قَنَاةُ أَبِي هِبَةِاللهِ الأَثَرِيِّ الْحَبَشِيِّ(حسين إسماعيل )


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


ይህ ቻናል ቁርኣንና ሀድስን፣ [በሰለፎች አረዳድ] እንዲሁም የሰለፎች ንግግርና ምክሮችን እና የታማኝ የሱና ዑለማዎች አስተምሮቶች ፈታዋወች ሙሐደራዎች የሚለቀቅበት የሰለፉነ አስሷሊህ ዕምነት የሚብራራበት ቻናል ነው።
ይ ቀ ላ ቀ ሉ
https://t.me/Abu_hibetillah_Asselfiy
አስተያየትና እርማት ካላችሁ 👇
@Abu_Hibetillah_bot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций




🌸20ዎቹ የጥሩ ባል መገለጫዎች

🌺ጥሩ ትዳር መስርቶ መኖር የማንኛዋም ሴት ምኞት ነው፤የጥሩ ትዳር መሰረቱ ደሞ ጥሩ ባል ነው፣ከጥሩ ባል መገለጫዎች በጥቂቱ 👇👇

1/ በሁሉም ነገር አላህን ይፈራል

2/ ከሚስቱ ጋር በጥሩ ስነ-ምግባር ይኗኗራል

3/ በተቻለው ያክል ቃሉን ይሞላል

4/ ለሚስትና ለልጆቹ መልካም አርዓያ ይሆናል

5/ ንግግርና ተግባሩ አንድ ነው (አታላይ አይደለም)

6/ ሚስቱን ያከብራል ለሷ ያለውንም ፍቅር ይገልጻል

7/ ሸሪዓ የሰጣትን ሐቅ ይጠብቃል

8/ ዘመድና ቤተሰቦቿን ያከብራል

9/ በሆነ ባልሆነው አይጨቃጨቅም

10/ ትርፍ ቃል ከመናገር በመታቀብ በመልካም ንግግሮቹ ሚስቱን ያስደስታል

11/ ሚስቱ አላህን እንድትታዘዝና ዲኗን እንድታውቅ ይገፋፋል ያግዛታልም

12/ ስትደሰትም ይሁን ስትከፋ ስሜቷን ይጋራል

13/ ከሚስቱ ጋር በመተባበር ልጆቹን በኢስላማዊ አደብና እውቀት ቀርጾ ያሳድጋል

14/ ሚስቱ ጥሩ እንድትለብስለትና ጥሩ እንድትሸት እንደሚፈልገው ሁሉ እርሱም ከሷ ጋር ሲሆን ይሄን ያደርጋል የመላ ሰውነቱን ንጽህናም ይጠብቃል

15/ ቤቷን ሳትጎዳ ቤተሰቦቿን መጠየቅ ስትፈልግ ከመፍቀድም አልፎ የሚያስፈልጋትን ነገር እንደ አቅሙ ያሟላላታል

16/ ለቤቱ በቂ ወጪ ያደርጋል ለልጆቹና ለሱ በምታደርጋቸው ነገሮች ሁሉ ያመሰግናታል
ድምበር ሳያልፍ፥ አለባበሷን፣ ገጽታዋንና የምትሰራቸውን ምግቦች ያደንቃል

17/ በሁሉም ነገር ላይ እርጋታና ትዕግስትን ተላብሶ ይኖራል

18/ አለመግባባትና ግጭቶች ሲፈጠሩም ሚስቱን ለሷ በማዘን ችግሩን ለመፍታት ብዙ ነገሮችን በመተውና ቁጣውን ዋጥ በማድረግ መፍትሄ ይፈልጋል🌸

19/  ሸርጡን የጠበቀ ሒጃብ እንዲትለብስ ዲኗን እንዲትማር ይጥራል


20/  ለአኼራዋ ኸይር ስራ እንዲታበዛ ይመክራታል  ለሴቶች ትልቅ ክብር አለው ሴትን ማስለቀስ አይፈልግም ሴትን መበደል አይፈልግም ሚስቱን መክዳት አይፈልግም  በአጠቃላይ ጥሩ ባል በሁለ ነገር እንዲጠነክሩ ጥሩ ነገር እንዲኖራቸው ያማክራታል ያጠናክራታል ያዝንላታል የጀነት ሴት እንዲትሆን ይጥራል ዱአም ያረግላታል 🌷


