🟢 የዙል ሒጃ ተክቢራ
የዙል ሒጃ ተክቢራ በሁለት ይከፈላል ። ልቅ የሆነና የተገደበ ተክቢራ በመባል ይታወቃል ።
– ልቅ የሆነው ተክቢራ ዙል ሒጃ ከገባበት ቀን ጀምሮ እስከ 13ኛው ቀን ድረስ ይቀጥላል ። ይህ በሶላት ወቅት የተገደበ ሳይሆን በማንኛውም ጊዜ የሚደረግ ተክቢራ ነው ። ይህን አስመልክቶ አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል :–
« لِّيَشْهَدُوا مَنَافِعَ لَهُمْ وَيَذْكُرُوا اسْمَ اللَّهِ فِي أَيَّامٍ مَّعْلُومَاتٍ عَلَىٰ مَا رَزَقَهُم مِّن بَهِيمَةِ الْأَنْعَامِ ۖ فَكُلُوا مِنْهَا وَأَطْعِمُوا الْبَائِسَ الْفَقِيرَ »
الحج ( 28 )
" ለእነሱ የሆኑ ጥቅሞችን ይጣዱ ዘንድ በታወቁ ቀኖችም ውስጥ ከለማዳ እንስሳዎች በሰጣቸው ሲሳይ ላይ የአላህን ስም ያወሱ ዘንድ (ይመጡሃል) ፡፡ ከርሷም ብሉ ፡፡ ችግረኛ ድሃንም አብሉ "፡፡
የተፍሲር ሊቃውንቶች በታወቁ ቀኖች የሚለው የዙል ሒጃ 10ሩ ቀኖች ናቸው ብለዋል ።
አያመ ተሽሪቅን አስመልክቶ በሚቀጥለው የአላህ ቃል እንዲህ የሚል እናገኛለን : –
« وَاذْكُرُوا اللَّهَ فِي أَيَّامٍ مَّعْدُودَاتٍ ۚ فَمَن تَعَجَّلَ فِي يَوْمَيْنِ فَلَا إِثْمَ عَلَيْهِ وَمَن تَأَخَّرَ فَلَا إِثْمَ عَلَيْهِ ۚ لِمَنِ اتَّقَىٰ ۗ وَاتَّقُوا اللَّهَ وَاعْلَمُوا أَنَّكُمْ إِلَيْهِ تُحْشَرُونَ »
البقرة ( 203 )
" በተቆጠሩ ቀኖችም ውስጥ (በሚና ጠጠሮችን ስትወረውሩ) አላህን አውሱ ፡፡ በሁለት ቀኖችም ውስጥ (በመኼድ) የተቻኮለ ሰው በርሱ ላይ ኃጢኣት የለበትም ፡፡ የቆየም ሰው በርሱ ላይ ኃጢኣት የለበትም ፡፡ (ይህም) አላህን ለፈራ ሰው ነው ፡፡ አላህንም ፍሩ ፡፡ እናንተ ወደርሱ የምትሰበሰቡ መኾናችሁንም ዕወቁ " ፡፡
እነዚህን ቀኖች አስመልክቶ የአላህ መልእክተኛ – ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም — እንዲህ ይላሉ : –
" أيام التشريق أيام أكل وشرب وذكر الله عز وجل "
رواه مسلم في صحيحه
" ሶስቱ የተሽሪቅ ቀናቶች ( 11,12,13, ) የመብያና የመጠጫ እንዲሁም አላህ የሚወሳባቸው ቀናቶች ናቸው "።
– የተገደበ ተክቢር ይህ ከአምስት አውቃት ሶላት በኋላ የሚደረግ ሲሆን ከ8ኛው ቀን ዐስር ሶላት ወይም ከ9ኛው ቀን ፈጅር ሶላት ጀምሮ እስከ 13ኛው ቀን ዐስር ሶላት ድረስ የሚደረግ ነው ። በዚህም ልቁና የተገደበው ተክቦራ ለአምስት ቀናቶች ይገናኛሉ ማለት ነው ።
በመሆኑም በእነዚህ ተወዳጅ ቀኖች ተክቢራ ማብዛትን አንርሳ ።
አላህ ከተጠቃሚዎች ያድርገን ።
http://t.me/bahruteka