Natnael Mekonnen


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Политика


በቀጥታ መረጃዎችን ለመስጠት ሲፈልጉና ማስታወቂያ ማሰራት ከፈለጉ 👉 @NatnaelMekonnen7
Facebook.com/natnaelmekonnen.et
Instagram.com/natnaelmekonnen21

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Политика
Статистика
Фильтр публикаций


አዲሱ የትግራይ ክልል ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት በመሆን አዲስ የተሾሙት ሌ/ጄ ታደሰ ወረደ ለአቶ ጌታቸው ረዳ የምስጋና ሽልማት ለመሸለም ያደረጉትን ጥሪ ተከትሎ አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ህዝብ ቡዙ ጋቢ ሸልሞኛል የእናተን ጋቢ አልፈልግም በማለት በዝግጅቱ ላይ እንደማይገኙ አሳውቀዋል::


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
በዚህ ልክ ዋጋ ቀንሶ አያውቅም!

ሳር ቤት አፍሪካ ህብረት አጠገብ

አፓርታማ በ5.7 ሚሊዮን ብር ጠቅላላ ዋጋ

90 ካሬ

ባለ ሁለት መኝታ

ለ1 ሳምንት ብቻ የሚቆይ ዋጋ ነው

ፈጥነው ይደውሉ!

ለበለጠ መረጃ (direct/ Whatsapp):- በ 0987170752 ወይም 0987335552 ይደውሉ።

WhatsApp
https://wa.me/qr/AKFMHWJTIAY2D1

@Temerpropertie


በሶማሊያ የሴክተር አራት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ያሰለጠናቸውን የመሀንዲስ ሙያተኞች አስመረቀ።


ስልጠናው በአካባቢው በድጋፍ ሰጪነት ተሰማርተው ለሚገኙ የምስራቅ ዕዝ  የአንድ ኮር አባላት ከUNMAS ጋር በመተባበር  በንድፈ-ሀሳብ እና በተግባር የተሰጠ ነው።

ለሙያተኞቹ ሰርተ-ፊኬት የሰጡት የሴክተሩ ምክትል አዛዥ ብርጋዲየር ጄኔራል ሹመት ጠለለው ሙያተኞቹ ከስልጠናው ባገኙት እውቀት የተሰጣቸውን ተልእኮ በብቃት ሊወጡ እንደሚገባ ገልፀዋል።

በየጊዜው ቴክኖሎጂዎች እየተሻሻሉ በመጡ ቁጥር ብዙ አማራጮች ይኖራሉ ያሉት ጄኔራል መኮንኑ ከግዳጅ ቀጠናው ጋር ተያይዞ አልሻባብ በዋናነት የሚጠቀምባቸውን ፈንጆች በመለየት እና ፍተሻዎችን በማድረግ ጉዳት ሳያደርሱ ማስወገድ ቀዳሚው ተግባር እንደሆነ ተናግረዋል።

ሙያተኞችም ይህንኑ በመገንዘብ ችግሮች ከመከሰታቸው በፊት ቅድመ ፍተሻ እና ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባቸው አስረድተዋል። ስልጠናው በቀጣይነት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን እና በየጊዜው ሙያተኞችን በማፍራት ግዳጅን በስኬታማነት ለማከናወን ይሰራል ብለዋል።

የUNMAS አሰልጣኞች በበኩላቸው ሙያተኞች በስልጠናው ስለነበራቸው ጥሩ ስነ-ምግባር እና የመረዳት ብቃት አድናቆታቸውን ገልፀዋል።

መሰረታዊ ወታደር ወረታው ወንዴ እና መሰረታዊ ወታደር ምንተስኖት በቀለ ከስልጠናው ያገኙት እውቀት አልሻባብ የፍተሻ ቦታዎች ላይ ምን አይነት ፈንጆችን ነጣጥሎ ይዞ ሊገባ እንደሚችል እና ይዞ የገባቸውንም እንዴት ቀጣጥሎ በአካባቢው ላይ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል መንገዶቹን በማወቅ ቀደምተኝነትን ማትረፍ የሚቻልበትን መንገድ በስልጠና አውቀናል ብለዋል።


