4-3-3 World News


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


ይህ የእርሶ፣ የአንተ፣ የአንቺ፣ የእናንተ፣ የኛ የሁላችንም ድምጽ ነው! ለሃሳብ አስተያየት ለመስጠት @atsbaha12 ይጠቀሙ

Связанные каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


ሲአይኤ ኮሮና ቫይረስ ከቤተሙከራ ያመለጠ ነው አለ

አዲሱ የአሜሪካ ማዕከላዊ ስለላ ድርጅት ወይም ሲአይኤ ሀላፊ ጆን ራትክሊፍ እንዳሉት የኮሮና ቫይረስ በተፈጥራዊ መንገድ የተከሰተ ሳይሆን ከቤተ ሙከራ ያመለጠ የመሆን እድሉ ሰፊ መሆኑን ተናግረዋል።

ሀላፊው አክለውም ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ አሜሪካዊያን መሞት ምክንያት የሆነው ቫይረስ እንደ ሀገር እስካሁን ወጥ አቋም አለመያዙ ትክክል አለመሆኑንም ጠቅሰዋል።

ቻይና በበኩሏ ቫይረሱ ከቤተ ሙከራ አምልጧል የሚለው አስተያየት አሜሪካ ቻይናን ለማጥቃት በሚል የምታሰራጨው መረጃ ነው በሚል ውድቅ አድርጋለች።

@Ethionews433 @Ethionews433


በኢትዮጵያ በጎግል ላይ ሰዎች በብዛት የፈለጉት ቃላቶች የትኞቹ ናቸው?

ጎግል በፈረንጆቹ 2024 ሰዎች በድረ ገጹ ላይ በመግባት በብዛት የፈረጉትን (ሰርች) ያደረጉትን ቃላቶች ይፋ አድርጓል።

1 ኢትዮጵያ (Ethiopia)

2 ዩ ትዩብ (youtube)

3 ትራንስሌት (Translate)

4 ጎግል (Google)

5 አፕ (app)

6 ዌዘር (weather)

7 ፕሪምየር ሊግ (premier league)

8 ቴሌግራም (telegram)

9 ከአማርኛ ወደ እንግሊዘኛ (amharic to English)

10 ቤስት ቤት (best bet)

12 ፌስቡክ (facebook)

13 ጎግል ትራንስሌት (google translate)

14 ቲክቶክ (tiktok)

15 ሊቨርፑል (Liverpool)

ዘገባው የዐል ዐይን ነው።

@Ethionews433 @Ethionews433


ትራምፕ ሰነድ አልባዎችን እጅ እግራቸውን በሰንሰለት አስጠፍሮ ወደ ሀገራቸው ማባረር ጀምሯል

USAID ለቀጣይ 90 ቀናት ማንኛውም ዓይነት ድጋፍ ለውጭ ሀገራት እንዳያደርግም ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ትላንት የኮሎምቢያ ፕሬዚዳንት Gustavo Petro አንድ ታሪክ ሰርተዋል:: ዶናልድ Trump በገባው ቃል መሠረት ስደተኛችን ወደየመጡበት ማበረር ጀምሯል::

ብራዚላዊያንን እጅ እግራቸውን በሰንሰለት አስሮ ወደ ቤታቸው ሸኝቷል:: ብራዚላዊያንን ስሸኝ በመንገደኞች አውሮፕላን ነበር:: የሚያሳፍረው ግን ስደተኞቹ ሀገራቸው ስደርሱ እንደወንጀለኛ እጅ እግራቸው እንደተሰረ ነበር:: ቢያንስ ሀገራቸው ደርሰው አውሮፕላኑ እንዳረፈ ለሰው ልጅ ክብር ስባል ሰንሰለቱን ፈተው ከህዝባቸው ጋር እንድቀላቀሉ ማድረግ ይችሉ ነበር:: አሳፋሪ በሆነ ሁኔታ ግን እጅ እግራቸው ታስሮ ከሕዝባቸው ጋር እንድቀላቀሉ ተደርጓል::

