የእምነት ጥበብ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


"የኦርቶዶክስ ክርስትና ጥልቅ ትምህርቶችን እና ጊዜ የማይሽረው እውነቶችን እወቅ።በእምነት ጥበብ በእምነታችን ላይ የተመሰረቱ ትርጉም ያላቸው መልሶችን እናካፍላለን። በመንፈሳዊ ጉዞዎ ላይ እድገትን፣ ግልጽነትን እና የሚያበረታቱ ትርጉም ላለው ንግግሮች እና ግንዛቤዎች ይቀላቀሉ https://www.youtube.com/channel/UCnpcMb39oukTKZAD9ns93ig?sub_confirmation=1.

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri




'https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk' rel='nofollow'>♥️🌹ጋብቻ ምን ማለት ነው⁉️🌹
ጋብቻ እና የዘር ሐረግ ምን ያገናኛቸዋል⁉️
ጋብቻ የሚፈቀደው ከስንት ዓመት ጀምሮ ነው⁉️
ሴት ሙሽራ ከወንድ ሙሽራ ቀኝ ለምን ትሆናለች⁉️
🌹ሙሽሮች በጫጉላ ጊዜያቸው ለምን አይጾሙም⁉️
ያገባሁት ሰው ካልተመቸኝ ብፈታው ምን ችግር አለው⁉️
እንደምንጋባ እርግጠኛ ከሆንን ግብረስጋ ግንኙነት ብንፈጽም ምን ችግር አለው⁉️


ከዚህ በታች ያለውን ቅዱስ ቄርሎስ ዘእየሩሳሌም ኢሳያስ 65፡15 ያለውን ጠቅሶ ሲናገር ማን ትዝ እንዳለኝ ታቃላችሁ ቅባቶች ምስራቅ ጎጃም ውስጥ ብቻ የሚገኙት😁😁😁አይሁዶች በአንድ አካባቢ ብቻ ናቸው፣ ክርስቲያኖች ግን እስከ ዓለም ዳርቻ ይደርሳሉ ቅባቶች እና አይሁዶች አንድ ናቸው

ይሄ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፣ ወደፊት ለሚመጣው መልካም ነገር ሊቀ ካህን ሆኖ የመጣው፤ በመለኮታዊ ቸርነቱ የራሱን ማዕረግ ለሁላችን አካፈለ። በሰው ልጆች መካከል ነገሥታት ልዩ የንግሥና ስልት አላቸው፣ ሌሎች ሊካፈሉት የማይችሉት፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን የእግዚአብሔር ልጅ ስለሆነ፣ ክርስቲያን ተብለን እንድንጠራ ክብር ሰጠን። አንዳንዶች ግን “የክርስቲያን” ስም አዲስ ነው፣ ከዚህ በፊት ጥቅም ላይ አልነበረም ይላሉ። አዲስ ዓይነት አባባሎች እንግዳ ስለሚመስሉ ብዙ ጊዜ ይቃወማሉ። ነቢዩ ይህን አስቀድሞ ተናግሯል፣ “በእኔ ባሪያዎች ላይ አዲስ ስም ይጠራል፣ በምድርም ላይ ይባረካል” ብሏል። አይሁዶችን እንጠይቅ፣ የጌታ ባሪያዎች ናችሁ ወይስ አይደላችሁም? እንግዲያውስ አዲሱን ስማችሁን አሳዩን። በሙሴና በሌሎች ነቢያት ጊዜ፣ ከባቢሎን ከተመለሳችሁ በኋላ እስከ ዛሬ ድረስ አይሁዶችና እስራኤላውያን ተብላችኋል፤ ታዲያ አዲሱ ስማችሁ የት አለ? እኛ ግን የጌታ ባሪያዎች ስለሆንን ያ አዲስ ስም አለን፤ በእርግጥም አዲስ፣ ግን በምድር ላይ የሚባረክ አዲስ ስም። ይህ ስም ዓለምን ያዘው፤ አይሁዶች በአንድ አካባቢ ብቻ ናቸው፣ ክርስቲያኖች ግን እስከ ዓለም ዳርቻ ይደርሳሉ፤ ምክንያቱም የአንድያዊው የእግዚአብሔር ልጅ ስም ስለሚሰበክ ነው።”(The Catechetical Lectures of S. Cyril
)


ይሄ ለቅባቶችም ድንግል ማርያም ጎስቋላ ሥጋን አልያዘችም ለምትሉ ፈውስ ነው አንብቡት


በነጻ የማይገኘ አማዞን ላይ ያሉ መጽሐፎችን በነጸ የምታወርዱበት ነው ስለሚያዘጉባቸው ዶሜን እየቀያየሩ ነው የሚመጡት እና ማንኛውም መጽሐፍ ቶሎ ሳይዘጋ አውርዱ ከዚህ ግቡና ዛሬ ይሰራል ወይ በመጽሐፉ ስም ወይ ደግሞ በጽሐፊው ስም ሰርች ማድረግ ትችላላችሁ "https://z-lib.gs/s/SEVERUS%20OF%20ANTIOCH/?content_type=book&page=1"


