MDA-Muslimነኝ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


✅👳የ አላህ ባሪያ ነኝ።
ሀዲሶች
ታሪክ እና ልብ ወለዶች
መረጃዎች
ግጥሞች
እናም ሌላ ሌላም
#Join now...
Le asteyayet @Temsalett

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


Murad Tadesse (Official Channel)☪️🇪🇹 dan repost
እነሆ… ተጀምሯል‼
==============
(የመረጣችሁበትን ስክሪን ሹት ኮመንት ላይ ላኩት፤ እናጠለቅልቀው፤ ዘመቻውን እንቀላቀል!)
||
✍ 10 ሚሊዮን ብር የሚያስሸልመው ውድድር ድምፅ መስጫው መንገድ ታውቋል። ትናንት በዚህ ፖስት (https://t.me/MuradTadesse/38825) በነገርኳችሁ መሠረት የአሚን ጠቅላላ ሆስፒታልን ባለቤት ዶ/ር ሙሐመድ ሽኩርን እንመርጣለን። እውነት ለመናገር ዶ/ር ሙሐመድ ሽኩር ይህንን ውድድር ካሸነፈ ሙሉ አስር ሚሊዮኑን ብር ለእናቶች ማዋለጃና ለጨቅላ ህፃናት ሕክምና አውላለሁ ባይል ኖሮ የምመርጣቸው ሌሎች ተወዳዳሪዎች ነበሩ።


ምክንያቱም ብሩ ወደ ኪሱ የሚገባ ቢሆን ያለውን በረካህ ያድርግለት እንጂ በአንፃሩ ለሌሎች ወጣቶች ቢሆን ይሻላል። ግን ለእናቶችና ለህፃናት መታከሚያ ሙሉውን አውላለሁ ብሎ ቃል ስለገባና እኔም በተጨባጭ እንኳን የተሸለመውን ሠርቶ ያገኘውንም ለሚስኪኖች ድጋፍ ሲያውል ስለታዘብኩ፤ በእናትና በህፃናት አይጨከንም ብዬ እነርሱን ብር አውጥቼ መርዳት ባልችል እንኳ ዶ/ር ሙሐመድን በመምረጥ መርዳት እንደምችል ስላወቅኩ ወደ 9355 SMS ላይ BIW03 ብዬ በመላክ መርጨዋለሁ።

እናንተም ለእናትና ህፃናት አትጨክኑም ብዬ ትመርጡት ዘንድ ጋበዝኳችሁ።

ስትመርጡ በፓጄጅ ስለማይቻል ቢያንስ 3 ብር ባላንስ ይኑረው ስልካችሁ።
ከዛ ሚሴጅ ላይ ግቡና 9355 ላይ BIW03 ብላችሁ ጻፉና ላኩት።

ባይሆን BIW በሚለውና 03 በሚለው መካከል ስፔስ (ክፍት ቦታ) መኖር የለበትም። BIW የሚለው በsmall letter biw ሳይሆን ሁሉም በካፒታል ሌተር BIW ነው። በትክክል መላካችሁን የምታረጋግጡት፤ BIW03 የሚለውን ወደ 9355 ከላካችሁት በኋላ «You have voted for ( Dr Mohamed shikur ). Thank you for your participation. Abbay TV 'Ethiopia's Best'» የሚል መልዕክት ወዳውኑ ይደርሳችኋል። ከአንድ በላይ ሲም ካላችሁ፣ ወይም መደጋገም ከፈለጋችሁ፣ ወይም ባላችሁ ቤተሰብ ስልክ ሁሉ መላክ ከፈለጋችሁ፣ ካርድ ለሌላቸው እየሞላችሁ … ምረጡት። ድምፃችን እንዳይበታተንና አንድ ቦታ ላይ አድምተን ድምፅ እንድንሰጥ ወጥሩ ቅመሞች።

መልዕክቱን በተለያዩ ገፆችና ግሩፖች አሰራጩት።
መታከሚያ ያጡ ሚስኪን እናቶችና ህፃናት ያሸንፋሉ፤ ኢንሻ አላህ! ያው የኔ ገፅ ቅመሞች በንቃትና በእንዲህ አይነት የኸይር ተሳትፎ አትታሙም። እንኳን በዚህች በቀላሏ ከኪሳችሁም ሚሊዮኖችን አዋጥታችሁ በተደጋጋሚ ለሚስኪኖች ሰድቃችሁ አሳይታችኋል። አላህ ይቀበላችሁ!
||
t.me/MuradTadesse