ልክ እንደ ብራዚላዊያን ሁሉ ከታች በፎቶ እንደሚትመለከቱት ኮሎምቢያያዊያንም እጅ እግራቸው በሰንሰለት ታስረው ወደ ሀገራቸው ልሸኙ አውሮፕላን እየተሳፈሩ ነው:: የነዚህ ከብራዚል የሚለየው በጦር አውሮፕላን መጫናቸው ነበር::

አውሮፕላኑ መነሳቱ የተነገረው የኮሎምቢያ መንግስት "በዚህ ሰውን ልጅ ክብር በሚነካ መልኩ ዜጎቼን አልቀበልም" በማለት የአየር ክልሉ ዘግቶ ዜጎቹን በክብር ለመቀበል ፕሬዝዳንሻል ፕሌን ወደ አሜሪካ የላከ ቢሆንም "እንደት የሃያሏን አሜሪካ ፕረዚዳንት ትዕዛዝ አታከብሩም" ያለው Trump በፍጥነት ከኮሎምቢያ ወደ አሜሪካ ሚገቡ ምርቶች ላይ የ25% ታሪፍ ጭማሪ፣ የኮሎምቢያ ባለስልጣናት ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ ክልከላ እና የኢኮኖሚ ማዕቀብ ስጥል፣ የኮሎምቢያ ፕረዚዳንት Gustavo Petro በበኩሉ ከአሜሪካ ወደ ኮሎምቢያ በሚገቡ ምርቶች ላይ የ50% ታሪፍ ጭማሪ ጥሏል::

ትራምፕ አሁን የጀመረው የሰውን ሰብዓዊ ክብር በማያከብር መልኩ ስደተኞችን ወደ መጡበት የመሸኘት ዘመቻ ሁሉን ሀገራት መነካካቱ የማይቀር በመሆኑ ኢትዮጵያውያን ምን ቢሆኑ ምን ቢያደርጉ ከመሰል ችግር ልያመልጡ ይችላሉ?

@Ethionews433 @Ethionews433


#alert

ከትንሽ ደቂቃዎች በፊት የመሬት መንቀጥቀጥ መሰማቱ የተለያዩ የቻናላችን ተከታታዮች ገልፀውልናል።

@Ethionews433 @Ethionews433


በቻይና የቤት ስራ ባለመስራቱ ቁጣ የደረሰበት ታዳጊ ወላጅ አባቱ አደንዛዥ እፅ እንደሚጠቀም ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠቱ አባት በቁጥጥር ስር ዋሉ

የቤት ስራውን ባለማጠናቀቁ በአባቱ የተገሰጸው የ10 አመቱ ልጅ ፖሊስ በመጥራት አባቱ አደንዣዥ እፅ እንደሚወስድ በመናገር ወላጁን ተበቅሏል።አስገራሚው ክስተት ያጋጠመው በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በቻይና ዮንግኒንግ ግዛት ውስጥ ነበር። የ10 አመቱ ታዳጊ የቤት ስራውን በሰዓቱ ስላልጨረሰ በአባቱ ከፍተኛ ተግሳፅ ከደረሰበት በኋላ ከቤት ወጥቶ በቀጥታ በአቅራቢያው ወደሚገኝ ሱቅ ሄዶ ስልክ በመጠቀም ሪፖርት አድርጓል።

የአምስተኛ ክፍል ተማሪ  የሆነው ታዳጊው 110 ወደ ቻይና የድንገተኛ አደጋ ስልክ በመደወል አባቱ ህገወጥ ዕፅ  በቤት ውስጥ እንደሚጠቀም የሚያሳይ ማስረጃ አለኝ በማለት ለፖሊስ ጥቆማ ሰጥቷል። ከዚያም ፖሊስ እስኪመጣ ተረጋግቶ በመጠበቅ ፍተሻ እንዲያካሂዱ እና የሰጠውን መረጃ እንዲያረጋግጡ አድርጓል። በፍለጋው ወቅት ፖሊሶች በልጁ ቤት በረንዳ ላይ ስምንት የደረቁ የአደንዣዥ እፅ አበባ እንዳገኙና የልጁ አባት መግዛቱን አምኗል።

