#አሜሪካ በኮቪድ-19 በፅኑ ለታመሙ የሚሆኑ 250 ሜካኒካል ቪንቲሌተሮችን #ለኢትዮጵያ ሰጠች❗️
⚡️ድጋፉን ያስረከቡት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምሳደር ማይክል ራይነር ሲሆኑ፥ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ተረክበዋል።
⚡️ሜካኒካል ቬንቲሌተር በኮቪድ-19 በጽኑ ለታመሙ የአየር ሥርዓት ፍሰትን ለማስተካከል የሚረዳ መሳሪያ ሲሆን÷ የቫይረሱ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ በዓለም ላይ እጅግ ተፈላጊና ውድ መሳሪያ መሆኑ ተጠቅሷል።
⚡️ዛሬ ድጋፍ የተደረገው የሜካኒካል ቬንቲለተር የአንዱ ዋጋ 8 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ሲሆን÷ አጠቃላይ ዋጋ 70 ነጥብ 9 ሚሊየን ብር ነው።
⚡️በኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ ድርጅት ቅጥር ግቢ በተካሄደ የርክክብ ስነስርዓት ላይ አምባሳደር ማይክል ራይነር÷ ኮቪድ-19 የዓለም ቀውስ ሆኖ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ዜጎቿን ከዚህ በሽታ ለመጠበቅ ሰፊ ስራዎችን በመስራት ላይ መሆኗን ጠቁመው÷ ይህንን ጥረት ለመደገፍም የአሜሪካ መንግስት የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
⚡️በዚህም ዛሬ 250 መሣሪያዎች ድጋፍ ማድረጉን በዚህም ደስተኛ መሆናቸውን ነው የገለፁት። ወደፊትም ሀገራቸው ኢትዮጵያ የምታደርገውን ጥረት ለማገዝ ድጋፉ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
•በቀጣይም 250 ሜካኒካል ቪንቲሌተሮችን ለማምጣት በሂደት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
ምንጭ ©ፋና
@EthioCovid19News @EthioCovid19News