የቁርአን ሱራህ►⁵
አላህ ራሱ ነው ቁርአንን ከፋፍሎ ያወረደው፦
وَقُرْآنًا فَرَقْنَاهُ لِتَقْرَأَهُ عَلَى النَّاسِ عَلَىٰ مُكْثٍ وَنَزَّلْنَاهُ تَنزِيلًا
►📗[ሱረቱ አል-ኢስራእ 17፤106]
ቁርኣንንም በሰዎች ላይ በዝግታ ላይ ኾነህ ታነበው ዘንድ ከፋፈልነው፡፡ ቀስ በቀስ ማውረድንም አወረድነው፡፡
ቁርአን ሱራ እንዳለው አላህ በቁርአን ላይ ነግሮናል፦
سُورَةٌ أَنزَلْنَاهَا وَفَرَضْنَاهَا وَأَنزَلْنَا فِيهَا آيَاتٍ بَيِّنَاتٍ لَّعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ
►📗[ሱረት አል-ኑር24፤1]
(ይህች) ያወረድናትና የደነገግናት ሱራ (ምዕራፍ) ናት፡፡ በእርሷም ውስጥ ትገሰፁ ዘንድ ግልጾችን አንቀጾች አውርደናል፡፡
ሱራህ ሁለት፦► ሱረቱል በቀራህ፦~بقرة~
በቀራህ ማለት ጊደር (ላም)ማለት ነው።
قَالُوا ادْعُ لَنَا رَبَّكَ يُبَيِّن لَّنَا مَا هِيَ ۚ قَالَ إِنَّهُ يَقُولُ إِنَّهَا بَقَرَةٌ لَّا فَارِضٌ وَلَا بِكْرٌ عَوَانٌ بَيْنَ ذَٰلِكَ ۖ فَافْعَلُوا مَا تُؤْمَرُونَ
►📗[አል-በቀራህ 2፤68]
«ለኛ ጌታህን ጠይቅልን፤ እርሷ ምን እንደኾነች (ዕድሜዋን) ያብራራልን» አሉ፡፡ «እርሱ እርሷ ያላረጀች ጥጃም ያልኾነች በዚህ መካከል ልከኛ የኾነች ጊደር ናት ይላችኋል፤ የታዘዛችሁትንም ሥሩ» አላቸው፡፡
አንቀጹ ላይ بَقَرَةٌ በቀራህ የሚል ቃል አለ ስለዚህ ስሙ እዛው ሱረቱል በቀራህ ላይ አለ ማለት ነው።
ታዲያ ይህንን ስያሜ ነብያችንصلى الله عليه وسلم እና ሰሀቦች ተጠቅመውበታል? አው በሚገባ፦
عَنْ أَبِي مَسْعُودٍ الْبَدْرِيِّ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم " الآيَتَانِ مِنْ آخِرِ سُورَةِ الْبَقَرَةِ مَنْ قَرَأَهُمَا فِي لَيْلَةٍ كَفَتَاهُ ".
አቡ መስዑድ አል-በድሪ እንደተረከው፡-
የአላህ መልእክተኛصلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል፦አንድ ሰው የመጨረሻዎቹን ሁለት የሱረቱ-አል-በቀራህ አንቀጾች በሌሊት ቢቀራ በቂ ነው።
Narrated Abu Masud Al-Badri:
Allah's Messenger صلى الله عليه وسلم said, "It is sufficient for one to recite the last two Verses of Surat-al-Baqara at night."
►📕[Sahih al-Bukhari: Vol. 5, Book 59, Hadith 345 ]
ሱረቱል በቀራህ ከሚቀራበት ቤት ሰይጣን ይሸሻል፦
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ " إِنَّ الشَّيْطَانَ يَنْفِرُ مِنَ الْبَيْتِ الَّذِي تُقْرَأُ فِيهِ سُورَةُ الْبَقَرَةِ " .
አቡ ሁረይራ እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛصلى الله عليه وسلمእንዲህ ብለዋል፡- ሱረቱል በቀራህ ከሚቀራበት ቤት ሰይጣን ይሸሻል።
Abu Huraira reported Allah's Messenger صلى الله عليه وسلمas saying:
Satan runs away from the house in which Surah Baqara is recited.