ካዛንቺስ ሳየይት ላይ የቤት ባለቤት ይሁኑ።
ጊዜው አሁን በማይታመን አጋጣሚ የቤት ባለቤት ይሁኑ

ከባለ 1 እስከ 4 መኝታ አፓርታማ ቤት መግዛት አሁን ነው ።

1. 20% ቅድመ ክፍያ
2. የሳይት አማራጭ
3. በ ኢትዮጵያ ብር
4, 60/40 የባንክ ብድር አግልግሎት

ዉጭ ሀገር ለምትኖሩ ዳስፖራዎች በህጋዊ ተወካይ በኩል መግዛት ትችላላችሁ።
የካሬ አማራጮች
45 ካሬ -169 ካሬ ድረስ

✅ እንዲሁም የስምንት ትርፋማ ድርጀቶች የአክስዮን ሽያጭ ላይ እንገኛለን::

ይደውሉ 0931283328


ከ100 በላይ የንግድ ማህበረሰብ አባላትን ያሳተፈው የኢትዮጵያ እና የሳዑዲ አረቢያ የንግድ ምክር ቤት የቢዝነስ ፎረም ተካሄደ

የኢትዮ-ሳዑዲ የጋራ ንግድ ም/ቤት የመጀመሪያ ስብሰባ እና የቢዝነስ ፎረም በሳዑዲ አረቢያ ዋና ከተማ ሪያድ ተካሄዷል።

ስብሰባው በኢትዮጵያ ወገን በኢፌዴሪ ንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አብዱልሃኪም ሙሉ ዶ/ር የተመራ ሲሆን የሳዑዲ አረቢያን ልኡካን የሳኡዲ አረቢያ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሃሰን ቢን ሙጂብ አልሁዋዚ መርተውታል።

በፎረሙ ላይ ከ100 በላይ የሁለቱ አገሮች የንግድ ማህበረሰብ አባላትን የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የተገኙ ሲሆን፥ በሁሉቱም አገሮች ለንግዱ ማህበረሰብ ያሉ መልካም እድሎችን በተመለከተ ገለጻዎች ተደርገዋል፥ በንግዱ ማህበረሰብ አባላት መካከልም የቢዝነስ ውይይቶች ተካሂደዋል።

በቢዝነስ ፎረሙ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አብዱልሃኪም ሙሉ ዶ/ር እኤአ በጁን 2024 በአዲስ አበባ የተቋቋመው የጋራ ንግድ ም/ቤት የሁለቱን አገራት ታሪካዊ እና ጂኦግራፊያዊ ቅርበትን እንደ እድል በመጠቀም ኢኮኖሚያዊ ትስስር ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን ጠቅሰው በኢትዮጵያ ሰፊ የንግድና የኢንቨስትመንት አማራጮች እንዳሉ በመግለፅ የሳዑዲ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

በተመሳሳይ በሳኡዲ አረቢያ የኢፌዴሪ ልዩ መልእክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሙክታር ከድር ዶ/ር የጋራ ንግድ ምክር ቤቱ ስራ መጀመርና የቢዝነስ ፎረሙ መካሄድ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትስስር እንደሚያጠብቅ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

አምባሳደር ሙክታር ጨምረውም በቀጣይ በግንቦት ወር 2017 በአዲስ አበባ በሚካሄደው ኢትዮጵያ ታምርትና ኢንቨስት እን ኢትዮጵያ መድረኮች የሳኡዲ አረቢያ ባለሀብቶች በስፋት እንዲሳተፉ ጥሪ ማስተላለፋቸውን ከኤንባሲው ያገኘነው መረጃ ያመልክታል።


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
❕❕ልዩ የሽያጭ መርሀግብር ከጊፍት ሪል ስቴት, ከአጓጊ ቅናሽ ጋር በለገሀር በ5% ቅድመ ክፍያ፣

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የጊፍት ሪል ስቴት አራተኛው መንደር ወይንም ስምንተኛው ሳይታችን በመሃል አዲስ አበባ በለገሃር መንደር፤ ዘመናዊ፣ ቅንጡ የመኖሪያ አፓርትማዎች ሽያጭ ተጀመረ.
⭐️የተለያዩ የቅናሽ አማራጮችን ይዞ
✅ ከ1-3 መኝታ
✅ ከ65-163ካሬ
✅ ከ5-10% ቅድመ ክፍያ
✅ በኢትዮጵያ ብር ብቻ

