👇👇የማይጠየቁ 12 ጥያቄዎች👇👇
ኧረ ሼም
1. እርቦኝ; ጠምቶኝ; ደክሞኝ ልክ ቤት ስገባ "መጣህ እንዴ ?" አትበሉኝ:: እንግዲህ እኔ እስከማውቀው ድረስ ስለመጣሁ ነው የታየኋችሁ ! ይልቅ የሚበላ የሚጠጣውን አቅርባችሁ ፈውሱኝ::😂
.
2.". ሰዓት ስንት ነው?" ስልህ "አሁን?" አትበለኝ::.ታዲያ መቼ
ሊሆን ይችላል?
ወይስ አቆጣጠሩን ስለማታውቅበት ጊዜ ለመፍጀት ነው!😂
.
3. 'Password'ህን ንገረኝ? አይባልም::
ከነገርኩህማ ምኑን password ሆነው ታዲያ?😂
.
4. ምን ልጋብዝህ? አይባልም::
ግብዣ በጋባዥ እንጂ በተጋባዥ ውሳኔ አይካሄድም! ሼም
ይዞኝ የወረደ ነገር እንዳዝ ፈልገህ ካልሆነ በስተቀር!😂
.
5. ለቅሶ ቤት ሄደህ የአሟሟቱን detail አትጠይቅ!
ማስተዛዘን እኮ ሀዘን ማረሳሳት እንጂ ማባባስ አይደለም::😂
፞
6· ጀለስሽ በታክሲ እየመጣ "የት ደርሰሀል" ብላቹት እየመጣው ነው አንድ 30 ደቂቃ… …… ሲል አናንተ "ቶሎ በል… ኧረ አፍጥነው " አይባልም ።ታከሲውን አይነዳው!! ወይስ ውስጥ እያለ ይሩጥ… ካላቹም ለታክሲው ሹፌር ነው ።😂
.
7. ሰላማዊ እንቅልፍ ተኝተህ ስምህን አስር ጊዜ ጠርቶ
ቀስቅሶህ ልክ ስትነቃ...
"ውይ! ተኝተሀል እንዴ?" የሚል ሰው አያበግናችሁም?
ባልተኛ ነው የቀሰቀስከኝ ታድያ ?😂
.
8. "የማትፈልገው እንትን አለህ?"
(ሲጀመር የማልፈልገው ነገር አይኖረኝም! ከኖረኝ በኋላ
እንደማልፈልገው ካወቅሁም እስካሁን እጥለው ነበር)😂
.
9. ሻወር ቤት ገብተህ አንዱ ያንኳኳና "Friend ጨርሰሻል?"
ይልሀል:: (ከጨረስኩ ምን እሰራለሁ?)😂
.
10. በር ሳንኳኳ ከውስጥ "ማነው?" እያለ ሊከፍት
የሚመጣ.ሰው ይገርመኛል!
ሌባ ብሆን "ሌባ ነኝ!" እንድለው ነው?
መክፈቱ ካልቀረ ማንስ ብሆን ምን ይጠቅመዋል?
"መጣሁ!" ማለት አይሻልም?😂
.
11. "አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ?" ብለህ አትጠይቅ! 'አንድ' ካልክ
እኮ በቃ "አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ?" ስትል ጥያቄህን
ጨረስክ::😂
.
12. ቂቅ ብለህ ዘንጠህ መጥተህ "አምሮብኛል አይደል?"
ብለህ ከነ መልሱ አትጠይቀኝ:: "አምሮብኛል?" የሚለው
ጥያቄ ብቻ ይበቃል:፡ "አይደል?"ን ከጨመርክ እኮ ሼም
ይዞኝ "አዎ" እንድል
እያስገደድከኝ ነው:: ወይም ደግሞ እንዳማረብህ አውቀሀል
ማለት ነው:: ታዲያ ለምን ታደርቀኛለህ ?😂😂😃😄😆
☆☆☆☆☆☆
@zizuman