የሱና ኡስታዞች መጽሐፍ የምተላለፍበት


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


በአላህ ፍቃድ በተለያዩ የሱና ኡስታዞች የተጻፉ መጽሐፍት የምተላለፍበት ይሆናል፡፡

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


ኑ ኪታቦችን አብረን እንቅራ dan repost
ሁሉም ሰው ተጠቃሚ ይሆን ዘንድ ለወዳጅ ዘመዶ share ያድርጉ

ኑ ኪታቦችን አብረን እንቅራ
"العلم قبل القول والعمل" البخاري رحم الله

ኢንሻአላህ በአላህ እገዛ አብረን ኪታቦችን እንቀራለን።
https://t.me/kitabe22


ኑ ኪታቦችን አብረን እንቅራ dan repost
#ኑ_ኪታቦችን_አብረን_እን-#ንቅራ


#ተቀርቶ_ያለቀ_ደርስ


🔊 በኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ [ሓፊዘሁሏህ]
የተቀራ ደርስ

نواقض الإسلا

📝 የኪታቡን pdf ለማውረድ 📝 👇 👇 👇 👇 👇

📚 https://bit.ly/34cWjy6 📚


🎵 ክፍል አንድ የድምጽ file ለማውረድ 🎵
👇 👇 👇 👇 👇

🎶 https://bit.ly/2HHih4C 🎶


🎵 ክፍል ሁለት የድምጽ file ለማውረድ 🎵
👇 👇 👇 👇 👇

🎶 https://bit.ly/36D8aZl 🎶


🎵 ክፍል ሶስት የድምጽ file ለማውረድ 🎵
👇 👇 👇 👇 👇

🎶 https://bit.ly/2G9ezAD 🎶


🎵 ክፍል አራት የድምጽ file ለማውረድ 🎵
👇 👇 👇 👇 👇

🎶https://bit.ly/2GjiPxd 🎶


🎵ክፍል አምስት የድምጽ file ለማውረድ 🎵
👇 👇 👇 👇 👇

🎶 https://bit.ly/2Gjj0sn 🎶


"العلم قبل القول والعمل" البخاري رحم الله

✅ያ ረብ ጠቃሚ እውቀትን ስጠን [አሚን]✅

🔛 https://t.me/kitabe22

🛑 share ማድረጎን አይርሱ 🛑


የአማኞች ጋሻ
በአላህ ስሞችና ባህሪያት ዙሪያ የሚነሱ ውዝግቦች የሚፈቱባቸው መርሆዎችን ያዘለ ጥናት

✅ የተሳሳቱት የሚታረሙበት

✅ የተጠራጠሩት የሚረጉበት

✅ ያረጋገጡት የሚፀኑበት

በሸኽ ኢልያስ አህመድ [ሀፊዘሁላህ] የተዘጋጀ መጽሐፍ።
https://t.me/ilypia


" ዓብዱረህማን ዑመር" dan repost
👉ልብ ብለህ ስማ ፦

👉ከሰማህም በኋላ ራስህን ፈትሽ፦


***********************************
አሁንም ቢሆን ሰዎችን ሳይሆን ትክክለኛ መንሀጅን እንዎቅ!
***********************************

መከፋፈል በበዛ ጊዜ እና ተሸንሸራታች ቡድኖች በበዙበት ሰዓት
|
ማንኛው ይሆን እውነተኛው ብለህ የምትዋልል ወይም እገሌ ተንሸራቷል ብሎ የሚነግርህን ወንድም ደግሞ ዛሬም ክፍፍል አመጣህብን የምትል ከሆንክ ወይም ሁል ጊዜ ስለ ክፍፍል ማውራት አይሰለቻችሁም እንደ እያልክ የምትሰላች ከሆንክ
|
- አንተ ሀቅን ሳይሆን ሰዎችን ነበር ስትከተል የበርከው
|
ምክንያቱም መንሀጅህ ከተስተካከለ የተስሳሳተውን ቡድን ማነም ሳይነግርህ ራስ ታውቀው ነበርና
|
ሰንትና ስንት ወንድሞች አውቃለሁ የሙመይዖችን ተንኮል እንድህ በሸይኾቻችንና በኡስታዞቻችን አንደበት ግልፅ ከመደረጉ በፊት ➮➮ እገሌ የሚባለው ኡስታዝ ተብየ እውነት መንሀጁ ከእናተ ጋር ተመሳሳይ ነውን? ብሎ ለኡስታዞቹ ለሸይኾቹ የሚጠይቅ ተማሪ አውቃለሁ
|
ለማንኛውም ያለፈውስ አለፈ ለቀጣዩ የሚከሰተውን ወይም አሁን ካለው አቋሙ የሚንሸራተተው አካል ማን እንደሆ አናውቅምና አሁንም ቢሆን ሰዎችን ሳይሆን ትክክለኛ መንሀጅን እንዎቅ !
ሰዎችን/ሸይኾችህን ሀቅ በመናገራቸው ወይም በማስተማራቸው ብቻ ውደዳቸው ከአቋማቸው ሲወርዱ አንተም እርግፍ አድርገህ ተዋቸው



🇸🇦"አብዱሮህማን ኡመር"🇸🇦
"ሱናን" የተላበሱ እስላማውይ ግጥሞችና ፁሁፎች
የሚለቀቁበት የቴሌግራም ቻናል
ተቀላቀሉ> ^


በኡስታዝ ሑሴን ዒሳ【حفظه الله تعالى】የቁርኣን ተፍሲር እና የኪታብ ደርሶች የሚተላለፍበት ቻናል💿🎙! dan repost
🌙*صيـــــام أيـــــام البيـض* 🌙
*‏لشهر شعبان ١٤٤١*
الأثنين ١٣*
٢٠١٣/٤/٦*
الثلاثاء ١٤*
*‏٢٠٢٠/٤/٧*
الأربعاء ١٥*
‏*٢٠٢٠/٤/٨ *
‏ان لم تغتنم صيامها فلايفوتك أجرها بتذكير غيرك*


Sadat_Text_Posts dan repost


" ዓብዱረህማን ዑመር" dan repost
በታታኙ ኢኽዋን በሰሜን ወሎ በመርሳ
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