📣 የሶላተል ኢክቲስቃዕ በደሴ ከተማ 📣
⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞⭞

በሃገሪቱና በሌሎች ከተሞች ላይ ዝናብ በመጥፋቱ ምክንያት እሁድ በሆጤ እስታዲየም እሁድ በጧት 01፡00 ሰአት ላይ የሶላት አልኢስቲስቃዕ ይሰገዳል ‼

ሁሉም ሰው እንዲገኝ በኡለማዎች ታዟል አላህ የሚጠቅምና በረካ ያለው ዝናብን እንዲለግሰንና ወንጀላችንንም ይቅር እንዲለን: እንዲታረቀን ዱአ እናደርጋለን እንድትገኙ አደራ።

ይህ ሱና በሌሎች ከተሞችም ቢደረግ ኸይር ነው እንላለን።

https://t.me/alruqyehsheriyeh


Репост из: الدعوة إلى التوحيد في مدينة الحربو(harbu)
اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎
አስደሳች ዜና !!


በአህሉ-ተውሂድ online የሴቶች አዳራሽ 💎
የሴትች ለሴቶች የነሲሃ ፕሮ ግራም !!


ዛሬ ጁሙዓ በኢትዩ ከምሽቱ 2:30 በቅርብ እርቀት ሁናችሁ ይጠብቁን !!

    መርከዝ  አህሉ ተውሂድ


ወደ አዳራሹ መቀላቀል የምፈልጉ ከታች ባለው username ➴➴➴➴
      
@Op_251
         @SofiyaAllsss

እህቶች ብቻ !! ሴት እና ወንድ ለመለየት🎤በድምፅ
  እህቶችን አናግሯቸው


ከአንድ በላይ ያገባ ሰው በሚስቶቹ አያያዝ ላይ ፍትሃዊ ሊሆን ይገባል። ይሄ ምርጫና ፍላጎት ሳይሆን ግዴታ ነው። ብዙዎች ላይ የሚታየው ግን ሁለተኛ ሲያገቡ የመጀመሪያዋን ይበድላሉ። እንዲያውም ከሷም አልፎ ልጆቿን ጭምር የሚበድል ብዙ ሰው አለ። እንዲህ አይነቱ አቀራረብ
1- ከአላህ ጋር ያጣላል። ኣኺራን ያበላሻል።
2- ልጆች አባታቸውን እንዲጠሉ፣ ከዚህም አልፎ ከተለያዩ ሴቶች የተገኙ ልጆች በመሀላቸው ጥላቻ እንዲነግስ ያደርጋል።

ስለዚህ በፍትህ ለማስተዳደር ቆፍጠን ያለ አቋም ይኑርህ። ይህንን ለማድረግ የምትልፈሰፈስ እና ወኔ የሚያጥርህ ከሆነ ይቅርብህ። ብዙ አስተዋይና ኃይለኛ የሚባል ወንድ ሳይቀር በአዲሷ ሚስቱ ጤነኛ ያልሆነ አቀራረብ በመረታት ዱንያ ኣኺራውን ሲያጠፋ ማየት በብዙ አካባቢ የተለመደ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor


➧የሚያምር ቂርአት

▪ሱረቱል በቀራ 1-16




ጀዋሌ

ፈራጅ እንደጠፋ እንዳለቀ ፍርዱ
አቅሜን እየነሳኝ ልቤ አንተን መውደዱ

ልርቅህ አስቤ ጓዜን ሳሰናዳ
ግዙፍ ሁኖ ታየኝ የመውደድህ  እዳ

እዳዬን ልከፍል አንተን ተከትዬ
ልሆን ካጠገብህ ሁሉን ነገር ጥዬ

ህ  በጣም ነው ምወድህ ልዩ ጓደኛዬ


👉የ ➊❽ ሰሃባዎች ቅፅል ስም (ረድየላሁ ዐንሁም አጅማዒን)