ነገርግን ለመድኃኒትነት አገልግሎት ብቻ ሊጠቀምባቸው እንዳቀደም አክሏል። የተገኘበት እፅ እንደ አደገኛ እፅ የሚመድበ በመሆኑ ህግ በመጣሱ መፀፀቱን ገልጿል፣ነገር ግን ሳያውቅ ይህን እንዳደረገ አጥብቆ ተናግሯል። ፖሊስ ማስረጃዎቹን እና ተጠርጣሪውን በአቅራቢያው ወደሚገኝ ጣቢያ በመውሰድ ጉዳዩን ለፀረ አደንዛዥ እፅ ብርጌድ አስተላልፏል።የቻይና ፖሊስ ያልተለመደ እፅ በመጠቀም ያለፈቃድ ማምረት ወይም መያዝ ህገወጥ መሆኑን እና አጥፊዎች የወንጀል ቅጣት እንደሚጠብቃቸው አስጠንቅቋል።

ምንም እንኳን የእፁ የደረቁ ቅርፊቶች ለመድኃኒትነት ወይም ህመም ማስታገሻነት ይወሰዳሉ። ለእንቅልፍ ማጣት እና ጭንቀት ለመቀነስ ተመራጭ ነው። ግን ቻይናን ኦፒየም የተባለውን መድሀኒት ከማምረት ጋር የተያያዘ በመሆኑ እፁን ማምረት ህገወጥ ብላ ፈርጃዋለች።

በስምኦን ደረጄ

@Ethionews433 @Ethionews433




በዛሬው ዕለት በመላው የትግራይ ከተሞች ሊባል በሚችል ደረጀ ሰልፎች እየተደረጉ ነው‼️

ስልፎቹ ገሚሶቹ ሰሞኑን "የትግራይ ሰራዊት የበላይ አመራሮች" ያስተላለፉትን ውሳኔ የሚቃወሙ ገሚሶቹ ደግሞ የሚደግፉ መሆናቸው ከማህበራዊ ትስስር ገፆች ለመመልከት ተችሏል።

መቐለ፣ተምቤን ዓብይ ዓዲ፣ ጣንቋ ምልሽ፣ ኮረም፣ ዓዲ ግራት፣ አኽሱም፣ ውቅሮና እንትጮ ሰላማዊ ሰልፍ ከተደረገባቸው ከተሞች መካከል ይጠቀሳሉ።

በሰልፎቹም በአንድ በኩል ከፍተኛ የጦር አመራሮቹ የወሰኑት ውሳኔ እንዲተገበርና ጊዝያዊ አስተዳደሩ እንደ አዲስ እንዲዋቀር የተጠየቀ ሲሆን በሌላ በኩል ደግሞ የጦር አመራሮቹ ውሳኔን የሚቃወም ብሎም ትግራይ ላይ ዳግም ጦርነት እንዲነሳ አንፈልግም የሚሉ ድምፆች ተሰምተዋል።

@Ethionews433
@Ethionews433


በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና በድጋሜ መውሰድ የምትፈልጉ የግል አመልካቾች የኦንላይን ምዝገባ አድርጉ!

