Postlar filtri






በቀልብ ዉስጥ ካሉ መልካም አምልኮቶች ሁሉ ትልቁ አላህን መውደድ ነው። በአላህ ይሁንብኝ አላህን ከመውደድ ዉጭ ባለ ነገር  ቀልብ ልትዋብም ይሁን ልትስተካከል አትችልም።
አንድ አማኝ ጌታውን ሲወድ አምልኮቶቹ ሁሉ ይቅሉታል፣ አካላቶቹም ይታዘዙታል፣ ልቡም ጌታውን በመፍራት ይተናነሳል፣ ዐይኖቹም ማንባት ይችላሉ፣ መልካም ምላሽ እምደሚያገኝ እርግጠኛ ሆኖም ዱዓእ ማድረግ ይችላል።
شيخ إبراهيم بن عامر الرحيلي حفظه الله
ሶሂሁል ሙስሊምን ሲያብራሩ ካስተላለፉት ምክር የተወሰደ
°°°°′°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ጌታችን ሆይ አንተን፣ አንተን የሚወዱን ሰዎች እንድሁም አንተ የምትወደውንና ወደ አንተ የሚያቃርበንን ሁሉ አስወድደን።


ሚገርም እኮ ነው!!!

አገሪቱ ላይ 2959 ትምህርት ቤቶች የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና አስፈትነዋል።

በ 1,161 ትምህርት ቤቶች። የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና አንድም ተማሪ አላለፉም።

ወደ 1798 የሚጠጉ ትምህርት ቤቶች አንድአንድ ተማሪ አሳልፈዋል።

ከ2959 ትምህርት ቤቶች መካከል 6 ትምህርት ቤቶች ያስፈተኗቸው ተማሪዎቻቸው ሙሉ አሳልፈዋል።

ለፈተና የተመዘገቡ ተማሪዎች ብዛት 985,354 ነበር።

ከነዚህ ውስጥ 8% ፈተና አልወሰዱም።

ወደ 20,000 ሺ የሚጠጉ ተፈታኞች ለፈተና ከተቀመጡ በኋላ በደንብ ጥሰት ከፈተና ተባረዋል።

ከ985,354 ተፈታኞች  ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የሚዘዋወሩት 29,909 ተማሪዎች ብቻ ናችው።