➊.➾አብደላህ ቢን አቢ ቁሃፋ ➛አቡበክር ሲዲቅ

➋ ➾ኡመር ቢን ኸጣብ ➛ፋሩቅ

➌.➾አሊይ ቢን አቢ ጣሊብ ➛አቡ ቱራብ

➍➾ኡስማን ቢን አፋን ➛ዘኑረይን

➎. ➾ኻሊድ ቢን ወሊድ ➛ስይፉ'ላሂል መስሉል

➏. ➾አቡ ዑበይደ ቢን ጀራህ ➛አሚኑል ኡማህ

➐➾ጀዕፈር ቢን አቢ ጣሊብ ➛አቡል መሳኪን

➑➾ሐምዛ ቢን አብዱልሙጠሊብ➛አሰዱ'ላህ

➒➾አማር ቢን ያሲር ➛አጠይቡ ሙጠይብ

➓.➾ዙበይር ቢን አዋም ➛ሀዋሪዩ ረሱል

❶❶.➾ሙስዓብ ቢን ኡመይር ➛ሰፊሩል ኢስላም

❶➋ ➾ቢላል ቢን ረባህ ➛ሙዐዚኑ ረሱል

❶➌ ➾ሁዘይፈቱል የማን ➛ሷሂቡ ስሪ ረሱሉ'ላህ

❶➍ ➾አምር ቢን አል ዓስ ➛ዳሂየቱል ኢስላም

❶➎➾ሙዐዊያህ ቢን አቡ ሱፍያን ➛ካቲቡ ወህየ ረሱል

❶➏➾ዘይድ ቢን ሐሪስ ➛ሁቡ ረሱል'ላህ

➊❼ ➾አብደላህ ቢን አባስ ➛ቱርጁማኑል ቁርዓን

➊❽➾ሃሳን ቢን ሳቢት ➛ሻዒሩ ረሱል


የአላህ መልካም የሆኑ ባሮች አንድን ሰው ሊወዱት አይችሉም አላህ እስከሚወደው ድረስ

አላህ የወደደው ከሆነ ነው መልካም የሆኑ ባሮቹ ያን ሰው እንዲወዱት የሚያረገው

የአላህን ውደታ ለማገኘት እንጣር
አላህ ከወደደን ጥሩ ሰዎች እኛን እንዲወዱን ያረጋል አላህ ተባረከ ወተአላ

አላህን ፈሪ የሆኑ ሰዎች የሚወዱት በመልካም በጥሩ ስሙን የሚያነሱት አላህ የወደደው ሲሆን ነው
አላህ ይውደደን ያሶድደንም


ለዚች እህታችን ንያ ያደረጋችሁ እህትና ወንድሞች ለአላህ የገባችሁን ቃላችሁን ብትሞሉ ንያችሁን ገቢ ያላደረጋችሁ ባረካለሁ ፊኩም


🌷ሴቶችን አደራ አደራዬን ተቀበሉ አሉ ነብዩ አለይሂ ሶላቱ ወሰላም
ከዚያም የባልና የሚስትን ሀቅ ጠቀሱ

🌾በእናንተ ላይ ሴቶች ያለባቸው ሀቅ ፍራሻችሁ ላይ የምትጠሉትን ሰው እንዳያወጡባችሁ
ያለ ፍቃዳችሁ የምትጠሉትን ሰው ቤታችሁ እንዳያስገቡ አሉ

🌺ሴት ልጅ ባሏ ቤት ከሌለ ሀጂ ነብይ ወንድ ቤት ልታስገባ አይፈቀድላትም ወንድ የለም ማለት አለባት እነዚህም የተጠቀሱትም ሆኑ ሌሎች በሴት ላይ ያለባትን ሀቅ መጠበቅ ግደታዋ ነው የባሏን ሀቅ መጠበቅ አለባት


🌷ሴቶች በእናንተ ላይ ያላቸው ሀቅ ደግሞ ጥሩን ልታለብሷቸውና ልትመግቧቸው ነው አሉ ነብዩ አለይሂ ሶላቱ ወሰላም

በሌላ ዘገባ ስትለብስ ልታለብሳት ስትመገብ ልትመግባትነው ብለዋል ነብዩ አለይሂ ሶላቱ ወሰላም

ሴቶች የባላቸው ሀቅ ምን እንደሆነ በማወቅ ሀቁን ለመጠበቅ መጣር አለባቸው ሀቁን ከማጉደል መጠንቀቅ አለባቸው ለጀሃነም የሚዳርግ ነገር ውስጥ ከመግባት መጠንቀቅ ያስፈልጋል