የማርያም ምሥጢር!
ድንቅ ነገር እንድናገር ቀሰቀሰኝ፤ አድምጡኝ፣
አስተዋዮች ሆይ! የማርያም ታሪክ በውስጤ ይንቀሳቀሳል፣
ድንቅነቱን ሊያሳይ፤ አእምሮአችሁን አዘጋጁ፣
ጥበበኞች ሆይ! ቅድስት ድንግል ዛሬ ትጠራናለች፤
የብርሃን ታሪኳን በንጽህና እንስማ።
ሁለተኛ ሰማይ፣ የሰማይ ጌታ ያደረበት፣
ከዚያም ተወልዶ ዓለምን ያበራበት።
ከሴቶች መካከል የተባረከች፣ እርግማንን ያስወገደች፣ ፍርድን ያቆመች።
ትሑት፣ ንጽሕትና በውበት የተሞላች፣ ስለዚህ ስለ እርሷ ምን ልበል!
የድሆች ልጅ፣ የነገሥታት ጌታ እናት የሆነች፣
ለተቸገረው ዓለምም ከእርሱ ሕይወትን ሰጠች።
ከአብ ቤት ሀብትንና በረከትን የተሸከመች መርከብ፣
መጥታም በድሃ ምድራችን ላይ ሀብትን ያፈሰሰች።
ያለ ዘር ብዙ ፍሬ ያስገኘች መልካም መሬት
፣ ያልታረሰች ሆና ብዙ ምርት አበቀለች።
በሟቾች መካከል ሕይወትን የወለደች ሁለተኛ ሔዋን፣ የእናቷን የሔዋንን ሒሳብ ከፍላ ቀደደችውም።
የተደናገጠችውን አሮጊት ሴት እርዳታ የሰጠች ድንግል፤ እባቡ በጣላት ውድቀት ውስጥ ሆና አስነሳቻት።
ለአባቷ የክብር ልብስ የሸመነችና የሰጠች ልጅ፤ በዛፎች መካከል ራቁቱን ስለነበር ራሱን ሸፈነ።
ያለ ትዳር አንድነት ድንቅ በሆነ መንገድ እናት የሆነች ድንግል፣ በድንግልናዋ ምንም ሳይለወጥ የቀረች እናት።
ንጉሥ የሠራውና የገባበትና የኖረበት ቆንጆ ቤተ መንግሥት፤
ሲወጣም ከእርሱ በፊት በሮቹ አልተከፈቱም።
ድንግል፣ እንደ ሰማያዊ ሠረገላ ጌታን ተሸከመች፣ ፍጥረትንም በክብር አነገሰች።
ሙሽራ፣ ሳታየው ፀነሰች፣ ከአባቱ ቤት ሳትሄድ ሕፃን ወለደች።
ይህችን ውብ ሴት እንዴት ልሳላት? በተራ ቀለማት፣ ለእርሷ በማይመጥኑ?
ውበቷ ከቃላቶቼ በላይ ግሩም ነው፤ ስለ እርሷ ለማሰብ እፈራለሁ።
ፀሐይን በሙቀትና በብርሃን መግለጽ ይቀላል፣ የማርያምን ታሪክ ግን እንዴት እገልጻለሁ?
ምናልባት የሰማይ ብርሃን በቀለም ይያዝ ይሆናል፣ ስለ እርሷ የሚነገረው ግን በስብከት አይደርስም።
ማንም ቢሞክር፣ እንዴት ይግለጻት?
ከማን ጋርስ ያወዳድራት?
ከድንግሎች፣ ከቅዱሳን፣ ከንጹሐን ጋር?
ከባለትዳሮች፣ ከእናቶች፣ ወይስ ከአገልጋዮች ጋር?
የተከበረችው አካል የድንግልናና የወተት ምልክት አለው፣ ድንግልናና ምጥ ሳይኖር መውለድ፤ ማን ይመስላታል?
ከድንግሎች ጋር ያለች ትመስላለች፣ ግን ደግሞ ልጁን እያጠባች እንደ አገልጋይ አያታለሁ።
ከዮሴፍ ጋር እንደምትኖር እሰማለሁ፣ ግን ደግሞ ከትዳር ግንኙነት ውጭ እንደሆነች አያለሁ።በድንግሎች መካከል ላስቀምጣት ስል፣ የምጥ ጩኸት ይሰማኛል።
ዮሴፍን ሳስብ፣ ያገባች ሴት ልትሆን ትችላለች ብዬ እገምታለሁ፣
ነገር ግን ማንም እንደማያውቃት አምናለሁ።
የምታፈራ እናት ልጅ እንደምትሸከም አያለሁ፣ ግን ደግሞ ድንግል ትመስላለች።
ድንግል፣ እናት፣ ባል የሌላት ሚስት ነች፤ እንዴትስ እገልጻታለሁ?
ምናልባት ለመረዳት ይከብዳል እል?
ፍቅር እንድናገር ያነሳሳኛል፣ ትክክልም ነው፤ ግን ስለ እርሷ መናገር ይከብደኛል፤ ምን ይሻለኛል?
እኔ እንደማልችልና አሁንም እንደማልችል በግልጽ እናገራለሁ፣ በፍቅር ተነሳስቼ ስለ እርሷ ድንቅ ታሪክ ለመናገር እመለሳለሁ።
ፍቅር ሲናገር አይነቅፍም፣ የሚናገረው ሁሉ ያማረና ለሚሰማውም ጥቅም ያለው ነው።
በግርማና በድንቅ ስለ ማርያም እናገራለሁ፣ ምድራዊት ሴት እስከዚህ ክብር ስለደረሰች።
ጸጋ ራሱ ልጁን ወደ እርሷ አዘነበለው ወይስ እርሷ በጣም ቆንጆ ስለነበረች የእግዚአብሔር ልጅ እናት ሆነች?
እግዚአብሔር በምድር ላይ በጸጋ መውረዱ ግልጽ ነው፣ ማርያምም በንጽህናዋ ተቀበለችው።
ትህትናዋን፣ የዋህነቷንና ንጽሕናዋን ተመለከተ፣ ከትንሹዎች ጋር መኖር ስለሚቀለው በእርሷ ውስጥ ኖረ። “በገርና ትሑት ላይ ካልሆነ በሌላ ማን ላይ እመለከታለሁ?” ተመለከተና በእርሷ ውስጥ ኖረ፣ ምክንያቱም ከሚወለዱት መካከል ትሑት ነበረች። እርሷም ራሷ እንደተናገረች፣ ትሕትናዋን ተመልክቶ በእርሷ ውስጥ ኖረ፣ በዚህ ምክንያት ትመሰገናለች፣ ምክንያቱም በጣም ደስ የምትል ነበረች።
ትህትና ፍጹምነት ነው፣ ስለዚህ ሰው ለመጀመሪያ ጊዜ እግዚአብሔርን ሲያይ በትህትና ይሠራል።
1 ሙሴ ትሑት ነበር፣ ከሁሉም ሰዎች መካከል ታላቅ፤ እግዚአብሔር በተራራው ላይ በራዕይ ወደ እርሱ ወረደ።
እንደገና ትህትና በአብርሃም ይታያል፣ ምንም እንኳን ጻድቅ ቢሆንም፣ ራሱን ትቢያና አመድ ብሎ ጠራ።
ደግሞም ዮሐንስ ትሑት ነበር፣ ምክንያቱም የሙሽራውን፣ የጌታውን ጫማ ለመፍታት እንደማይገባው እያወጀ ነበር።
በትህትና፣ በየዘመኑ ጀግኖች ደስ የሚያሰኙ ሆነዋል፣ ምክንያቱም ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብበት ታላቅ መንገድ ነው።
ነገር ግን በምድር ላይ እንደ ማርያም ዝቅ ያለ ማንም አልነበረም፣ ከዚህም ማንም እንደ እርሷ ከፍ ያለ እንዳልነበረ ግልጽ ነው።
ጌታ ለመገለጥ የሚመርጠው ትሑታንን ነው፤እናቱ አደረጋትና በትህትና ማን ይመስላታል?
ከእርሷ የበለጠ ንጹሕና የዋህ ሌላ ቢኖር፣ በዚህ ውስጥ ይኖር ነበርና በዚያኛው ውስጥ ለመኖር ይተዋት ነበር።

(ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ: on the mother of God )


የተባረከች ድንግል ማርያም፣ የእግዚአብሔር እናት፣ ምስጋና
ቸር አምላክ፣ በርህን ለክፉዎችና ለኃጢአተኞች የከፈትክ፣ ውበትህን አይቼ እንድደነቅ ግባ በልኝ።
የምሕረት መጋዘን፣ ፍትሕ የሌላቸው እንኳን ከአንተ የሚጠግቡበት፣ከአንተ ልመገብ፣ ምክንያቱም አንተ ለሚካፈልህ ሙሉ ሕይወት ነህና።
የነፍስን ሐዘን የሚያረሳ ጽዋ፣ ጠጥቼ ከአንተ ጥበብን ላገኝና ታሪክህን ልተርክ።
ያለጸጸት ለሰው ዘር ክብረትን የምትሰጥ፣ በመዝሙርህ ውብ ነገሮችን ልዘምር።
የልዑል ልጅ፣ ትሕትናን የመረጥክ፣ ስለ ታላቅነትህ ልናገር እርዳኝ።
ከሰማይ የወረድክ፣ ከእኛ ጋር መኖርን የወደድክ፣ ቃሌ ወደ ላይ ከፍ ይበልና ይማጸንህ።
ጌታችን ሆይ፣ ሕያው ቃልና ጥልቅ ንግግር ነህ፣ ለሚሰማህም ጸጋን የምትሰጥ።
ስለ አንተ የሚናገር ሁሉ ከአንተ በተነሳ ነው የሚናገረው፣ ቃል፣ አእምሮና ሕሊናም አንተ ነህና።
ያለ አንተ ሐሳብ አይመላለስም፣ ያለ ፈቃድህም ከንፈር አይንቀሳቀስም።
ያለ ትእዛዝህ ድምፅ አይሰማም፣ ያለ ቸርነትህም መስማት አይቻልም። እነሆ፣ ጸጋህ በሩቅም በቅርብም ሞልቷል፤
በርህ ለጻድቅም ለኃጢአተኛም ወደ አንተ ክፍት ነው።
ሁሉም በአንተ ባለጸጋ ነው፣
አንተም በልግስና ትሰጣለህ፤
ንግግር ከአንተ በውበት ይበልጽግና ለአንተ ይናገር።
የድንግል ልጅ ሆይ፣ ስለ እናትህ እንድናገር ፍቀድልኝ፣
ስለ እርሷ የሚነገረው ነገር ከእኛ በላይ መሆኑን እያወቅሁ።

(ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ: on the mother of God )


