በዚህ ጉዳይ ላይ ያለኝን የግል ሃሳብ ለማጋራት ያህል፡በሪያል ማድሪድ በኩል፦ ራሱን መመርመር ከማይፈልግ አካል ጋር በዚህ ደረጃ ውዝግብ ውስጥ መግባት ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል።
እንደ ግል ሳስበው ደግሞ አንዳንዴ የሪያል ማድሪድ አቋም ጥሩ ነው... ማናቸውም ክለቦች ያሽቃበጡለት ላሊጋ ልክ የዳኝነት ነገሮች ከነሱ እጅ ሲወጣ ማድሪድ በላሊጋው ይደገፋል የሚለውን መፈክር ለማሰማት ቢፈልጉም ሞራሉን ያሳጣቸዋል።
አትሌቲም ሆነ ባርሳ የእጃቸውን ላሊጋው ይሰጣቸዋል። የስፔን ዳኝነት ተበላሽቷል በሚለው አንስማማም ካሉ ከዚህ በኋላ በየጨዋታዎቻቸው ለሚፈጠሩ ጉድለቶች ቅሬታ ስለማቅረብ የማያስቡበት ሁኔታ ነው የሚፈጠረው።
ከፍትህ ጎን ያልቆመ ነግ በኔ የሚለውን አያውቅም፤ ስለዚህ እስኪያርር ድረስ ተከድኖ ይበስላል የሱ ጊዜ ሲመጣ... ወደው ነው የተደፉት።
@ETHIO_REAL_MADRID_15@ETHIO_REAL_MADRID_15