👉 ይህ ዘመናዊ መንደራችን በውስጡ

የጋራ መገልገያዎች
✔️ የመዋኛ ገንዳ
✔️የልጅ መጫወቻ ሜዳ
✔️ ደረጃውን የጠበቀ የእግር ኳስ ሜዳ
✔️ትምህርት ቤት እና  የህክምና ተቋም
✔️የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ (ጣቢያ)
✔️ሰፊ አረንጓዴ አካባቢ
✔️GYM፣የውበት ሳሎን፣ስፓ
✔️በቂ የመኪና ማቆሚያ ቦታ
✔️የራሱ የሆነ ቢዝነስ ሴንተር የያዘ ነው

ጊፍት ሪል እስቴት
"ማህበረሰብን እንገነባለን"

ለበለጠ መረጃ:-0955-744566


የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በኢትየጵያ አየር መንገድ ባለቤትነት ግንባታው እተከናወነ ባለው ፕሮጀክት፤ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ለሠራተኞች እና ለአካባቢው ማሕበረሰብ የምሳ ግብዣ መርሀ ግብር አካሄደ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ውል ወስዶ ግንባታው በፍጥነት በመካነወን ላይ ባለው የቢሾፍቱ ኢትየጵያ አየር መንገድ ፕሮጀክት ለሚሳተፉ ሠራተኞችና እና ለአካባቢው ማሕበረሰብ የምሳ ግብዣ መርሀ ግብር አካናውኗል፡፡

በመርሐ ግብሩ ላይ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ክቡር አቶ ረሻድ ከማል ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የፕሮጀክቱ አፈጻጸም ከተያዘለት የጊዜ ገደብ በፊት ማጠናቀቅ የሚያስችል እንደሆነም ነው ክቡር ዋና ሥራ አስፈጻሚው የተናገሩት፡፡

የፕሮጀክት ሳይቱን ሰራተኞችና የአካባቢውን ማሕበረሰብም ክቡር ዋና ሥራ አስፈጻሚው አበረታተዋል፡፡

ክቡር ዋና ሥራ አስፈጻሚው ኮርፖሬሽኑ ፕሮጀክቱን ከተያዘው ቀነ ገደብ በፊት ለማስረከብ ከቀኑ የሥራ ክፍለ ጊዜ በተጨማሪ በማታ ጭምር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ሳይት ሠራተኞች እና የፕሮጀክቱ ባለቤት የሆነው የአካባቢው ማሕበረሰብ ፕሮጀክቱ እንዲሰካ እያደረገ ያለውን ጠንከራ ሥራና ትብብር አጠናክሮ እንዲያስቀጥልም አሳስበዋል፡፡

ለአካባቢው ማሕበረሰብ ከ2ሺህ በላይ የሥራ እድል መፍጠር መቻሉን ነው ክቡር ዋና ሥራ አስፈሚው ያነሱት፡፡ የውሃ አቅርቦት እና የኢኮኖሚ ትስስር ለአካባቢው ማህበረሰብ በፕሮጀክቱ መፍጠሩንም ዋና ሥራ አስፈጻሚው ጠቁመዋል፡፡

የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር የዲባዩ ክፍለ ከተማ እና የዳካቦራ ወረዳ አስተዳዳሪ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ፕሮጀክቱ በአጭር ጊዜ እንዲጠናቀቅ ከተማ አስተዳደሩና ወረዳው ድጋፉን አጠንክሮ እንደሚቀጥል አመራሮቹ ተናግረዋል፡፡


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ጎጃም ውስጥ የበቀለ የጎጃም ጠላት

ጎጃም ውስጥ ያለ ፀረ አማራ ቡድን ትምህርትና ትምህርት ነክ የሆነ ነገር አምርሮ ይጠላል። ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በአማራ መምህራን ላይ የጅምላ ግድያ (Mass Murder) ፈፅሟል። አሁን ያ አልበቃ ብሎት ምስኪን መምህራንን እንደእንሰሳ አጎንብሳችሁ ሂዱ እያለ ያዋርዳል። አዋርዶም በቪዲዮ ቀርፆ ይለቃል። ይሄ ቡድን አማራን ከነፍሳቸው በሚጠሉ ሃይሎች የተቋቋመና የአማራን ክብር ለመግፈፍ የመጣ ለመሆኑ ትልቅ ማሳያ ነው።

አንድን ህዝብ ማድቀቅ ስትፈልግ የእውቀት ብርሃን የሆኑ መምህራንን ታጠፋለህ። የዘመነ ካሴ ቡድን በትክክል እየሰራ ያለው ይሄን ነው። በጅምላ የረሸናቸው መምህራን፣ አንድ ክፍል ውስጥ አጉሮ የጨፈጨፋቸው ተማሪዎችና የተማሪዎቹ ዘመዶች ለዚህ ምስክር ናቸው። የትኛው አለም ላይ ያለ ታጣቂ ነው ተማሪና አስተማሪን በጅምላ የረሸነ? የትኛው ታጣቂ ነው ሽማግሌዎችን ካህንን ጨምሮ በዳዴ እያስኬደ የተሳለቀ? የዚህ ቡድን ደጋፊዎች ይህንን እንዳያስተውሉ አዚም ያደረገባቸው ማን ነው?