“ ልጄ ስለሆንክ፣ በሕፃንነቴ ዜማ አጽናናሃለሁ። እናትህ ስለሆንኩኝ፣ አከብርሃለሁ። የወለድኩህ ልጄ፣ ከእኔ በላይ አንተ ነህ። ጌታዬ፣ ብሸከምህም፣ የምትደግፈኝ አንተ ነህ… ሰማይ በክንፎቹ ይደግፈኝ፤ ከእርሱ በላይ እኔ የተከበርኩ ነኝና። ሰማይ በእውነት እናትህ አልነበረም፣ ነገር ግን አንተ እንደ ዙፋንህ አደረግኸው። የንጉሥ እናት ከዙፋኑ ምን ያህል የበለጠ ክብርትና የተከበረች ናት። ጌታ ሆይ፣ እናትህ እንድሆን ስለወደድክ አመሰግንሃለሁ። በጣፋጭ መዝሙሮች ምስጋናህን አከብራለሁ… ሔዋን፣ የመጀመሪያ እናታችን፣ አሁን ትስማኝና ወደ እኔ ትምጣ… ፊቷን ትግለጥና ታመሰግንህ፣ ምክንያቱም ኀፍረቷን አስወግደህልናል። የፍጹም ሰላም ድምጽ ትስማ፣ ሴት ልጇ ዕዳዋን ከፍላለችና። እባቡ፣ አታላሏ፣ ከደረቴ በበቀለው ቡቃያ ተቀጥቅጧል። በአንተ ኪሩቤልና ሰይፉ ተወስደዋል፣ አዳም ከገነት ወደተባረረበት እንዲመለስ።” (ቅዱስ ኤፍሬም ማርያም መዝሙሮች፣ 19


“ነቅተሽ፣ በገናዬ፣ የማርያምን ድንግልን ለማመስገን በሽቦዎችሽ ላይ ቃኝ። ድምጽሽን ከፍ አድርገሽ፣ ይህች ድንግል፣ የዳዊት ልጅ፣ ለዓለም ሕይወትን ያመጣችው እጅግ ድንቅ ትውልድ ዘምሪ… በፍቅር የሚደነቅ በፍርሃት ይመለከታታል፤ የማወቅ ጉጉት ያለው ፈላጊ በኀፍረት ይዋጣል፣ ጆሮውም ይደፈናል፣ ድንግልናዋ ሳይጣስ የወለደችውን እናት ለመመርመር እንዳይደፍር… በማርያም ማኅፀን ውስጥ ሕፃን ሆነ። ከዘላለም ከአብ ጋር እኩል የሆነው እርሱ ነው። ከራሱ ግርማ ሞገስ አካልን ሰጠን፣ የራሳችንንም ድካም አገኘ። በውስጣችን ሕይወትን በማስገባት ዳግመኛ እንዳንሞት ከእኛ ጋር ሞተ… ማርያም ከአብ የበረከት ዝናብ የወረደባት ገነት ናት። ከዚያ ዝናብ እራሷ የአዳምን ፊት ረጨችው። በዚህም ከሞት ተነሳ፣ በሲኦል በጠላቶቹ የተቀበረው ከመቃብር ተነሳ… እነሆ፣ ድንግል እናት ሆነች፣ ድንግልናዋን ሳይሰበር ጠበቀች… የእግዚአብሔር እናትና በተመሳሳይ ጊዜ አገልጋይ፣ የጥበቡም ሥራ ሆነች… በኤደን ሔዋን ዕዳ ውስጥ ገባች፣ ዘሯም በትውልዳቸው ለሞት የተፈረደበት ዕዳ በትልልቅ ፊደላት ተጻፈ። ክፉ ጸሐፊ የሆነው እባቡ ጻፈው፣ ፈርሞ በሽንገላው ማኅተም አጸደቀው… ሔዋን ለኃጢአት ዕዳ ነበረባት። ገር ግን ዕዳው ለማርያም ቀርቶ ነበር፣ ሴት ልጅ የእናቷን ዕዳ እንድትከፍል፣ በእናቷ እንባ ለትውልድ ሁሉ እንደ ርስት የተላለፈውን የሞት ጽሑፍ እንድትሽር… ማርያም ንጽሕት ድንግል ስለነበረች – ምድር ገና ከመታረስ፣ በኤደን በረከት ምድር አስቀድሞ እንደተመሰለች – ከደረቷ የሕይወት ዛፍ በቅላለች፤ ጣዕሙም… ለነፍሳት ሕይወትን ይሰጣል።…” ቅዱስ ኤፍሬም Hymns on the Blessed Mary, 18


በነገራችን ላይ በሥረዓት ዙሪያ እንዴ ኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን የሚያምር እና የጥንት ሥርዓት ያለው የለም በተለይ ከንቂያ በፊት ያለው የአባቶች ትምህርት ስታነቡ የዚያኔዋን ቤተክርስቲያን ሥርዓት የምታገኙት ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ካለባበስ ጀምሮ ምናምን..። የግብጽ ቤተ ክርስቲያን በሥርዓት ዙሪያ እንኳን ከኢትዮጵያ መወዳደር አትችልም ። በነሱ የምቀናው ካህናቶቹ ከአማኙ ጋ ያላቸው ግንኙነት ፓትሪያሪኮቹ የሚጽፋቸው መጸሐፎች ስታዩ የእኛ ግን ምን ሁነው ነው ትላላችሁ የነሱን ትጋት አይታችሁ በዚህ በዚህ እቀናለሁ እና ደግሞ ሁሉም ለሥራ ያላቸው ትጋት ሲባል እሰማለሁ


አዳም ከሰማይ ወደ ምድር ያመጣውን፣ ክርስቶስ ከምድር ወደ ሰማይ አሳረገው፤ አዳምም ያለ ኃጢአትና ያለፍርድ ወደ ጥፋትና ሞት ፍርድ ያመጣውን፣ ክርስቶስ ይህን የማይበሰብስና የሞት ነፃ አደረገው፤ በምድር ላይ ኃጢአትን የመተው ሥልጣን እንዲኖረው፣ ከመቃብርም አለመበስበስን እንዲያሳይ፣ በሲኦል ላይ ሞትን እንዲያጠፋ፣ ለሁሉም ትንሳኤን እንዲሰብክ። ቅዱስ አትናቲዎስ


ድንግል ማርያም የወደቀውን ሥጋ አልያዘችም ለምትሉ ቅዱስ አትናቴዎስ እንድህ ይላችኃል
"ምንም እንኳን ለእኛ ሰው የሆነው ከእኛ በኋላ ቢሆንም፣ በሥጋም ወንድማችን ቢሆንም፣  ከሁላችን ‘የመጀመሪያ ልጅ’ ተብሎ ይጠራል። ምክንያቱም፣ ሁሉም ሰዎች በአዳም መተላለፍ ምክንያት በጠፉበት ጊዜ፣ ሥጋው — የቃል አካል እንደመሆኑ — ከሌሎች ሁሉ በፊት ድኖና ነፃ ወጥቷል።" St. Athanasius Discourse 2 Against the Arians :61
አይደለም ድንግል ማርያም ጌታ ኢየሱስ እራሱ የያዘው የወደቀውን ሥጋ ነው ያን ሥጋ የቃል አካል ስለሆነ ነው የዳነው እና ነጻ የወጣው እያለህ ነው ። በእናንተ አካሄድ ከሄድን ጌታ ኢየሱስ ሳይሆን በኩር ድንግል ማርያም ልትሆን ነው። ብዙ ልል ነበር ግን ይሄ በቂ ይመስለኛል።
@WisdomOfTheFaith


ስሜ መሸ በከንቱ ለሚመስላችሁ በዚያው ስሜ ሰማኝ ነው የተረጎመልኝ ግን AI ነው😁


ትምህርተ ጽድቅ dan repost
Church and Civil Laws, 13th Century A.D. page 6) (ሄኖክ ኃይሌ (ዲ/ን)፣ ተአምረ ማርያምና አንዳንድ ጉዳዮች)

- በራእየ ማርያም ውስጥ የዘረኝነት በሽታ የጸናበት አካል ያልኾነ ሥርዋጽ አስገብቷል። ራእየ ማርያም መጀመሪያ የተጻፈው በግሪክ ሲኾን ወደ ሀገራችን ከመምጣቱ በፊት ወደ ዐረብኛ ተተርጉሟል። ከ39 በላይ የራእየ ማርያም ቅጂዎች ይገኛሉ። ወደ አማርኛ የተተረጎሙ የ1961 የተስፋ ገብረ ሥላሴ ትርጉም ቀሲስ ዶ/ር አምሳሉ አላገኘኹትም ይላሉ። 1985 በተስፋ ገብረ ሥላሴ የተተረጎመ እና በ2007 በአክሱም ማተሚያ የተተረጎመ አመሳክረው ጥናት አቅርበዋል። (አምሳሉ ተፈራ (ቀሲስ፡ ዶ/ር)፣ ነቅዓ መጻሕፍት፣ 2011 ዓ.ም፣ ገጽ 294-302)