የተቀሩት 955,445  ተፈታኞች የሚፈለገውን የማለፊያ ውጤት አላስመዘገቡም።


ሙስሊማት ያልሆኑ ሴቶችን ማግባት
~ ~ ~ ~ ~
ለሙስሊም ወንዶች ከነ ጭራሹ ሃይማኖት የሌላቸውን ሴቶች ማግባት ፈፅሞ አይፈቀድላቸውም። ሙስሊማት ያልሆኑ ሴቶችን ባጠቃላይ ማግባትም እንዲሁ የተፈቀደ አይደለም። ከዚህ ተለይቶ የሚወጣው እራሳቸውን ከዝሙት የሚጠብቁ ክርስቲያን ወይም አይሁድ ሴቶችን (ኪታቢያት) ማግባት ብቻ ነው። ክርስቲያን ወይም አይሁድ ሴቶችን (ኪታቢያት) ማግባት እንደሚፈቀድ ግን ቁርኣን ውስጥ ተጠቅሷል። አላህ እንዲህ ይላል፡-
(وَالْمُحْصَنَاتُ مِنَ الَّذِينَ أُوتُوا الْكِتَابَ مِنْ قَبْلِكُمْ)
“ከነዚያ ከናንተ በፊት መፅሐፍ ከተሰጡት (አይሁድና ክርስቲያን) ሴቶች ጥብቆቹም (ልታገቧቸው የተፈቀዱ ናቸው።)” [አልማኢዳህ፡ 5]
.
ይህንን መነሻ በማድረግ ሙስሊም ካልሆኑ ሴቶች ጋር ጋብቻ የሚመሰርቱ ሙስሊም ወንዶች አሉ። ነገር ግን እዚህ ላይ የቁርኣኑን መልእክት በደንብ ማጤን ያስፈልጋል። ጋብቻ የተፈቀደው በመልካም ስነ ምግባር ከሚታወቁ እራሳቸውን ከዝሙት ከጠበቁ ሴቶች ጋር ነው። ይሄ ሁኔታ ባልተሟላበት ዝም ብሎ ልብ ስላዘነበለ ብቻ ወይም ፍቅር ላይ ስለወደቁ ብቻ የሚፈፀም ልቅቅ ያለ ህግ አይደለም። ስለዚህ የቁርኣኑን መልእክት ለስሜታዊ ዝንባሌያችን ምርኩዝ እንዳናደርግ መጠንቀቅ ይገባል።
.
በዚህ ዘመን ሙስሊም ያልሆኑ ህዝቦች ከጋብቻ በፊት ያለ ህይወታቸው እጅግ የተጨመላለቀ እንደሆነ በተጨባጭ እያየን ነው። ዝሙቱ ቀርቶ ከትዳር ውጭ መውለዱ እንኳ እንደ ‘ኖርማል’ እየተቆጠረ ነው። ሰፊ እውቅና ያላቸው ስብእናዎች ሳይቀሩ ህዝብ በሚከታተለው ሚዲያ ላይ ቀርበው “ትዳር የለኝም፣ ግን ልጅ አለኝ” ሲሉ ምንም አይሰቀጥጣቸውም። ልጅ እንዳላቸው የሚታወቁ ግን ትዳር ባለመመስረታቸው የተነሳ ዛሬም “ወይዘሪት እንትና” እየተባሉ የሚጠሩ ብዙ ናቸው። ባጭሩ ከትዳር በፊት የዝሙት ህይወት ማሳለፍ ብዙዎቹ ዘንድ ነውርነቱ ቀርቷል። እንዲያውም “ዝሙት” መባሉ ቀርቶ “ከጋብቻ በፊት ግንኙነት” እየተባለ ነው እየቀረበ ያለው። ይሄ ከጋብቻ በፊት ያለ ግንኙነት ምናልባት በስሱ ከተነቀፈም በፀያፍነቱ እየተኮነነ ሳይሆን ለቀጣይ ህይወት መሰናክል እንዳይሆን ያክል ብቻ ተራ የግል አስተያየት ሆኖ ነው የሚቀርበው። በዝሙትነቱ ሳይሆን ለሴቷ ከሚያስከትለው ጥቅምና ጉዳት አንፃር ብቻ ነው የሚቃኘው። ዝሙት፣ ማመንዘር ይህን ያክል ቀሏል።
ቁርኣናችን ደግሞ ከመፅሐፉ ሴቶች ጋር ጋብቻን የፈቀደው “ከዝሙት የተጠበቁ መሆናቸው” ከታወቁት ጋር ብቻ ነው። ይሄ መስፈርት ባልተሟላበት ከነሱ ጋር ትዳር መፈፀም አይፈቀድም። ይሄ አንድ ነው።