ከዚህ ቀደም በመደበኛ ፕሮግራም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ የማለፊያ ነጥብ ያላመጣችሁና ፈተናውን በድጋሜ መውሰድ የምትፈልጉ የግል አመልካቾች ምዝገባ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡

https://register.eaes.et/Online ሊንክ ላይ በመግባት Apply Now የሚለውን ይጫኑ፤ የሚመጣላችሁን ቅፅ በጥንቃቄ ይሙሉ፤ አስፈላጊ ሰነዶችን ይጫኑ፤ የምዝገባ ክፍያ ብር 750 ክፍያ በመፈጸም ምዝገባዎትን ያከናውኑ፡፡

ምዝገባው የሚያበቃው፦ ጥር 20/2017 ዓ.ም

በምዝገባ ሒደቱ ማንኛውም ድጋፍ ቢያስፈልግዎ ከላይ በምስሉ ላይ በተጠቀሱት የስልክ ቁጥሮች በመደወል ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ፡፡

@Ethionews433 @Ethionews433


አሜሪካ በ2024 318.7 ቢሊየን ዶላር የሚያወጡ የጦር መሳሪያዎችን መሸጧ ተነገረ

የዩክሬን እና የጋዛው ጦርነት የዋሽንግተን የጦር መሳሪያ ንግድ ከ2023ቱ በ29 በመቶ አድጎ ክብረወሰን ሆኖ እንዲመዘገብ አድርገዋል።(አል አይን)

@Ethionews433 @Ethionews433


ኢንተር ሌግዢሪ ሆቴል ተቀጣ

በአዲስአበባ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ካሳንቺስ አካባቢ ጨለማን ተገን በማድረግ የመጸዳጃ ቤት ፍሳሽ ወደ ኮሪደር ልማት አስፓልት የለቀቀው ኢንተር ሌግዢሪ የተባለ ኢንተርናሽናል ሆቴል 300 ሺህ ብር መቀጣቱን እና ቦታውን እንዲያጸዳ መደረጉን የአዲስ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታውቋል፡፡

ባለስልጣኑ በከተማዋ ውስጥ የተለያዩ ስራ ላይ የተሠማሩ የንግድ ድርጅቶች እና ግንባታ ገንቢዎች በመንግስትና በህዝብ ሀብት የተገነቡ መሠረተ ልማቶችን ደህንነት በመጠበቅ እንዲሰሩ መልዕክት አስተላልፏል፡፡

በተጨማሪም በከተማዋ ደንብ በሚተላለፉ የግልና የመንግስት ድርጅቶች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል፡፡(AMN)

@Ethionews433 @Ethionews433


የአለም ጤና ድርጅት የአሜሪካን መውጣት ተከትሎ የወጭ ቅነሳ ሊያደርግ እንደሆነ ተገለጸ

አሜሪካ የአለም ጤና ድርጅትን አጠቃላይ በጀት 18 በመቶ መሸፈን እስካሁን ከፍተኛ ገንዘብ ከሚያዋጡ ሀገራት ውስጥ ቀዳሚ ነበረች።

@Ethionews433 @Ethionews433


ሰበር ዜና

የመሬት መንቀጥቀጥ በአሁን ሰዓት እየተሰማ ነው።

@Ethionews433 @Ethionews433


ቲክቶከሮች ወደ ፌስቡክ እንዲገቡ የ5 ሺህ ዶላር ጉርሻ ቀረበላቸው

የፌስቡክ እና ኢንስታግራም እናት ኩባንያ ሜታ ተጽዕኖ ፈጣሪ ቲክቶከሮች እንዲቀላቀሉት ጥሪ አቅርቧል

ኩባንያው ከ5 ሺህ ዶላር በተጨማሪም የሰማያዊ ባጅ እና ሌሎች አገልግሎቶችንም እሰጣለሁ ብሏል

@Ethionews433 @Ethionews433


የትራምፕ ውሳኔ በጊዜያዊነት ታገደ

ዶናልድ ትራምፕ በመወለድ የሚገኝ ዜግነትን እንዲከለከል ያሳለፉትን ውሳኔ ዳኞች በጊዜያዊነት እንዲታገድ አድርገውታል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በነጩ ቤተመንግሥት በገቡ በሰአታት ውስጥ ካሳለፏቸው ውሳኔዎች አንዱ ሰነድ አልባ በሆኑ ስደተኞች የሚወልዷቸው ልጆች የሚያገኙትን በመወለድ የሚገኝ ዜግነት የሚያስቀር ትዕዛዝ ነበር።