በሰሜን ወሎ ዞን በሀብሩ ወረዳ መርሳ ከተማ ሱንይ ወንድሞቻችን ኢስላምን ለመርዳት እና ተውሂድና ሱናን ለማጠናከር እየሱሩ ይገኛሉ ሀቅን የሚያስተምር ኡስታዝ ለዘላቂት ባያገኙም ይሄን ለማሳካት በልፋት ላይ ናቸው
አንዳንድ ጊዜ ሸይኽ አደም አዙበይር የተባሉ ሸይኽ ከሱዳን እየመጡ ያስተምራሉ ሰሞኑንም መጥተዋል
ሸይኸ አደም አዙበይር የሱዳን ሰው ሲሆኑ ግብፅ ላይ ያለው ታላቅ ዓሊም የሸይ ሙሀመድ ሰዒድ ረሰላን ተማሪ ናቸው
ታድያ ሸይኽ አደም የሱዳን ተዎላጅ ቢሆኑም ሰለፍዮች ዘንድ ዘረኝነት ቦታ ስለማይሰጠው የሀገራችንን የመርሳ ልጅ አግብተው ግብፅ ሀገር ይኖራሉ

የባለቤታቸውን ቤተሰብ ለመዘየር ወደ መርሳ በመጡበት ሰዓት ወደ ሀገራቸው እስኪመለሱ ድረስ አንዳንድ ሙሀዶራዎችንና ትንሽ የቂርዓት ደርስ በመስጠት ትክክለኛውን የነብያት ጥሪ በማካፈል ላይ ይገኛሉ
ታድያ በዚህ ሰራቸው ሀቅ ፈላጊ ሰለፍይ ወጣቶችን በማንቃትና ከተለያዩ ኮተቶች ከሸርከያትና ከቢድዓ እንዳይገቡ በትልቅ ትግል ባሉበት ሰዓት እና እንድሁም የሙስሊሙን አንድነት በሀቅ ላይ እያጠናከሩ እያበዙ ባሉበት ሰዓት ላይ

አንድነት የማይፈልጉ ግን በውሸት አንድነት ሰዎችን እናጭበረብራል ብለው የተነሱ የኢኽዋን ፊክራ ያለባቸው አካላቶች ይሄን እንቅስቃሴ ሲያዩ አይናቸው ደም እለበሰባቸው ና ያዙኝ ልቀቁኝ እያሉ ይገኛሉ
የመርሳ ኢኽዋኖች ይሄም ብቻ ሳይሆን ከአሁን በፊት በሀቅ ፈላጊና ሙስሊሙን ለማገልገል በሚንቀሳቀሱ ወጣቶች ላይ ብዙ ጫናዎችን በማድረስ ይታዎቃሉ
ለምሳሌ፦
1/ በቋሚነት ሲያስተምር የነበረ ጀማል ዘሀቤ ሚባለውን ኡስታዝ በማስፈራራት ፣ ስም በመለጠፍ ፣ ሙስሊሞችን በታታኝ በማለት ፣ የተለያዩ ሙከራዎችን በማድረስ አባረዋል
2/ከሌላ ቦታ መጥተው ትምህርት የሚቀስሙ ደረሶች ላይ/የመርሳ ተወላጅ ያልሆኑ ሰዎች ላይ እናንተ መጤዎች መንገደኛ የተለያዩ ስድቦችና ጫናዎች እያሳደሩ ይገኛሉ
3/በድን የማይታወቅ አድስ ቢድዓ መጥፎ ስራዎችን እሚቃዎሙ እና ወጣቱን በበጎ ስራ ላይ የሚያነሳሱ ወንድሞቻችንን በሽጉጥ ሳይቀር እያስፈራሩ ይገኛሉ

ለመሆኑ የመርሳ ኢከኽዋኖች እነማን ናቸው?
ብዙዎቹ አህባሽ ጋ ሲተሻሹ የነበሩና አህባሽም የነበሩ እንድሁም አባገትዮ ከሚባለው የሸርክ መናሀሪያ ተሳትፎ የነበራቸው ሲሆነ ከፊሎቹ ደግሞ ከአህባሽ ጋር ሰልጣንና ገንዘብ የመስጅድ ንብረት ሀላፊ መሆን ያጣላቸው ነበሩ
አሏህ ብሎት መርዘኛው አህባሽ ቀኑ ሲደርስ በሰለፍይ ወጣቶች ሰበብ ድምጥማጡ ሲጠፋ ኢኽዋኖች ተሸቀዳድመው መሪነትን ፣ ኮሚቴነትን ፣ በሁሉም ነገር አለን አለን ማለትን በፍጥነት ያዙ
ከዛም በመቀጠል የዛሬ አመት አካባቢ ከአህባሽ ጋ እንቀራረብ ብለው በሬ አርደው ወረላሎ ከሚባለው ሰፋር መስጅድ ውስጥ ጫት እየበሉ በውሸት ለቅሶ ከእንግድህ ታረቅን በውሸት አንድነት አንድ ሆን ብለው ኢኽዋን በመሪነት አህባሽ በተከታይነት ጨዋታውን ቀጠሉ
አደገኛው አህባሽ የኢኽዋንን ማንነት ሰለሚያውቁ በእምነታቸውም መተማመን እንደሌላቸው ጠንቅቀው ስለሚያቁ ዝናብ ቀርቷል ምክንያቱም የኛ ዱዓ ከ(❌ሙጄ❌) ከሚባለው ቀብር ላይ ማድማት ማረድ ሰለተውን ነው ብለው ሲጠይቁ በሀቅ በተውሂድ ያልተሰበሰበ የኢኽዋን ጥርቅም መስጅዱን ለአህባሽ ፈቅደው ሸርክ ሲያሰሩበት ቆዩ ✖️ሲጥል የነበረው ዝናብም አቆመ አህባሽም መስጅዱን በመቆለፍ ከዛ ቀን ጀምረው የራሳቸው አደረጉ
በጣም እሚገርመው ሰሞኑን አሰፓልቱ ዳር ያለውንም ትልቁን መሰጅድ ፈቅደው በጫት እና በቢድዓ ሲያንቋሽሹ ቆይተዋል

