ተከታታይ መንፈሳዊ ልብወለድ#ሁለት ሰይፍ
ክፍል አምስት(ሜርሲ✍️)
"ይሀውልሽ ሱዚያና አሁን ላይ የጣልኩትን ነገር የማነሳበት ሰዓት አይደለም::የድሮው ናቲ ሞቷል::ሕይወትሽን ኑሪ::"
"እርዳታህን የምጠይቀው እኮ ማንም ሰው እዛ ስለሌለኝ ነው::እማዬ ብቻዋን ከቤተሰብ ተነጥላ እንዳሳደገችኝ ታውቃለህ::ማንንም አምኘ ያንን ዕቃ ልሰጠው አልችልም::እባክህን.. እንደ አንድ እርዳታን እንደሚጠይቅህ ሰው ብቻ አድርገህ ቁጠረኝ እና ተበባረኝ::"
ዝም ብሎ ይቆያል::
"ህ.. ናቲ..."
"እሺ::ድጋሚ ግን ባትደውይልኝ ደስ ይለኛል::"
"አመሰግናለሁ ናቲዬ::እባክህን ለእናቴ ዕቃው ባልኩህ ሰዓት ሊደርስላት ይገባል::"
"እሺ አልኩሽ እኮ::ቻው::" ስልኩን ዘግቶ ሶፋው ላይ ወርወር ያደርጋል::
ድምፅ የሰማ ስለመሰለው ወደ ውጭ ሲወጣ ዮሃና ወደ ውጭ በር እየተጣደፈች ስታመራ ይመለከታታል::
"ዮሃና ተመለሺ::በዚህ ለሊት የት ልትሄጂ ነው!?" አለች ሳራ ከበሩ ቆማ::ናትናኤል ወደ ሳራ ይዞራል::
"የትም ልህዲ አያገባሽም::" በሩን ልትከፍተው ስትል በቁልፍ እንደተዘጋ ትመለከት እና በቁጣ ወደ ሳራ ትመለከት እና ትመለሳለች::
"ቁልፉን ስጪኝ::"እጇን እየዘረጋች::
"እባክሽ እንደ ሕፃን አትሁኚ::ወደ ቤት ግቢ!"
"እሱን አንቺ አትነግሪኝም... ቁልፉን ስጪኝ::"
"ዮሃና::" ሁለቱም ወደ ናትናኤል ይዞራሉ::
"ነገሩ ምንም ይሁን ምን በዚህ ሰዓት ብትወጪ ተጎጂዋ አንቺ ነሽ::ሲነገ ብታወሩ አይሻልም::ለእሱም ስትይ::"
ዮሃና ከበሩ በባዶ እግሩ የቆመውን ማክቤልን ትመለከተው እና ወደ ሳራ ትመለከታለች::
"ነገ አዘጋጅተሽ ጠብቂኝ::" በትከሻዋ ገፋ አድርጋት የማክቤልን ግንባር ስማ ትገባለች::
"ማክ ግባ እመጣለሁ::"
"አንቺ ጋር ዛሬ ማተኛት እችላለሁ?"
"አዎ የኔ ጣፋጭ::"
እሱ ሲገባ ወደ ናትናኤል ትዞራለች::
"ይቅርታ ናትናኤል ይሄን ክፍል ማከራየት ያልፈለግኩት ለዚህ ነበር::በየቀኑ ባህሪዋ ይቀያየራል::"
"ኢ ት ኢዝ ኦኬይ... ስልክ ተደውሎልኝ ነቅቼ ነበር::"
"እምም... እሺ..." ፊቷን አዙራ ስትገባ ይመለከታታል::
* * *
ሳራ እንደለመደችው በጠዋት ተነስታ ቁርሳቸውን ከሰራራች በኋላ እያቀራረበች እያለ ዮሃና ዩኒፎርሟን ለብሳ ትወርዳለች::
ሳራ ቀና ብላ አይታት :-"ቁርስ ቀርቧል..."
ቦርሳዋን ከትከሻዋ ታወርድ እና በእጇ አንጠልጥላው በተሰላቸ ስሜት ትመለከታታለች::
"ማታ ያልኩሽን ገንዘብ አዘጋጀሽልኝ?"
"የምለፋው.... አንቺ ፓርቲ ለፓርቲ እየዞርሽ እንድትበትኚው አይደለም::"
"ልበትን.. ሁ ኬርስ.... አባዬ ያስቀመጠልኝን ገንዘብ ነው የጠየኩሽ::"
"አስራ ስምንት ዓመት አልሞላሽም...."