ሁለተኛ ልጆችህን በኢስላማዊ ስርአት የምታሳድግበት ሁኔታ መኖር አለበት። አንዲት ሙስሊም ያልሆነች ሴት ከዝሙት የተጠበቀችና ግብረ ገብ ብትሆን እንኳ በዚህ ዘመን ልጆችህን እርሷ በምትፈልገው እምነትና መንገድ ላይ ማሳደግ ብትሻ የሚያግዳት ገደብ የለም። በዚህ የተነሳ ልጆች እምነታቸው ሊቀየር ይችላል። ይሄ በተጨባጭ እየገጠመ ያለ ዘግናኝ ጥፋት ነው። ሙስሊም ካልሆኑ ሴቶች ጋር ትዳር ፈፅመው ከዚያ ልጆቻቸው የከፈሩ ስንቶች ናቸው? አንዳንዶቹ እንደዋዛ ልጆቹ 18 አመት ሲሞላቸው ሃይማኖታቸውን ይመርጣሉ ይላሉ። ይሄን ሁሉ አመት ኢስላምን አልተማረም፣ ሶላት የለም፣... ። በዚያ ላይ ለልጆች ከአባቶች ይልቅ እናቶች የበለጠ የቀረቡ ናቸው። ጊዜው አይነቱ የበዛ የሞራል ዝቅጠት የተንሰራፋበት ነው። በነዚህና መሰል ምክንያቶች የተነሳ ልጆቹ ኢስላምን የመያዛቸው እድል የመነመነ ይሆናል። እንዲህ አይነት ከባቢ ባለበት ደግሞ ሙስሊም ያልሆኑ ሴቶችን ማግባት አይፈቀድም።
.
ስለዚህ እነዚህ ሁለት መስፈርቶች ባልተሟሉበት ከመፅሐፉ ሴቶች ጋር ጋብቻ መፈፀም የሚፈቀድ አይደለም። ታላቁ የዘመናችን የሐዲሥ ሊቅ ሸይኽ ሙሐመድ ናሲሩዲን አልአባኒይ ረሒመሁላህ እነዚህን ሁለት ቅድመ ሁኔታዎች በመጥቀስ በዚህ ዘመን ከክርስቲያን ሴቶች ጋር ጋብቻ መፈፀም እንደማይቻል አጥብቀው ያሳስባሉ። [ሲልሲለቱል ሁዳ ወኑር ቁጥር 523]
እንዲያውም ኢስላም አላህን መፍራትና ግብረ ገብነት ያላቸውን ሴቶች እንዲያገቡ ነው ወንዶችን የሚያነሳሳው። ይህንን ህግ መጠበቅ ለራስም፣ ለቤተሰብም፣ ለሚወለዱ ልጆችም፣ ለሙስሊሙ ማህበረሰብም፣ ለኢስላምም ውለታ መዋል ነውና ተገቢውን ትኩረት ልንሰጠው ይገባል።
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor




📢 አስደሳች ዜና የነሕው ትምህርት ለከበዳቹ እና በቀላል መንገድ ለመያዝ ያስቸገራቹ በሙሉ
--------------------------------------------------------------

السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

النحو الواضح

አንዳንድ ሰዎች (ተማሪዎች) የነሕውና የሰርፍ  ት/ት እንዳስቸገራቸው እየተናገሩ ነው።

ሰለዚህ እነሱን ለማገዝ እንዲሆን (እንዲሁም ደግሞ ሌሎችንም ማጠናከሪያ እንዲሆን ) النحو الواضح ኪታብን በኡስታዝ አብዱሰመድ ይቀራል

ቂርአቱን የምንለቀው ደግሞ በቪድዮ ይሆናል :: ማለትም የኪታቡና የፅሁፍ ቪድዮ (ተማሪዎች እንዲገባቸው )::

ደርሱ በሳምንት አንድ ቀን ነው የሚሰጠው። በኪታቡ መሠረት የቤት ስራዎች ይኖሩታል ::

=> ደርሱን ለመከታተል የሚከተለውን የዪትዪብ ቻናል ይቀላቀሉ።

https://www.youtube.com/c/MedresetulImamuAhmed

=> ደርሱ (ትምህርቱ)

- በ Youtube

https://www.youtube.com/c/MedresetulImamuAhmed

ይለቀቃል።


إن شاء الله


١=ፈጣንና አገናዛቢ
٢=አለመሰልቸት/ጉጉት ሊኖረው
٣=ልፋት/ትጋት
٤=ለምንማረው ትምህርት የሚያስፈልጉ ቁሶች ሟሟላት
٥=ከኡስታዙ/ከመምህሩ ጋር ወዳጅ መሆን/መተናነስ
٦=የጊዜው ርዝመት/ መቼም በአንዴ አሊም መሆን አይቻልምና:በትዕግስት መማር


ምንም አይነት ትልቅ ኸይር ስራ ቢኖርህ: ጥሩ ብትሆን:
ጥሩ ነኝ: የተሻልኩኝ ነው አትበል።
ባይሆን አላህን አመስግን።
ባለህ ነገር አላህን ስታመሰግን: ካለህ ኸይር ስራ ሌላ ኸይር ስራ እየፈለክ ነው ማለት ነው።


"ይህ ሰው ጭራሽ በሰለፊዎች አፍ ስሙ ሚነሳ አይደለም። ስሙ ባትጠቅሱ ጥሩ ይመስለኛል።"
ክብር ለኒቃብ።


✅ውሃብይ ነሽ ተባለች??