የመርሳም ኢኽዋኖችም ሆኑ በጠቅላላ ሀገሮች የሚገኙ ኢኽዋኖች ተግባራቸው ለሸርክ ሰዎች ጫት መቃሚያ መስጅድ ይፈቅዳሉ ትክክለኛውን የነብያቶች ሁሉ ጥሪ የሆነውን ተውሂድ የሚያስተምሩ ወንድሞችን ደግሞ ለአንድነት ሲባል መስጅድ ውስጥ አታስተምሩም እያሉ በየ መስጅዱ በር ማስታዎቂያ ይለጥፋሉ
ይገርማል {{{ለአንድነት ሲባል ተውሂድ አታስተምሩ ይባላል}}} ሰሞኑን መርሳ ላይ የለጠፉትን ማስታዎቂያ ከሰር መመልከት ይቻላል
ስለዚህ ኢኽዋኖችን አንድ እሚያደረጋቸው ነገር ሸርክ ፣ቢድዓ ፣ጫት፣ ሲሆን የሚለያያቸው ተውሂድና ሱና ነው እኛ ደግሞ አንድነት የሚመጣው ተውሂድን በማስተማር ከአህባሽ ከሱፍይ ከኢኽዋን በየ ቀኑ ቢያን አንድ ሰው እንኳ ወደ ሀቅ ቢመጣ እና ሀቅ ላይ በመሰብሰብ አንድ በመሆን ነው ብለናል
ታድያ ይሄን ስናደርግ ኮሚቴነት ና የመስጅድ ጥቅማጥቅም ሊለያቸው ያልፈለጉ ሰዎች ህብረተሰቡ ሀቅን ሙሉ በሙሉ ካወቀማ እኛ ተመልካች አናጣለን በሚል ስጋት የማይሞክሩት ሙከራ የለም
ይሄው ነው በሀገራችንም ደረጃ ሰዎች መጥፎ እያዩ ዝም ሚሉት ሀቅ ከመናገር የከለከላቸው ሀቅን ከተናገሩ ቤት መኪና የሚገዛላቸውን ሰው ማጣት ስላልፈለጉ ነው
ፁሁፌን ከመጨረሴ በፊት የመርሳ ሀቅ ፋላጊ ሰለፍይ ወጣቶች መልዕክታቸውን አስተላልፉልን ብለዋል
እሱም፦ 1/ከመርሳ ኢኽዋኖችም ሁኑ በሀገራችንም ደረጃ ያሏችሁን መሻይኽ የምትሏቸውን ሰዎች አምጡ በቁርዓን በሀድስ እንወያይ
2/ሌላ ደግሞ መወያየት ሲከብዳችሁ ስማችንን መጥፎ በመርጨት ህዝቡን በውሸት እምትመረዙ ሰዎች ረፉልን ብለዋል።

መጋቢት 16/7/2012 ዓል

"♦አብዱሮህማን ኡመር♦"
የተለያዩ "ሱናን" የተላበሱ እስላማውይ ግጥሞችና ስድ ፁሁፎች
የሚለቀቅበት የቴሌግራም ቻናል
ተቀላቀሉ> ^


" ዓብዱረህማን ዑመር" dan repost
, ታላቁ ኮሮና
, !!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

አዑዙ ቢላሂ ምኑ ወረረን?
አሸናፊው አሏህ አንተው ጠብቀን
ከዚህ ከኮረና ሚስኪን ሙስሊምችን
ብርቅየ ባሪያዎች አንተን ያልካዱትን
ወዳንተ ሸሽተናል በእዝነትህ ጠብቀን

ልንፈራ አይገባም በኮሮና መምጣት
ከአሏህ ውሳኔ ውጭ ላይከሰት ቅንጣት
ያለ ቀን ገደቧ አትጠፋም ሂዎት
በጌዜ ተወስኗል የሁላችንም ሞት

አብሽሩ ሙስሊሞች አርቁ ጭንቀትን
ጠንቀቅን እንወቅ ምንሰራው
ካለንበት ሰፈር ብንሰማ መግባቱን
መቆየት ይገባል በቦታው ታግሰን
ሰፈር ለቆ መሄድ ኢስላም መች አዘዘን
እዛው መሶበር ነው በአሏህ ተመክተን

ምላልባት በሽታው እኛን ካገኘን
አሏህ ሰበብ አርጎ በዚህ ቢገድለን
መሞት ይጠበቃል በአቋማችን ፀንተን
በጌታችን ውሳኔ ወደን ተደስተን

እደዚህ ከሆነ የኛ ፍፃሜያችን
ሰማዕታቶች ጋራ ይፃፋል ስማችን
ያማረ ይሆናል ያኛው ሀገራችን
ከሞትን በኋላ አሏህ የቀጠረን
ጀነት ውስጥ ይሆናል ዘላለም ኑሯችን

ግን ግን ይሄን ስልህ በደንብ አሰምርበት
ከሰራሀው ስራ ሸርክ ከገባበት
ከአሏህ ሙጭ ሌላ አምልኮ ካለበት
ነብዮች ወልዮች ድረሱ ያልክበት
ለቀብር ለቆሌ ለጅን ያረድከበት
እንደ ክርስቲያኖች ሰው ያመለክበት

ታላቁ ኮሮና ይሄ ነው ንቃበት
ዘውታሪ ሚያደርግ በገሀነም እሳት
ይች ቫይረስማ ጥቂት ወረርሽኝ ናት
ቢጠና ቢበዛ ታሰከትላለች ሞት
ምልክት ትሆን ዘንድ በአሏህ ለካዱት

ህዝቡ ይረበሻል ይህ ወረርሽኝ መጥቶ
ምክንያቱ ግልፅ ነው ፈጣሪ ተረስቶ
ያለ ቁጥር ስፍር ወንጀል ተበራክቶ
በቆላ በደጋ ክህደቱ በዝቶ
በውጭ ባገር ቤት ሸርክ ተሰራጭቶ
የሰው ልጆች አንገት በዋዛ ተቀጭቶ
ዝሙት በየ ሰፍራው ለጉድ ተንሰራፍቶ
ምድር አስከ ሰማይ በፈሳድ ተሞልቶ
የኮሮና መምጣት ምን ይገርማል ከቶ?

አሏህ ያመጣውን ማስወገድ ቢሳካ
ለምን ተሳናቸው ቻይና አሜሪካ?
ኢቦላ ሲረብሽ ኮሮናው ሲተካ?
ያ ስልጣኔያቸው ያ እርጉም ፖለቲካ
ምነው ድምፁ ጠፋ ቀረ ሳያረካ
ጌታችን እንድህ ነው በመጥፎ ሲነካ
በሰሩት ተግባር ላይ እኩኩል ሊተካ
መከራ ያወርዳል ኢስላምን ለነካ

የቻይና ጭቆና የባለፈው ሴራ
ክቡር ሙስሊሞችን ለማጥፋት ተዳፍራ
በሙሉ ልብ ዘምታ ምንም ሳትፈራ
እሷ ተተክታ በአሜሪካ ተራ
ቻይና የ ይገባል ቅመሽ መከራ
በኮሮና ሰበብ ያሻሻል ሙከራ
ኢቦላ በአሜሪካ አድርጓል ወረራ
በተንኮሏ ሰበብ ቀምሳለች መራራ

ወይዘሮ ኢትዮጲያ በቅርብ የሰራችው
ክርስቲያን ህዝቦች ጋር በአንድነት ተባብረው
መስጅድ ሲያቃጥሉ ጨክነው ተዳፍረው
ረግጠው ሲሄዱ ሙስሊሙን ጨቁነው
ሲደፉ ሲቀሙ ማን አለብን ብለው
አሸናፊው አሏህ ውሳኔው ቅርብ ነው
የኮረና መምጣት ከቃጠሎው ጋር ነው
ታላቁ ኮሮና የአሏህ ቁጣ ነው

