን የተጠማው ጦልሓ ኡሁድ ላይ ጀግንነቱን አሳየ!
ዘይነልዉጁድ ﷺ በተጣሩ ቁጥር ቶሎ የሚመልሰውና ካጠገባቸው ስለማይጠፋው ጦልሓ አንዲህ አሉ፡
«♦️
لقد رأيتُني يومَ أُحُدٍ ، و ما في الأرضِ قُرْبِي مخلوقٌ ، غيرُ جبريلَ عن يميني ، وطلحةَ عن يَسَاري♦️»✨♦️የኡሁድ ወቅት እራሴን ተመለከትኩት ማንም ለኔ ቅርብ አልነበረም። በቀኜ ሰይዲና ጂብሪልና በግራዬ ጠልሓቱ ውጪ...🥹
ወደ ዘይነልዉጁድ ﷺ የሚወረወሩትን እያንዳንዱን ቀስቶች በአንድ እጁ እየተከላከለ በሌላኛው እጁ ደግሞ በሰይፍ ይዋጋ ነበር..መገን እሱን😍
... ቁስል ቁስል ላይ ቢደራረበበትም እስከሚችለው አቅም ለዘይነልዉጁድﷺ ተከላከለ። ሠይደልዉጁድንﷺ በቆሰለው ጀርባው ላይ ተሸክሞ ተጓዘ! እሳቸውን ማትረፍ ላይ ቁዋው መጣለት።
ጌታው ሸይኽ ሚስባህ ዳና ከነቢ ዘይኔ ድርሳናቸው፡
ለዕነቱላህ አለይ ኢብነ ቀመዐት፣
በሰይፍ መታና አቆሰለዎት፣
ትካሻዎን ገፍቶ ጉርቢያ ዶለዎት፣
በፊተዎ ደሙን አፈታበዎት፣
ልበዎ ፈሰሰ መቼም ሰው ነዎት፣
በወገቡ አድርጎ ጦልሀቱ አወጣዎት ፣
የዚያንለታ ታየ የጦልሀቱ ኦኔ፡፡
♦️✨♦️✨♦️✨💚✨♦️✨♦️✨♦️
ያንን ሁላ ቁስል ምንም አላጀበዉ፣
የነቢ ደም መፍሰስ ነው ያንገበገበዉ፣
እንኳን እሱን እኔን ልቤን አዋከበዉ፣
አይኔን አስለቅሶ ዛቴን አራገበው፣
ዋ ከቶ ዋ ከቶ ዋልኝ ዋልኝ ለኔ🥹በማለት ቃኙ።
ሙሉ ሰውነቱ ቁስል ብቻ የሆነው ጠልሓ ሠይዲን ﷺ በነበሩበት ሁናቴ ዳግም ሩህ ዘራበት፤ እግሮቹ ተንቀሳቀሱለት። ተሸክሟቸውም ወደ ተራራው ወጣ! ይህንን ክስተት ከሩቅ የተመለከቱት ሲዲቂዩ እና አቡ ኡበይዳ ኢብኑል ጀራህ ሲመጡ ሠይዲምﷺ በደከመው አንደበት ወደ ጠልሓ እየጠቆሙ «እኔን ትታቹ ጓድ'ኣቹ ጋር ሂዱ!»አሏቸው።
ሲዲቂዩ አህዋሉን ሲናገገሩ : «ጠልሓን ስናየው ሙሉ ሰውነቱ ቁስል በቁስል ነበር..ከእያንዳንዱ ሰውነቱ ደም ይፈስ ነበር! ከቀስት፣ ከድንጋይ፣ ከጦር፣ ከጎራዴ ብዙ ቁስሎች አርፈውበት ነበር። እራሱንም ስቶ ከአፉም ደም እየተፋ ነበር»አሉ።
«
ጀነት ጦልሓቱ ላይ ዛሬ ወጅቦበታል!»አሉ ዘይነልዉጁድ😭... አወይ መሐባ.. የማያደርገው የለምስ!
https://t.me/sufiyahlesuna