ዋሺንግተንን ጨምሮ ሌሎች ሶስት ግዛቶች ለፍርድ ቤት ባቀረቡት ጥያቄ ውሳኔው በጊዜያዊነት እገዳ እንዲጣልበት ተደርጓል ።

ዳኞችም ውሳኔው ህገመንግስታዊ አይደለም በማለት ጊዜያዊ እገዳን የጣሉበት ሲሆን በቀጣይ ምርመራ እንደሚደረግበት ተገልጿል። (ቢቢሲ)

@Ethionews433 @Ethionews433


የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር መግለጫ

የትግራይ ሐይል አዛዦች ያስተላለፉት ውሳኔ ተከትሎ አስቸኳይ የካቢኔ ስብሰባ መጥራቱን የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር አስታወቀ። የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ማምሻው ባወጣው መግለጫ የትግራይ ሐይሎች ከፍተኛ አዛዦች "ከተልእኳቸው ውጭ ለአንድ ሕገወጥ ቡድን ወግነው ግዚያዊ አስተዳደሩን የማፍረስ፣ ስርዓት አልባነት የማንገስ እና ሰራዊት የመበተን ግልፅ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆናቸውን አሳውቀዋል" ብሏል።

የትግራይ ሐይል አዛዦች በዛሬው ዕለት ያስተላለፉትን ውሳኔ ግዚያዊ አስተዳደሩ የማያውቀውና "ሕጋዊ ይሁን ሞራላዊ ቅቡልነት የሌለው" ሲል ያመለከተው የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር መግለጫ፤ ከዚህ በተጨማሪ የፕሪቶርያ ውልንም ለአደጋ የሚያጋልጥ እና ሃላፊነት የጎደለው ብሎታል። ካለፈው ጥር 10 ቀን 2017 ዓመተምህረት ጀምሮ ስብሰባ ሲያደርጉ የሰነበቱ ሁለት መቶ ገደማ የሚሆኑ የትግራይ ሐይሎች ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ በሰጡት መግለጫ በዶክተር ደብረፅዮን የሚመራው የህወሓት ክንፍ በትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ያለው ሃምሳ ሲደመር አንድ ድርሻ እንዲረከብ እንደሚሹ አስታውቀዋል። ከዚህ በተጨማሪ በትግራይ ያሉ ታጣቂዎች በትግራይ ሰላም እና ፀጥታ ሴክሬታሪያት ስር እንዲሆኑ፥ ከዚህ ውጪ በሆነ ላይ ግን እርምጃ ይወሰዳልም ብለዋል።

የወታደራዊ መሪዎቹ መግለጫ በንባብ ያቀረቡት ኮነሬል ገብረ ገብረፃዲቅ "የደከመ እና ተልእኮው የዘነጋ ግዚያዊ አስተዳደር እንዲጠናከር የሚተኩ አመራር ተተክተው ሊስተካከል ይገባዋል። በግዚያዊ አስተዳደሩ ማቋቋሚያ መሰረት ሓምሳ ሲደመር አንድ ድርሻ ያለው፣ የፕሪቶርያ ውል ተደራዳሪ እንዲሁም 14ተኛ ጉባኤ ያደረገ ህወሓት ግዚያዊ አስተዳደር ለማስተካከል የወሰነው ውሳኔ ያለ ያለመዘግየት ተግባራዊ እንዲሆን ድጋፋችንን እንገልፆለን" ሲሉ አስታውቀዋል።