"♦አብዱሮህማን ኡመር♦"
የተለያዩ "ሱናን" የተላበሱ እስላማውይ ግጥሞችና ስድ ፁሁፎች
የሚለቀቅበት የቴሌግራም ቻናል
ተቀላቀሉ> ^


Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
*ለአሏህ ብላችሁ የሚነይት ብቻ ይግባ*

*አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ*
*ውድ እና የተከበራቹህ ወንድም እህቶች እነሆ እንደሚታወቀው ኢብኑ አባስ መድረሳ ለማስገንባት ከዚህ በፊት ብዙ ጥረቶችን አድርገናል። ነገር ግን ለመድረሳው የሚሆን በቂ ገንዘብ ባለማግኘታችን ምክንያት በድጋሚ ወደናንተ ዞረናል።

*ስለሆነም ይህንን ታላቅ ፕሮጀክት ከጫፍ ለማድረስ እንረባረብ። ስለሆነም የተቀረውን 400,000 ብሩን ለመብሰብ*

👉 ① *በግል አንድ ኩፖን ለመግዛት አቅም ያለው እና የነየተ ወንድም እህት በ 4,000 ብር*

እንዲሁም

👉② *በግሉ አንድ ኩፓን መግዛት ለማይችል በጋራ በመሆን ማለትም 2 ወይም 3 በመሆን አንድ ኩፓን ባለ 4000 ብሩን በመውሰድ*

*የተቀረውን ገንዘብ ቶሎ ለማሰባሰብ ከሚረዱን ነገሮች ውስጡ አንዱ ስለሆነ በአላህ ስም እጃቹህ በመዘርጋት የ ጀነት ቤታቹሁን ለመስራት ከአሁን ስንቃቹሁን እንድታዘጋጁ እንጠይቃለን ።*

*አላህ ለሁላችም ስራችንን የሚቀበል ያድርገን* ‼️‼️
⚡️👇👇👇⚡️


*ለ መድረሳው እንቅስቃሴ እነይታለው የአቅሜን አስተዋፅኦ አደርጋለው ለ አላህ ብዬ የሚል ብቻ በዚህ ግሩፕ ውስጥ ይቀላቀል*

https://chat.whatsapp.com/Ebg5jkgHoFSLaymo5Rn8zh


*بلغنا الله وإياكم صيام هذا الشهر المبارك وقيامه*

*الْلَّھُم أَهِلَهُ عَليْنَا بِالْأمْنِ وَالإِيْمَانِ وَالْسَّلامَةِ وَالْإِسْلَامِ وَالْعَوْنٓ عَلَى الْصَّلاةِ وَالصِّيَامِ وَتِلَاوَةِ الْقُرْآَنِ الْلَّھُمّ سَلِّمْنَا لِرَمَضَانَ وَسَلِّمْهُ لنا وَتَسَلَّمْهُ مِنّا مُتَقَبَّلاً يٓارٓبٓ العٓالِٓمينْ ..*

*مُبارٓكٌ علٓيْكُمْ شّٓهرُ رٓمٓضٓان*


Ahmed Siraj dan repost
አልሐምዱሊላህ
ጨረቃ ታየች።
ረመዳን ነገ መሆኑም ተረጋገጠ።


«👑ሴቶች በኢስላም النساء في الاسلام👑» dan repost
ምክር ለ (ሴቶች) - ከታላቁ አሊም ኢብኑ ባዝ!!

ታዲያ እህቴ ስለ ትዳር በቂ እውቀት ቅሰሚ! ካለ እውቀት ዘው ብለሽ ገብተሽ መውጫው እንዳይጠብሽ!፣በአሁኑ ሰዐት እየተስተዋለ ያለውም ይኃው ነው የተወሰኑ ቀናቶች ካስቆጠረች በኃላ ለፈትዋ ኡስታዞች ጋር መራወጥ ይታያል!

ትዳር መስእዋትነትን ይጠይቃል በአንደበት እንደ ሚነገረው ቀላል አይደለም!!
ይህን መስእዋትነት በትእግስት በተቅዋ እንድታልፊ የሚረዳሽ ዋናው ችካል ዒልም ብቻ ነው።
የህይወት አጋርሽ በድሎቱም ከጎኑ ሆነሽ አላህን አመስጋኝ ባሪያ እንዲሆን ፀጋውንም በመልካም አላህ በሚወደው ተግባር ላይ እዲያውለው ልታበረታችውና በችግሩም ከጎኑ ሆነች አብሽር ሁሉም ለኸይር ነው እያልሽ ብርታቱ ትሆኝለት ዘንዳ በዒልም ላይ መበርታት ይኖርብሻል! እሱም በእንክብካቤና በስስት እያየ በክብር ያኖርሻል!
………!!የሴት ልጅ ክብር አንዴ ነው!!

ክብርሽን፣ማንነትሽን በእውቀት ላይ ሆነሽ ለማን አሳልፈሽ እንደ ምትሸጪ እወቂ!
ጅህልና ገዳይ በሽታ ብዙ እህቶች ላይ እየተጫወተ ነው። እናም እህቴ በዒልም ላይ በርታ በይ ደስተኛ ህይወት አላህ እንዲገጥምሽ ከፈለግሽ!

t.me/Setoch_Be_Islam


الدين هو النصيحة dan repost
🌸ከቁርኣን ጥበቦች...