ወንዶችም በሚስት ላይ ያለባቸውን ሀቅ በማወቅ ሀቋን ለመጠበቅ መጣር ያስፈልጋል በተለይ እሷን ከማሰቃየት ከማስለቀስ ከመክዳት መራቅ አለበት ኢ ወረቢ ሴትን የሚበድል ወንድ በሴት ልጅ የሚጫወት ወንድ አላህን ሊፈራ ይገባል

ቢያንስ ባይጠቅማትኳ ሊበድላት አይገባም ጥሩ ሰው ሊሆን ይገባል
ነብዩ አለይሂ ሶላቱ ወሰላም ሴቶችን አደራ አደራዬን ተቀበሉ ያዙ ብለዋል

የነብዩን አደራ እንቀበል አላህ ሚስትን የሰጠው ሰው አይበድላት እሷ መጥፎ ከሆነችበት ወደ መጥፎ ተግባር አይግባ

🌸ሴቷም ባሏን አትበድል መጥፎ ከሆነባት ወደ መጥፎ ተግባር አትግባ አላህ ወደ ሚወደው ኸይር ነገር ትግባ
አኼራ የሚያበላሽ ነገር ውስጥ ከመግባት መራቅ ያስፈልጋል


በባል ላይ ባል መደረብ
~
አንዳንድ ሴቶች ከባላቸው ጋር ፍች ሳያፈፀም ሌላ ሰው "ያገባሉ"። ከባሏ በፍች እንዳልተለያየች እያወቀ የማይሆነውን "ኒካሕ አስሬያለሁ" ብሎ ከሌላ ሰው ሚስት ጋር በዝሙት የሚጨማለቅ ወንድ በተጨባጭ አለ። ይሄ ከባድ ጥፋት ነው። ፍቺ ባልተፈፀመበት ሁኔታ አንዲት ሴት ለሌላ ወንድ ፈፅሞ ሐላል አትሆንም።

ስለዚህ ከባሏ ጋር መኖር አቅቷት መለያየትና ሌላ ሰው ማግባት የፈለገች ሴት ከባሏ ፍቺ ማግኘት አለባት። እሱ ፈቃደኛ ካልሆነ ወይም ደግሞ ለረጅም ዘመን ከአገር ርቆ ሊገኝ ካልቻለ ጉዳዩን ፍርድ ቤት በማቅረብ በቀላሉ በቃዲ መጨረስ ይገባል። ይህ እስከሚሆን ድረስ ከሌላ ሰው ጋር ኒካሕ መፈፀም አይቻልም። ተደርጎም ከሆነ እንደ ኒካሕ ስለማይቆጠር ባስቸኳይ መለያየት ግድ ነው። ከዚህ ከሁለተኛው "ባል" ለመለያየት ፍቺ አያስፈልግም። ኒካሕ በሌለበት ፍች የለምና። የመጀመሪያው ኒካሕ ባልወረደበት ሌላኛው ኒካሕ ካለም አይቆጠርም። ስለዚህ ባለማወቅ ወይም በመዘናጋት በእንዲህ አይነት ነገር ውስጥ የወደቃችሁ ወገኖች ባስቸኳይ የማስተካከያ እርምጃ ውሰዱ።
=
የቴሌግራም ቻናል:-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor


የባልሽን ልብ መክፈቻ ቁልፍ ያስፈልግሻል

ይህ ቁልፍ ቻይና አታመርተውም ወይም ከሱቅ አትገዢውም

ቁልፉ የምታገኚው በሁለት አይነት መንገድ ነው

👉 አንደኛው  ምን እንደሚወድና  ምን እንደሚጠላ ምን አይነት ሴት እንድትሆኚለት እንደሚፈልግ እራስሽ ጠይቀሽው ከነገረሽ ቁልፉን በቀላሉ አግኝተሻል ማለት ነው

👉 ሁለተኛው ምን እንደሚወድና  ምን እንደሚጠላ ምን እንደሚያስደስተውና ምን እንደሚያስከፋው ባህሪውን ተከታተልሽ ቁልፉን ማግኘት ትቺያለሽ

