MADO NEWS


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


Your go-to source for the latest, most reliable news from Ethiopia and beyond! Get real-time updates, breaking stories, and insightful coverage from trusted sources. Stay ahead, stay informed, and never miss a beat! 📲
🔻ሼር በማድረግ እና ለወዳጆ በማጋራት ተባበሩን!

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri






በአዲስ አበባም ሆነ በዙሪያዋ በጦር መሣሪያ በመታገዝ ተደራጅተው የሚፈፀሙ ወንጀሎች የሉም ሲል የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይሉ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ እና ዙሪያዋ ያለው የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ  ነው ሲል  የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይሉ ገልፃል፡፡

የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት በአፈፃፀሙ ላይ ባካሄደው ግምገማ የአዲስ አበባ ከተማ እና ዙሪያዋ የፀጥታ ሁኔታ አስተማማኝ መሆኑን አረጋግጫለው ብሏል።

የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይል ታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በአዲስ አበባ ከተማና ዙሪያዋ ያለውን የፀጥታ ሁኔታን ገምግሞ በአጠቃላይ እንደ ሀገር በሁሉም ክልል በተቀናጀ መልኩ እየተሰራ ባለው የፀጥታ ስራ ከፍተኛ ውጤት መገኘቱን አንስቶ፤ በተለይም በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል በኮማንድ ፖስት እየተመራ በተከናወነ የፀጥታ ስራ  እና   በዙሪያዋ በተካሄደው ተከታታይ ኦፕሬሽን አሁን ላይ ህብረተሰቡን ስጋት ውስጥ የሚከቱ በጦር መሣሪያ በመታገዝ ተደራጅተው የሚፈፀሙ ወንጀሎች አለመኖራቸውን የፀጥታና ደኅንነት ጥምር ኃይሉ ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡

በተመሳሳይ በአዲስ አበባ ከተማና ዙሪያዋ የፀጥታ ሁኔታን አስተማማኝ ለማድረግ ተካሂዷል ባለው  ኦፕሬሽን በህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር፣ በኮንትሮባንድ፣ በህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር፣ በሀሰተኛ ሰነዶች፣ በእገታ እና በስርቆት ወንጀል ህብረተሰቡን ሲያማርሩ የነበሩ በርካታ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጥምር ኃይሉ አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም ሀገራችንን የአደገኛ ዕፅ ዝውውር መዳረሻ ለማድረግ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ በመግባት በአዲስ አበባ ከተማ ቤት ተከራይተው ሲሰሩ የነበሩ ስምንት የውጪ ሀገር ዜጎች እና አስራ አምስት ኢትዮጵያዊያን አምስት ኪሎ ኮኬይን አደገኛ ዕፅ፣ የሚዋጡ 189 የታሸገ ኮኬይን፣ የዕፁ ማሸጊያና መጠቅለያ ማሽን፣ የዕፁ መመዘኛ አነስተኛ ሚዛን እና በርካታ ዕፁን ለማሸግ ከሚያገለግሉ ቁሶች ጋር ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ጥምር ኃይሉ ገልጿል።