Mohammedamin Kassaw dan repost
አህባቢ የባቱ ልጆቻችንን መድረሳ ምንጣፍ ዘነጋችሁት እንዴ?
እስካሁን 9850 ብር ሰብስበናል:: ለምንጣፉ የተጣራ 15200 ብር እንደሚበቃ አሁን ገልፀውልኛል:: ተረባርበን እንሙላው:: 5350 ብር ብቻ ነው የቀረን:: 54 ሰው 100 ብር ቢሰጥ ሞላ ማለት ነው:: 1 ሰውም 5350 ብር ከሰጠ ይሞላል::

ብቻ መድረሳው የነገ ትውልዶችን የሚያንፅ ነውና የበኩላችንን እናበርክት:: የአኼራ ቤታችንን በመገንባት ውስጥ የልጆቻችንን መድረሳ እናንፅ::

የባንክ account: 1000635482099 / Batu Bilal Mosque Medresa

🔺 መልዕክቱን ለሌሎች በማጋራት የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ!

 @MohammadamminKassaw


Mohammedamin Kassaw dan repost
በባቱ/ዝዋይ ከተማ ለሚገኘው ቢላል መስጂድ መድረሳ ምንጣፍ እንግዛላቸው!

ይህ የምትመለከቱት ጎስቋላ መድረሳ የግቢ ተማሪ ወንድማችን የሆነው ሙስዓብ በባቱ/ዝዋይ የሚያቀራበት መድረሳ ነው:: ለእረፍት ወደ ቤት በሚመለስበት ሰዓት ተማሪዎቹንና መድረሳውን እንደምታዩት አጊኝቶታል:: መድረሳው ብዙ ማሻሻያዎች የሚያስፈልጉት ቢሆንም ለአሁን ግን የምንጣፉ ነገር አስቸኳይ እንደሆነ ገልፆል:: ሙሉ መድረሳውን በጅባ/ሰሌን ለማንጠፍ 20ሺ ብር ገደማ ያስፈልጋል::

ይህንንም በአቅማቸው ማሟላት ስላልቻሉ እናግዛቸው ዘንድ ጠይቀዋል:: ስለሆነም ሁላችንም ተረባርበን የወንድሞቻችንን መድረሳ እናንጥፍ:: በመድረሳው የነገ ልጆች ይሰራሉና በዚህ ቅዱስ ተግባር ላይ አሻራችንን በማሳረፍ ለራሳችን ሶደቀተል ጃሪያ እንሸምት::

የባንክ account: 1000635482099 / Batu Bilal Mosque Medresa

🔺 መልዕክቱን ለሌሎች በማጋራት የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ!

ለሌሎች ማነቃቂያ ይሆን ዘንድ screenshot በማድረግ ንያችሁን @Mohammadamminm አሳውቁኝ::

@MohammadamminKassaw


Mohammedamin Kassaw dan repost
"እገሌ ይሰድብሃል" አሉት ለአንድ ደግ ሰው ሰዎች ።
" ሁሉም ሰው የየራሱ የሥራ መዝገብ አለው። ደስ ባለው ነገር ቢሞላ ምን ገዶኝ።" አላቸው ።

@MohammadamminKassaw


Mohammedamin Kassaw dan repost
ሊመረቅ ሳምንታት የቀሩትን የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪ እናሳክም! - መልዕክቱ ይዳረስ ዘንድ ሼር አድርጉ!!

ተማሪ አህመድ ሱለይማን ይባላል:: አባቱ እድሜያቸውን በመስጂድ ኢማምነት የጨረሱ እርሱ ቁርዓን ሀፊዝ ሲሆን በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በኬሚካል ኢንጂነሪንግ የ5ኛ አመት ተማሪ ነው:: ለምርቃቱ ሳምንታት እንደቀሩት acute lymphoblastic leukemia በተባለ የደም ካንሰር ሰለባ ሆኖ በአልጋ ላይ ይገኛል::

ህክምናውን ባህር ዳር ከሚገኘው ጋምቢ ሆስፒታል እስከ ጥቁር አንበሳ ቢሞክርም የህክምና ቦርዱ ከካንሰር ሙሉ በሙሉ ነፃ የሚሆነው ወደ ውጭ ሄዶ የመቅኔ ንቅለ ተከላ ሲያደርግ ብቻ እንደሆነ አሳውቀውታል:: ለዚህም የተጠየቀው ከ5 ሚልየን ብር በላይ ከአቅሙ በላይ ስለሆነ እጁን ወደ ማህበረሰቡ እንዲዘረጋ አስገድዶታል::

