የተለያዪ ጣፋጭ ዳዕዋዎች የሚያገኙበት ኢስላሚክ ቻናል🍃


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ይህ ቻናል የተለያዩ ጣፋጭ ዳዕዋዎች እንዲሁም ከድናችን ወጣ ያላሉ ትረካዎች እናስተላልፋለን
አስተያየት ካለዎት
@Nesriyaaa
በዚህ ያናግሩን

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter




Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ጥቂት ወሳኝ ነጥቦች በለይለተል ቀድር ዙሪያ
~
ለይለቱል ቀድር ማለት ትልቅ ደረጃ ያላት ለሊት ማለት ነው። ከፊል ዓሊሞች ዘንድ ደግሞ ፍጡራንን የሚመለከቱ የአመቱ ውሳኔዎች የሚተላለፍባት ለሊት ማለት ነው።

የለይለተል ቀድር ደረጃዎች፦

1. ቁርኣን የወረደባት ለሊት ነች። ጌታችን “እኛ (ቁርኣኑን) በለይለተል ቀድር አወረድነው”ብሏል። [አልቀድር፡ 1]
2. በሷ ውስጥ የተፈፀመ ዒባዳ ከሌሎች ለሊቶች ምንዳው የበለጠ ነው። አላህ “ለይለተል ቀድር ከሺህ ወር በላጭ ናት” ይላል። [አልቀድር፡ 3]
3. በሷ ውስጥ መላእክት ኸይርን ይዘው ወደ ምድር ይወርዳሉ። ጌታችን “በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ (ጂብሪል) በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ” ብሏል። [አልቀድር፡ 4]
4. ለሊቷ ዒባዳ የሚበዛባት፣ ሰላም የሚሰፍንባት ለሊት ናት። ጌታችን “እርሷ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት” ብሏል። [አልቀድር፡ 5]
5. የተባረከች ለሊት ናት። ጌታችን “እኛ (ቁርኣኑን) በተባረከች ለሊት ውስጥ አወረድነው” ብሏል። [ዱኻን፡ 3]
6. በዚች ለሊት አላህ በአመቱ ውስጥ ያሉ የፍጡራኑን የእድሜና የሲሳይ ልኬታዎችን ይፅፋል። “በውስጧ የተወሰነው ነገር ሁሉ ይልለያል” ብሏል አላህ። [ዱኻን፡ 4]
7. በዚያች ለሊት ምድር ላይ የሚኖሩት የመላእክት ብዛት ከጠጠሮች ብዛት የበዛ ነው። [አልባኒ ሐሰን ብለውታል]
8. ለተጠቀመባትና አጅሩን ከአላህ ላሰበ ሰው ከወንጀል መማርያ ለሊት ነች። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- “ለይለተል ቀድር አምኖና አስቦ የቆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይታበስለታል።” [ቡኻሪና ሙስሊም]
ስለዚህ ይህቺን ወሳኝና እጅግ የላቀ ዋጋ ያላት ለሊት ለማገኘት የምንችለውን ሁሉ ልንጣጣር ሌሎችንም ልናበረታታ ይገባል። ኢብኑል ቀይም ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “ለይለተል ቀድር በአመት ውስጥ የምትገኝ አንዲት ቀን ብትሆን እሷን ለማገኘት ስል አመቱን ሁሉ እቆም ነበር። በ(ረመዳን) አስር ለሊቶች ውስጥ ከሆነችማ ምን ነካህ? (እንዴት እዘናጋለሁ?!)” [በዳኢዑል ፈዋኢድ፡ 1/55]

ለይለቱል ቀድር የምትገኘው በየትኛው ጊዜ ነው?

