“ ቢድዓ ነው “ የመሀይማን መደበቂያ
————
ብዙ ወሀቢዮች የሆነ ጠና የሚል ጥያቄ ስትጠይቃቸው ወይም በነርሱ ቁንፅል እውቀት መሰረት ያልደረሱበትን ነገር ስታነሳላቸው ቢድዐ ነው ብለው ይገላገላሉ
ለሞተ ሰው ቁርአን መቅራት
-----------------------
ሸይኽ ሰዒድ ሙስጠፋ ለሞተ ሰው ቁርአን መቅራት ይቻላልን ተብለው ተጠይቀው : “ ይህ አዲስ መጤ ተግባር ነው ፣ ማህበረሰባችን በዘልማድ የሚፈፅመው ተግባር ነው ፣ ብለው ምላሽ ሰጡ ። ይህን ምላሻቸውን ስሰማ ለተከታዮቻቸው አዘንኩኝ ፣ ይህን ፈትዋ የሚያዳምጠው ወገናችን ለሞተ ሰው ቁርአን መቅራት የሀበሻ ሱፊዮች የፈጠሩት ቢድዐ አድርጎ እንዲያስብ ነው ያደረጉት
እውነታው ግን ይህ ጉዳይ ከሰለፎቹ ከነ ኢማም አሽሻፊዒይ ፣ ኢማሙ አህመድ ዘመን ጀምሮ በዑለሞቻችን ብእር የተቃኘ ተግባር ነው ።
ሸይኽ ሙሀመድ ሀሚዲን
ሸይኹ ከሸይኽ ሰዒድ ሻል የሚያደርጋቸው “ ቁርአንን ለሞተ ሰው መቅራት “ በቀደምት ዑለሞች መካከል ልዩነት እንዳለበት ማመናቸውና በተለይም በሀንበሊይ መዝሀብ ለሞተ ሰው ቁርአን ቢቀራ ምንዳው እንደሚደርሰው መናገራቸው ነው ።
ከሸይኽ ሰዒድ ጋር የሚያመሳስላቸው ደግሞ “ ሰደቃ አድርጎ ለሞተ ሰው ቁርአን ማስቀራት “ እኛ ሀገር ብቻ የሚፈፀምና መጥፎ የሆነ ቢድዐ እንደሆነ መናገራቸው ነው ።
የሚገርማችሁ ይህ ተግባር አለም ላይ ባሉ መዝሀብን በሚከተሉ ሙስሊሞች ዘንድ የሚተገበር መሆኑ ነው ፣ ዑለሞቹም ፅድቅ ችረውት እየተተገበረ ያለው ነው ።
ሟች ቀብር ዘንድ ሄደው ቁርአን የሚቀሩ ሰዎችን በክፍያ መቅጠርን ሁላ የፈቀዱ ዑለሞች አሉ ፣ ከነዚህም መካከል 462 አመተ ሂጅራ ላይ ያረፉት ታላቁ የሻፊዒያ ዐሊም ቃዲ አል ሁሰይን አንዱ ናቸው ።ይህ ማለት ከዛሬ 900 አመት በፊት ማለት ነው ።
https://t.me/sufiyahlesuna