አላህ "አንድን ነፍስ ህያው ያደረገ ሙሉ ህዝብን እንዳዳነ ይቆጠራል።" ብሏልና በቻልነው አቅም ተረባርበን ወንድማችንን እናሳክም:: ድጋፍ ለማድረግ Account name muhammed suleiman &or taju suleiman - Comercial bank 1000632758638 / Zemzem  bank 0042125420101 / Awash bank 014251356745900 ይጠቀሙ::

ለበለጠ መረጃ:- 0921572121  ሙሀመድ ሱለይማን (ወንድም)
0910373510  ታጁ ሱለይማን (ወንድም)

@MohammadamminKassaw


ከ ደጋጎቹ ዓለም dan repost
ሀጅን መሄድ ያልቻለ፣ በመቅረቱ ያዘነ፤ ማን ያውቃል በንጹህ ንያው ምንዳ ተጽፎለት ይሆናል።

"በመዲና ውስጥኮ የቀሩ ሰዎች አሉ።ጉዞንም አልተጓዛችሁም፣ ሸለቆንም አላቋረጣችሁም ከናንተ ጋር በምንዳ የተጋሩ ቢሆኑ እንጂ። የሚያስቀር ነገር አስቀራቸው እንጂ!" ብለው ነበር ረሱል صلي الله عليه وسلم ከተቡክ ዘመቻ በስንቅ እጥረት ምክንያት እያለቀሱ ስለቀሩ ሶሃቦች ሲናገሩ

ይህንን አያይዘው ኢብኑ ረጀብ رحمه الله

"አንድን መልካም ስራ መስራት ያቃተው ሰው፣ ያንን ባለመስራቱ ደግሞ ካዘነ፣ ነገሩ ቢከሰት ብሎ የተመኘ ያንን ስራ ከፈጸመው ሰው ጋር በምንዳ ይጋራል ይላሉ።"


Mohammedamin Kassaw dan repost
Mariin biyyaalessaa maali?  Maaliif hundeeffame?  Muslimaaf maaltu tola?

    Mariin biyyoolessaa komishinii rakkoolee fi waldhabdee biyyoolessaa seenaa keessattis ta’e haala yeroo keessatti uumaman mariidhaan hiikuuf hundaa’eedha.  Seenaawwanii fi seeneffamawwan durii akkamitti barreeffamuu akka qaban kallattii kaa’a.  Gootota biyyattii bal'inaan tarreessa.  Mallattoo fi mul’annoo akkamii biyyattiin har’a qabaachuu akka qabdu (alaabaa, faaruu biyyaalessaa, maqaa daandii fi kkf) murteessa.  Lammiileen biyyattii keessatti mirga akkamii qabaachuu akka qabaniifi daangaan mirga isaanii maal akka ta’e ibsa.  Heerri mootummaa sarara waliigalaa fooyya’uu qabu kaa’a.

📌 Akka Muslima tokkootti ajandaawwan armaan olitti ibsaman fi kanneen biroo hin kaafamne nu tuqa.  Bu’aan isaa gaariis ta’ee hamaa ta’us, ejjennoo hawaasni Musliimaa biyyattii keessatti qabu mirgaa fi dirqama isaatiin murtaa’a.  Seenaan keenya ni barreeffama.  Mirgi keenya ni eegama.  Bakka bu'ummaan keenya ni ibsama.  Dhimmoota Muslima waliigalaa kaasan irratti murteen ni darba.

📌 Marii kana keessatti hirmaattonni hawaasa keessaa kan filataman yoo ta’u, hirmaattoota 2,000 Addis Ababa keessa jiran keessaa Muslimoonni dhibbeentaa 5 gadi jechuunis naannoo namoota 100 ta’u.  Naannolee Musliimoonni guutumaan guututti keessa jiraatan kan akka naannoo Affaarii fi Somaalee keessatti lakkoofsi hirmaattota waliigalaa dhibbantaa 50 gadi ta’uu ibsameera.  Naannolee biroo keessattis gara dhibbeentaa 1.8 ta’a.

📌 Murtoon kana keessatti murtaa'u negaatiivii yoo ta'e rakkoon akkuma duraanii itti fufa.  Salphumatti ijoolleen keenya ammas gootichi biyya keenyaa Ahmed giraany akka weeraraatti barachaa jiran.mana barumsaa keessatti ajandaan hijaabaa ajandaa ta'ee itti fufaa jira.salaata dhiisuun humna waraanaatti seenuuf ulaagaa ta'ee itti fufaa jira.Kanneen biroos...

🔺 Dhugaa fi balaan hamma kana guddaa ta'us ammallee hanqinni dammaqiinsaa jira.  Rakkoon Muslimoota hamma kana gadi fagoo ta'us Komishiniin Marii hirmaachisuunii dide.