የምትገኘው በረመዳን ብቻ ነው። ከረመዳንም በመጨረሻዎቹ አስሮች ውስጥ። ነብዩ ﷺ “ይቺን ለሊት እየፈለግኩ የመጀመሪያውን አስር ኢዕቲካፍ አደረግኩኝ። ከዚያም መካከለኛውን አስር ኢዕቲካፍ አደረግኩኝ። ከዚያም (የሆነ አካል) መጥቶኝ ‘እሷ በርግጥም የመጨረሻው አስር ላይ ናት’ አለኝ” ማለታቸው ይህን ያስረግጣል።
ይቺ ታላቅ ለሊት እንዳታልፈን የምንችለውን ሁሉ ልንጣጣር ይገባል። ነብዩ ﷺ በሐዲሣቸው እንዲህ ብለዋል፡- “በሱ ውስጥ ከአንድ ሺ ወር የምትበልጥ ለሊት አለች። የሷን ኸይር የተነፈገ በእርግጥም (ትልቅ ነገር) ተነፍጓል።” [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 2247]
መቼ እንፈልጋት?
ይበልጥ የሚገመተው ጊዜ 27ኛዋ ለሊት ናት። ይሁን እንጂ “ለይለተል ቀድርን በ23ኛዋ ለሊት ፈልጓት” ማለታቸው እንዲሁም “ለይለተል ቀድርን በመጨረሻዎቹ አስሩ (ለሊቶች) ፈልጓት። ከተረታችሁ በመጨረሻዎቹ 7 ላይ አትረቱ” ማለታቸው ለይለተል ቀድር ሁሌ በአንድ ለሊት ላይ እንደማትገደብ ያስረዳል። በተለይ ደግሞ በዊትሮቹ (21፣ 23፣ 25፣ 27፣ 29) የመሆን እድሏ ሰፊ ነው። ይህን አስመልክተው ነብዩ ﷺ “ለይለተል ቀድርን ከረመዳን በመጨረሻዎቹ አስሩ (ለሊቶች) በዊትሮቹ ፈልጓት” ብለዋል። [ቡኻሪና ሙስሊም]
ይህ ማለት ግን ከነጭራሹ በሸፍዕ ለሊቶችም (22፣ 24፣ 26፣ 28፣ 30) አትሆንም ማለት አይደለም። ምክንያቱም ነብዩ ﷺ “ከረመዷን የመጨረሻዎቹ አስሮች ውስጥ ፈልጓት። ዘጠኝ ሲቀረው፣ ሰባት ሲቀረው፣ አምስት ሲቀረው” ብለዋልና። ወሩ 29 ቀን ከሆነ 9፣ 7፣ 5 ሲቀር ዊትር የሚሆኑት ከመጨረሻ ወደ ኋላ ሲቆጠር ነው። ከመጀመሪያ ለሚቆጥር ግን ዊትር ሳይሆን ሸፍዕ ቁጥር ነው የሚሆኑት። ይህም ሸፍዕ ለሊቶችም ላይ የመሆን እድል እንዳለ ያስረዳናል። ቢሆንም ግን “ከ(መጨረሻው አስር) በዊትሩ ፈልጓት” ስላሉ ዊትሩ ላይ ይበልጥ ማተኮር ይገባል።

በለይለተል ቀድር ምን ይጠበቅብናል?

ዒባዳ ማብዛት። ነብዩ ﷺ “ለይለተል ቀድር አምኖና አስቦ የቆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይታበስለታል” ይላሉ። [ቡኻሪና ሙስሊም] እናም በዚች ለሊት ታላቅነትና መደንገግ አምኖ፣ ከዚያም ለመታየት ለጉራና መሰል አላፊ ኒያ ሳይሆን አጅሩን ከአላህ በማሰብ እንደሶላት፣ ዱዓእ፣ ቁርኣን መቅራት፣.. የፈፀመ ሰው ወንጀሉ ይታበስለታል ማለት ነው።