ታኀሣሥ 17 ቀን 2017 ዓ.ም
Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail (mailto:?subject=%E1%89%A0%E1%8A%A0%E1%8B%B2%E1%88%B5%20%E1%8A%A0%E1%89%A0%E1%89%A3%E1%88%9D%20%E1%88%86%E1%8A%90%20%E1%89%A0%E1%8B%99%E1%88%AA%E1%8B%AB%E1%8B%8B%20%E1%89%A0%E1%8C%A6%E1%88%AD%20%E1%88%98%E1%88%A3%E1%88%AA%E1%8B%AB%20%E1%89%A0%E1%88%98%E1%89%B3%E1%8C%88%E1%8B%9D%20%E1%89%B0%E1%8B%B0%E1%88%AB%E1%8C%85%E1%89%B0%E1%8B%8D%20%E1%8B%A8%E1%88%9A%E1%8D%88%E1%8D%80%E1%88%99%20%E1%8B%88%E1%8A%95%E1%8C%80%E1%88%8E%E1%89%BD%20%E1%8B%A8%E1%88%89%E1%88%9D%20%E1%88%B2%E1%88%8D%C2%A0%20%E1%8B%A8%E1%8D%80%E1%8C%A5%E1%89%B3%E1%8A%93%20%E1%8B%B0%E1%8A%85%E1%8A%95%E1%8A%90%E1%89%B5%20%E1%8C%A5%E1%88%9D%E1%88%AD%20%E1%8A%83%E1%8B%AD%E1%88%89%C2%A0%C2%A0%20%E1%8A%A0%E1%88%B5%E1%89%B3%E1%8B%88%E1%89%80%E1%8D%A1%E1%8D%A1&body=Hey%20check%20this%20out:%20https%3A%2F%2Fethiofm107.com%2F2024%2F12%2F26%2F%25e1%2589%25a0%25e1%258a%25a0%25e1%258b%25b2%25e1%2588%25b5-%25e1%258a%25a0%25e1%2589%25a0%25e1%2589%25a3%25e1%2588%259d-%25e1%2588%2586%25e1%258a%2590-%25e1%2589%25a0%25e1%258b%2599%25e1%2588%25aa%25e1%258b%25ab%25e1%258b%258b-%25e1%2589%25a0%25e1%258c%25a6%25e1%2588%25ad-%25e1%2588%2598%25e1%2588%25a3%25e1%2588%25aa%2F)

via Ethio FM 107.8 (author: Ethio Admin)


በአራት ግለሰቦች ላይ የእገታ ተግባር በመፈፀም እስከ 1 ሚሊዮን ብር የጠየቁ አምስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አምስቱ ተከሳሾች ታህሳስ 2 ቀን 2017 ዓ.ም ቶርበናሼ ሸበል አቦ የተባለ ስፍራ ነዋሪ የሆኑ አራት ግለሰቦችን አግተው ወደ ፊቼ ከተማ በማምጣት በድብቅ አግተው አስቀምጠዋል።

ተከሳሾቹ አንደኛ በለው ተሾመ ፣ ሁለተኛ አቡ መገርሳ፣ ሶስተኛ አማረ መገርሳ ፣ አራተኛ አቡ ፍቃዱ የተባሉ ሲሆን አምስተኛው ለጊዜው ስሙ ያልተገለፀ ግለሰብ ሆነው ቅንጅት ፈጥረው አራት ግለሰቦች አግተው ሙውሰዳቸውን የፊቼ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ፅህፈት ቤት ኃላፊ ኢኒስፔክተር ታምሩ ባይሳ ገልፀዋል። አግተው ካስቀመጧቸው በኋላ ለቤተሰቦቻቸው በመደወል ከ500ሺህ እስከ 1ሚሊየን ብር ጠይቀዋል።

ፖሊስ የአራቱን ግለሰቦች መታገት ከቤተሰቦቻቸው በደረሰው መረጃ መሠረት ክትትል በማድረግ አጋቾቹ የጠየቁትን ብር ሳያገኙ እና ያገቷቸው ግለሰቦች ላይ ጉዳት ሳያደርሱ በተደረገ የረቀቀ ክትትል በድርጊቱ ፈፃሚዎችን በቁጥጥር በማዋል የታገቱትን አራትም ግለሰቦች በማስለቀቅ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ ተደርጓል።በፊቼ ከተማ እና አካባቢው በተለያየ ጊዜያት የተለያዩ ግለሰቦች በሀሰት ታግተናል በማለት ቤተሰቦቻቸውን በማስጨነቅ ከፍተኛ ብር በመጠየቅ የማታለል እና የማጭበርበር ወንጀል ይፈፅሙ እንደነበር ያነሱት ኢንስፔክተር ታምሩ ባይሳ አንዳንድ ግለሰቦች ይህንን ተግባር እንደ አንድ የገቢ ማስገኛ አድርገው በመንቀሳቀስ ላይ በመሆናቸው ማህበረሰቡ ከምንጊዜውም በላይ ከፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ እንዲሰራ አሳስበዋል።