🔺 Dhaabbanni adda duree mormii erga dhageessise bubbuleeti jira.Dhaabbata keenya cinaa akka jirruu fi kana cal'ifnee akka hin ilaalle agarsiisuufis dirqama qabna.  Waa'ee marii fi komishinichaa karaa Facebook, telegram, X, Youtube fi fuula miidiyaa hawaasaa kana fakkaataniin ergaa haa dabarsinu.  Mormii keenya sanduuqa yaadaa fuula komishinichaa keessa haa galchinu. manaa fi iddoo hojiitti aa'ee kanaa qofa haa dubbannu.  Sana booda fedha Rabbiitiin hooggantoonni keenya ni cimu.sana booda gurri tuffii keenyaaf callise sodaadhaan dhaggeeffata.mirga keenyallee nuuf nahuudhaan otuu hin taane nu kabajuun nuuf eegu.  Mirga keenya kadhaadhaan otuu hin taane falmiidhaan ni kabachiifanna.


Rabbiin marii biyya keenyaaf fayyadu haa godhu!!

@MohammadamminKassaw


Mohammedamin Kassaw dan repost
የሚጠበቅ ነው! ሴራቸውም ይህ እንዲመጣ ነበር!!

እንደ ቅመም ለይስሙላ ላያጣፍጡ የገቡት ሙስሊም ተሳታፊዎች ቁጥራቸው አናሳ ስለሆነ የሚያነሷቸው አጀንዳዎች በእጅ ብልጫ እያለፉ እንዳልሆነ ለሃሩን ሚዲያ ገልፀዋል:: ይህ እንግዲህ አጀንዳ ማስያዙ ላይ ነው:: even አጀንዳ ተብለው የሚያልፉ አጀንዳዎች ቢኖሩ ደግሞ በምን መልኩ መፍትሔ ይሰጣቸው የሚለው ላይ አሁንም በእጅ ብልጫ ነው የሚወሰነው:: የዚያኔም እጃችን ትንሽ ነው:: እነሱ በፈለጉት መልኩ ይወስናሉ::

የሁላችን ኢትዮጵያ ትምከር!

@MohammadamminKassaw


Mohammedamin Kassaw dan repost
ሀገራዊ ምክክር ምንድን ነው? ለምን ተቋቋመ? ለሙስሊሙስ ምን ይፈይዳል?

   ሀገራዊ ምክክር በዋናነት እንደ ሀገር በታሪክ ውስጥም ሆነ አሁን ባለው አውድ የተፈጠሩ ሀገራዊ ችግሮችንንና አለመግባባቶችን በምክክር ለመፍታት ታስቦ የተቋቋመ ኮሚሽን ነው:: በትላንት ውስጥ ያለፉ ታሪኮችና ትርክቶች እንዴት መፃፍ እንዳለባቸው አቅጣጫ ያስቀምጣል:: የሀገሪቱን ጀግኖች በዝርዝር ያስቀምጣል:: ሀገሪቱ ዛሬ ላይ ምን አይነት ምልክቶችና መገለጫዎች (ባንዲራ : ብሔራዊ መዝሙር: የአደባባይና መንገድ ስያሜዎች ወዘተ) ሊኖራት እንደሚገባ ይወስናል:: ዜጎች በሀገሪቱ ላይ ምን አይነት መብት ሊኖራቸው ይገባል የመብታቸው ድንበርስ እስከየት ነው የሚለውን ያስቀምጣል:: ህገ-መንግስቱ የሚሻሻልበትን አጠቃላይ መስመር ይዘረጋል::

📌 እንደ ሙስሊም ከላይ የተጠቀሱትም ሆነ ሌሎች ያልተጠቀሱ አጀንዳዎች ይነኩናል:: ውጤቱ አሉታዊም ሆነ አዎንታዊ ሙስሊሙ ማህበረሰብ በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ቦታ መብትና ግዴታ ያስቀምጣል:: ታሪካችን ይፃፋል:: መብታችን ይቀመጣል:: ውክልናችን ይገለፃል:: እንደ አጠቃላይ ሙስሊሙ ጥያቄ ብሎ በሚያነሳቸው ጉዳዮች ላይ ውሳኔ ያልፋል::