►📕[Sahih Muslim, Book 4, Hadith 1707]
، عَنْ عَائِشَةَ، قَالَتْ لَمَّا أُنْزِلَ الآيَاتُ مِنْ سُورَةِ الْبَقَرَةِ فِي الرِّبَا، خَرَجَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم إِلَى الْمَسْجِدِ، فَقَرَأَهُنَّ عَلَى النَّاسِ، ثُمَّ حَرَّمَ تِجَارَةَ الْخَمْرِ."
አኢሻህ እንደተረከችው፦ስለ አራጣ፣ሪባ የሱረቱ አል-በቀራህ አንቀጽ በወረደ ጊዜ፦
ነብዩصلى الله عليه وسلم ወደ መስጊድ ወጡና በሰዎች ላይ ቀሩላቸው ከዚያም ከለከሏቸው።
Narrated `Aisha:
When the verses of Surat "Al-Baqara"' about the usury Riba were revealed, the Prophetصلى الله عليه وسلم went to the mosque and recited them in front of the people and then banned the trade of alcohol.
►📕[Sahih al-Bukhari, 459 Vol. 1, Book 8, Hadith 449]
عَنْ أَبِي مَسْعُودٍ الأَنْصَارِيِّ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم “ الآيَتَانِ مِنْ آخِرِ سُورَةِ الْبَقَرَةِ مَنْ قَرَأَ بِهِمَا فِي لَيْلَةٍ كَفَتَاهُ
አቢ መስዑድ አል-አንሷሪ እንደተረከው፦ ነቢዩምصلى الله عليه وسلمእንዲህ አሉ፦ በሌሊት ከሱረቱል በቀራህ ከመጨረሻው ሁለት አንቅጽ ከቀራ በቂው ነው።
The Prophetصلى الله عليه وسلمsaid, "If one recites the last two verses of Surat al-Baqarah at night, it is sufficient for him (for that night).
►📕[Sahih al-Bukhari, Vol. 6, Book 61, Hadith 560]
እንግዲህ ነብያችን صلى الله عليه وسلم እና ሰሓቦች سُورَةِ الْبَقَرَةِ ሱረቱ አል-በቀራህ እያሉ እንደሚጠቀሙበት አይተናል በጣም ብዙ ሐዲስ ማምጣት ይቻላል ግን ግዜ አይበቃንም ነብያችንصلى الله عليه وسلم ሱረቱል በቀራህ ብለው ጠርተውታል ሰሓቦችም እንዲሁ ታላቁ አምላካችን አላህም ሱረቱል በቀራህ ቁጥር 68ላይ በቀራህ የሚለውን ቃል አስቀምጦልናል እናም በተጨማሪም ይመልከቱ፦
►📕[Sahih al-Bukhari,Vol. 3, Book 34, Hadith 297]
►📕[Sahih al-Bukhari, Vol. 6, Book 61, Hadith 571]
►📕[Sahih Muslim, : Book 4, Hadith 1576]
►📕[Sahih Muslim, Book 4, Hadith 1759]
►📕[Sunan an-Nasa'i, Vol. 1, Book 10, Hadith 836]
►📕[Sunan Abi Dawud, Book 3, Hadith 872 ]
ብዙ መጥቀስ ይቻላል ግን ግዜ አይበቃንም ከላይ ያለሁትን ሐዲሳት እንደሚያስረዱን ነብያችንصلى الله عليه وسلم እና ሰሓቦች ይጠቀሙበት እንደነበር ነው።
ማጠቃለያ፦►
እንግዲህ ከላይ ጀምረን እንዳየነው
►አላህ ቁርአንን ከፋፍሎ እዳወረደ አይተናል
►አላህ ቁርአን ሱራ እንዳለው ቁርአን ውስጥ እንደነገረን አይተናል
►ነብያችንصلى الله عليه وسلمእና ሰሐቦች አል-በቀራህ ~البقرة~ ብለው እንደተጠቀሙ ከጊዜ በኋላ እንዳልመጣ አይተናል።
سُورَةٌ أَنزَلْنَاهَا وَفَرَضْنَاهَا وَأَنزَلْنَا فِيهَا آيَاتٍ بَيِّنَاتٍ لَّعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ
►📗[ሱረት አል-ኑር24፤1]
(ይህች) ያወረድናትና የደነገግናት ሱራ (ምዕራፍ) ናት፡፡ በእርሷም ውስጥ ትገሰፁ ዘንድ ግልጾችን አንቀጾች አውርደናል፡፡