የድሬዳዋ ስታድየም የፊፋን ሙሉ ፍቃድ እየጠበቀ ነው

ኢትዮጵያ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) መስፈርት ያሟላ ስቴድየም ባለማዘጋጀቷ ዋናው የወንዶች ብሔራዊ ቡድን ባለፉት አራት ዓመታት ዓለም አቀፍ ጨዋታዎቹን በገለልተኛ ሀገር ለማድረግ መገደዱ ይታወቃል፡፡ በተለያዩ ክልሎችና ከተሞች የተገነቡና እየተገነቡ የሚገኙ በርካታ ስቴድየሞች ቢኖሩም የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳው ሳር ካፍና ፊፋ በሚፈልጉት ደረጃ አለመገኘቱ ትልቁ ችግር ሆኖ ዘልቋል፡፡

ይህን የካፍና የፊፋ ጥያቄ ይመልሳል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት በእድሳት ላይ የሚገኘው አንጋፋው የአዲስ አበባ ስታዲየም ነው፡፡ ይሁን እንጂ የዚህ ስታድየም የመጫወቻ ሜዳና ሌሎች ከእድሳቱ ጋር በተያያዘ ምክንያት አሁንም ድረስ አገልግሎት ለመስጠት ። የብሄራዊ ስታዲየም ግንባታም ቢሆን በታቀደለት ጊዜ መጠናቀቅ አልቻለም፡፡

የባህር ዳር ስታዲየም የካፍን ግብረመልስ መሠረት አድርጎ የመጫወቻ ሜዳው በሚፈለገው መስፈርት መሠረት እንዲሠራ ለማድረግ አበረታችና ተስፋ ሰጪ ጥረት እየተደረገበት ይገኛል፡፡

የእነዚህ ስታድየሞች ግንባታና የመጫወቻ ሜዳ ጉዳይ ችግር መች እልባት ያገኛል ለሚለው ጥያቄ አሁንም ድረስ ቁርጥ ያለ መልስ ማግኘት አይቻልም፡፡ ዋልያዎቹን በቅርቡ ከስደት ይታደጋል ተብሎ የተሻለ ተስፋ የተደረገበት አንድ ስታድየም ግን ከወደ ምስራቅ ተገኝቷል፡፡

50 ዓመታትን ያስቆጠረው አንጋፋው የድሬዳዋ ስታዲየም እድሳትና የመጫወቻ ሜዳው ሰው ሠራሽ ሳር የማልበስ ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ቀደም ሲል ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያን ፕሪምየር ሊግ ከ1ኛ እስከ 11ኛ ሳምንት ሲያስተናግድ የቆየው የድሬዳዋ ስታድየም የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጨዋታዎችን ደረጃቸውን በጠበቀ መንገድ እንዲያስተናግድ ነው እየተሠራ የሚገኘው፡፡ 50 ሚሊዮን ብር የወጣበት የመጫወቻ ሜዳው ሥራ ካለፈው ዓመት አንስቶ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎችን ሲያስተናግድ ቆይቷል፡፡

የመጫወቻ ሜዳው ለሶስት ዓመት የዓለምን እግር ኳስ በበላይነት በሚመራው ፊፋ መስፈርት ማረጋገጫ ማግኘቱ ከተገለፀ ሰንብቷል፡፡ አሁን ደግሞ ስታድየሙ ቀሪ የእድሳት ሥራዎቹን አጠናቆ ሙሉ ፈቃድ ለማግኘት እየጠባበቀ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡ ስታዲዮሙን ኢትዮጵያ ለማስተናገድ ላቀደችው የ2029 አፍሪካ ዋንጫ ከወዲሁ ዝግጁ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ቢሮ አሳውቋል።

የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ሰሞኑን በስታዲየሙ ተገኝተው ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት እንደ ተጠቆመው፣ የድሬዳዋ ስታድየም አራት የመልበሻ ክፍሎች፣ የማሳጅ ክፍል፣ ሱቆች፣ ግዙፍ ስክሪን፣ ፋርማሲዎች፣ ባንኮች እና ሌሎች አገልግሎቶችን ፊፋ በሰጠው የማስተካከያ ግብረመልስ መሠረት በማካተት ተገንብቶ ተጠናቋል።

በጉብኝቱ ወቅት እንደተገለፀው፣ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ለስፖርት ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የስታዲየሙ እድሳት ዓለም አቀፍ መስፈርት እንዲያሟላ ከማድረግ በተጨማሪ በተለያዩ ስፖርቶች ብቁ ስፖርተኞችን ለማፍራት የሚያስችል የስፖርት አካዳሚ በመገንባት ላይ ይገኛል፡፡ የአካዳሚው ግንባታ ሂደትም 92 ከመቶ የደረሰ ሲሆን፤ የሜካኒካል ሥራዎች ብቻ እንደሚቀረው በሚኒስትሯ የተመራው ልኡክ ሥፍራው ላይ ተገኝቶ ምልከታ ባደረገበት ወቅት ተገልጿል።

አካዳሚው የውሃ ዋና ገንዳ፣ የእግር ኳስ መጫወቻ ሜዳ፣ የሜዳ ቴንስ፣ ጂምናዚየም፣ የሠልጣኞች መኖሪያ ክፍሎች፣ የመመገቢያና የስብሰባ አዳራሾች፣ ቤተመጽሃፍት እንዲሁም አንፊ ቴአትር በውስጡ የሚይዝ ይሆናል።

በምልከታው ወቅትም የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስትሯ ሸዊት ሻንካ፤ የስፖርት መሠረተ ልማት ላይ የከተማው ከንቲባ ለሰጡት ትኩረት እና እየተገነቡ ለሚገኙ ፕሮጀክቶች ምስጋናቸውን ገልፀዋል፡፡ ትውልድን ለማነጽና ሀገርን ለመገንባት መሰል መሠረተ ልማቶች ያስፈልጋሉ ያሉት ሚኒስትሯ፣ እነዚህ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችም ተጠናቀው አገልግሎት ወደመስጠት መግባት እንደሚ ኖርባቸው አሳስበዋል።

ብርሃን ፈይሳ

አዲስ ዘመን ሐሙስ ታኅሣሥ 17 ቀን 2017 ዓ.ም

via የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት


የቀድሞ የሶሪያ አማጺዎች ተዋህደው በመከላከያ ሚኒስቴር ስር ለመሆን መስማማታቸው ተገለጸ

የሶሪያ አማጺያን በጥቂት ቀናት ውስጥ በፈጸሙት መብረቃዊ ጥቃት ደማስቆን በመቆጣጠር የበሸር አላሳድ ቤተሰባዊ አገዛዝ እንዲያከትም አድርገዋል