- "ማክሰኞና ሐሙስ እባብን የገደለ እንደ ዐርባ ቀን ሕፃን ይኾናል" የሚል ትምህርት የመጣው በደብረ አስቦ ለነበሩ ገዳማውያን ዋናዎቹ ፈተናዎች እባብና ዘንዶ ስለ ነበሩ ነው። በዚያ ዘመን ዕባቡንና ዘንዶውን መታገሥ፣ አልፎም ማጥፋት ጽናትን ማሳያ ነበርና። (ዳንኤል ክብረት፣ ኢትዮጵያዊው ሱራፊ፣ 2011 ዓ.ም፣ ገጽ 660፣ የግርጌ ማስታወሻ 1974)። ይህ አባባል በመጀመሪያ ቅጅ ላይ የለም፤ ሥርዋፅ ኾኖ የገባው ኋላ ነው። የገባው ግን ከላይ የተገለጸውን ሐሳብ ለማስጠበቅ ነበር። መናፍቃን ግን ይህን ለጥጠው "እባብን የገደለ ይጸድቃል" እያልን እንደ ኾነ ለማስቆጠር ይጥራሉ። ይህ ግን Straw man Fallacy (ያልተባለን ነገር እንደ ተባለ አድርጎ የማሰብ ስሕተት) ነው። ይህ አካሄድ ቅንነት የሌለው ጥላቻንና ማነወርን ማዕከል ያደረገ ስሑት አካሄድ ነው።

- በዚቅ ላይ ደግሞ "ኦ አምላክ መርቆሬዎስ ዘአሠርገውከ ሰማየ " የሚል ንባብ በሥርዋፅ ገብቶ መገኘቱን ልብ እንላለን። የተሐድሶ መናፍቃንም እንዲህ ብለን እንደማናምንና ይህ ሥርዋፅ እንደ ኾነ ቢረዱም የመስማት ፍላጎት የሌላቸውና እነርሱ የሚሉትን ብቻ እንድንቀበል የሚፈልጉ ስሑታን ስለ ነበሩ ያልኾኑ ነገሮችን ሲያራግቡ ተመልክተናል። ሌሎችም ይህን የመሰሉ ጉዳዮች ሊገኙ ይችላሉ። ያን ኦርቶዶክሳዊ በኾነ መንገድ በጉዳዩ ላይ በሥርዓትና በጥንቃቄ ጥናት ለሚያደርጉ በጉዳዩ ብዙ ለቆዩበት ለነ ቀሲስ ዶ/ር አምሳሉ ተፈራ ዓይነት ለቀቅ ብናደርግ መልካም ነው። በኹሉ ነገር ላይ ራስን አዋቂ አድርጎ ያውም በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ንባብና ጥናት ሳያደርጉ ኦርቶዶክሳዊ ባልኾነ መንገድ አዋልድ መጻሕፍትን እያዩ ደረቅ ትችት ማቅረብ አግባብ አይደለም። ደረጃን እና አቅምን በመረዳት በማያውቁት ነገር በመሰለኝ ከማውራት እንቆጠብና ብዙ ዓመታትን በሥነ ድርሳናት ለቆዩት አካላት በአክብሮት ቦታውን ለቀቅ ብናደርግ መልካም ነው። በችኩልነትና በድርቅና የቤተ ክርስቲያን አረዳድ ኹሉ በኔ በር በኲል ሲያልፉ ነው የሚያገኙት ከሚያሰኝ አካሄድ ብንቆጠብ መልካም ነው።


ትምህርተ ጽድቅ dan repost
ይህ ማለት ግን ደጋግሜ እንዳልኹት በአዋልድ መጻሕፍት ላይ ያሉን በሙሉ ከዳር እስከ ዳር ምንም ችግር ስለሌ ተቀበሉ ማለት አይደለም። እንዲህም ያለ የለም፤ ያልተባለን ነገር እንደ ተተባለ አድርጎ ማቅረብም Straw man Fallacy ነው። ማን ነው እንዲያ ያለው? ማንም እንዲያ ሊል አይችልም። ሌላው ቀርቶ አንድ በሌላ ቤተ እምነት የቆየ ሰው ኦርቶዶክስ መኾን ሲፈልግ በአእማደ ምሥጢራት አምኖ ተምሮ ምሥጢራትን ፈጽሞ አካል ይኾናል እንጂ አዋልድ መጻሕፍትን በአጠቃላይ ትቀበላለህ አትቀበልም እየተባለ አይጠየቅም፤ እንዲያ እንዲጠየቅ የሚያዝ ሕግም ሥርዓትም የለም። በሌለበትና ባልተባለው በድፍረትና በምንአለብኝነት "ገድላት ድርሳናትን አልቀበልም ማለት ትችላለህ ችግር የለውም ዓይነት አካሄድ ከየት የመጣ ነው?" የሌለ ነገር እየተባለ እንዴት ውዝግብ ይፈጠራል? ይህን አካሄድ ብንተወውና ትክክለኛ በኾነውን መንገድ ትምህርቱን በሥርዓቱ ብናቀርብ መልካም ነው። ሌሎችም ያላሰቡትን ጥያቄ እየፈጠርን ባናደክማቸው መልካም ነው። በአዋልድ መጻሕፍት ውስጥ ስሕተት ሊኖር እንደሚችል ማሳያ በማቅረብ እንቋጭ።


አዋልድ መጻሕፍት እና አንዳንድ ስሕተቶች

1) የትርጒም ስሕተት ሊኖር ይችላል። ለምሳሌ አንቀጸ ብርሃን ላይ

«ወኢያኀትዉ ፡ ውስቴታ ፡ ማኅቶተ ።»

በዛሬው ጥቆማዬ ለማሳየት የፈለኩትና በብዙ ቦታ ያገኘኹት የመጀመሪያው የትርጕም ግድፈት፥ የቅዱስ ያሬድ ድርሰት በኾነው አንቀጸ ብርሃን ላይ ይገኛል። ክፍለ ጸሎቱም፥ በልሳነ ግእዝ፦ «አንቲ ፡ ውእቱ ፡ ተቅዋም ፡ ዘወርቅ ፡ ዘኢገብራ ፡ እደ ፡ ኬንያ ፡ ዘሰብእ ። ወኢያኀትዉ ፡ ውስቴታ ፡ ማኅቶተ ። አላ ፡ ለሊሁ ፡ ብርሃነ ፡ አብ ።» የሚለው ነው።

ትርጕሙም፦ «የብልኻተኛ እጅ ያልሠራት፣ በውስጧም መብራት የማያበሩባት የወርቅ መቅረዝ አንቺ [ማርያም] ነሽ። የአብ ብርሃን ይበራባታል እንጂ፤» ወይም፦ «የብልኻተኛ እጅ ያልሠራት የወርቅ መቅረዝ አንቺ ነሽ። በውስጧም መብራት አያበሩባትም። እርሱ የአብ ብርሃን ይበራባታል እንጂ፤» ማለት ነው።

በዚኽ ክፍለ ጸሎት፦ «የማያበሩባት» መባል የሚገባው ቃል፥ በብዙ መጻሕፍት፦ «የሚያበሩባት» ተብሎ ተተርጕሟል። ግእዙ፦ «ወኢያኀትዉ» እያለ፥ «የሚያበሩባት» ብሎ መተርጐም አለማስተዋል ነው። ከቃሉም ባሻገር፦ «አላ ለሊሁ ብርሃነ አብ» የሚለው ሐረግ ራሱ ትርጕሙን ያመላክታል። ምሥጢሩም፦ ‹መቅረዝ› በተባለች እመቤታችን ማርያም ላይ፥ የእግዚአብሔር አብ ብርሃን [ወልድ] እንደሚበራባት እንጂ ሌላ መብራት እንደማያስፈልጋት ያጠይቃል። ‹የአብ ብርሃን› የተባለም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ነገር ግን ይኼን ምሥጢር በሚያፋልስ አገላለጽ፦ «የሚያበሩባት» ተብሎ ተተርጕሟል። (ኤፍሬም የኔሰው (ዲ/ን)፣ የትርጒም ግድፈቶች በጸሎት መጻሕፍት በሚል ካዘጋጀው ጽሑፍ የተወሰደ)


«ዘሠረፀ ፡ እምአብ ፡ ወእምወልድ ፡ ዘነሥአ ።»