👌 እህቴ በትዳርሽ ላይ ከባልሽ ውጪ ማንም ሊያስደስትሽ አይችልም

👌 አንቺን በትዳርሽ ደስተኛ ማድረግ የሚችለው ከአላህ ቀጥሎ ባልሽ ብቻና ብቻ ነው ይህ ማለት ባልሽ ከፍቶት ወይም ደብሮት አንቺ ደስተኛ ልትሆኚ አትቺይም ስለዚህ ያንቺን ደስታ የሱን ደስታ ተከትሎ ነው የሚመጣው ማለት ነው


👉 እናት አባትሽ ልጃቸው ስለሆንሽ ይፈወዱሻል

👉 ልጆችሽ እናታቸው ስለሆንሽ ይወዱሻል

👉 ወንድሞችሽና እህቶችሽ እህታቸው ስለሆንሽ ይወዱሻል


👌 ባልሽ ግን የሚወድሽ በባሂርሽ ልክ ነው ጥሩ ከሆንሽለት ይወድሻል መጥፎ ከሆንሽበት ይጠላሻል


👌 ግን ቤተሰቦችሽ ሁሉ ቢሰባሰቡ ባል ሊሆኑሽ አይችሉም


🔸ባልሽ ጋር የሚያኖርሽ ባህሪሽ ነው የሚያጣላሽም ባህሪሽ ነው

🔸 አትኩሪ ተናነሺለት ለባል ይቅርና ለተራ ሙስሊም መተናነስ በሸሪዓችን የታዘዝንበት ነገር ነው

👌 ለባልሽ መተናነስሽ ውርደት ሳይሆን ክብርሽ ነው


🌷ለትዳርሽ ከባልሽ በላይ አንቺ መጠንቀቅ አለብሽ ምክንያቱም አንቺ ብትሄጂ ያንቺን ቦታ ሌላ ሴት ልትሞላው ትችላለች የባልሽ ቦታ ግን ክፍት ሆኖ ሊቀርብሽ ወይም ሊቆይብሽ ይችላል

🌸ሴት ልጅ ከባልዋ ጋር ሀይልን ከተጠቀመች ትሸነፋለች ግን ሴትነትዋን ከተጠቀመች ሁሌም አሻናፊ ነች


🌸በሸሪያ ሴት ልጅን ማግባት በእድሜ አይደለም እድሜዋ ስላነስ አትመረጥም እንዲሁምም እድሜዋ ስለገፋም አትተውም።

🪴ሴት ልጅ የምት መረጠው በዲኗ ነው። ለዚህም በአቡ  ሁረይራ {ረዲየላሁ ዓንሁ} የተተላለፈዉን ሀዲስ እንመልከት፦

የአላህ መልዕክተኛ {ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም} እንዲህ ይላሉ፦ ሴት ልጅ ለአራት ነገራቶች ትታጫለች
1↝ለመልኳ
2↝ለገንዘቧ
3↝ለዘሯና
4↝ለዲኗ
ዲን ያላትን ያልመረጠ እጁ አመድ ይፈስ ብለዋል።

🌸መልካም ሴትስ ማናት? እሷ ማለት አላህ በቁርአኑ ያወሳትና በሱናም መልዕክተኛው{ሰለላሁ ዓይሂ ወሰለም} የጠቀሷት ናት!

وقال الله تعالى
فَالصَّالِحَاتُ قَانِتَاتٌ حَافِظَاتٌ لِلْغَيْبِ بِمَا حَفِظَ اللَّهُ
ከፍ ያለው አላህ እንዲህ ይላል፦
« መልካሞቹም ሴቶች (ለባሎቻቸው) ታዛዦች አላህ ባስጠበቀው ነገር ሩቅን ጠባቂዎች ናቸው፡፡»

የአላህ መልዕክተኛም ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም  እንዲህ ይላሉ፦

«ሴት ልጅ አምስት ወቅት ሶላቷን ከሰገደች፣ረመዳኗን ከፆመች፣ብልቷን ከጠበቀች ፣ባሏን ከታዘዘች በፈለግሺው የጀነት በር ግቢ ትባለለች»

