☞ሐምሌ 19 እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡
☞ቂርቆስ ማለት የኤፍራን ቀለም ማለት ነው፡፡ አባቱ ቆዠሞስ እናቱ ኢየሉጣ
ይባላሉ፡፡ ኢየሉጣ ማለት ምልእት ሃይማኖት ማለት ነው፡፡ ሀገሯ ሮም (አንጌቤን)
ነው፡፡
☞እስክንድሮስ በነገሠ ጊዜ በሃይማኖት ምክንያት በምእመናን ላይ ስደት
ደረሰባቸው፡፡
]☞እየሉጣም የ3ዓመት ሕፃን ቂርቆስን ይዛ ከሮም ወደ ጠርሴስ ቸሰዳ
ተቀመጠች፡፡
☞ንጉሡ ክርስቲያኖችን እያደነ ወደ ሸሹበት ሀገር ደርሶ አገኛትና ተይዛ ቀረበች፡፡
መኩንኑም ሀገርሽ የት ነው ስምሽ ማን ይባላል፡፡ ወገንሽስ ማን ነው ብሎ
ጠየቃት፡፡ ኢየሉጣም ሀገሬ አንጌቤን ዘሮም ስሜ ክርስቲያን ነው፡፡ ከአንተ ሸሽቼ
ብመጣ አገኘኽኝ አለችው
☞መኮንኑም መልሶ ለጣዖት ስገጂ ሰምሽን ግለጪ እንዳትሞቺ ሲል ጠየቃት፡፡
እሷም እውነትን ለማወቅ ከፈለግሽ ወደ መንደር ልከ የ3 ዓመት ሕፃን አሰመጣና
የምናመልከውን እሱ ይንገረን አለችው፡፡
☞ህፃኑ ቂርቆስም መጣ ንጉሡ ለጣዎት ስገድ አለው ራሳቸውን ማዳን
ለማይቻላቸው ለረከሱ ጣዖታትኽ አልሰግድም አለው፡፡
☞በዚህ ምክንያት መኮንኑ ተቁጥቶ በታላቅ የብረት ጋን ውሃ አስፈልቶ
እንዲጨምሯቸው አዘዘ፡፡ የፍላቱም ድምፅ እንደ ክረምት ነጉድጎድ ኾነ ይህን
ሲጮኽ ሰምታ ኢየሉጣ ያን ጊዜ ፈራች፡፡ ቂርቆስ ግን እናቴ ጠንክሪ 3ቱ ደቂቃን
ያዳነ ያድነናል እያለ ወደ ጌታ ለመነላት፡፡
✞ጌታም ልባን ወደ ሰማይ አሳርጎ የተዘጋጁላትን የብርሃን ማደሪያዎች አሳያትና
ጽናት አግታ ጌታን አመሰገነች፡፡ ልጇንም አመሰገነች፡፡
☞ልጇንም እንዲህ አለችው ከዛሬ ጀምሮ አንተ አባቴ እኔ ልጅኽ ነኝ ከእኔ
የተወለድኽበት ቀን ብፅዕት ናት አለችው፡፡ ይህን እያለችው በጋን በፈላ ውሃ እና
አሳት ውስጥ ገቡ፡፡
☞ያን ጊዜ ቅዱስ ገብርኤል በጌታ ፈቃድ ከሰማይ ወርዶ የእሳቱን ኀይል እንደ
ንጋት ውርጭ ቀዠቃዛ አደረገውና ከእሳቱ በሰላም ወጥተዋል፡፡ ይቺ ሊቀ
መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ከእሳት የወጡበት ቀን ነች ሐምሌ 19 በዓመታዊ
በዓል ታስቦ በደማቅ ሁኔታ ከዋዜማው ጀምሮ በሊቃውንቱ በቅኔ ማህሌት
በምስጋና በቤተክርስቲያናችን ታከብረዋለች፡፡
☞(መድብለ ታሪክ መጻሐፍ ቁጥር 1)
☞ደስታን አብሳሪው ሊቀመላዕክት ቅዱስ ገብርኤል እኛንም እንደ አሳት
ከሚያቃጥል ሀጥያት ያውጣን፡፡
]በዚህ ሰአት በረሀብ እሳት ፤ በጥም አሳት ፤በስደት አሳት ውስጥ ያሉ
ወገኖቻችን ከዚህ እንደ አሳት ከሚያቃጡ ነገሮች ውሉ ያውጣልን፡፡
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
@wiseholyfathersአስተያየት ካላቹ በ
@Wisecomment_bot ይላኩልን