➘ኒቃብ በመልበሷ!
➴ወንድን አልፈትንም ብላ በመሰተሯ
➴ሽቶ ተቀብቼ፣ ጉርድ ለብሼ፣ ሚሰቅል ጫማ ለብሼ እየተዘነበልኩ ሰውን አላዘነብልም በማለቷ
➴የተጣበቀ ልብስ በመልበስ፣ ፀጉሬን በመክፈት፣ ደረቴን በማሳየት፣ የዝሙትን በር አልከፍትም በማለቷ
➴ፀጉሬን አልቆልልም፣ የግድግዳ ቀለም ፊቴን አልቀባም፣ ወንድን አልጨብጥም፣ በማለቷ: ወሃብይ ከተባለች
አዎ ሁሌም እሷ ወሃብይ ናት።
ለዲኗ-በሷናዋ ምትኮራ።


ኢናሊላሂወኢናኢለይሂራጂዑን!!
መጨረሻችን የት ነው?
ይህ ትውልድ ወዴት እያመራ ነው?

ኳስ ዘመናዊ ጣዖት: ኳስ የዘመናችን ወጣት ልብ የተቆጣጠረ: ኳስ ወደ ዲን ቀርቤያለሁ የሚለው ሳይቀር የተፈተነበት በሽታ።
እግር ኳስ መመልከት ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ጥፋትና መዓት ብቻ። ነው። ምክንያቱም ይበሳጫል: ይወራጫል: ይናደዳል: ቡድንተኝነት ይዘዋል: ሌላም ሌላም።
ተጫዋቾቹ የራሳቸው የሆነ እብደት ያሳያሉ። ወይ በደስታ  ወይ በብስጭት። አስቡት አንዴ ቲሸርት ሲያወልቅ: አንዴ ሲወድቅ: አንዴ መሬት ሲመታ: አንዴ ተመልካች ሲሰድብ: መጮኽ: ጭፈራ: ያለ ቅጥ መደሰትና መማረር:መበሳጨት ያለበት የፈሳድ ሜዳ። ይህ ሁሉ ቆም ብሎ ላሰበውና ትንሽ የዲን እውቀት ለቀሰመ: ጥፋትነቱ አይሰወረውም።
ግን ለምን  ጭፍንተኛ ሆንን? ለምን ፈረንጅ በተራገጠበት እኛ ወገንተኝነት ያዘን?
ደጋፊዎችና ተመልካቾች ሳይቀሩ: ልብሳቸውን ይቀዳሉ። ቅጥ ያጣ ደስታ ውስጥ ይገባሉ። ቅጥ ያጣ ብስጭት ውስጥ ይገባሉ። ከቤተሰብ ይጣላሉ። እቤታቸው ምግብ አንበላም እስከማለት ይደረሳሉ። ይህ ሁሉ የኳስ በሽታ የያዛቸው ደዩሶች ስራ ነው። እኔ አንዳንድ ሰዎች ይገርሙኛል: ምንም ሳያፍሩ; ወደ ዲን ቀርበው; ሰለፊይ ነን እያሉ: ፂማቸው አሳድገው: ሱሪያቸው ቆርጠው: "እኔ የእገሌ ደጋፊ ነኝ" ይላል። አኡዙቢላህ። ኧረ ልክህን እወቅ?? በኳስ መለከፍ ማለት ሳይታወቅ በኩፍር መለከፍ ነው። ኳስ የዘመናችን ህዝብ በዘመናዊነት የሚያመልከው ጣዖት ነው"  አያፍሩም ደግሞ የተጫዋች ፎቶ ፕሮፋይል አድርገው ዘና ሲሉ። ኳስ ጊዜህ: አቅልህ: እድሜህ: እምሽክ አድርጎ ሚበላ የሰይጣን ጥሪ ነው። የሰው ልጅ አዕምሮ: ጭንቅላቱ ሁለት ተቃራኒ ነገር መያዝ አይችልም። ወይ ቁርአንና ሃዲስ ወይ ፊልም: ሙዚቃ ኳስ: ምርጫው በእጅህ ነው። ተውሒድ የተረዳ ፈፅሞ በእንዲህ አይነት ሰይጣናዊ ስራ አይገባም። እንዴ የተውሒድ ባለቤት አላህን የሚያስቆጣ ስራ ይሰራል?
90 ደቂቃ ነገ አላህ ሲጠይቅህ: ምን አረኩባት ልትለው ነው።
መዓት ተጫዋቾች ሃፍዘሃል!!
እስቲ ነብይህ ታውቃቸዋለህ?
የስንት ሶሐቦች ስም ታውቃለህ?
ታቢኢዎችስ: አኢማዎችስ?
ይህ የምልበት የራሴ ተሞክሮ ስላለኝ ነው። (ወላሂ) አራቱ ኸሊፋዎች ማናቸው ብትለው- ኧረ ተወው አራቱም ስማቸው ጠቅሰህ ማናቸው እነዚህ ሶሐቦች ብትለው ማያውቅ: ግን እያንዳንዱ አለም ላይ በሰፊው የሚታወቁ ክለቦች ከነ ተጫዋቾቻቸው ያውቃል። የት እንደተሸጠ: ስንት እንደተሸጠ: እንዴት እንደተሸጠ ብቻ ስለእያንዳንዱ ተጫዋች ያውቃል። ግን ሐዋሪያቶች የማያውቁ መዓት የቁም ሙቶች ሞልተዋል: በኳስ ተበልተዋል። ኳስ የሰው ነብስ ያጠፋል: ወንድም ለወንድም ያቀያይማል: እልህ ያሲዛል ብቻ የሙስሊሙ ባህሪ ጭራሽ የራቀ ነው። ሙስሊሞች ከዚህ የሸይጧን በሽታ መራቅ አለባቸው። አሁን ከወንዶች አልፎ ሴት እህቶቻችንም እዚህ ቆሻሻ ውስጥ ተንቦራጭቀዋል።  የዘንድሮው ደግሞ በጣም ሚያሳዝነው: ሚያስለቅሰው የወንጀላችን ጥግ: የአላህ ቤት መስጅድ ውስጥ ኳስ ሲታይ። 
TG https://t.me/iliyasNassir/4792