በኀሙሱ ሰይፈ ሥላሴ፥ በግእዙ ጸሎት፦ «አአምን ፡ ሥልሰ ፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ዘወፅአ ፡ እምአብ ፡ ወእምወልድ ፡ ዘነሥአ ፡ ከመ ፡ ይቀድሶ ፡ ለኵሉ ፡ ዐለም ።» የሚል ኀይለ ቃል አለ። ትርጕሙም፦ «ዐለሙን ኹሉ ይቀድሰው ዘንድ ከአብ በሠረፀ፣ ከወልድ በተሰጠ መንፈስ ቅዱስ አምናለኹ፤» ማለት ነው። እኔ ባየኋቸው አንዳንድ መጻሕፍት ላይ ግን፦ «.... ከአብ እና ከወልድ በሠረፀ (በወጣ) በመንፈስ ቅዱስ አምናለኹ፤» ተብሎ ተተርጕሟል። የዶግማ ተፋልሶን የሚያመጣ የተሳሳተ አተረጓጐም ነው። (ኤፍሬም የኔሰው (ዲ/ን)፣ የትርጒም ግድፈቶች በጸሎት መጻሕፍት በሚል ካዘጋጀው ጽሑፍ የተወሰደ)

-ግእዙ አንድ ባሕርይ የሚለውን ኹለት ባሕርይ ብለው መጽሐፈ ባሕርይ ላይ የተረጎሙት ንባብ አለ። ስሕተት ነው። ክሕደት ነውና።

- ንሕነሰ ነአምን ከመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኅቡራነ ህላዌ ወኅቡራነ መንግሥት ኅቡራነ ራእይ ወኅቡራነ መለኮት፦ እኛ ግን አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ 'በአካል አንድ' በመለኮት አንድ እንደ ኾኑ ..." ይላል። በዚህ መንባብ ውስጥ ሥላሴ በአካል አንድ መኾናቸውን የሚገልጽ የለም። ይህ ዳኅፅ ነው። ጠማማ ልቡና ያለው ያነበበው እንደ ኾነ አባ ጊዮርጊስን ባላሉት እንዳሉት አድርጎ ሊናገር ይችል ይኾናል።
(ኅሩይ ኤርምያስ (መ/ር፣ ተርጓሚ)፣ 2001 ዓ.ም፣ ምዕራፍ ስድስት የጥምቀት ምንባብ፣ ገጽ 73)።

2) ሥርዋፅ ኾኖ የገቡ አሉ። ለምሳሌ፦

- በሚያዝያ 10 በሚነበበው ስንክሳር ላይ የተቀመጠው ‘“ወሰብአ ኢትዮጵያሰ ኢይሲሙ ሊቀ እማዕምራኒሆሙ’ /የኢትዮጵያ ሰዎች ከሊቃውንቶቻቸው ጳጳስ አይሹሙ/ የሚልን በ318ቱ ሊቃውንት የተነገረ አንቀጽ በመተላለፋቸውና በንጉሥ ሐርቤ ዘመን ጵጵስናን በመጠየቃቸው ምክንያት ድርቅ መቅሠፍት ሆኖ ወረደባቸው’ የሚል የሐሰት ታሪክ አንዱ ነው፡፡ ይህንን የውሸት ታሪክ ግብፃውያኑ ሆን ብለው ኢትዮጵያን ለማስፈራራት የጨመሩት አንቀጽ ቢሆንም የ318ቱ ሊቃውንትን ቃል የምታከብረዋ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንም ያለ ጥያቄ አምና ተቀብላው ኖራለች፡፡

የሚገርመው ግብፃውያኑ ይህንን የሐሰት ትርክት ሲጨምሩ ያበላሹት ሦስት መጻሕፍትን መሆኑ ነው፡፡ አንደኛው መጽሐፈ ስንክሳር ፣ ሁለተኛው ፍትሐ ነገሥት ሦስተኛው የኒቅያ ጉባኤ ድንጋጌ ነው፡፡ ይህንን ሥራ በወቅቱ ከነበሩት ጳጳስ ጋር ተስማምቶ የሠራው የፍትሐ ነገሥት አስተጋባኢ Safey Ibn Al-Assal (13 Ad) ነበረ፡፡ ይህንን ስኅተት የግንቦት 2009 ዓ.ም. ርክበ ካህናት ላይ የብፁዕ ዶ/ር አቡነ ገሪማን ቀደምት ጥናታዊ ጽሑፍ እንደማስረጃ በመጥቀስ ከስንክሳር እንዲወጣ ወስኖአል፡፡ በመጻሕፍት ላይ ‘በሊቃውንት ጉባኤ ታርሞና ተስተካክሎ የወጣ’ የሚል አንቀጽ በመጻሕፍት ላይ የምናገኘው ይህ በቤተ ክርስቲያኒቱ የኖረ አሠራር ስለሆነ ነው፡፡

የሚገርመው በእኛ ቤተ ክርስቲያን ይህ ውሳኔ ከመወሰኑና ከመታረሙ አስቀድሞ ግን የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ባሳተመችው የፍትሐ ነገሥት አዲስ ቅጂ ላይ ‘ይህንን የኢትዮጵያ ሰዎች ከሊቃውንቶቻቸው ጳጳስ አይሹሙ’ የሚል አንቀጽ ስኅተት መሆኑን በመግለጽ አብራ እንደሚከተለው ከእርማት ጋር አሳትማዋለች :-

‘The Ethiopians are not to have a Patriarch from their scientists or by their own choice alone because their patriarch should be under the hand (authority) of the one on the chair of Alexandria’ [This again is wrong, because the council of Nicea did not have any knowledge of Ethiopia which did not have a bishop at the council and did not have a bishop until St. Athanasius ordained Fremenatous for them after the council of Nicea]

‘ኢትዮጵያውያን ከሊቃውንቶቻቸው መካከል በራሳቸው ምርጫ ብቻ ፓትርያርክን ሊሾሙ አይገባቸውም፡፡ ምክንያቱም ፓትርያርካቸው በእስክንድርያ መንበር ሥልጣን ሥር መሆን ይገባዋል’ [ይህም ዳግመኛ ስኅተት ነው ፤ ምክንያቱም የኒቅያ ጉባኤ በጉባኤው ወቅት ጳጳስ ስላልነበራት ኢትዮጵያ ምንም የሚያውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ኢትዮጵያም ቅዱስ አትናቴዎስ ከኒቅያ ጉባኤ በኋላ ፍሬምናጦስን እስከሾመላት ድረስ ጳጳስ አልነበራትም] (Al Magmou Al-Safawy Le Ibn Al Assal – The Collection of


ትምህርተ ጽድቅ dan repost
ምእመናን እንዲረዱ ማድረግ የሚገባን መሠረታዊውን የታምራትን አረዳድ ነው። ተአምር በቃ እንደ ተአምር የሚወስዱት መኾኑን ልብ ማለት ይገባል። መቼስ ተአምራትን እንደ ተለመደ ክስተት አድርገን ብቻ እንውሰዳቸው ካልን ትልቅ ችግር ውስጥ የምንገባ መኾኑን አንዘነጋም። አረዳዳችን ካልተስተካከለ ኦርቶዶክሳዊ መኾን አንችልም። ሕሊናችንን አበዋዊ ለማድረግ መጣር ይጠበቅብናል። የአበውን አረዳድ ትተን በኛ መጠን ልክ ብቻ ነገሮችን የምንቃኝ ከኾነ መጽሐፍ ቅዱስንም ቢኾን የመቀበል ዕድላችን አናስ ይኾናል። ስለዚህ በጣም በጥንቃቄ እና በእርጋታ በትሕትናም ኾኖ አካሄድን መመርመር ያስፈልጋል።

መርሳት የሌለብን ነገር "አዳኛችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ አምላክን ያለምንም እንከን የወለደች የአምላክ እናት እና ቅዱሳን የሚያደርጉትን ልዩ ተአምራት በንጽሕና፣ በፍጹም እምነት በፍጹም ነፍስና በፍጹም ልብ ኾነው የማይቀበሉ ነገር ግን ይህን ማድረግ አይችሉም በማለት የሚያሾፉ፣ በራሳቸውም ሐሳብ አጣመው የሚተረጒሙ፣ በራሳቸው ሐሳብ ብቻ የሚመዝኑ፣ ውግዘት የሚገባቸው መኾናቸውን የሚጠቁሙ ምንባባት ኹሉ አሉ። (The Synodikon of Orthodox)። በተአምረ ማርያም መቅድም ላይ ያለውንም ግዝት የምናውቀው ነው። ስለዚህ ስላልመሰለን ብቻ ቸኩለን ሌላ ባዕድ ነገር ለማምጣት ባንጥር መልካም ነው።

¤ በአዋልድ መጻሕፍት ውስጥ ያሉ ጸነን የሚሉ ምንባባት ይውጡን?

