ሩበን አሞሪም ይሁንታቸውን ሰጥተዋል !!!
ፖርቱጋላዊው አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም የፓትሪክ ዶጉ ዝውውር እንዲፈፀም ለክለባችን ባለስልጣናት ይሁንታቸውን እንደሰጡ ተገልጿል።
ይሄንን ተከትሎም የክለባችን ሰዎች በዚህ ሳምንት ከተጨዋቹ ክለብ ሊቼ ጋር ጠንከር ያሉ ድርድሮችን እንደሚያደርጉ ይጠበቃል ተብሏል።
በሌላ ዜና የምእራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ አሌሀንድሮ ጋርናቾን ከክለባችን ለማስፈረም የተጨዋች ቅይይር ሐሳብ አቅርቦ እንደነበር ተገልጿል።
ሰማያዊዎቹ ይሄንን ጥያቄ የጥር የዝውውር መስኮት በተከፈተበት ሰሞን አቅርበው እንደነበር ሲገለፅ ...
አርጀንቲናዊውን የመስመር አጥቂ ወስደው ማንን በምትኩ ሊሰጡ እንዳሰቡ ግን እስካሁን የተገለፀ ነገር የለም።
ዘገባውን ከእውቁ ፋብሪዚዮ ሮማኖ አጠናቀርን ።
@Man_United_Ethio_Fans @Man_United_Ethio_Fans