ምልክቶቿ

1. “በዚያን ቀን ማለዳ ፀሀይዋ ነጭ ሆና ጨረር ሳይኖራት ትወጣለች።” [ሙስሊም]
2. በዚያን ለሊት ዝናብ ሊዘንብ ይችላል። [ቡኻሪና ሙስሊም]
3. ቀጣዩ ቀን አየሩ ሞቃትም ብርዳማም ሳይሆን የተስተካከለ ይሆናል። ፀሀይዋም ደካማና ቀይ ትሆናለች። [ሶሒሑል ጃሚዕ]
እነዚህ ምልክቶች ግን አንፃራዊ ናቸው ይላሉ ሸይኹል አልባኒ ረሒመሁላህ። በአካባቢው ባለው የአየር ሁኔታ ሊወሰን ይችላል። ስለሆነም በትክክል ለይለተል ቀድር በተከሰተበት ጊዜም እነዚህን ምልክቶች ብዙ የማያያቸው ሊኖር ይችላል።
ለይለተል ቀድር ለሰጋጆች ብቻ አይደለችም!
የወር አበባ ላይ፣ የወሊድ ደም ላይ ያሉ፣ መንገደኞች… የዚች ለሊት ትሩፋት አያልፋቸውም። ማስረጃው ጠቅላይ ነውና። ባይሆን ከሶላት ውጭ ባሉ ዒባዳዎች ላይ ሊበራቱ ይገባል። በዚያች ለሊት ዱዓእ ማብዛት ጥሩ ነው። እንዲያውም ሱፍያኑ ሠውሪ ረሒመሁላህ “በለሊቷ ከሶላት ይልቅ ዱዓእ እኔ ዘንድ የተወደደ ነው” ይላሉ።

ለይለተል ቀድር በአይን ትታያለች?

አንዳንዶች እግራቸውን ዘርግተው፣ እያወሩ ሰማይ ሰማይ ያንጋጥጣሉ። የሚጠባበቁት ተወርዋሪ ኮከብ ነው። እሱን ሲያዩ “አኑረን አክብረን” ብለው ይንጫጫሉ። ይሄ ባዶ እምነት ነው። ለይለተል ቀድር አላህ በአንዳንድ ባሮቹ ቀልብ ላይ ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ የመረጋጋት ወይም የመለየት ስሜት ከማሳደሩ ውጭ በአይን የሚታይ ነገር አይደለም። የሚታየው ምልክቶቿ እንጂ እራሷ አይደለችም። ሰዎች የሚጠበቅባቸውን ከተወጡ ለሊቱ ለይለተል ቀድር መሆኑን ባያውቁ እንኳን ትሩፋቷን አያጡም።
ለይለተል ቀድር እንደሆነ ውስጡ ያደረ ሰው ምን ያድርግ?
በተለይ ደግሞ ለሊቱ ለይለተል ቀድር እንደሚሆን ውስጣችንን ከተሰማን ይበልጥ ልናተኩርበት የሚገባን ዱዓእ “አሏሁመ ኢነከ ዐፉውዉን ቱሒቡል ዐፍወ ፈዕፉ ዐኒ” (“ጌታዬ ሆይ! አንተ በርግጥም ይቅር ባይ ነህ። ይቅር ማለትን ትወዳለህ። ስለሆነም ከኔ ይቅር በለኝ” የሚለው ነው። [አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል] ስለዚህ ዋናው ትኩረታችን የአላህን ይቅርታ ለማግኘት ይሁን።
ግን ለምን አላህ ለይለተል ቀድርን ስውር አደረጋት?
ዑለማዎች እንደሚሉት ታላላቅ ትሩፋቶች በሚገኝባቸው የረመዳን የመጨረሻ ለሊቶች ሙስሊሞች በዒባዳ ይበራቱና ይጠናከሩ ዘንድ ነው አላህ ይቺን ለሊት ስውር ያደረጋት። እናም ለይለተል ቀድርን እንዳታመልጣቸው ሲጣጣሩ ለይተው ቢያውቋት ሊኖራቸው ከሚገባው በበለጠ ለዒባዳ ይተጋሉ። በዚህም ይበልጥ ይጠቀማሉ። ለይተው ቢያውቋት ግን እሷ ብቻ ላይ አነጣጥረው ሌሎቹ ለሊቶች ላይ ይዘናጉ ነበር። እናም መሰወሯ ነብዩ ﷺ እንዳሉት ለኛ ኸይር ነው። [ቡኻሪ]
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ሰኔ 29/2007)
የቴሌግራም ቻናል :-
https://t.me/IbnuMunewor