📌 በምክክሩ ውስጥ የሚመካከሩት ከማህበረሰቡ ውስጥ የተመረጡ ተሳታፊዎች ሲሆኑ እስከ አሁን አዲስ አበባ ላይ ከሚሳተፉ 2ሺህ ገደማ ተሳታፊዎች የሚሳተፉ ሙስሊሞች ከ5 ፐርሰንት በታች ማለትም 100 ሰው አካባቢ ነው:: ሙሉ ለሙሉ ሙስሊም በሆኑባቸው እንደ አፋርና ሱማሌ ክልል ያሉ ተሳታፊዎች ከአጠቃላዩ ከ50 ፐርሰንት በታች ነው:: በሌሎች ክልሎች ደግሞ 1.8 ፐርሰንት ገደማ ነው::

📌 በዚህ ውስጥ የሚወሰኑ ውሳኔዎች አሉታዊ ከሆኑ ችግሮች እንደ በፊቱ ይቀጥላሉ:: በቀላሉ አሁንም ልጆቻችን የግራኝ አህመድ ወረራ እያሉ የሀገራቸውን ጀግና እንደ ወራሪ ተደርጎ ይማራሉ:: በትምህርት ቤት ውስጥ ያለው የሂጃብ አጀንዳ አጀንዳ ሆኖ ይቀጥላል:: ወታደር ቤት ለመግባት ሶላትን መተው መስፈርት ሆኖ ይቀጥላል:: ሌላም ሌላም...

🔺 እውነታውና አደጋው የዚህን ያክል ቢሆንም አሁንም ድረስ የግንዛቤ እጥረት አለ:: የሙስሊሙ ችግር የዚህን ያክል ጥልቅ ቢሆንም የምክክር ኮሚሽኑ ለማሳተፍ ፈቃደኛ አልሆነም::

🔺 መሪ ተቋሙ ተቃውሞ ካሰማ ሰነባብቷል:: እኛም ከተቋማችን ጎን እንደሆንና ይህንን ዝም ብለን እንደማናየው የማሳየት ግዴታ አለብን:: በFacebook, telegram, X, Youtubeና መሰል የማህበራዊ ትስስር ገፆች ስለ ምክክሩና ኮሚሽኑ መልዕክት እናስተላልፍ:: ተቃውሟችንን በኮሚሽኑ ፔጅ Comment box ላይ እናስቀምጥ:: የቤትም ሆነ የስራ ቦታ ወሬያችንን ስለዚህ ብቻ እናድርግ:: የዚያኔ በአላህ ፈቃድ መሪዎቻችን ወኔያቸው ይበረታል:: በንቄት ዝም ያሉን ጆሮዎች በፍርሃት ያደምጥናሉ:: መብታችንንም አዝነውልን ሳይሆን አክብረውን ይስጡናል:: መብታችንን ለምነን ሳይሆን ታግለን እንወስዳለን:: አራት ነጥብ💪💪

የሁላችን ኢትዮጵያ ትምከር!
አላህ ምክክሩን ለሀገራችን የሚበጅ ያድርገው!!

@MohammadamminKassaw


Mohammedamin Kassaw dan repost
እውነት ነው!

መብቴን ተቀማሁ ብሎ አንገቱን በመድፋት የሚረገጥ ትውልድ አይደለንም!!

@MohammadamminKassaw


Mohammedamin Kassaw dan repost
የሁላችን ኢትዮጵያ ትምከር!

📌 የሀገሪቱን ግማሽ አካል ያገለለ ሀገራዊ ምክክር ሀገሪቱን አይወክልም!

📌 ሙስሊሙን በሚገባ ያለወከለ ሀገራዊ ምክክር ሙስሊሙን አይወክልም!

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ራሱን ይፈትሽ!

🔺 የፕሮፋይል ቻሌንጅ እንጀምር:: ለጓደኞቻችን በinbox እንላክ:: ወደ ግሩፖች እናጋራ:: ቻናሎቻችን አጀንዳቸው ይሄ ይሁን:: ያልሰማ ይስማ:: ሁሉም እስኪሰማ ድረስ በአንድነት ድምፃችንን እናስተጋባ::