Facebook ላይ የሸይኽ አብዱራዛቅ አል በድር ሃፊዘሁላህ አጭር ምክርም አለበት። ገብታቹ ተመለከቱ። https://fb.watch/h_pddyi4hN/


ይህ ነገር ብዙዎች ቢያስደነግጥም ሃታ!! ኳስ አፍቃሪዎችም ቢደነግጡም: ግን ይህ ነገር የመጣው በኔ ምክንያት ነው ብለው አለመደንገጣቸው ነው። ዝሙት በአንድ ቀን አይፈፀምም: ቀናት: ወራት ሊያስቆጥር ይችላል። ኳስ ወደ ሙስሊሙ ወጣት ልብ ሲገባ ቀስ-በቀስ ነው። ዘንድሮ መስጅድ ውስጥ ሲታይ ብዙዎች ደነገጡ። ቀጣይ ከተደገመ: ይለመዳል።  መደገንጥ ብቻ መፍትሔ አይደለም: በቃ በኔ ሰበብ ነው ይህ ፈሳድ የመጣው ብለህ ኳሱን ተወው። "አንተም-ቤተሰብህም-የዲንህም ክብር አስጠብቅ- "ኳስ እኮ ሙስሊሞችም ያያሉ" ሲባል ወላሂ ያሳፍራል። ምንም ካልተሰማህ: አንተ የገዛ አዕምሮህ ለሰይጣን አስረክበሃል ማለት ነው። በነገራችን ላይ ኳስ መመልከት የልብ በሽታና የተያያዙ ሌላም እስከሞት የሚያስከትል በሽታ ያመጣል። "cardiovascular mortality and proarrhythmic effect" ይጨምራል ይላሉ።(ዶክተሮች)
በመጨረሻም ለሌላ ባታስብ ለነፍሲያህ እዘንላት።


ABU-AHILAM (ibnu Nassir) dan repost
‼️‼️ወንድሜ ሆይይይይ‼️ ለነገሩ ሴቶችም አሉበት ለካ⁉️
ሴቶችም የጀመሩ ስላሉ ነው። አላህ አቅል ይስጥሽ። ላንተም‼️ ላንቺም‼️