via جديد አል ዐይን ኒውስ




#NewAlert
አንጋፋው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በመንግስት መታገዱን ዋዜማ ሰምታለች። የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ኢሰመጉን ያገደው፣ ከተቋቋመለት ዓላማ ውጭ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ያደርጋል በማለት ነው። የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች በአመራሮቹና ሠራተኞቹ ላይ ማስፈራሪያና ዛቻ እንደሚፈጽሙ ለበርካታ ወራት ሲገልጽ የቆየው ኢሰመጉ፣ ዋና ዳይሬክተሩ ዳን ይርጋ በዚኹ ዛቻና ማስፈራሪያ ሳቢያ ከአገር ለመሰደድ እንደተገደዱ በቅርቡ መግለጡ ይታወሳል። ባለሥልጣኑ በዲሞክራሲና መብቶች ዕድገት ማዕከል እና ጠበቆች ለሰብዓዊ መብቶች በተሰኙት ሲቪል ማኅበራት ላይ ባለፈው ኅዳር ወር በተመሳሳይ ምክንያት ጥሎት የነበረውን እገዳ ካነሳ በኋላ፣ ድርጅቶች የተሰጧቸውን የማስተካከያ ርምጃዎቾ ተግባራዊ አላደረጉም፤ ይልቁንም የቀድሞ ጥፋታቸውን ቀጥለውበታል በማለት በቅርቡ በድጋሚ እንዳገዳቸው አይዘነጋም። [ዋዜማ]


በ አዲስ አበባ ከ ኤሌክትሪክ መስመር ጥገና ጋር በተያያዘ ሃይል የሚቋረጥባቸው ቦታዎች።

ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዘዋል።


በትግራይ ኤችአይቪ ኤድስ ከጦርነቱ በኋላ አሻቅቧል

‘በትግራይ፣ የኤይድስ ሥርጭትን መከላከል እና መግታት’ በሚል ርእስ ከሰሞኑ አንድ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ተከናውኗ፡፡ በርቀት መገናኛ በተከናወነው ጉባዔ ላይ ከደቡብ ካሮላይና፣ መቀሌ እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች የተወከሉ ተመራማሪዎች ጥናታዊ ጽሑፎች አቅርበዋል። በጥናታቸውም፣ ትግራይ ክልል ውስጥ ጦርነት ከመቀስቀሱ አስቀድሞ የነበረው የበሽታው ስርጭት ፣ ከጦርነቱ በኃላ በእጅጉ ማሻቀቡን አመላክተዋል። የቪኦኤ ትግርኛ ክፍል ባልደረባ በትረ ስልጣን ያሰናዳውን ዘገባ ሀብታሙ ስዩም ያቀርብልናል።

via የአሜሪካ ድምፅ (author: voadigital@voanews.com (በትረ ሥልጣን, ሀብታሙ ስዩም))


የኤርትራው ባለሥልጣን የቢቢሲውን ዘገባ “ሃስት” ሲሉ ገለጹ

የቢቢሲ ሶማሊኛ ቋንቋ አገልግሎት፣ አብዱልቃድር ኢድሪስ የተባሉና ‘በኤርትራ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካና ሶማሊያ ጉዳዮች አማካሪ’ መሆናቸው የተገለጸ ባለሥልጣን በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል አንካራ ላይ የተደረሰው ሥምምነት እንደሚያሳስባቸው ገልጸዋል የሚል ዘገባ ማውጣቱን ተከትሎ፣ የኤርትራው ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገ/መስቀል "በተጠቀሰው ስም የሚጠሩ ባለሥልጣንም ሆነ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የተባለው ቢሮ አለመኖሩን" ለቪኦኤ አፍሪካ ቀንድ አስታውቀዋል። ቢቢሲ ሶማሊኛ ባለሥልጣኑ “ኢትዮጵያ የምትሻው የባሕር ኅይል መሠረት እንጂ የባሕር አቅርቦት አይደለም” ሲሉ መናገራቸውን ጠቅሷል። “ሶማሊያ ለኢትዮጵያ የባሕር መሠረት የምትሰጥ ከሆነ፣ ኤርትራ ከሶማሊያ ጋራ ያላትን ግንኙነት እንደገና ታጤናለች” ሲሉ አብዱልቃድር ኢድሪስ የተባሉት ባለሥልጣን...

via የአሜሪካ ድምፅ (author: voadigital@voanews.com (ቪኦኤ ዜና))