ጎጃም የካህናት ሐገር ነች። ጎጃም የቅዱሳን ምድር ነች። ጎጃም የታቦታት ማደሪያ ነች። ጎጃም የአርበኞች መፍለቂያ ነች። ጎጃም የሀዲስ አለማየው የሊቃውንቱና የጠቢባኑ መፈጠሪያ ነች። ጥይት እንዳይመታኝ ብሎ የጅብ ቆዳ እጁ ላይ የሚያስርና ግልገል ጅብ ተሸክሞ የሚዞር የደንቆሮ መንጋ ጎጃምንም ሆነ አማራን ሊወክል አይችልም። ከሊቅ ሐገር ተፈጥሮ የጎጃም ሊቃውንትን ለምን ትምህርት አስተማርክ ብሎ የሚያሳድድና የሚያጠፋ ቡድን የጎጃም ጭንብል የለበሰ ጠላት እንጂ ጎጃሜ ሊሆን አይችልም።


የሱዳኑ መሪ ጄኔራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን ከቱርክ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

ጀነራሉ በቱርክ የልማት ፕሮጀክቶች፣ የሰብአዊ እርዳታ አሰጣጥ እና የአየር መንገድ አገልግሎትን እንደገና ማስጀመር ላይ ያተኮሩ ውይይቶች ከቱርኩ አምባሳደር ፋቲህ ይልዲዝ ጋር አካሂደዋል። በፖርት ሱዳን የተካሄደው ስብሰባ የሁለትዮሽ ግንኙነቱን በማጠናከር ላይ ያተኮረ ሲሆን ቡርሃን ከቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ጋር በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ያደረጉትን ውይይት መከታተላቸውን ባለስልጣናቱ ተናግረዋል።

የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ምክትል ሴክሬታሪ ሁሴን አል-አሚን በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንደተናገሩት ከሆነ ውይይቶቹ “የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ሂደት የሚያሻሽሉባቸው መንገዶች እና አንካራ በሱዳን በመጪው ጊዜ ውስጥ ልተገብራቸው ያቀደቻቸውን የልማት ፕሮጀክቶች” ያካተተ ነበር ተብሎለታል። ውይይቶቹ የሱዳን አየር መንገድ ከፖርት ሱዳን ወደ አንካራ በሰኔ ወር መጀመሪያ ላይ እንደገና ለመጀመር የታቀደውን በረራ ያካተቱ መሆኑ አል-አሚን አክለዋል።

ባለሥልጣናቱ ቱርክ በምትሰጠው ሰብዓዊ ዕርዳታ እና በተለዋጭ መንገዶች ወደ መካከለኛው እና ምዕራብ ሱዳን በቀጠለው ግጭት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸውን አካባቢዎች ዕርዳታ ለማድረስ በተደረገው ዝግጅት ላይ ተወያይተዋል። የምዕራብ ዳርፉር ክልል ውስብስብ የሆነ ሰብአዊ ቀውስ የተጋረጠበት ሲሆን እንደ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ግምት ከሆነ 79 በመቶ የሚሆነው ህዝብ በጦርነት እና በቀደሙት ግጭቶች ምክንያት እርዳታ እና ጥበቃ ያስፈልገዋል ብሏል።

እንደ አል-አሚን ገለጻ ቡርሃን ቱርክ ለሱዳን ያላትን ድጋፍ በአህጉራዊ እና አለም አቀፍ መድረኮች አወድሷል። በቅርቡ በለንደን በተካሄደው የሱዳን የሚኒስትሮች ኮንፈረንስ ላይ አንካራ ስለተሳተፈችበት መግለጫ አምባሳደር ይልዲዝ አመስግነዋል። በእንግሊዝ፣ በፈረንሳይ፣ በጀርመን እና በአውሮፓ ህብረት በሚያዝያ 15 ያዘጋጀው ጉባኤ ከ800 ሚሊዮን ዩሮ (850 ሚሊዮን ዶላር) በላይ ለሰብአዊ ርዳታ የተሰበሰበ ቢሆንም ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለማስቆም የሚያስችል ፖለቲካዊ መግባባት ላይ ግን አልደረሰም።