የእድሜዋ መብለጥ መልካም ሴትን ለማግባት የሚከለክል ነገር አይደለም

🌸ታላቁ መልዕክተኛ ተምሳሌትነት  ሞዴል ናቸው ኸድጃን{ረዲየላሁ ዓንሃ} ሲያገቧት በእድሜ ትበልጣቸው ነበር

ከሰዎች እሳቸው ዘንድ ተወዳጅና ተፈቃሪም ነበረች   በሷም ነው ልጆችን ያገኙት  የዘር ምትካቸውም የቀጠለውም  በእሷ የልጅ ልጅ  በሀሰንና ሁሴን ነው {አላህ መልካም ስራዎቻቸውን ይውደድላቸው}

👉ወንድ ልጅ መልካም ሴትን ለማግባት እድሜዋ ሊከለክለው አይገባም

በዲን ጉዳይ ላይ የምታግዘው፣ የሚረጋጋባትን፣ የምትታዘዘው የምትንከባከውን    አላህ በቁርአን የጠቀሳትን አይነት ሊመርጥ ይገባል

وَمِنْ آيَاتِهِ أَنْ خَلَقَ لَكُمْ مِنْ أَنْفُسِكُمْ أَزْوَاجًا لِتَسْكُنُوا إِلَيْهَا وَجَعَلَ بَيْنَكُمْ مَوَدَّةً وَرَحْمَةً ۚ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَآيَاتٍ لِقَوْمٍ يَتَفَكَّرُونَ

🌷ለእናንተም ከነፍሶቻችሁ (ከጎሶቻችሁ) ሚስቶችን ወደእነርሱ ትረኩ ዘንድ መፍጠሩ፣ በመካከላችሁም ፍቅርንና እዝነትን ማድረጉ ከአስደናቂ ምልክቶቹ ነው፡፡ በዚህ ውስጥ ለሚያስተውሉ ሕዝቦች ተዓምራቶች አልሉ


መርሳና ውርጌሳ ውጫሌ ጋራው
ደሴና ኮምቦልቻ ጦሳ ተራራው

ከለላና ማሻ ወግዲና አቀስታ
ሻፊ ና ኩታበር ወገልጤና ተንታ

ጠረኑ ናፈቀኝ
#የወሎዎች ሽታ ....


Репост из: 🌏Abu Hafsua [አቡ ሐፍሷ]
~ ስላንተ ለሚያወሩት ሁሉ መልስ ሰጥተህ እራስህን አብራርተህ አትዘልቀውም። አንተነትህን እስኪረዱህ ድረስ ዝም በላቸው. ያውሩ። አንተም አትድከም ።

@AbuHafsuaImam


🌸ባልን መታዘዝ
➖➖➖➖
የሆነች ሴት ሸይኽ አልባኒይን እንዲህ ብላ ጠየቀቻቸዉ፦
የተከበሩ ሸይኽ ከማግባቴ በፊት ፆም እና የሌሊት ሶላት የማበዛ ከቁርአን አስገራሚ የሆነን ጥፍጥናን የማገኝ ሴት ነበርኩኝ አሁን ግን የኢባዳ ጥፍጥናን አጥቻለሁ ?

🌷ሸይኹል አልባኒይ እንዲህ አሏት፦
ከባልሽ ጋ  ያለሽ ትኩረት እንዴት ነዉ?

እሷም እኔ ስለ ቁርአን ስለ ፆም ስለ ሶላት ስለ ኢባዳ ጥፍጥና እየጠየኩህ አንተ ስለ ባሌ ትጠይቀኛለህ አለቻቸዉ!?

👉ሸይኹም`አይዋን እህት አንዳንድ ሴቶች የኢማንን ጥፍጥና የአምልኮን ጥፍጥና የኢባዳን ፋና እንዴት እንደማያገኙ ታዉቂያለሽን?