የዛሬ ዘጠና ደቂቃህ ያባከንካት ነገ አላህ ፊት ስትቆም መልስ አዘጋጅተሃልን⁉️ ወጣትነትህ በምን አሳለፍከው ተብለህ ሳትጠየቅ እግር ንቅንቅ የለም። (ታውቃለሃ??) ታዳ "ዲ'ኤስ'ቲቪ" እያየሁ: ወይስ አይ "ሲኒማ ነበርኩ" ወይስ ምን ላይ⁉️
አትዋሸውም/አታመልጠውም‼️ (ነገሩ ለአባትህ:ለመ/ርህ: ለጓደኛህ አይደለም እኮ ምትዘረዝረው። እወቅ (ያ- የውስጥ/የቅርቡ የሩቁንም አዋቂው ለአላህ ነው ምትነግረው። ታዳ መልስህ ምንድነው⁉️

ሲቀጥል ኳስ ማየት ኻራም ነው። የሴቶችም የወንዶችም: ለወንዶችም ለሴቶችም; ምክንያቱም:-
አውራቸው ይታያል: ጊዜያችን ያባክኑብናል: ምንም ነገር ስለማይጠቅመን, በሸሪያ በማይጠቅም በማይጎዳ ነገር ዘው ብሎ መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው። አይምሮዋችን ስለሚቆጣጠሩብን: ኳስ አፍቃሪዎች የሸሪዓ/የእስልምና ህግጋቶ ለመሃፈዝ በጣም ሲቸገሩ እናያለንና።

እኔ የማውቀው ሰው አለ።‼️
የእግር ኳስ ክለቦች ብዙዎችን የሚያውቅ: ብዙ ይዘረዝራል።
ተጫዋቾች ሁሉም የሚያውቅ: ግን የነብዩ "ሰለላሁአለይሂወሰለም" ስም ከነ-አያታቸው የማያው አውቃለሁ።

እና ከዚህ አሲድ (acid) ከሆነው ኳስ በላይ ወጣቶችን ያባከነ: ያከሰረ አለን⁉️
ምናልባት አንዳንድ እህቶች በፊልም ከዚህ የሚብሱም ቢኖሩም...!

እና አላህን እንፍራ ጊዜያችን በአግባቡ እንጠቀም። እንማር የተማርነውን እናስተምር።

(ከኡስታዜ ሳዳት:- አላህ ወፍቆህ 30 አመት ቢያቆይህ 5 አመት ቁጭ ብለህ ብትማር 25 አመት ሙስሊሞችን ትጠቅማለህ።)
ይቀጥላል:- (የምታወቀውን/የተማርከውን ሳትቀንስ ሳትጨምር አሰራጭ።) ይላል። ሃፊዘሁላህ

ሃቂቃ ይህ ንግግር ላስተነተነው በውስጡ ብዙ ትርጉሞች ይዟል። እና ጊዜ ሂወት ነው። አንዴ ከሄደ የሚይመለስ።

አላህ ለኔም ለናንተም ያግራልን።

✍الياس

ለተጨማሪ ፅሁፎች ይቀላቀሉ።
👇
Share Share & join channel
https://t.me/iliyasNassir
@iliyasNassir


"ታውቃላችሁ ግን? አብዘሃኛው ሚዲያ ላይ ሁለት ሚስት ካላገባህ...! እያለ ሚጮህ.... በአንድ ሚስት እንኳ መድፈር ያቃተው አካል ነው።
አቅም ኖሮት ከሆነ ግን በዚህ ድርጊቱ ሊያፍር ይገባል።"


ሀዘንህ ሲያጋጥምህ በነብዩ (صلى الله عليه وسلم) ሞት ሶብር።


የሰየፊያ ወንድም እና እህቶቼ አንድ ጠቃሚ ነው ብዩ የገመትኩት መረጃ ላካፍላቹ።

የአብዛኞቻችን ጥያቄ ይዤ መጥቻለሁ።

አብዘሃኞቻችን ኪታብ ስንጀምር ኬት መጀመር እንዳለብን አናውቅም።

እና ኢንሻአላህ በዚህ ዙሪያ ትንሽ ልበላችሁ።

(የተተረጎመ ነው)