አምባሳደር ይልዲዝ ስብሰባው በኤፕሪል 12 ቡርሃን ወደ ቱርክ ያደረጉትን የአንታሊያ ዲፕሎማሲ መድረክ ከፕሬዚዳንት ኤርዶጋን ጋር የተገናኘበትን ውጤት መገምገሙን አረጋግጠዋል። ይልዲዝ እንደተናገሩት እነዚያ የከፍተኛ ደረጃ ውይይቶች የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ወደ አዲስ ደረጃ ያሸጋግሩታል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል።  የቱርክ አየር መንገድ ወደ ሱዳን ቀጥታ በረራ እንደሚጀምር እና የቱርክ ዚራአት ባንክ ቅርንጫፍ በፖርት ሱዳን እንደሚከፈት አስታውቋል። በካርቱም እና በአንካራ መካከል ያለው ግንኙነት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በከፍተኛ ደረጃ እያደገ መጥቷል። ኤርዶጋን ከዚህ ቀደም በሱዳን እና በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች መካከል ያለውን አለመግባባት ለመፍታት ሀሳብ አቅርበው ነበር።


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
❕❕ልዩ የሽያጭ መርሀግብር ከጊፍት ሪል ስቴት, ከአጓጊ ቅናሽ ጋር በለገሀር በ5% ቅድመ ክፍያ፣

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የጊፍት ሪል ስቴት አራተኛው መንደር ወይንም ስምንተኛው ሳይታችን በመሃል አዲስ አበባ በለገሃር መንደር፤ ዘመናዊ፣ ቅንጡ የመኖሪያ አፓርትማዎች ሽያጭ ተጀመረ.
⭐️የተለያዩ የቅናሽ አማራጮችን ይዞ
✅ ከ1-3 መኝታ
✅ ከ65-163ካሬ
✅ ከ5-10% ቅድመ ክፍያ
✅ በኢትዮጵያ ብር ብቻ

👉 ይህ ዘመናዊ መንደራችን በውስጡ

የጋራ መገልገያዎች
✔️ የመዋኛ ገንዳ
✔️የልጅ መጫወቻ ሜዳ
✔️ ደረጃውን የጠበቀ የእግር ኳስ ሜዳ
✔️ትምህርት ቤት እና  የህክምና ተቋም
✔️የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ (ጣቢያ)
✔️ሰፊ አረንጓዴ አካባቢ
✔️GYM፣የውበት ሳሎን፣ስፓ
✔️በቂ የመኪና ማቆሚያ ቦታ
✔️የራሱ የሆነ ቢዝነስ ሴንተር የያዘ ነው

ጊፍት ሪል እስቴት
"ማህበረሰብን እንገነባለን"

ለበለጠ መረጃ:-0955-744566


በፑንትላንድ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት የአልሸባብ ታጣቂዎች ሳይሆኑ አይቀሩም በተባሉ ታጣቂዎች ተገደሉ

በሱማሊያዋ ፑንትላንድ ራስ ገዝ የኢትዮጵያ ቆንስላ ውስጥ ተመድበው ይሠሩ የነበሩት ኢትዮጵያዊው ዲፕሎማት ፋራህ አይዲድ ጃማ ከሱማሌላንድ ራስ ገዝ በቅርቡ በተነጠለችው "ኤስ ኤስ ካቱሜ" ግዛት ላስ አኖድ ከተማ ውስጥ በጥይት ተመትተው ሕይወታቸው ማለፉን የሱማሊያ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

የግዛቲቷ ባለሥልጣናት፣ ግድያውን የፈጸሙት ለጊዜው ታጣቂዎች የአልሸባብ አባላት ሳይኾኑ አይቀርም የሚል ጥርጣሬ እንዳላቸው ዘገባዎቹ መባሉን ዳጉ ጆርናል ከዋዜማ ዘገባ ተመልክቷል። በዲፕሎማቱ ሕልፈት ዙሪያ የግዛቲቱ ባለሥልጣናት ምርመራ እያደረጉ እንደኾነ ተገልጧል።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር፣ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ በዲፕሎማቱ ሕልፈት ዙሪያ በይፋ ያለው ነገር የለም።