السلام عليكم ورحمةلله وبركاته
➰ዱዓ ስታደርግ ያ ረቢ "يا رب" አትበሉ ረቢ"رب" በሉ
ለመሆኑ ለምንድነው አሏሁ ሱብሃነሁ ወተዓላ በቁርኣን ውስጥ የዱዓ አንቀፆችን ሲጠቅስ" يا" "ያ " የምትለዋን ሃርፈ ኒዳዕን የሚደብቃት? ምስጥሩና ጥበቡ ምንድነው?
እነዚህን አንቀፆች ልብ በሏቸው፦
َ رَبِّ أَرِنِىٓ أَنظُرْ إِلَيْكَ
«ጌታዬ ሆይ! (ነፍስህን) አሳየኝ ወደ አንተ እመለከታለሁና»
•"ረቢ" ነው ያለው ያ ረቢ አላለም
رَبَّنَآ أَفْرِغْ عَلَيْنَا صَبْرًۭا
«ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ትዕግስትን አፍስስ፡፡ »
•"ረቢ" ነው ያለው ያ ረቢ አላለም
ُۥ رَبِّ لَا تَذَرْنِى فَرْدًۭا وَأَنتَ خَيْرُ ٱلْوَٰرِثِينَ
«ጌታዬ ሆይ! ብቻዬን አትተወኝ፡፡ አንተም ከወራሾች ሁሉ በላጭ ነህ »
•"ረቢ" ነው ያለው ያ ረቢ አላለም
َ رَبِّ إِنَّ ٱبْنِى مِنْ أَهْلِى
«ጌታዬ ሆይ! ልጄ ከቤተሰቤ ነው፡፡»
•"ረቢ" ነው ያለው ያ ረቢ አላለም
رَبِّ ٱجْعَلْنِى مُقِيمَ ٱلصَّلَوٰةِ وَمِن ذُرِّيَّتِى ۚ رَبَّنَا وَتَقَبَّلْ دُعَآءِ
«ጌታዬ ሆይ! ሰላትን አዘውትሬ የምሰግድ አድርገኝ፡፡ ከዘሮቼም (አድርግ)፡፡ ጌታችን ሆይ! ጸሎቴንም ተቀበለኝ፤
•"ረቢ" ነው ያለው ያ ረቢ አላለም
رَبِّ هَبْ لِى مِن لَّدُنكَ ذُرِّيَّةًۭ طَيِّبَةً ۖ إِنَّكَ سَمِيعُ ٱلدُّعَآءِ
«ጌታዬ ሆይ! ከአንተ ዘንድ መልካም ዘርን ለኔ ስጠኝ አንተ ጸሎትን ሰሚነህና» አለ፡፡
•"ረቢ" ነው ያለው ያ ረቢ አላለም

( ربِ اغفر وارحم وانت خير الراحمين )
•"ረቢ" ነው ያለው ያ ረቢ አላለም
( ربِ ابن لي عندك بيتا في الجنة )
•"ረቢ" ነው ያለው ያ ረቢ አላለም
(ربِ إني لما انزلت الي من خير فقير)
•"ረቢ" ነው ያለው ያ ረቢ አላለም
( ربنا لاتزغ قلوبنا بعد إذ هديتنا )
•"ረቢ" ነው ያለው ያ ረቢ አላለም
( ربِ إني مسني الضر وأنت أرحم الراحمين )
•"ረቢ" ነው ያለው ያ ረቢ አላለም
( ربِ هب لي من لدنك ذرية طيبه انك سميع الدعاء )
•"ረቢ" ነው ያለው ያ ረቢ አላለም

👌በተከበረው ቁርዓን በዱዓ ቦታዎች አንድም ቦታ አላህን በሃርፈ ኒዳእ አልጠራም ። ማለትም አንድም ቦታ ረቢ ከሚለው በፊት ያ ን አላስገባም። ባይሆን ሙሉ ቁርዓኑን ብታዩት አንድም ቦታ አልገባችም። ለምን?

ይህ ነው ምስጥሩ፦
🎁የአረብኛ ቋንቋ ምጡቆች በዚህ ዙሪያ ምስጥሩን ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ፦ "يا" (ያ) የምትለዋ ፊደል የምትገባው እሩቅ ያለን አካል ስንጠራ ነው። አሏህ ደሞ ለባርያው ከደም ስሩ በላይ ቅርቡ ነው። ለዚህም ለመነጠቀ ዕውቀት ሲል "ያ" ን አስወገዳት። 🎁
ይህንንም አለን፦
وَنَحْنُ أَقْرَبُ إِلَيْهِ مِنْ حَبْلِ ٱلْوَرِيدِ
... እኛም ከደም ጋኑ ጅማት ይበልጥ ወደርሱ ቅርብ ነን፡፡

وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِى عَنِّى فَإِنِّى قَرِيبٌ
ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡

❓ታድያ አሁን የምትጠራው ጌታህ ምን ያህል ቅርብ እንደሆነ አላወክም?ታድያ፦

وَٱسْجُدْ وَٱقْتَرِب ۩
ስገድም፤ (ወደ አላህ) ተቃረብም፡፡

➰ወደ ጌታህ ቅርብ ለመሆን መጓዝ አያስፈልግም። በጣራም መውጣትን አይጠይቅም።
✂️የድምፅህንም መጮህ አይፈልግም!! መስፈርትም አልተደረገም
ብቻ [ اسجد ] ስገድ... ከፊት ለፊቱ ትሆናለህ!! ከዛም የፈለከውን ጠይቀው!!

✍ጅብሪል ሱልጣን (አቡ ፈቲ)

ማንኛውም አስተያያት ካላችሁ፦
@SeluAlelHabib
አድርሱኝ
ሼር ማድረጉ አትርሱት
ቅድሚያ ለሚሰጠው ቅድሚያ እንስጥ።
🌻 • • • ● ❀ 🎀 ❀ ● • • • 🌻
┏━━━━━━━━
🌷 @Abufetiya1
┗━━━━━━━━
https://telegram.me/Abufetiya1


አድኑ ነሲሐ ለሙስሊሟ ዕንስት!!! dan repost
اسلام عليكم وراحمت اللہ وبركاته


ዉድ የሱና እህቶቼ
በአሏህ ፍቃድ ይህ ቻናል ከቁርኣንና ከሀድስ የምናገኘውን ደርስ ወደናንተዉ የምናስተላልፍበት ይሆናል ።ሌሎችም ይጠቀሙበት ዘንድ ሊኩን ሸር እናድርግ

አላህ ኸይርን የሻለት ሰው ድኑን ያስገነዝበዋል።ነብዩ ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም!!! ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
[ "الدين النصيحة"، قلنا ፡ لمن يا رسول الله؟ قال፡" لله ولكتابه ولرسوله ولأئمة المسلمين وعامتهم "].ሙስሊም ፥ 55

https://t.me/joinchat/AAAAAEox3cEIR9907RjUMw


الدين هو النصيحة dan repost
Share ...

Join ይበሉ ጠቃሚ ከሌላ ቦታ ሼር ያልተደረጉ አዳዲስ ሃሳቦች ስለዲንዎ ጠቅላላ እውቀት ይቀስማሉ

ቅድሚያ ለሚሰጠው ቅድሚያ እንስጥ።

አቡ ፈትያ
ቅድሚያ ለሚሰጠው ቅድሚያ እንስጥ።
🌻┈┈••◉❖◉●••┈🌻
┏━━━━━━━━
🌷 @Abufetiya1
┗━━━━━━━━
https://telegram.me/Abufetiya1


📚ሰፊና ከክፍል 1-25 (እስከ መጨረሻዉ ክፍል)📚

🔊 በኡስታዝ ሙሐመድ አረብ [ሀፊዘሁላህ]