Forward from: Suna Islamic Library
🔖ወርቃማ ምክሮች🙏
🖍1⃣6⃣

👉🏾👉🏾 ለእውነታ እንጂ ለይሉኝታ አትኑር ፤ ያን ስልህ የምትኖርበት ሕዝብና ባሕል ከእውነት ጋር እስካልተጋጨ መጋፋት የለብህም። ሠዎች የሚቀበሉህ ባሕላቸውን ስታውቅና ስታከብርላቸው ነው።
ቻናላችን፦ t.me/sunatube
Join> t.me/sunatube
Share> t.me/Sunatube


Forward from: Suna Islamic Library
Hadith

حَدَّثَنَا قَيْسُ بْنُ حَفْصٍ، وَمُوسَى بْنُ إِسْمَاعِيلَ، قَالاَ حَدَّثَنَا عَبْدُ الْوَاحِدِ بْنُ زِيَادٍ، حَدَّثَنَا أَبُو قُرَّةَ، مُسْلِمُ بْنُ سَالِمٍ الْهَمْدَانِيُّ قَالَ حَدَّثَنِي عَبْدُ اللَّهِ بْنُ عِيسَى، سَمِعَ عَبْدَ الرَّحْمَنِ بْنَ أَبِي لَيْلَى، قَالَ لَقِيَنِي كَعْبُ بْنُ عُجْرَةَ فَقَالَ أَلاَ أُهْدِي لَكَ هَدِيَّةً سَمِعْتُهَا مِنَ النَّبِيِّ، صلى الله عليه وسلم فَقُلْتُ بَلَى، فَأَهْدِهَا لِي‏.‏ فَقَالَ سَأَلْنَا رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم فَقُلْنَا يَا رَسُولَ اللَّهِ كَيْفَ الصَّلاَةُ عَلَيْكُمْ أَهْلَ الْبَيْتِ فَإِنَّ اللَّهَ قَدْ عَلَّمَنَا كَيْفَ نُسَلِّمُ‏.‏ قَالَ ‏
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
‏ قُولُوا اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ ‏"

‌‌‏

Narrated Abdur-Rahman bin Abi Laila:

Kab bin Ujrah met me and said, "Shall I not give you a present I got from the Prophet?" `Abdur- Rahman said, "Yes, give it to me." I said, "We asked Allah's Messenger (ﷺ) saying, 'O Allah's Messenger (ﷺ)! How should one (ask Allah to) send blessings on you, the members of the family, for Allah has taught us how to salute you (in the prayer)?' He said, 'Say: O Allah! Send Your Mercy on Muhammad and on the family of Muhammad, as You sent Your Mercy on Abraham and on the family of Abraham, for You are the Most Praise-worthy, the Most Glorious. O Allah! Send Your Blessings on Muhammad and the family of Muhammad, as You sent your Blessings on Abraham and on the family of Abraham, for You are the Most Praise-worthy, the Most Glorious.' "



Sahih al-Bukhari 3370
In-book : Book 60, Hadith 49
USC-MSA web (English) : Vol. 4, Book 55, Hadith 589  (deprecated)
Sahih Bukhari

ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 60, ሐዲስ 48
አቡ ሑመይድ አሥ-ሣዒዲይ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ *”ሰዎች፦ “የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” ሆይ! በእርሶ ላይ እንዴት ሰለዋት እናውርድ? አሉ፤ የአላህ መልእክተኛም”ﷺ”፦ “አላህ ሆይ! ሰለዋትን በሙሐመድ፣ በባልተቤቶቹ እና በዝርዮቹ ላይ አውርድ፥ ሰለዋትን በኢብራሂም ቤተሰብ ላይ እንዳወረድክ በረካትን በሙሐመድ፣ በባልተቤቶቹ እና በዝርዮቹ ላይ አውርድ ልክ በኢብራሂም ቤተሰብ ላይ እንዳወረድክ፤ አንተ የተመሰገንክ እና የተከበርክ ነህ*። أَخْبَرَنِي أَبُو حُمَيْدٍ السَّاعِدِيُّ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّهُمْ قَالُوا يَا رَسُولَ اللَّهِ كَيْفَ نُصَلِّي عَلَيْكَ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ قُولُوا اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَأَزْوَاجِهِ وَذُرِّيَّتِهِ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، وَبَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَأَزْوَاجِهِ وَذُرِّيَّتِهِ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ ‏”‌‏.‏
T.me/sunatube