ዋሊያዎቹ በደርሶ መልስ ጨዋታ በሱዳን አቻቸው ተሸነፉ

ታሕሣሥ 16/2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) የመጨረሻ ዙር ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን በሱዳን 2 ለ 1 ተሸነፈ፡፡ ጨዋታው ዛሬ 11 ሠዓት ላይ በሊቢያ ቤንጋዚ ቤኒና…

The post ዋሊያዎቹ በደርሶ መልስ ጨዋታ በሱዳን አቻቸው ተሸነፉ appeared first on .

via https://waltainfo.com/am/feed/ (author: Helen Tadesse)


የየመን አማፂያን ሚሳዬል ወደ ቴል አቪቭ አስወነጨፉ

የየመን አማፂያን ወደ ቴል አቪቭ፣ እስራኤል ዛሬ ረቡዕ ሚሳዬል ማስወንጨፋቸውን አስታውቀዋል። ጥቃቱ የአደጋ ማስጠንቀቂያ እንዲደወል ሲያደርግ፣ ጉዳት ግን አላደረሰም ተብሏል። የእስራኤል ሠራዊት በበኩሉ ሚሳዬሉ ድንበር ከማቋረጡ በፊት መመታቱን አስታውቋል። ሁቲዎች ሚሳዬል ሲያስወነጭፉ በሁለት ቀናት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው። በጋዝ ሰርጥ እስራኤል በምታካሂደው ጦርነት ከፍልስጤማውያን ጋራ ያላቸውን አንድነት ለማሳየት እንደሆነ የሁቲ አማጺያን አስታውቀዋል። በእስራኤል ላይ ሚሳዬል ከማስወንጨፍ በተጨማሪ፣ ሁቲዎች በቀይ ባሕር እና በኤደን ባሕረ ሰላጤ በሚተላለፉ መርከቦች ላይ ጥቃት በመፈጸማቸው ቁልፍ የሆነው የንግድ መርከቦች መተላለፊያ ተስተጓጉሏል። የእስራኤል ባለሥልጣናት በበኩላቸው በኢራን በሚደገፉት ሁቲዎች ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ በመዛት ላይ...

via የአሜሪካ ድምፅ (author: voadigital@voanews.com (ቪኦኤ ዜና))


የሶማሊያዉ ፕሬዝዳንት ወደ አስመራ መጓዛቸዉ ተነገረ

የሶማሊያዉ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ማህሙድ   ለይፋዊ የስራ  ጉብኝት ኤርትራ መግባታቸዉ ታዉቋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ  አስምራ ሲደርሱም በአገሪቱ ፕሬዝዳንት አቀባበል ተደርጎላቸዋል ተብሏል፡፡

መሪዎቹ  በሁለቱ አገራት፤በቀቀጠናዉና በአለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪይ እንደሚመክሩ    ታዉቋል፡፡

ሶማሊያ ልዑኳን ወደ አዲስ አበባ መላኳ የሚታወስ ነዉ፡

አባቱ መረቀ

ታኀሣሥ 16 ቀን 2017 ዓ.ም

via Ethio FM 107.8 (author: Ethio Admin)




የሩሲያ መርከብ በሜዲትራኒያን ባህር መስጠሟን የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ

መርከቧ ሁለት ግዙፍ የወደብ ክሬኖችን ይዛ ወደ የሩሲያዋ ሩቅ ምስራቅ ወደብ ቭላዲቮስቶክ እያመራች ነበር ተብሏል

via جديد አል ዐይን ኒውስ


በሶሪያ የገና ዛፍ መቃጠሉን ተከትሎ የክርስትና እምነት ተከታዮች ለተቃውሞ አደባባይ ወጡ

ተቃዋሚዎቹ አዲሱ በመቋቋም ላይ የሚገኘው መንግስት አነሳ ቁጥር ላላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ጥበቃ እንዲያደርግ ጠይቀዋል

via جديد አል ዐይን ኒውስ







20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.