ይህ ተከትሎ መግለጫ ያወጣው በአቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራዉ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር፥ የትግራይ ሐይል አዛዦች ውሳኔ የህዝብ ችግርን የሚያባብስ እና የጦርነት እና ስርዓት አልበኝነት አዋጅ ነዉ ሲል የኮነነው ሲሆን፥ በመሆኑም በትግራይ ያሉ የፀጥታ ሐይሎች ውድቅ እንዲያደርጉት እንዲሁም ከዚያ የሚመጣ ትእዛዝ ተግባራዊ እንዳታደርጉ ሲልም ጥሪ አቅርቧል። የትግራይ ሐይል አዛዦች ከውሳኔ በዘለለ በችኮላ ወደታች ለማውረድም እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው፥ ይህ በአስቸኳይ ይቁም ሲልም ግዚያዊ አስተዳደሩ ገልጿል።

ዘገባ፤ ሚሊዮን ኃይለሥላሴ ከመቀሌ

@Ethionews433 @Ethionews433


ቭላድሚር ፑቲን ዛሬ ዓለማቀፍ የስልክ ጥሪ ያስተናግዳሉ ተባለ

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዛሬው እለት አስፈላጊ አለምአቀፍ የስልክ ጥሪ እንደሚያደርጉ ክሪሚሊን ማስታወቁን ስፑትኒክ አፍሪካ በዘገባው አስታውሷል።

የስልክ ጥሪውን ከማን ጋር እንደሚያደርጉ አልታወቀም ቢልም ዘገባው፤ የፕሬዝዳንቱ ቃል አቀባይ ግን ፑቲን የስልክ ውይይቱን የሚያደርጉት ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር እንደማይሆን አሳውቋል።

@Ethionews433 @Ethionews433


በአሜሪካ ሎስ አንጀለስ አቅራቢያ አዲስ ሰደድ እሳት ተቀሰቀሰ

በአሜሪካ ካፎርኒያ ግዛት በምትገኘው ሎስ አንጀለስ ከተማ ሰሜናዊ ክፍል ትናንት አዲስ የሰደድ እሳት መቀስቀሱ ተነግሯል።

በሰዓታት ውስጥ ከ3 ሺህ 800 ሄክታር በላይ መሬት የሸፈነው ይህ ሰደድ እሳት ነዋሪዎችን ከመኖሪያ ስፍራቸው እያፈናቀለ መሆምኑ ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎም 31 ሺህ ነዋሪዎች መኖሪያ ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ የተላለፈ ሲሆን ለ23 ሺህ ሰዎች ደግሞ በተጠንቀቅ ላይ እንዲሆኑ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

ደረቅ አየርና አደገኛ ንፋስ ለሰደድ እሳቱን መዛመት ምክንያት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ወደ ሌላ አካባቢ እንዳይስፋፋም ተሰግቷል።

በፍጥነት እየተስፋፋ ያለውን ሰደድ እሳት ለማስቆምም በርካታ የእሳት አደጋ መከላከያ አውሮፕላኖች እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ጥረት እያደረጉ መሆኑም ተገልጿል።

በሎስ አንጀለስ ከተማ እና አካባቢው ከ16 ቀናት በፊት ከተቀሰቀሰው እሳት ውስጥ ከባድ የተባሉት የኢቶንና ፓላሲደስ እሳቶች አሁንም እየነደዱ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል።

በሔለን ተስፋዬ

@Ethionews433 @Ethionews433


ምክር ቤቱ ዛሬ እያካሄደ ባለው መደበኛ ስብሰባው ሦስት ረቂቅ አዋጆችን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል

የህዝብ ተወካዮች ምክር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ሲሆን ሦስት ረቂቅ አዋጆችን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በዚህም የከተማ መሬት ይዞታ እና መሬት ነክ ንብረት ምዝገባ፣ የከተማ መሬትን በሊዝ ስለመያዝ የወጣ እና የአጠቃላይ ትምህርት ረቂቅ አዋጆች የተመራላቸው ቋሚ ኮሚቴዎች የሚያቀርቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ ምክር ቤቱ መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴርን የ2017 በጀት ዓመት የ6 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚያደምጥም ይጠበቃል።