@MohammadamminKassaw


Ametel-Halim dan repost
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱሁ ውድ እና የተከበራችሁ የአል ኡስዋህ (ተምሳሌት )በጎ አድራጎት አባላቶች እንዲሁም ሙስሊም እህት ወንድሞች እንደሚታወቀው ይህ ጀመዓ ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ ለ ኡምማው ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል
በየሳምንቱ የ አቅመ ደካሞች ቤት በመሄድ አንደ ልብስ ማጠብ ቤት ማፅዳት ምግብ ማብሰል አስቤዛ ማሟላት የታመሙትን ማሳከም ከመሳሰሉት ጥቃቅን ሥራ እስከ ቤት  መስራት ሥራ መስራት ለሚችሉት ሥራ ማስጀመር ለ ረመዷን ማፍጠሪያ የሚሆን ፓኬጅ መስጠት ሁለቱን ኢዶች ምግቦች ና አልባሳትን በቻልነው መጠን አሟልተን ከነሱጋር ማሳለፍን እና ሌሎችንም ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ላለፉት 5 አመታት በቻለው አቅም ልክ ሲሰራ ቆይቷል .... አሁን ደግሞ ለምን በጭሮ ከተማ ብቻ ተወስኖ ይሰራል ለምንስ ሀገሪቷ ውስጥ ያሉትን አቅመ ደካሞች እና የተቸገሩትን አንረዳም በሚል እሳቤ  የምትመለከቱትን ለ 3ቀን የሚቆይ ቻሌንጅ  በትላንትናው እለት ጀምሮ ዛሬን ቆይቶ እስከ ነገ ለመዝለቅ አስቧል. ቻሌንጁም የሚሆነው የጀመዓውን ተደራሽነት ለማስፋት የጀመዓውን ሎጎ ፕሮፋይልና ስቶሪ በማድረግ እንዲሁም የጀመዓውን ግሩፕ በመቀላቀል👉 📎 t.me/Aluswahvoluntaryassociation ዛሬን ና ነገን
ማታ 2፡00 ላይ አቅማቹ የፈቀደውን ገንዘብ ይዞ በመገኘት ነው ረሡላችን (ﷺ) "በወንድሙ ሀጃ ላይ የሆነ አላህ በእርሱ ሃጃ ላይ ይሆንለታል" ብለዋል መቼም የራሡ Uጃ የሌለበት ሰው የለም በማለት ይህን ቻሌንጅ እንድትቀላቀሉን በአላህ ስም እንጠይቃቹሃለን 🙏

የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ  :1003700126407
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ : 1000490697571


Aluswah (temsalet) voluntary association charity dan repost
Assalamuaelykum warahmatuahi wabarakatuh

Miseensota Jama'a al uswah hunda keessanu jazakalllah jecha haasawa kiyya eegala akkuma beekamu challenge suura maxxansuu akkuma itti fufee jiraa haata'u malee kanuma jidduutti miseensoonni keenya yaada haaraa kaasan yaadni sunis suura qofa maxxansuun maal bu'a qabaa yoo wal moggaan #challenge qarshiidha hin godhin jachuun yaada kana kaasani jiruu nutis yaada isaani fudhachuun #challenge qarshii sa'aa 2 irraa kaasudhaan hundi keessanu gara account al uswah akka ergitan akka iratti hirmaattan dhaamsa keenya isif dabarsinaa

#challenge_qarshii har'a galgala sa'a 2:00 iratti ni gaggeeffama hundi keenyahu qarshii #100 irraa kaasnee itti haaqophoynu

Share walif godhaa

t.me/AluswahVoluntaryAssociation

https://t.me/Aluswahtemsaletvoluntary


ከ ደጋጎቹ ዓለም dan repost
ወንጀል በመፈፀም ከዚያም
ወንጀለኛ ነኝና በጎ ስራ ላይ መሰማራቴ ምንም አይጠቅመኝም ብለህ በማሰብ 
ሁለት ጊዜ አትሸነፍ።


ከ ደጋጎቹ ዓለም dan repost
በርግጥም ሲያወሩት የነበረውን እንጽፋለን
{سنكتبوا ما قالوا }

በቀልድም ይሁን በቁምነገር
በደስታም ይሁን በብስጭት
በማስታወስም ይሁን በመዘናጋት
በሚድያም ይሁን በወረቀት
በምላስም ይሁን በእስክርቢቶ
የሰራነውም ይሁን ያወራነው
ጥሩውም ይሁን መጥፎው

በማይሰረቅ፣ በማይደበዝዝ፣በማይጠፋ የስራ መዝገብ ላይ ይመዘገብብናል።
ሂሳብም እናወራርድበታለን።


ከ ደጋጎቹ ዓለም dan repost
#ከሰለዋት_ጥቅሞች

🌲ዱዓእ በምታደርግበት ጊዜ ከፊት ካስገባኃው፤ዱዓህ ተቀባይነት እንዲኖረው ያደርጋል ተብሎ ይከጀላል።

🌲ወሲላ የምትባለውን ጀነት አሏህን ከጠየቅክላቸው፣ወይም ብቻውን ካልክ ሸፋዓቸውን ለማግኘትህ ምክንያት ይሆናል።

🌲ወንጀልህ ይቅር እንዲባልልህ ምክንያት ይሆናል።

🌲ካስጨነቀህ ነገር ሁሉ አሏህ እንዲበቃህ ምክንያት ይሆናል።

🌲ነገ የውመል ቂያማ ወደ ረሱል ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንድትቀርብ ምክንያት ይሆናል።