ጸነን የሚሉ ምንባባት ይውጡ ከማለት ይልቅ የሚሻለው አረዳዳቸውን ማወቅ ነው። ትክክል ቢኾኑ እንኳን ጸነን ስለሚሉ እያሉ በራስ የመረዳትና የማሰብ መጠን ልክ አድርጎ ማሰብ ወደ ከባድ ሌላ ስሕተት ሊወስድ ይችላልና። ኹሉን ነገር በራሱ መጠን ልክ አድርጎ ማሰብ የሚፈልግ ሰው እንዴት ኾኖ ኦርቶዶክስ ሊኾን ይችላል? ይህ ሰው ኋላ ሃይማኖትን በራሱ መጠን ልክ አድርጎ ወደ መረዳት እንደማይወርድ ማን እርግጠኛ ይኾናል? የአረዳድ መንገዱ ስሑት ከኾነ ያን አቅንቶ መሠረታዊ በኾነው የክርስትና ትምህርት መሠረት ላይ እምነቱን እንዲተክል ማድረግ ይገባል እንጂ እምነቱን በሥነ አመክንዮው ልክ አድርጎ እንዲያስብ የሚያደርግ በር መክፈት ተገቢ አይደለም።

ለምሳል "ፍጥረት ኹሉ እመቤታችንን ለማመስገን ተፈጠረ" የሚል ንባብ ያየ ሰው ኦርቶዶክሶች ቅድስት ድንግል ማርያም ያመልኳታል ከሚለው ቀድሞ በንጹሕ ልቡና አረዳዱን ይፈልጋል። አይ ይሄ ንባቡ ጸነን ይላልና ይውጣ ቢባል፤ ይህን አካሄድ የለመደ ሰው ምን ሊኾን ይችላል? ደረቅ ንባብ እያየ መልእክቱን ከመፈለግ ይልቅ ይጸናልና ይውጣ ወይም አልቀበልም ወደ ማለት አይወርድምን? እነ መርቅያንን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ቆነጻጽለው የሉቃስ ወንጌል ላይ ወስዶ የጣላቸው፣ እነ ሉተርን በሕሊናዬ ውስጥ ካለው ሐሳብ ጋር ይጋጫል ብሎ ከማሰብ የተነሣ የያዕቆብን መልእክት ገለባ መልእክት ለማለት የዳረገው ምን ኾኖ ኖሯል? ሌሎች ብዙ መናፍቃን እስካኹን ድረስ ውጭ አውጥቶ የጣላቸው ምንድን ነው? በራሳቸው ልክ መጥነው ማሰባቸውና የራሳቸውን አረዳድ እንዳለቀለት እውነት ማቅረባቸው አይደለምን?

ሊቁ አባ ጀሮም "መርቅያንና ባሲሊድስ፣ እና ሌሎችም መናፍቃን ኹሉ... የእግዚአብሔርን ወንጌል ገንዘብ አላደረጉም። ... ወንጌል ማለት ትርጒሙ (ሐሳቡ፣ መልእክቱ) ነው እንጂ ገጸ ንባቡ ነው ብለን አናስብም፤ በውጫዊ ቆዳው ሳይኾን በውስጣዊ ይዘቱ፣ በስብከቱ ቅጠሎቹ ላይ ሳይኾን በትርጒም ሥሩ ነው እንጂ። በዚህ ኹኔታ መጽሐፍ ቅዱስ ለሚያነቡትና ለሚሰሙት በእውነት የሚጠቅማቸው የሚኾነው ያለ ክርስቶስ የማይነገር ሲኾን ነው፥ ከአባቶች አስተምህሮና አረዳድ ሳይለይ የቀረበ ሲኾን ነው፥ የሚሰብኩት ሰዎች ያለ መንፈስ ቅዱስ የማይናገሩ ሲኾኑ ነው። ... የክርስቶስን ወንጌል በተጣመመ አተረጓጎም የሰዎች ወንጌል እንዳናደርግ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለ ጥንቃቄ መናገር ታላቅ አደጋ አለው።" እንዲል። (in Galat, I, 1. II. M.L. XXVI, c. 386) (ያረጋል አበጋዝ (ዲያቆን)፣ መድሎተ ጽድቅ ቅጽ 2፣ 2013 ዓም፣ ገጽ 176)። እንግዲህ አዋልድ መጻሕፍት የዐሥራው መጻሕፍት ልጆች ናቸው ካልን ልጅ አባቱን በሚመስልበት መንገድ እናየዋለን እንጂ በደረቁ ስሕተት ይገኝባቸዋልና እያልን ባላወቅነው ኹሉ በድፍረት መናገር ድፍረትም አለፈ ሲልም ነውርም ነው።

የአንድን ሰው አረዳዱን ኦርቶዶክሳዊ እስካላደረግነው ድረስ ምንም ያህል ዝቅ ብንል ላይረዳ ይችላል። ከዚያ ይልቅ ራሱን ብቁ ገምጋሚና አስተካካይ፤ የሃይማኖታዊ ጉዳይ ሚዛን በማድረግ ስሕተት ውስጥ እንዳይወድቅ ልንጠነቀቅለት ይገባል። መሠረታዊውን አስተምህሮ የተረዳ ነው፤ ምንም ነገር አያናውጸውም። የተኛውንም ንባብ ከወንጌል እውነታ አንጻር ነው የሚያየው እንጂ በውስጡ ባለ ምናባዊ ሥዕል ችግር አይፈጥርም። አምላክ ሰው ኾነ የሚለው እኛን የማይረብሸን ሙስሊሞችን ግን ለመቀበል የሚከብዳቸው በእነርሱ መጠን ውስጥ አድርገው ስለሚያስቡት ነው። የማስረጃ ዓይነት ቢጠቀስላቸው እንደ ተረት የሚቆጥሩት የተዘጋ አረዳድ ስላለ ነው። ይህን ዝግ የኾነ አረዳድ ካልከፈትንላቸው ነጻ ሊወጡ አይችሉም። ልክ እንዲሁም የኑፋቄ ዝናም ዘንቦባቸው፣ የክሕደት ጎርፍ ውስዷቸው ከእውነተኛው በረት ውጭ የነበሩ አካላትም መጀመሪያ ማጥራት ያለባቸው አረዳዳቸውን ነው። ንባብ ላይ ብቻ እየሄዱ መለጠፍን ማቆም አለባቸው። "ንባብ ይቀትል ወትርጓሜ የሐዩ ሕይወተ" ንባብ ይገድላል ትርጓሜ ሕይወትን ይሰጣል የሚለውን ልብ ይበሉት።