ክፍል-1
https://goo.gl/E4hhZW
ክፍል-2
https://goo.gl/Zcpnrf
ክፍል-3
https://goo.gl/tCmjkY
ክፍል-4
https://goo.gl/g1Um7a
ክፍል-5
https://goo.gl/7nZE89
ክፍል-6
https://goo.gl/eyXA8n
ክፍል-7
https://goo.gl/GJn3J9
ክፍል-8
https://goo.gl/eGB9gX
ክፍል-9
https://goo.gl/zRxU9u
ክፍል-10
https://goo.gl/FqZgzD
ክፍል-11
https://goo.gl/9twhqe
ክፍል-12
https://goo.gl/zL1W3n
ክፍል-13
https://goo.gl/NrccDx
ክፍል-14
https://goo.gl/dDskuc
ክፍል-15
https://goo.gl/BQnY8v
ክፍል-16
https://goo.gl/RDqWLg
ክፍል-17
https://goo.gl/iZgC5b
ክፍል-18
https://goo.gl/d5tb9A
ክፍል-19
https://goo.gl/V67UEJ
ክፍል-20
https://goo.gl/P6Tyvu
ክፍል-21
https://goo.gl/YtUUVv
ክፍል-22
https://goo.gl/HqtqdR
ክፍል-23
https://goo.gl/KF3tTg
ክፍል-24
https://goo.gl/xZuEhY
ክፍል-25
https://goo.gl/y4ffR1

Pdf
https://goo.gl/48G85j

ሁሉንም በአንድ ላይ የያዘ link
https://goo.gl/bLKxNP


Join 👉 @Twehid


Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
ሚችለውን ሁሉ ሁንላቸው። የሚረኩብህ እንጂ የሚሸማቀቁብህ፤ የሚዘኑብህ እንጂ የሚሳቀቁብህ፤ የምታሳርፋቸው እንጂ የምታሳፍራቸው አትሁን። ቤተሰብህ ላይ ጥገኛ ሆነህ ሳለ አልፈህ የምትፏልልባቸው ከሆነ ግን በርግጠኝነት መጥፊያህን ይዘሀል። "የማያድግ ልጅ ታዝሎ ያፏጫል።"
"የቤት ቀጋ፣ የውጭ አልጋ አትሁን።"

(15) አላማ ይኑርህ። ለአላማህ ትጋ። ወደ አላማህ ተጓዝ። ወዴት ነው የምትሄደው? ታውቀዋለህ? ምንድነው የምትፈልገው? ይገባሃል? ምን ሰበብ እያደረስክ ነው? መቼስ ሰሜን ለመድረስ ወደ ደቡብ አይኬድም። ጤፍ ዘርቶ ባቄላ አይጠበቅም። ባጭሩ አላማህንም፣ አቅጣጫህንም፣ ሚናህንም እወቅ።
"የሚሄድበትን የማያውቅ የትኛውም መንገድ ይወስደዋል።"

(ኢብኑ ሙነወር፣ ጥር 21/2011)


Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር) dan repost
15 ምክሮች ለሙስሊም ተማሪዎች
~~~~~~~~~~~~~
·
① መምህርህን አክብር። አስተማሪህ ለደሞዝ ቢሰራም ላንተ ውለታ እየዋለ ነው። ኋላ ከሚፀፅትህ ዛሬ ለአስተማሪህ ትሁት ሁን። እድሜውንም አክብር። መምህር "አስተማሪ" የተባለው ስለሚያስተምርህ ነው። የሚያስተምርህን መናቅ የሚያጎርስህን መንከስ ነው። እንዲያዝንብህ፣ "ባጎረስኩ እጄን ተነከስኩ" እንዲል አታድርገው። ውለታ ይግባህ። የወጣትነት ስሜት ድፍን ቅል አያድርግህ።
"አስተማሪን መናቅ እውቀትን መናቅ ነው።"
"ለእውቀት ያለህ ክብር መጠኑ ለአስተማሪህ ባለህ ክብር ልክ ነው።"

② ተባባሪ ሁን። እንዳቅምህ የምታግዛቸው በርካታ ደካማ ተማሪዎች በዙሪያህ አሉ። የእለት ጉርስ የሚገዳቸው፤ የደንብ ልብስ አቀበት የሆነባቸው፤ የሳሙና፣ የሃንዳውት፣ የታክሲ፣ የቤት ኪራይ፣ የህክምና፣ የደብተር፣ … የሚቸግራቸው፤ ብዙ ናቸው። ቢቻል አስተባብራችሁ የተቀናጀ ስራ ስሩ። ካልሆነ የራስህን ሐላፊነት ተወጣ። ደካማ ተማሪዎችን አስጠና፣ አግዝ። በዱንያ እርካታን ታገኝበታለህ። ልምድን ትቀስምበታለህ። ህይወትን ትማርበታለህ። በኣኺራ እጥፍ ድርብ ትሸለምበታለህ።
"መተባበር የሰብአዊነት መለኪያ፣ የሥልጣኔ ማማ ነው።"

③ ከመንደሬነት ራቅ። የሰፈር፣ የቀበሌ፣ የወረዳ፣ የአካባቢ ብሽሽቅ ውስጥ አትግባ። ዘረኝነትን በየትኛውም መልኩ ተፀየፍ። ዘረኞችንም ከቻልክ ምከር። ካልሆነ አፍንጫህን ይዘህ ሽሻቸው። በዘርህ ከማንም በላይም፣ ከማንም በታችም አይደለህም። ሌሎችን በዘር አትውጋ። በዘር ለሚተነኩስህም ንቀህ እለፍ እንጂ እሳት ጎርሰህ አትነሳ። ትእግስት ፍርሃት እንዳልሆነ ለራስህ ሹክ በለው።
"ዘረኝነት ጥንብ ሲሆን ዘረኛ ደግሞ ጥንብ አንሳ ነው።"

④ ለዲንህ ጊዜ ስጥ። አንተ ያለ ዲንህ ባዶ ነህ። ያለ ዲን ስኬትም ስኬት፣ ህይወትም ህይወት አይደለም። ስለ ዲንህ ስትማር ክፍል ውስጥ ዲንህን አታስነካም። የተሳሳተ ቲዎሪ አያነቃንቅህም። ውሎህ በፕሮግራም ይሆናል። ሕይወትህ ጣእም ይኖረዋል። ስለዚህ ቁርኣን ቅራ። ኪታብ ተማር። ሶላት ስገድ። ስታልፍ ስታገድም ዚክርህን አድርግ። ዲንህን በራስህ ላይ አንፀባርቅ። ዲንህ የሚወራ ሳይሆን የሚንኖር ነው።
"ዲንህ ህይወትህ ነው። ዲንህ ከሌለ አንተ እራስህ የለህም።"

⑤ በትምህርትህ ላይ ሃላፊነት ይሰማህ። ቤተሰብ የላከህ ለዋዛ አይደለም። ገንዘቡም፣ ጊዜውም፣ ድካሙም ዋጋ አይጣ። ስለዚህ በወጉ ተማር። ክፍል ውስጥ በሚገባ ተከታተል። ንቁ ተሳትፎ ይኑርህ። በሚገባ አጥና ። ስንፍናን አትቀበል። "አልችልምን" አርቅ ። ኩረጃን፣ ጥገኝነትን ተፀየፍ። በጥረትህ የተሻለ ደረጃ ላይ ለመድረስ ወኔ ይኑርህ። አትጠራጠር! ስትጥር ዛሬ ካለህበት የተሻለ ትሆናለህ። ባለ መጣሩ እንደ ሰነፍ የሚታይ፣ እራሱን የማያውቅ ስንት ባለ ብሩህ አእምሮ አለ?! መማርህ ካንተ አልፎ ለወገን የሚተርፍ ዋጋ እንዳለው ተረዳ። "Education is a better safeguard of liberty than a standing army."

⑥ እራስህን ሁን። የመጣውን ፋሺን ሁሉ ካልሞከርኩ አትበል። ለራስህ ክብር ስጥ እንጂ። አንተ'ኮ የማስታወቂያ አሻንጉሊት አይደለህም። አርአያህን ለይ። መልካም ስብእና ያላቸውን እንጂ፣ ያለ ቁም ነገር ስማቸው የገነነ ሰዎችን ለመምሰል አትፍሰስ። አንተ ህሊና የተሰጠህ ክቡር ፍጡር እንጂ በቀደዱለት የሚፈስ የቦይ ውሃ አይደለህም።
"እራሱን ያላገኘ ሌሎችን ሲከተል ይኖራል።"

⑦ ጊዜህን በአግባቡ ተጠቀም ። አንተ ዘንድ አላህ ከሰጠህ ሐብት ሁሉ ርካሹ ጊዜህ የሆነ'ለት ያለ ጥርጥር ከስረሀል። ወደ ጨለማ ጥግ ከሚያደርስ የድንግዝግዝ ባቡር ላይ ተሳፍረሀል።
እባክህን ሕይወትህ ላይ አንዳች እሴት በማይጨምሩ ነገሮች ዳግም የማታገኘው ውድ ጊዜህን አታባክን። የምልህ እየገባህ ከሆነ በሙዚቃ ከመመሰጥ፣ ፊልም ጋር ከመርመጥመጥ፣ የፈረንጅ እርግጫ ከማሳደድና መሰል አልባሌ ነገሮች ራቅ እያልኩህ ነው። እነዚህ ነገሮች ከእለት መዝናኛነት ባለፈ ተሻጋሪ ሱስ የሚሆኑ ወጥመዶች ናቸው።
"ጊዜ ሰይፍ ነው። ካልቆረጥከው ይቆርጥሀል።"
"አንተ የጊዜያት ድምር እንጂ ሌላ አይደለህም። እያንዳንዷ የጊዜ ክፍልፋይ ስታልፍ አንተ እራስህ እያለፍክ ነው።"

⑧ ጓደኞችህን ለይ። ጓደኛህ ወይ የምትጠቅመው ወይ የሚጠቅምህ መሆን አለበት። ከዚህ ውጭ የሆነ ጓደኛ የፋንዲያ ያክል ዋጋ የለውም። እንዲያውም ያጠፋሀል። በዱንያ ቁም ነገር ላይ ከመድረስ ያሰናክልሀል። አልፎም ኣኺራህን ያጨልመዋል። ኧረ ለመሆኑ አንተ እራስህ ምን አይነት ጓደኛ ነህ? አልሚ ወይስ አጥፍቶ ጠፊ? በል ከዛሬ ጀምሮ ከጓደኛህ ጋር ቁጭ ብላችሁ የአብሮነታችሁን ሂሳብ አወራርዱ። ጓደኝነታችሁ የምትጠቀሙበት እንጂ የምትጎዱበት እንዳይሆን በስርኣት ተመካከሩ።
"ሰው በወዳጁ እምነት ላይ ነው። ስለሆነም አንዳችሁ ማንን እንደሚወዳጅ ይመልከት።"

⑨ መልካም ስነ ምግባርን ተላበስ። አትሸማቀቅ፤ ግን አትኮፈስ። ትሁት ሁን፤ ግን አትልፈስፈስ። አትንበጣረር፤ ግን አትጥመስመስ። ሰከን በል፤ ግን አትፍዘዝ። ረጋ በል፤ አትንጣጣ። ከአንደበትህ ክፉ አይውጣ።
ፊትህ ሁሌ በፈገግታ ይታጀብ። ተግባቢና ለሰዎች ቀላል ሁን። የደረስክበትን ሁሉ በሰላምታ አውደው። በትህትና አጊጥ። በቅንነት አሸብርቅ።
"መጣብን" ሳይሆን "መጣልን" የምትባል ሁን። አታጣላ። አታባላ። ሃሜትና ውሸትን ክላ።
"ህዝብ ማለት ስነ ምግባር ነው። ስነ ምግባር የሌለው ህዝብ ካለ አይቆጠርም።"

(10) በትምህርት ሕይወትህ ላይ ሳለህ መዝናኛህን ቁም ነገር መጨበጫ አድርገው። ቁም ነገር አዘል መፃህፍትን አንብብ። ከቻልክ እንደ የመጀመሪያ እርዳታ /first aid/ አሰጣጥ፣ እንደ ቴኳንዶ ያሉ ራስን መከላከያ ሥልጠና፣ የችግኝ ወይም የጓሮ አትክልት አተካከል፣ እና መሰል ጠቃሚ ስልጠናዎችን ሰልጥን፣ አሰልጥን። አካባቢህን አስተባብረህ አፅዳ።