የሱማሊያ ፌደራል መንግሥት፣ ከሶማሌላንድ መገንጠል እንፈልጋለን ያሉ የጎሳ ሚሊሻዎች ከደም አፋሳሽ ውጊያ  በኋላ የመሠረቷትን "ኤስ ኤስ ካቱሜ" ግዛት፣ ባለፈው ሳምንት የፌደሬሽኑ አባል ግዛት አድርጎ መቀበሉን ማወጁ ይታወሳል።


ካዛንቺስ ሳየይት ላይ የቤት ባለቤት ይሁኑ።
ጊዜው አሁን በማይታመን አጋጣሚ የቤት ባለቤት ይሁኑ

ከባለ 1 እስከ 4 መኝታ አፓርታማ ቤት መግዛት አሁን ነው ።

1. 20% ቅድመ ክፍያ
2. የሳይት አማራጭ
3. በ ኢትዮጵያ ብር
4, 60/40 የባንክ ብድር አግልግሎት

ዉጭ ሀገር ለምትኖሩ ዳስፖራዎች በህጋዊ ተወካይ በኩል መግዛት ትችላላችሁ።
የካሬ አማራጮች
45 ካሬ -169 ካሬ ድረስ

✅ እንዲሁም የስምንት ትርፋማ ድርጀቶች የአክስዮን ሽያጭ ላይ እንገኛለን::

ይደውሉ 0931283328


አዲሱ ህግ ፀደቀ

ተራ አስከባሪ ግብር እንዲከፍሉ ተወሰነ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ የታክሲ ተራ አስከባሪ ማኅበራት ከገቢያቸው 20 በመቶውን ለመንግሥት እንዲሰጡ የሚያስገድድ ደንብ አጽድቋል።

ደንቡ ማኅበራቱ “ዝግ እና መደበኛ የባንክ አካውንት" እንዲከፍቱና ከሁለት ዓመት በኋላ “ወደ ሌላ የሥራ ዘርፍ እንዲሸጋገሩ” ግዴታ ይጥላል።

“የተርሚናል አገልግሎት አሠራርና ቁጥጥር” የተሰኘው ደንብ፣ ኢንተርፕራይዝ በማለት የሠየማቸው ማኅበራት የሚደራጁት በከተማዋ የሥራና ክህሎት ቢሮ መስፈርት መኾኑን ታውቋል።

ኢንተርፕራይዞቹ 30 በመቶ  “የግዴታ ቁጠባ” መቆጠብ፣ 50 በመቶውን በተንቀሳቃሽ የባንክ ሒሳብ ማስቀመጥና ያንድ ዓመት ውል መፈረም እንዳለባቸውም ይደነግጋል።


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
በዚህ ልክ ዋጋ ቀንሶ አያውቅም!

ሳር ቤት አፍሪካ ህብረት አጠገብ

አፓርታማ በ5.7 ሚሊዮን ብር ጠቅላላ ዋጋ

90 ካሬ

ባለ ሁለት መኝታ

ለ1 ሳምንት ብቻ የሚቆይ ዋጋ ነው

ፈጥነው ይደውሉ!

ለበለጠ መረጃ (direct/ Whatsapp):- በ 0987170752 ወይም 0987335552 ይደውሉ።

WhatsApp
https://wa.me/qr/AKFMHWJTIAY2D1

@Temerpropertie


ልዩ መረጃ‼️

በቁጥጥር ስር የዋለውን ኃይለ ሊባኖስ ኃይለሚካኤልን በሚመለከት በርካታ መረጃዎች እየተፈለፈሉ ነው።

በተገኘው መረጃ መሰረት ኃይለ ሊባኖስ የፈትለወርቅ ገብረእግዛብሔር (መንጆሪኖ) ባለቤት ነው። ግለሰቡ ከጦርነቱ በፊት በለንደን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አታሼ በመሆን ሲሰራ ቆይቷል። በዚህ ቆይታው ከሀገራዊ ስራ ይልቅ በዋናነት በህገ ወጥ ገንዘብ ዝውውር፣ ማዕድን ዝውውር እና ህገ ወጥ ጦር መሳርያን በአስፈፃሚዎቹ በኩል በማስተሌለፍ በርካታ ሚሊዮን ዶላሮችን ያፈራ ነው። ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላም ቢሆን መከላከያ ሰራዊት መቀሌን ለመቆጣጠር ባለበት ጊዜ 25 ኩንታል ወርቅ እና 300ሺ ዶላር በካሽ ይዞ ለንደን ገብቷል። ለዚህም ዶ/ር ደብረፅዮን እና መንጆሪኖ ተመካክረው “ህወሓትን ወክሎ እየተጓዘ መሆኑን እና ንብረቱም የህውሓት ነው” የሚል ደብዳቤ ፅፈውለት ነበር። እንደሚታወሰው የወርቅ ጉዳይ የሕወሓት ሰዎችን ብዙ ሲያባላ ቆይቷል። አሁን ፍንጭ የተገኘ ይመስላል።