"ላኢላሀ ኢለሏህ" ከሚለው የሴቶች ደርስ የተወሰደ

🎙ሰዑድ ጀማል


T.me/anti_bed


ውድ የቻናላችን @sunatube ቤተሰቦች #ቢድዓና_ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ በቻናላችን አጫጭር #ፅሁፎች_መፅሀፍ_እና_ሙሀደራዎችን ወደናንተ እናደርሣለን ትኩረት ሠቶ በመከታተል #ራሣችንን አልፎም ሙሥሊሙን ማህበረሠብ #ከቢድዓ እንጠብቅ በዕውቀትም እራሣችንን እናበልፅግ👆👆👆👆👆
__
#ቢድዓ_ሁሉ_ጥሜት_ነው
📌ረሱል - ﷺ - እንዲህ ይላሉ ፦ [ ከዚህ በመቀጠል ; ከንግግሮች ሁሉ በላጩ የአላህ ኪታብ ነው ፤ ከመመሪያዎች ሁሉ በላጩ የሙሐመድ መመሪያ ነው ፤ ከነገራቶች ሁሉ መጥፎው አዳዲስ የተፈጠሩ ነገራቶች ናቸው ፤ ቢድዓ በሙሉ ጥሜት ነው ]
📕(ሙስሊም ዘግቦታል)
➖ ➖ ➖ ➖ ➖ ➖ ➖ ➖ ➖ ➖ ➖
📣ጆይን ያድርጉ፦ https://telegram.me/sunatube


Forward from: የእስልምና ህይወት
ስትሄዱ አጀብ ብላችሁ ሂዱ። ሙሽሪኮችን ታሸብራላችሁ።» አሉ የአሏህ መልእክተኛ ነቢያችን ﷺ
የትኛዋም ስብስብ የከሓዲያንን የልብ ትርታ ትጨምራለች።
(ይህ የውኃ ሙላት መስሎ በፎቶው የሚታየው የኢትዮጲያ ሙሥሊም ሕዝብ ነው ።🥰

አሏህ ሆይ የካዱህን ፍጡራን ሁሉ የእሥልምናን ጣፋጭ መዓዛ በእዝነትህ ታቀምሳቸው ዘንድ እንማጸንሃለን ።

https://t.me/Eslamicfreedomm


"በረመዳን 10 ለሊቶችን መጠባበቅ ይቅርና ለይለቱል ቀድር በአመት ውስጥ በአንድ ለሊት ነው የምትገኘው ቢባል እንኳን አመቱን ሙሉ ለይለቱል ቀድር ለማግኘት ጥረት አደርግ ነበር"ኢብኑ ቀዩም (ረሒመሁሏህ)
https://telegram.me/JEMAL79




Forward from: Sαlαh Responds ⛉
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
🔰ማነው የፈጠረው

ብቻዋን ታላላቅ ብርሃናትን(ፀሐይና ጨረቃ) #ለፈጠረች ለመድኃኒት ድንግል ማርያም ኑ እንስገድላት ለርሷም #እንገዛ::
[ዚቅ ዘየካቲት ኪዳነ ምህረት ገፅ 144]


👆VS👇

(እግዚአብሔር) ብቻውን ታላላቅ ብርሃናትን የሠራ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና፤”
[መዝሙር ዳዊት 136፥7]


T.me/mahircomp123


Forward from: Sαlαh Responds ⛉
📜 የነቢዩ ሙሐመድ "ﷺ" ተዓምራት።

📀 ክፍል 1⃣

🔰Hadith Evidence
[ጃምዒ አት-ተርሚዚ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3600]

🔰Historical Evidence
Indian Manuscript Reference number: Arabic, 2807, 152-173. It is quoted in the book “Muhammad Rasulullah,” by M. Hamidullah