🎤አንድ ተማሪ መጀመሪያ ምን ይማር ⁉️

1ኛው ዙር=   አቂዳው ይማር‼️

👂1ኛ=الواجبات المتحتمات المعرفة على كل مسلم ومسلمة
አል-ዋጂባት በሁሉም ሙስሊም ወንድና ሴት ላይ ማወቅ ግዴታ የሆነው።

👂2ኛ=ኡሱሉ ሰላሳ
👂3ኛ ቀዋኢዱል አርባእ
👂4ኛ ኪታቡ ተውሒድ "ሸይህ ሙሐመድ አብዱልዋሀብ"
👂5ኛ ከሽፈ-ሹብሃት
👂6ኛ ነዊቂዱል ኢስላም
👂7&8 ጠሃውያና ዋሲጢያ ብትቀሩ። የተሻለ ነው።
🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲


በ2ኛው ዙር = ከሃዲስ

👂1ኛ አርባኢን
👂2ኛ ኡመደቱል አህካም
👂3ኛ ቡሉኽ መራም
👂4ኛ ሪያዱ ሷሊሂን
👂5ኛ ሶሒሕ ቡኻሪ እያልን እንሄዳለን......
🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲



በ3ኛው ዙር =ከፊቂሂ👇

👂1ኛ (ከሻፊዒ) ሰፊነቱ ሰላህ ወሰፊነቱ ነጃህ
👂2ኛ አቢ ሹጃዕ ይቀጥላል....
🎤ከሃናቢሎቹ ደግሞ:- ከፊቂህ ማለት ነው:-
👂3ኛ ኡመደቱል ፊቂህ ኢብኑ ቁዳማህ አል-መቅደሲ:
👂4ኛ ዛዱል ሙስተቃዕ
🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲



በ4ኛው ዙር = ከኡሱሉ ፊቂህ👇

👂1ኛ አል-ወረቃት
👂2ኛ ኡሉሙል ቁርኣን
👂3ኛ አል ኢትቃን ኡሉሙ ቁርኣን
🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲


በ5ኛው ዙር=  ከተፍሲር

ብዙ ስለሆኑ
👂1ኛውና ዋነኛው ብቻ :- ኢብኑ ከሲይር
🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲



በ6ኛው ዙር = ከኡሉሙል ሃዲስ:- 👇

👂1ኛ ቢቁኒያ
👂2ኛ ኡቅበቱል ፊክር
👂3ኛ ሙቀዲመቱል ኢብኑ ሰላህ ፊ አሉሙል ሀዲስ
🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲


በ7ኛው ዙር = ከእውቀት አባት (ከነህው)👇

👂1ኛ አጅሩሚያህ
👂2ኛ ቱህፈቱል ሰኒያ
👂3ኛ ሙተሚት አጅሩሚያህ
👂4ኛ ቀጥሩ ነጃ
👂5ኛ አልፊያ


በ8ኛው ዙር = ከእውነት እናት (ሶርፍ)👇

👂1ኛ ቢናዕ
👂2ኛ መቅሱድ
👂3ኛ ሸጀር አልፍ እና አል-መራህ
ወላሁ አእለም።

Share Share &  join channel
https://t.me/iliyasNassir


ኢማሙል አውዛኢ እንዲህ ይላል

"ሙእሚን የሆነ ሰው ትንሽን ይናገራል ብዙ ይሰራል ሙናፊቅ ግን ብዙ ይናገራል ትንሽ ይሰራል"

     📚[7/125]


ለተራው/ለሰፊው ማህበረሰብ መንሃጅ ያልተረዱ ሰዎች ደዕዋ ስናደርስ የተጣራና ጥበብ የተሞላበት ጥሪ ማድረግ አለብን
ይህ ሰፊ ህዝብ በተራ ርዕሰ እንዲጠመድ ማድረግ በጣም የከፋ ስህተት ነው።
(ለአዲስ ተማሪዎችም "ለጧሊበል ኢልሞችም")


(የኒያ ቦታው ቀልብ ሲሆን- የዚክር ቦታ ምላስ ነው።)


ዝምታ!!

تعلمنا ان هيبة الصمت أجمل من ألف حديث .

የዝምታ ክብር ​​ከሺህ ቃላት የበለጠ እንደሚያምር ተምረናል።
ይላሉ.....

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

767

obunachilar
Kanal statistikasi