🌲ለጉዳይህ መፈፀም ምክንያት ይሆናል

اللهم صل وسلم وبارك على نبينا محمد


ሱረቱል ከህፍን መቅራት እንዳትረሱ፣ከዓስር በኃላ ፀሃይ እስከምትጠልቅበት ድረስ ባለው ጊዜ ላይ ዱዓእ ላይ በርቱ። ሌላው ቢቀር ችግር ውስጥ ላሉ ጓደኞቻችንም ቢሆን ብናደርግ ምንም አይቀንስብንም፤የቀልብ ድርቀት እንጂ ሌላ አልከለከለንም። ለሌሎች የምንጠይቀው ነገር ለኛም መደረጉ አይቀርም።


ሙከሚል የንፅፅር ቤተ መጽሐፍ dan repost
አዋጅ አዋጅ ለስልጤ  ማህበረሰብ በሙሉ

በሁሉም የስልጤ ማህበረሰብ ላይ የታቀደ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች አድማ ወጥቷል

ይህም አድማቸው ከነገ ጀምሮ የረመዷን ስጦታ በሚል ድግምት የተሰራበትን የተለያዩ ቁሳቁሶች ዘይት ዱቄት ቴምር ልብስ ከረሜላ መሰል ነገራቶችን እንለግሳለን እያሉ ህዝቡን ለማጭበርበርና በድግምት ለማሰቃየት ከዛም በድግምት ሲሰቃይ ና ጌታን ተቀበል ትፈወሳለህ እያሉ ህዝቡን ለማክፈር ዝግጅታቸውን ጨርሰዋል።

ስለሆነም ሁሉም የስልጤ ማህበረሰብ በረመዷን ስጦታ ስም የተደገሰለትን መተታዊ ተንኮላቸውን ሊጠነቀቅ ይገባል።

ማሳሰቢያ ይህንን ስጦታ ለመስጠት የሚመጡ ሰዎች ፍጹም ሙሥሊም መስለው ጀለቢያና ኮፊያ ሴቶችም ሒጃብና ጅልባበ ኒቃብ ለብሰው ስለሆነ ጥንቃቄ አድርጉ።

ህጻናት በየ ትምህርት ቤቱ በየ መንገዱ የሚሰጣቸውን ከረሜላና መሰል ነገሮችን እንዳይቀበሉ ጥንቃቄ አድርጉ።

ጽሑፉን ሼር ሼር እንድታደርጉልኝ በአላህ ስም እጠይቃለሁ።

يُرِيدُونَ لِيُطْفِئُوا نُورَ اللَّهِ بِأَفْوَاهِهِمْ وَاللَّهُ مُتِمُّ نُورِهِ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُونَ
(ሱረቱ አል - ሶፍ - 8)
የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ፡፡ አላህም ከሓዲዎቹ ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን ገላጭ ነው፡፡

🎙ሙከሚል ሙሥሊም ልጅ።
https://t.me/mukamil12


ከታች የምትመለከቱትን መልዕክት የአአዩሙተህ የሒጃቡን ንቅናቄ በጀመረ ማግስት አንድ ወንድማችን በቴሌግራም ግሩፖችን ላይ ያጋራው ነው :: አንብቡት:-

"እስኪ ያ ጀማዓ እዚህ ላይ እንደውም አንድ ቆንጆ ሀሳብ ትዝ አለኝ። አስተውላችሁ ከሆነ አንድ ኒቃቢስት የሆነች የፅዳት ሰራተኛ እዚሁ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ግቢ ውስጥ አለች። አብዛሀኛውን ጊዜ 502 ህንፃ አካባቢ ስታፀዳ ነው የማያት እና ወላሂ በተቻለን አቅም ብንረዳት ምን ይመስላችኋል። ወላሂ እንደውም አንድ ቀን የሆኑ ሰዎች ጋር ቆማ ስታለቅስ አገኘኋት።ከዛ ምን ሆና ነው ብዬ  ለመጠየቅ ፈልጌ  ፈራሁና ስልክ እየነካካሁ መስዬ ባጠገባቸው ሳልፍ ከዛ አንዱ የፅዳት አስተባባሪ ነው መሰለኝ አንቺ ለፅዳት ተመደበሻል እንዴ?? አይተንሽ አናውቅም ደሞ ይሄ ፊታቸው ላይ የሚያረጉት ነገር ነውኮ። ምናምን እያለ ሲቀበጣጥርባት ወላሂ ስታለቅስ በ አይኔ አይቻለሁ። ከዛ በኋላ እስኪ ስምሽ መኖሩን እስከምናረጋግጥ ድረስ ወደ ስራ እንዳትገቢ ሲላት ሰማሁኝ። እሷ ግን በጣም እያለቀሰች ነበር። አስባችሁታል በጣም ከመቸገሯ የተነሳኮ ነው እንደዚህ ገና ለገና ይችኑ ስራዬን ያሳጡኛል ብላ ያለቀሰችው። ግን አሁን አልሀምዱሊላህ ሁሌም አያታለሁ ስራዋን ትሰራለች። እና ያጀመዓው ወንድም እና እህቶቼ ኒቃቧን ሳታዋልቅ በፅዳት ላይ ለተሰማራችው የምድር ጨረቃ ለሆነችው እህታችን ብንደግፍት ምን ይመስላችኋል። እስኪ አስቡበት እና ወላሂ አንድ ቁም ነገር እናድርግላት።"