"ሰው ማለት፣ ሰው የሚሆን ነው ሰው የጠፋለት።"

(11) ከህገ ወጥ ፆታዊ ግንኙነት አጥብቀህ ራቅ። ህጋዊ በሆነ መልኩ ተረጋግተህ ለምትደርስበት ነገር በህገ ወጥ መልኩ ለማግኘት እየቸኮልክ ስብእናህን አታቆሽሽ። የሌላን ህይወትም አታበላሽ። ከአላማህም አትሰናከል። ክፉ ምሳሌም አትሁን።
"ስድ ግንኙነት ለህሊና ጠባሳ፣ ለቤተሰብ ጦስ፣ ለህዝብ መቅሰፍት ያስከትላል።"
"ከጓደኞቿ የወጣች ማሽላ አንድም ለወፍ አንድም ለወንጭፍ ትሆናለች።"

(12) የት/ቤት ክበባት አብዛኞቹ ቁም ነገር የማይሰራባቸው ትርኪ ምርኪ ናቸው። ካልተገደድክ በስተቀር አትግባባቸው። ከተገደድክ መርጠህ ለመግባት ሞክር። ከገባህም ሸሩን ለመቀነስ፣ እሴት ለመጨመር ጣር።
"ህይወት መቀለጃ አይደለም።"
"ብልህ ሰው በሚወረወርበት ድንጋይ ቤት ይሰራል።"

(13) ከደባል ሱሶች ራቅ። አላማ ያለው ሰው ከሱስ ጋር አይነካካም። ለነፃነት ዋጋ የሚሰጥ ሰው ለቆሻሻ ነገሮች አይንበረከክም። ደግሞም ውለታ ቢስ አትሁን። አንተ አክብረህ ያማረ ቪላ፣ ወይም ቆንጆ መኪና፣ ወይም ሚሊየን ገንዘብ ቆጥረህ የሰጠኸው ሰው አይንህ እያየ ከፊትህ በእሳት ቢያጋየው ምን ይሰማሀል? ኣ? ሰውስ ምን ይላል? አላህ በክብር የሰጠህን ህይወት በጫትና በሲጋራ መግደል ማለት ከዚህ የከፋ ውለታቢስነት ነው። እራስህን በሱስ የምትገድለው ከቤተሰብ በተቆነጠረ ሳንቲም ከሆነ ግን አንተ ዘመን ተሻጋሪ ገልቱ ነህ። እንስሳ ነህ ብየ የእንስሳን ክብር ዝቅ ማድረግ አልፈልግም።

"እራስን በሱስ በመጉዳትና እራስን በማጥፋት መካከል ያለው ልዩነት የጊዜ ርዝማኔ ነው።"

(14) ለወላጆችህ በጎ ሁን። አቅምህ የ


ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል dan repost
📌ሴት ወንድን ለትዳር መጠየቋ ⁉️
#በውስጥ_መስመር_ከተላኩ_ጥያቄዎች❓
♻️ : ክፍል 178

📌ጥያቄ📌
📌 ሴት ልጅ የወደደችውን ወንድ #ለትዳር መጠየቅ ትችላለችን ወይስ በተለምዶ የግድ #ቤተሰብ የመረጡላትን ነው የምታገባው⁉️

✅መልስ✅
✅ ሴት ልጅ አንድ ዲኑን ፣ ስነምግባሩን ፣ እውቀቱን #የወደድችለትን ወንድ ለትዳር እንደምትፈልገውና ብታገባው ፍላጎቷ #እንደሆነ መግለፅ ትችላለች።

✅ ለዚህም #ቡኻሪ (4828) ላይ እንደተዘገበው አንድ ጊዜ አንዲት #ሴት ራሷ ልታገባቸው እንደምትፈልግና ራሷን ለነብዩ #ሶለሏሁ_አለይሂ_ወሰለም ለማቅረብ መጣችና: "#ትፈልገኛለህን?" ብላ መጠየቋና ነብዩም መጠየቋን #አለማጥላላታቸው የሚፈቀድ መሆኑን ያመለክተናል።

📌 ነገር ግን አብዛኛው ኡለሞች እንደሚናገሩት እርሷ ቀጥታ #በአካል ሂዳም ይሁን #በስልክ ደውላ ሀሳቧን ከምትገልፅ ይልቅ ፊትናን #ከመከላከል እንፃርና ብዙ ወንዶችም ከሴቶች ይህ ጥያቄ ሲመጣ #የመኩራትና_የማጉላላት ስሜት ስለሚያሳዩ #በላጩ በቤተሰቦቿ በኩል እንዲገለፅ ማድረጓ ነው።

📌 በተጨማሪም ጥያቄውን ካቀረበች #በኃላ መልሱ #እሽታ ከሆነ ቀጥታ ወደ #ኒካህ መሄድ እንጅ መደዋወልና ሌላ ግኑኝነት መፍጠት ተገቢ አይደለም። መልሱ #እምቢ ከሆነ ደግሞ ቀጥታ ያለውን ግኑኝነት #ማቋረጥ እንጅ እሱን #በማሰብና_በመለመን ጊዜዋን መፍጀትና ወደ #ሀራም ነገራቶች የሚያስኬደውን መንገድ ማመቻቸት የለባትም።

♻️ ምንጭ :— 📚ኢማሙ ነወዊይ ፣ ፈትሁል ባሪ ፣ 9/175 ፣ 📚ኢማሙል ቁርጡቢይ ፣ ተፍሲሩል ቁርጡቢ ፣ ‏13 / 271 ‏
__________________
©@mohammedjud
*ያለፈዎትን ፈትዋዎች ለመከታተል
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/yeilmkazna


الدين هو النصيحة dan repost
🌹 *የጨረቃ ቁራጭ ይመስል ነበር...* 🌹
*ከርሶ የኖሩ ሰሃቦች ምንኛ ታደሉ...*
አነስ መልካም ስራውን አለህን ይውደድለት ሲናገር ... ውዱ ነብይ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም የቆዳቸው ቀለም የሚያምር ነው። ላባቸው ልክ እንደ ሉል ነበር። የአለህ መልዕክተኛን እጅ ያህል የሚለሰልስ ሀር ነክቼ አላውቅም ።ከነብዩ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ሽታ የተሻለ ሽቶም ሆነ እጣን አሽትቼ አላውቅም ። የእጃቸው ሽታ ከሽቶ ማምረቻ ቦታ የወጡ ይመስላል። ከሩቅ ሲመጡ በሽታቸው ይታወቃሉ...
አነስ አክሎም " ነብዩ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ሽቶ ልቀባዎት የሚላቸውን ሰው ተቃውመው አያውቁም። ፊታቸው እንደፀሃይ የፈካ ነው። ደስ ባላቸው ግዜ ፊታቸው ቁራጭ ጨረቃ ይመስል ነበር" ብሏል።
ጃቢር ቢን ሰሙራህ በበኩላቸው " አንዴ የአለህ መልዕክተኛን ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም በምሽት አገኘኋቸው። የሚያምር ቀይ ጀለቢያ ለብሰዋል። ጨረቃ ወጥታ ነበር። እሳቸውንና ጨረቃን ማወዳደር ጀመርኩ ለኔ እሳቸው ከጨረቃዋ ይበልጥ ያምራሉ " ብሏል ።

ያ.....አለህ በጀነት የራሳቸውን ጉርብትና ወፍቀን...


*ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም*


✍ ጅብሪል ሱልጣን(Abu fetiya)

አቡ ፈትያ
ቅድሚያ ለሚሰጠው ቅድሚያ እንስጥ።
🌻┈┈••◉❖◉●••┈🌻
┏━━━━━━━━
🌷 @Abufetiya1
┗━━━━━━━━
https://telegram.me/Abufetiya1

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.

210

obunachilar
Kanal statistikasi