"አሃ.... ጥሩ...."ወደ በሩ በፍጥነት ታመራ እና በሩን በርግዳ ትወጣለች::
"እህቴ.... ቁልፌን አስተካኪይልኝ::"አላት ማክቤል::ዞራ በስስት ትመለከተዋለች::
* * *
አቤነዘር እና ናትናኤል ፀጥታ ከሰፈነበት ካፌ ተቀምጠው ከፊታቸው ቡና ተቀምጦ ያወራሉ::
"እምም... የተወሰነ አውቃለሁ::እናት እና አባታቸውን ካጡ በኋላ ቦታ ተቀያየሩ ማለት ይቻላል::ሳራ ወደ እራሷ ስትመለስ ደህና የነበረችው ዮሃና ደግሞ ፍፁም ነው የተለወጠችው::ምን እንደተፈጠረ መረዳት አልቻልኩም::ምን አሰብክ ታዲያ::ቤት ትቀይራለህ?"
"አይ በፍፁም::እስኪ ትንሽ ልያቸው::"
"አዎ ልክ ነህ::እግዚአብሔር ያለምክንያት እዛ ቤት እንድትገባ ፍቃዱ አይሆንም::እርግጠኛ ሆኘ የምነግርህ ሶስቱም በጣም ንፁህ ልብ ያላቸው ልጆች ናቸው::የገጠማቸው ችግር ነው::"
"አይ ሲ..." ደገፍ ይል እና ይተነፍሳል::
"የሆነ የማደርሰው ዕቃ አለኝ::ነገ እንገናኛለን::" ተሰናብቶት ሂሳብ ሊከፍል ሲል አቤነዘር አሻፈረኝ ሲለው ቅር እያለውም ቢሆን ተሰናብቶት ወጥቶ ወደ መኪናው ያመራል::
* * *
መኪና እየነዳ እያለ ስልኩ ሲጠራ መኪናውን ከዳር አቁሞ ያነሳል::
"ሄለው..."
"እንዴት ነህ ናትናኤል::ሳራ ነኝ..."
"ኦውው ሳራ.. እንዴት ነሽ?"
"ደህና ነኝ::እባክህን አንድ ነገር ላስቸግርህ ነበር::"
"ችግር የለውም... ምን ነበር?"
"ወደ ሃያት ሄድኩኝ እና መንገድ ተዘጋጋብኝ::ሹፌሩ ደግሞ ስልኩ አይሰራም::ሥራ ካልያዝክ ማክቤልን ፒክ ታደርግልኛለህ?... በጣም ከይቅርታ ጋር::"
"እምም... ችግር የለውም::የት ነበር የሚማረው?"
መኪናውን ያዞራል::
* * *
ሰዓቱን ሲመለከት ለአንድ ሩብ ጉዳይ ይላል::መኪናውን ከኩርባው ላይ ሲያደርስ ግርግር እና ጩሀት ይመለከታል::መንገዱ በሰዎች ስለተሞላ መኪናውን እዛው ያቆም እና ኮፈኑን ከፍቶ ከሱዚያና የተላከውን እና ከፍቶት ያላየውን ቦርሳ በእጁ ይዞ ኮፈኑን በመዝጋት ቀና ብሎ ሲያስተውል ግርግሩ እና ጩሀቱ ያለው ከሱዚያና እናት ቤት መሆኑን ይመለከት እና ደንገጥ ብሎ ከጎኑ ወዳሉት ሁለት ሴት ወጣቶች ጠጋ ብሎ:-
"ምን ተፈጥሮ ነው?"
አንዷ ዘወር ብላ አስተውላው ከተመለከተችው በኋላ:-
"ያቺ ካናዳ ልጅ ያለቻት እናት አርፈው ነው አሉ::"
"የሱዚያና እናት!?"ድምፁን ከፍ አድርጎ::
"አው.. ሱዚያና... ምስኪን እናት.. እንደው ምን አጣው ብለው ነው በፈጣሪ ሥራ የገቡት::በገመድ ተንጠልጥለው ነው የተገኙት አሉ...."
"በኢየሱስ ስም.."ቦርሳውን ከመሬቱ በድንጋጤ ይጥላል::
Like🥰 Comment📩 Share💫ቀጣዩ እንድለቀቅ
ይቀጥላል...
ግጥሜን ለኢየሱስ
💙እወዳችኋለሁ 💙
---------------------------------------------------------
SHARE
|
@GITIM_ALEM |
|
@GITIM_ALEM |
--------------------------------------------------------
SHARE
Contact me
@abu_ND8