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ጠሚ አቢይ እና የአዲስ አበባ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ክብርት ቀዳማዊ እመቤትን ጨምሮ የትንሳኤ በዓልን በኮሪደር ልማት ከካዛንችስ ወደ ገላን ጉራ ከተዘዋወሩት ነዋሪዎቻችን ጋር በዚህ መልኩ አክብረዋል


የትንሳኤ በዓል ከእሳትና መሰል አደጋዎች ተጠብቆ በሰላም ተከብሮ ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ

ኮሚሽኑ እንዳስታወቀው በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበረዉ የትንሳዔ በዓል እና ዋዜማው ከአደጋ ክስተት ተጠብቆ በሰላም ተከብሮ አልፏል ብሏል ።

ሆኖም በበዓሉ ዋዜማ በየካ ክፍለ-ከተማ ፈረንሳይ ጉራራ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በአንድ የምግብ ማብሰያ ክፍል ዉስጥ ቀላል የእሳት አደጋ ማጋጠሙን የኮሚሽኑ የህዝብ ገንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከበዓሉ ቀናት አስቀድሞ በከተማዉ በተመረጡ ቦታዎች በቋሚነትና በተንቀሳቃሽ እንዲሁም በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ሰፊ የግንባቤ ማስጨበጥና የጥንቃቄ መልዕክቶችን ሲያስተላልፍ መቆየቱን አስታውቋል።

በተከናወነው የቅድመ ጥንቃቄ ስራና 
ህብረተሰቡ የተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን በአግባቡ በመተግበሩ በአከባበር ሂደቱ አደጋዎች እንዳይፈጠሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል።ኮሚሽኑ ለህብረተሰቡና ለባለድርሻ አካላት እንዲሁም የጥንቃቄ መልዕክቶችን ለህብረተሰቡ በማድረስ ሚዲያዎች ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጾ ምስጋናዉን አቅርቧል።

ህብረተሰቡ በበዓላት ሰሞን ሲያደርጋቸዉ የነበሩትን የጥንቃቄ ተግባራት በመደበኛ እንቅስቃሴ ወቅትም እንዲተገብር ኮሚሽኑ አሳስቧል።


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
❕❕ልዩ የሽያጭ መርሀግብር ከጊፍት ሪል ስቴት, ከአጓጊ ቅናሽ ጋር በለገሀር በ5% ቅድመ ክፍያ፣

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የጊፍት ሪል ስቴት አራተኛው መንደር ወይንም ስምንተኛው ሳይታችን በመሃል አዲስ አበባ በለገሃር መንደር፤ ዘመናዊ፣ ቅንጡ የመኖሪያ አፓርትማዎች ሽያጭ ተጀመረ.
⭐️የተለያዩ የቅናሽ አማራጮችን ይዞ
✅ ከ1-3 መኝታ
✅ ከ65-163ካሬ
✅ ከ5-10% ቅድመ ክፍያ
✅ በኢትዮጵያ ብር ብቻ

👉 ይህ ዘመናዊ መንደራችን በውስጡ

የጋራ መገልገያዎች
✔️ የመዋኛ ገንዳ
✔️የልጅ መጫወቻ ሜዳ
✔️ ደረጃውን የጠበቀ የእግር ኳስ ሜዳ
✔️ትምህርት ቤት እና  የህክምና ተቋም
✔️የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ (ጣቢያ)
✔️ሰፊ አረንጓዴ አካባቢ
✔️GYM፣የውበት ሳሎን፣ስፓ
✔️በቂ የመኪና ማቆሚያ ቦታ
✔️የራሱ የሆነ ቢዝነስ ሴንተር የያዘ ነው

ጊፍት ሪል እስቴት
"ማህበረሰብን እንገነባለን"

ለበለጠ መረጃ:-0955-744566

Показано 18 последних публикаций.