🌸የአሏህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦

"አንዲት ሴት የኢማንን ጥፍጥና አታገኝም የባሏን ሃቅ እስከምታደርስ ድረስ"
---------------
❒ صحيح الترغيب 1939📚


የጀነት የምትሆነውን የጀነትን ሴት አልነግራችሁምን አሉ ነብዩ አለይሂ ሶላቱ ወሰላም

ባሏን  ሲቆጣ እጇን እጁ ላይ አርጋ አንተ ሳትወድ አንተ ደስ ሳይልህ አንተ ከፍቶህ እንቅልፍ አይወስደኝም አፉ በለኝ ይቅርታ እያለይ ባሏን የምትማፀን ነች አሉ

የባሏን ደስታ ማየት የምትፈልግ ባሏን ታዛጅ ባሏን ከማስቆጣት የምትጠነቀቅ ከተቆጣም ደስ እንዲለው ይቅርታ በመጠየቅ የምትማፀነው ደስተኛ እንዲሆን ጥረት የምታረግ ይቺ መልካም የሆነች ሴት ነች ጀነት ለመግባትም ይከጀልላታል


መጥፎ ሴት ደግሞ ባሏን የማትታዘዝ ባሏን አዛ የምታረግ አመፀኛ ምክር የማሰማ ባሏን የምታስከፋ ለባሏ ክብር የሌላት ተሳዳቢ  አረመኔ የሆነ ባህሪ ያላት ይቺ አይነት ሴት ጀሃነም ይፈራላታል
የዚች አይነት በጣም መጥፎ  ሴት ከሆነች አላህ ይቆጣባታል


ነብዩ አለይሂ ሶላቱ ወሰላም እንዲህ አሉ

ሶስት አይነት ሰዎችን አላህ ዱአቸውን አይቀበላቸውም አሉ ከነዚያ ውስጥ አንዱ

መጥፎ ሚስት ያለችው ያልፈታት የሆነ አሉ ነብዩ አለይሂ ሶላቱ ወሰላም

በጣም መጥፎ ሴት ከሆነይ ምክር የማሰማ ሶብር ሲደረግላት ሲታዘንላት አሻፈረኝ የምትል አላህን የማፈራ ሸረኛ መጥፊ ከሆነይ ሊፈታት ይገባል ማለት ነው በነብዩ ሀዲስ መሰረት



አደራዬን ተቀበሉኝ የሴቶችን ነገር አደራ በኸይር ተኗኗሯቸው አሉ  ነብዩ አለይሂ ሶላቱ ወሰላም

በብዙ ሀዲሳቸው ሴቶችን በጥሩ ባህሪ እንዲንኗኗር አደራ ብለዋል ነብዩ አለይሂ ሶላቱ ወሰላም

ሴቶችም ጥሩ እንዲሆኑ ባላቸውን ታዛጅ እንዲሆኑ ባላቸውን ከማስከፋት እንዲጠነቀቁ አዘዋል

ደጋግ ቀደምቶች ስለሴቶቻቸው  ሲናገሩ

ባላቸውን ሲያናግሩ ልክ እናንተ ንጉስ የሀገር መሪ ባለስልጣን እንደምታናግሩት አይነት ነው በሙሉ አይናቸውኳ ቀጥ ብለው አያዩም ለባላቸው ካላቸው ክብር የተነሳ ይላሉ 


ለዛ ነው ነብዩ  ሰው ለፍጡር እንዲሰግድ ባዝ ኖሮ ሴት ልጅ  ለባሏ እንዲትሰግድ አዝ ነበረ ያሉት


" ካልከፈልሽኝ አልፈታም "


የሴቷን ሐቅ ሳይጠብቁና. ፣ ሲያስለቅሱና በገንዘቧ ያሻቸውን ሲያደርጉ ከርመው የከበደ ነገር ተፈጥሮ የፍቺ ነገር ሲነሳ
" ካልከፈልሺኝ ፣ ይሄን ያህል ካልሰጠሽኝ አልፈታም " የሚሉ ወሮ በሎች መኖራቸውን መስማት ይገርማል ! ያሳፍራል !

ኧረ አላህን ፍሩ ! የመጀመሪያው በደል አልበቃ ብሏችሁ እኒህን ደካሞች ዳግም ልታስለቅሱ ትንነሣላችሁ ! ኧረ አላህን ፍሩ! የምርም ወንዶች ሁኑ ...

አለያ ዋጋችሁን ታገኛላችሁ - ከአላህ ! ደካሞችን መበደል የመልስ ምት የሚችሉትን ጠንካሮች የመበደል ያህል የቀለለ አይደለምና ለነፍሳችሁም ቆይ ብላችሁ አስቡ !

ደሞም ቀብሩን እና አላህ ፊት መቆሙን አትርሱ !

https://t.me/Muhammedsirage

Показано 20 последних публикаций.