T.me/mahircomp123




بِسْمِ اللَّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيمِ

وَالذَّارِيَاتِ ذَرْوًا (1) فَالْحَامِلَاتِ وِقْرًا (2) فَالْجَارِيَاتِ يُسْرًا (3) فَالْمُقَسِّمَاتِ أَمْرًا (4) إِنَّمَا تُوعَدُونَ لَصَادِقٌ (5) وَإِنَّ الدِّينَ لَوَاقِعٌ (6) وَالسَّمَاءِ ذَاتِ الْحُبُكِ (7) إِنَّكُمْ لَفِي قَوْلٍ مُخْتَلِفٍ (8) يُؤْفَكُ عَنْهُ مَنْ أُفِكَ (9) قُتِلَ الْخَرَّاصُونَ (10) ...



🌺سورة الذاريات 🌺

🍀ሱረቱ ዛሪያት 🍀

አፊፍ ታጅ(ወሎ - ከሚሴ)

ተጨማሪ ቲላዋዎችን ለማድመጥ የአፊፍን የቁርአን ቻናል ይቀላቀሉ⤵️⤵️
http://t.me/AfifTajQuran

You Tube(ዩቲዩብ):

http://www.youtube.com/AfifTaj


Forward from: Sαlαh Responds ⛉
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
🔰የቁርአን ማሰባሰብ 2ኛ ዙር ጀምረናል በኽይር ስራ እንሽቀዳደ::

🎯በዚህ በኸይር ስራ ላይ መሳተፍ የምትፈልጉ ወንድም እህቶቼ ከታች ባለው ሊንክ ያናግሩን።
https://t.me/Sayu_ymam


የቻለ ይቅራ ያልቻለ ያድምጥ 🌹


Forward from: Sαlαh Responds ⛉
መፅሐፍ ቅዱስ ዐይናችሁን ሊያጠፋ ቆርጦ ተነስቷል።




Forward from: Sαlαh Responds ⛉
🔰ለጠቅላላ እውቀት🔰
"Non-trinitarianism"

በአለማችን ወደ 25,000 የክርስትና ቅርጫፎች ብሎም በሀገራችን ወደ 15 የተለያዩ የክርስትና አይነቶች አሉ። እያንዳንዱ ቡድን ከሌላው የሚለየው እና አንድ የሚያደርገው ነጥቦች አሉት። አንዱ ከአንዱ የሚለየው በጥቃቅን ነገሮች ላይ ሳይሆን ዋና በሚባሉት ነገሮች ላይ ነው። ለምሳሌ መፅሐፍ ቅዱስ፣ኢየሱስ፣ስላሴ ወዘተ በእንደዚህ አይነት ጉዳዮች ነው የሚለያዩት።

እስኪ ዛሬ ከክርስትና አይነቶች ስላሴን የሚያወግዙትን ሃይማኖቶች እንይ። እነዚህ ስላሴን የማይቀበሉ የክርስትና ቅርንጫፎች "Nontrinitarianism" ወይም "ገለልተኞች" ይባላሉ።
Nontrinitarianism is a form of Christianity that #rejects the doctrine of the #Trinity. እስኪ እነዚህን ስላሴን የሚያወግዙ የክርስትና አይነቶችን እንይ:-
1-Mormonism.
2-Jehovah's Witnesses
3-Christian Science
4-Armstrongism
5-Christadelphians
6-Oneness Pentecostals
7-Unification Church
8-Unity School of Christianity
.
.
.
https://www.learnreligions.com/faith-groups-that-reject-trinity-doctrine-700367

👉ተጨማሪ የንፅፅር ትምህርቶች ለማግኘት t.me/Mahircomp123


Forward from: Sαlαh Responds ⛉
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
📀እውን 26 አይነት ቁርኣን አለን ⁉

💾መጠን=40 MB

⌚️ደቂቃ=25 min.

🎙ወንድም አቡ ዩስራ

🎥 ክፍል አንድ (1)

--- @Mahircomp123 ---


هزاع البلوشي سورة الكهف
🌸 ሀዛዕ አልቡሉሽ
ሱረቱል ካህፍ🌸
https://t.me/halalmeznagna1

20 last posts shown.

99

subscribers
Channel statistics