እንዲሁም የኢትዮጵያ ህዝብ ዕምባ ጠባቂ ተቋም እጩ ዋና ዕምባ ጠባቂ፣ ምክትል ዕምባ ጠባቂ እና የዘርፍ ዕምባ ጠባቂ ሹመቶችን መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል።

@Ethionews433 @Ethionews433


ፈረንሳይ በበሽር አል አሳድ ላይ አዲስ የእስር ማዘዣ አወጣች

አሳድ በፈረንጆቹ 2017 በደራ ከተማ ንጹሃን ያለቁበት ጥቃት እንዲፈጸም በማዘዝ በጦር ወንጀል ተሳትፈዋል በሚል ነው የእስር ማዘዣው የወጣባቸው።

@Ethionews433 @Ethionews433


የደንበኞች ቁጥር እየበዛለት የሚገኘው ኔትፍሊክስ ዋጋ ለመጨመር ማቀዱ ተገልፆል

የደቡብ ኮሪያ ፊልም ስኩዊድ ጌም የተመዝጋቢዎችን ቁጥር ከፍ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጉንም ኔትፍሊክስ አስታውቋል።

ኔትፍሊክስ በ2024 ዓመት የመጨረሻ ወራት ወደ 19 ሚሊዮን የሚጠጉ ደምበኞችን ካፈሩ በኃላ የዋጋ ጭማሬ ለማድረግ አቅደው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። ኩባንያው በአሜሪካ፣ በካናዳ፣ በአርጀንቲና እና በፖርቱጋል የደንበኝነት ምዝገባ ወጪዎችን እንደሚጨምር ተናግሯል። ኔትፍሊክስን የበለጠ ለማሻሻል እንደገና ኢንቬስት ማድረግ እንድንችል አባሎቻችንን ትንሽ ተጨማሪ ክፍያ እንዲከፍሉ እንጠይቃለን ሲልም ኩባንያው ተናግሯል።

ኔትፍሊክስ በተከታታይ የደቡብ ኮሪያ ፊልም ስኩዊድ ጌም ታግዞ ከተጠበቀው በላይ የተመዝጋቢ ቁጥሮችን ማግኘቱ ያሳወቀ ሲሆን፤ ከዚህ በተጨማሪ በተፅእኖ ፈጣሪው ቦክሰኛ ጄክ ፖል እና በቀድሞው የዓለም የከባድ ሚዛን ሻምፒዮን ማይክ ታይሰን መካከል የተደረገውን የቦክስ ግጥሚያም ለአዳዲስ ተመዝጋቢዎች ቁጥር መጨመር የራሳቸውን አስተዋፅኦ አድርገዋል ተብሏል።

በአሜሪካ ውስጥ መደበኛ ምዝገባን ጨምሮ በሁሉም የኔትፍሊክስ አገልግሎቶች ላይ ዋጋ ይጨምራል የተባለ ሲሆን ይህም ዋጋውን በወር እስከ 17.99 ዶላር ያደርሰዋል። ኔትፍሊክስ በአሜሪካ ውስጥ ለመጨረሻ ጊዜ የዋጋ ጭማሪ ያደረገው ጥቅምት 2023 ነበር።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኩባንያው ባለፈው አመት በድምሩ ከ300 ሚሊዮን በላይ ተመዝጋቢዎችን ማግኘቱን ገልጿል። በጥቅምት እና ታኅሣሥ መካከል 9.6 ሚሊዮን አዳዲስ ተመዝጋቢዎችን ይጨምራል ተብሎ ይጠበቃል ነገር ግን ቁጥሩ እጅግ ከፍተኛ ነው ተብሏል።

በሚሊዮን ሙሴ

@Ethionews433 @Ethionews433

Показано 20 последних публикаций.