ይህን አካሄድ ትተን ይህን አልቀበልም ይውጣ ይጸናል ዓይነት አካሄድ ከጀመርን ለኔ የሚታየኝ መርቅያን ነው። ጌታችን "በኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ያደርጋል፤ ከእኔም የሚበልጥ ያደርጋል" ሲል ስናነብ ይህ በጣም ይጸናል፤ ተገላበጠ እኮ! ፍጡር ፈጣሪ የሚያደርገን እንዴት ያደርጋል? ከዚያም ብሶ ፈጣሪ ከሚያደርገው በላይ ያደርጋል ይባላልን? ኧረ ይሄስ ይውጣ ሊባል ነውን? "ሰላምን ላመጣ የመጣው አይምሰላችሁ ሰይፍን እንጂ" ሲል ስናነብ እንዴ ጨካኝ ነው ማለት ነውን? ይህን እንዴት ያደርጋል ልንል ነውን? "ከኔ አብ ይበልጣል" ሲል ታዲያ ከአብ የሚያንስ ከኾነ እንዴት ልናመልከው እንችላለን? ይህ ንባብ ያሰናክላልና በሌላ ግልጽ ንባብ ይቀየርልን ልንል ነውን? ጌታ በወንጌል "ነገር ግን እነዚያን በላያቸው ልነግሥ ያልወደዱትን ጠላቶቼን ወደዚህ አምጧቸው በፊቴም እረዱአቸው" ሉቃ 19፥27 ስላለ ግድያን እየበረታታ ነውና ይህ ምንባብ ይውጣ ይባላልን?
መዝ 136፥9 "ሕፃናቶችሽን በዓለት ላይ የሚፈጠፍጥ ብፁዕ ነው" ይላል። ይህ ንባብ ጸነን ያለ ነውና ለመረዳት ስለሚያስቸግር ይውጣ ሊባል ነውን? "ኀጥእ የጻድቅ ቤዛ ነው፤ በደለኛም የቅን ሰው ቤዛ ነው፡፡" ይላል መጽሐፍ ቅዱስ፡፡ ምሳ 21፡18፡፡ ኀጥእ እንዴት የጻድቅ ቤዛ ነው ይባላል? ስንኳንስ ኀጥእ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ጻድቃን ስንኳን ቤዛ አይባል ይሉ የነበሩ ይህን ንባብ እንዴት ሊቀበሉ ይችላሉ? እንግዲህ እንዲህ እያልን ከሄድን የሚቀረን ምንድን ነው? የምንደርሰውስ ወዴት ነው? ስለዚህ ጭንቀታችን መኾን ያለበት ንባብ ላይ ሳይኾን አረዳድ ላይ ነው ሊኾን የሚገባው።


ትምህርተ ጽድቅ dan repost
+#አዋልድ_መጻሕፍት_ለሃይማኖት_ማስረጃ_ኾነው_አይጠቀሱምን?+++

[] የሚጠቀሱ አሉ፤ የማይጠቀሱም አሉ!

አንዳንዴ ገድላትም ሃይማኖታዊ ጉዳይ ለማስረዳት ይጠቀሱ ይኾናል።

ለምሳሌ በሃይማኖተ አበው " ቅዱስ ባስልዮስ ... ስለ ቦሊጣ ሰማዕት በተናገረው ድርሳኑ ስለኛ እግዚአብሔር በሰው መካከል ተገለጠ፤ ብሉይ ሥጋን ለማደስ ቃል ሥጋ ኾነ፤ ባሕርያችንንም ገንዘብ አደረገ፤ የኃጢአት ምርኮኞችን ነጻ የሚያወጣቸው፥ ከበደለኞች ጋር ተቈጠረ፤ በጨለማ ውስጥ ለነበሩ ሰዎች እውነተኛ ፀሐይ ወጣላቸው፤ የማይታመመው በመስቀል ላይ ታመመ፤ ሕይወት እርሱ ሞተ፤ ብርሃን በሲኦል ተገለጠ፤ የተቀበሩትን የሚያነሣ እርሱ ከሙታን ጋር ተቈጠረ ብሎ ተናገረ" ይላል። (ሃይ ዘባስልዮስ ምዕ 96፥42)።

- "የቤተ ክርስቲያን ዐምድ ቅድስ ባስልዮስም ስለ ኢየሉጣ ሰማዕት በተናገረው ድርሳኑ አምላክ ስለኛ ሰው ኾነ፤ በሰው መካከል ተመላለሰ፤ ከተገፉት ጋር የሚገፋ ኾነ፤ የተጎዱትን ያድን ዘንድ ረዳት ለሌላቸውም ረዳት ይኾናቸው ዘንድ ይህን ኹሉ ሠራ፤ ቀድሞ ሥጋ ያልነበረው ዛሬ ሥጋን ተዋሐደ፤ ተሰቀለ፤ ሕይወት እሱ በሥጋ ሞተ፤ ብርሃን እሱ ወደ ሲኦል ገባ፤ ይህም ኹሉ የኾነው አዳምና ልጆቹም ስለ ተጎዱ ነው አለ" እንዲል። (ሃይ ዘዮሐንስ (የአንጾኪያ፣ የሶርያ፣ የባቢሎን ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሐንስ) ምዕ 114፥20)።

- አድማሱ ጀንበሬ በአጽንዖት የሚሉን አለ፦ "ሃይማኖተ አበው፣ አፈወርቅ፣ ቄርሎስ፣ ፍትሐ ነገሥት፣ 14ቱ ቅዳሴያት፣ ፊልክስዩስ፣ ማር ይስሐቅ፣ አረጋዊ መንፈሳዊም ሠለስቱ ምዕት በፍትሐ ነገሥት ከቈጠሯቸው ጋር አንድ ኾነው ይቆጠራሉ። ቅዱሳት መጻሕፍት ይባላሉ።" ይላሉ። (አድማሱ ጀንበሬ፣ ኰኵሐ ሃይማኖት፣ 2012 ዓ.ም፣ ገጽ 176)። ለአበው የትርጓሜያት መጻሕፍትና ሥርዓተ አምልኮትን የሚፈጸምባቸው የሥርዓት መጻሕፍትን እንዲሁም ኅብስትና ወይን ቀርቦ ወደ አማናዊው ቅዱስ ሥጋና ደም (ቅዱስ ቍርባን) የሚለወጥበት ጸሎት የሚከወንበትን የቅዳሴያት መጻሕፍት እንዴት በጥንቃቄ እንደ ጠቀሷቸው ልብ እንበል። እነዚህን አዋልድ መጻሕፍት እንደ መሠረታዊ መጻሕፍት አድርገው መጥቀሳቸውን ልብ ማለት ይገባል። ከዚህ በተጨማሪ በጒሜ ትምህርት የሚሰጥበትን የምንኲስናን ሕይወት ማዕከል አድርጎ የተዘጋጀውን መጽሐፍም ትልቅ ቦታ እንዳለው ይጠቁሙናል። አድማሱ ጀንበሬ ፕሮቴስታንታዊውን መናፍቅ "... እንግዲህ የእግዚአብሔርን አምላክነት ከሚናገሩት መጻሕፍት ውስጥ ይህ ሰው የጻፈው ነው፤ ይህም አዋልድ ነው፤ አልቀበልም ማለት የተሳሳተ ንግግር መኾኑን ትረዳ ዘንድ ..." ይላሉ። (እንደ ላይኛው ገጽ 168)። እንዲሁ በመሰለን ተነሥተን ይሄን አልቀበልም፣ ይህን እቀበላለሁኝ እያልን በመጻሕፍት ተጽፈው ለተቀመጡ ምንባባት የራስን አእምሮ መጣኝ ወይም መዛኝ ከማድረግ ስሑት አካሄድ እንድንወጣ ይመክሩናል። ማንኛውንም ሃይማኖታዊ ጉዳይ በራስ መረዳት ልክ አድርጎ መጓዝ ኦርቶዶክሳዊ አካሄድ ካለመኾኑም በተጨማሪ መዳረሻው በትዕቢት እሾህ ተወግቶ በክሕደት ገደል ውስጥ መግባት ነው።

አድማሱ ጀንበሬ መልክአ ማርያምን ጠቅሶ ለሚተቸው ፕሮቴስታንት ሲመልሱ "ከዚህ ከፍ ብሎ በሚገኘው መሥመር መጻሕፍት ማታለያ አዋልድ የተባሉ ልብ ወለድ መነኰሳቱ ሰበኩት ብለህ አዋልድ መጻሕፍትን ስትነቅፍ ተናግረህ ነበረ። እኛ ከጸሎት በቀር ለሃይማኖትና ለምግባር ምስክር አድርገን የማንጠቅሳቸውን መልካ መልኮችን በቂ ምስክሮች አድርገህ ከጠቀስክልኝ ከላይ የተናገርከውን አዋልድ መጻሕፍት ማታለያ መባላቸው ቀርቶ ባንተው ቃል ተሠይመው ለምስክርነት የበቁ እውነተኞች መጻሕፍት መኾናቸውን ማረጋገጥህን አስተውል። እንግዲህ አንተ የጠቀስካቸውን አዋልድ ምናልባት እኔ የጠቀስኩልህ እንደ ኾነ ቅር እንዳይልህና ሰው እንዳይታዘብህ አደራ" ይላሉ። (እንደ ላይኛው ገጽ 85-86)። ይህ ደግሞ በአንድ በኩል እንደ መልካ መልኮች ዓይነት መጻሕፍት የተዘጋጁበትን ዓላማ የሚያሳስብ ነው በሌላ በኩል አዋልድ መጻሕፍትን አልቀበልም የሚሉ መናፍቃን ያን አናምንበትም ያሉትን መጻሕፍት ጠቅሰው የመሞገት ሥልጣን እንደ ማይኖራቸው አመልካች ነው። እንግዲህ መጻሕፍትን ባልተጻፉበት ዐውድ መገምገም ፍጹም ስሑት የኾነ አካሄድ መኾኑን ልብ ከማለት ጋር አዋልድ መጻሕፍትን የማይቀበሉ መናፍቃን ለማዘናጋት የሚሄዱበትን መንገድ መለየት ያስፈልጋል።