ለእህታችን ከዚህ ቤት ስጦታ እናበርክት ብለው የአአዩ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት እንቅስቃሴን ጀምረዋል የምትችሉትን በ 1000485306432 - AAU Muslim students union አስገቡ :: ካስገባችሁ ቡሃላ screenshot በ @Mohammadamminm በመላክ የዚህ መልካም ተግባር ተሳታፊ ይሁኑ ለሠው ሀጃ የተሯሯጠ አላህ ሀጃውን ይሞላለታል ብለውናል ሀቢቡና ﷺ

መልዕክቱን ሼር በማድረግ ይተባበሩን ደግሞ ረሡልም ﷺ እንዲህ ብለውን የለ
قال رسول الله ﷺ
من دلّ على خير فله مثل أجر فاعله  رواه مسلم
>ወደ ኸይር ያመላከተ እርሱ ተመሳሳይ አጅር ያገኛል በሰሪዉ ሳይቀንስበት
ሙስሊም ዘግቦታል


ከ ደጋጎቹ ዓለም dan repost
"ዑመር ሆይ! እሱኮ #በድር ዘመቻን ተሳትፏል"

ይህ ረሱል ﷺ ሃጢብ رضي الله عنه መካ ያሉትን ቤተሰቦቹን ከ አጋሪያን ጥቃት ለመጠበቅ ሲል ለ አጋሪዎች ረሱልና ባልደረቦቻቸው ስላሉበት ሁኔታ ደብዳቤ በ አንዲት ሴት ሲልክ ተይዛ ቀርባ ደብዳቤው ሲነበብ ዑመር እንዲህ አይነት ክህደትን የፈፀመን ሰው ልግደለው ብሎ ፍቃድ ሲጠይቃቸው የሰጡት መልስ ነው። እንደምታውቁት በድር ዘመቻን የተሳተፉትን ሰዎች አሏህ የፈለጋችሁትን ስሩ ይቅር ብያቹሃለሁ ማለቱ ይታወሳል።

እናም አንድ ጓደኛችሁ ስህተትን ሲፈጽም ስትመለከቱ ከዚህ በፊት ሰርቶ የነበረውን መልካም ነገር ፈልጉለትና ይቅርታ አድርጉለት። በሁሉም ህይወት ውስጥኮ ይቅርታ የሚደረግለት #በድር ይኖራል።

t.me/kedegagochu_alem


ከ ደጋጎቹ ዓለም dan repost
እንግዳውን ወይም የሚያከብረውን ወንድሙን ለማክበርና ለመንከባከብ ብቻ በማሰብ

ወላሂ ልትበላ
ወላሂ ልትዘይረኝ
ወላሂ ቤት ልትገባ
ወላሂ ይሄን ስጦታ ልትቀበለኝ ያለ ሰው

ምናልባት እንግዳው ወይም ተጋባዡ  ስጦታውን አሻፈረኝ ቢል (እምቢ ማለት ግን አልነበረበትም) መሀላ የፈጸመው ሰው ምንም አይነት ከፋራ (የመሃላ ማካካሻ) ማውጣት አይጠበቅበትም።

ምክንያቱም አስተናጋጁ የማለው ያኛው ሰው ጉዳዩን እንዲፈጽም ለማስገደድ ሳይሆን ለማክበርና ለመንከባከብ ነውና። በሁለቱ መሀላዎች መካከል ደግሞ ልዩነት አለ።

ይህ የኢብኑ ተይሚያ፣ የኢብኑ ዑሰይሚኒም ምርጫ ነው።

"ዶክተር ፈህድ ሱነይድ حفظه الله ከጻፉት"

t.me/kedegagochu_alem

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.