ሌላው እዚህ ጋር ልብ ማለት የሚገባን የጸሎት መጻሕፍት ኹሉ ለሃይማኖት አስረጅ ተደርገው አይጠቀሱም ግን አይባልም። ለምሳሌ ውዳሴ ማርያም፣ 14 ቅዳሴያት፣ ... ሊጠቀሱ ይችላሉና። በኦርቶዶክስ የምናምነውን እንጸልያለን የምንጸልየውንም እናምናለን የሚለውን መሠረታዊ ሐሳብ ቸል የምንል አይደለምና። ዶግክትሪናችንን በራሱ እንደምንጸልየው ልብ ማለት ይገባልና። ጸሎተ ሃይማኖት ብለን የምንጸልየውም ለዚህ ማሳያ መኾኑ ግልጽ ነውና። መሠረታዊ ዓላማቸው ግን ርእሰ ጉዳያቸውን ማዕከል ያደረገ መኾኑን ልብ ማለት ይገባል። የተለያዩ ዓይነት አዋልድ መጻሕፍት አሉ ማለታችንም ከርእሰ ጉዳያቸው አንጻር ነው። ዋና ጉዳይ ያደረጉትን ትተን ወደ ሌላ ወስደን ቸኩል ድምዳሜ ውስጥ መግባት አይጠበቅብንም።

በቦሩ ሜዳ ላይ ሦስት ልደት የሚል ከመጻሕፍት ምንጭ አምጣ ሲባል "በደብረ ብርሃን በሚገኝ ተአምረ ማርያም ላይ አለ" ማለቱ ትችትን ያመጣበት ተአምረ ማርያምን አንቀበልም ለማለት ወይም አያስፈልግም ለማለት ሳይኾን ሃይማኖታዊ ዶክትሪንን ለማስተማር ታቅዶ የተጻፈ አይደለም ለማለት ነው። የተአምር ማርያም ዋና ዓላማው እግዚአብሔር በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አድሮ ያደረገውን መክራት ማሳየት እንጂ ትምህርተ ቤተ ክርስቲያንን ማስተማር አይደለምና። ብዙ ጊዜ Missing the point Fallacy (ነጥቡን የመሳት ስሕተት) ይሠራል። አዋልድ መጻሕፍት ሲጠኑ ከተጻፉበት መሠረታዊ ሐሳብ አንጻር ይገመገማሉ እንጂ ወደ ሌላ ዘወር ተደርገው ሊገመገሙ አይገባም። ተአምር የሚታየው ከታምር አንጻር ነው፤ ገድልም ከገድል አንጻር፤ ሌላውም ከዚያ አንጻር እንጂ ገድልን ሃይማኖተ አበው፥ ሃይማኖተ አበውንም ገድል አድርጎ ማሰብ መሠረታዊውን ነጥብ መሳት ነው። የቦሩ ሜዳው ጒባኤ አዋልድ መጻሕፍት ብዙም ጥቅም እንደሌላቸው አስረጅ ሳይኾን እንዲያውም እጅጉን ጠቃሚ መኾኑን ጠቋሚ ነው። ኹለት ልደት የሚለው በዋነኛነት ትክክል መኾኑ የተረዳው በሃይማኖተ አበው ባሉ ምንባባት ነውና። ሃይማኖተ አበው ደግሞ ቍጥሩ ከአዋልድ መኾኑ ግልጽ ነው። ከዚያ ውጭ ያልተባለን ማለት አግባብ አይደለም። ይህም ማለት ተአምረ ማርያምን ሃይማኖተ አበው አድርጎ ከማሰብ ነጥብን ከመሳት ስሕተት መጠበቅ ይገባል።

ታምራትን በተመለከተ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ የቅድስት ማክሪንን ሕይወት ሲጽፍ የሰጠው ጠቃሚ አስተያየት አለ። ይኸውም፦ "በጣም ትንሽ እምነት ያላቸውና በእግዚአብሔር ስጦታ የማያምኑ ሰዎች ወደ መጎዳት እንዳይመጡ፥ በዚህ ምክንያት ታላቅ ታምራትን መጻፍ ትቼያለሁኝ፤ ስለዚህ እንደማስበው ከኾነ አስቀድሜ ያልኹት የማክሪንን ታሪክ መጽሐፍ ለመፈጸም በቂ ነው።" ይላል። (The Life of SAINT MACRINA BY Gregorry, BisHop of Nyssa /Translated, with introduction and notes, by Kevin Corrigan p.54)። ይህ እንግዲህ አስተውሎት ያለበት ጥንቃቄ ነው። ይህን ሊቁ ማለት በፈለገበት መንፈስ ብቻ ኾነን የምንረዳው እንጂ ታላላቅ ታምራት በዐሥራው መጻሕፍት ውስጥ ተጽፈው ስለምናገኝ


የጌጣጌጥ፣ የልብስና የውበት ማሳሳቻ ነገሮች ለጋለሞታዎችና ለኀፍረት ለሌላቸው ሴቶች እንጂ ለማንም አይገቡም፤ የትኛውም ልብስ የትሕትናቸው መገለጫ ከሆነው የበለጠ ዋጋማ አይደለም። ጌታ እኛን ሊያስተምረንና ሊገስጸን በቅዱሳት መጻሕፍት ሲገልጽ፣ ጋለሞታይቱ ከተማ ይበልጥ በሚያምር ሁኔታና በጌጣጌጦቿ ያጌጠች ተደርጋ ተገልጻለች፤ እነዚያ ጌጣጌጦች ሊጠፉ ስለተቃረቡም ጭምር ነው። “ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ፣ ሰባቱንም ዋኖሶች ይዘው ከነበሩት፣ ከእኔ ጋር ተነጋገረና፣ ና፣ በብዙ ውሃ ላይ የተቀመጠችውን የታላቂቱን ጋለሞታ ፍርድ ላሳይህ፣ የምድር ነገሥታትም ከእርስዋ ጋር ዝሙት ፈጸሙ አለኝ። በመንፈስም ወሰደኝ፤ አንዲት ሴት በአውሬ ላይ ተቀምጣ አየሁ፣ ሴቲቱም ሐምራዊና ቀይ ልብስ ለብሳ፣ በወርቅና በከበሩ ድንጋዮችና በእንቁዎች ተጌጣ፣ በእጇም የመርገምና የርኩሰትና የመላው ምድር ዝሙት የሞላበት የወርቅ ጽዋ ነበራት።” ንጹሐንና ጨዋዎች ደናግል የርኩሰት ልብስ፣ የኀፍረት የሌላቸውን ባህሪ፣ የዝሙት ቤቶች ምልክቶች፣ የጋለሞታዎች ጌጣጌጦች ይራቁ። Cyprian (A.D. 250) Ante-Nicene Fathers vol. 5 pg. 433


እንግዲህ በፈርዖን በተነገሩት ቃላት እንጀምር፥ ሕዝቡን እንዳይለቅ በእግዚአብሔር እንደተደነደነ ይነገራል፤ ከእርሱ ጉዳይ ጋር ደግሞ የሐዋርያው ቃልም ይታሰባል፥ እርሱ “ስለዚህ እርሱ በሚወደው ላይ ይምራል፥ በሚወደውም ላይ ያደነዳል።” እነዚህን ክፍሎች መናፍቃን በዋነኝነት የሚታመኑት ድኅነት በራሳችን ኃይል ውስጥ እንዳልሆነ፥ ነፍሳት ግን እንደዚህ ዓይነት ተፈጥሮ ያላቸው በመሆናቸው በምንም መንገድ መጥፋት ወይም መዳን እንዳለባቸውና፥ ክፉ ተፈጥሮ ያለው ነፍስ በምንም መንገድ ጥሩ ሊሆን ወይም በጎ ተፈጥሮ ያለው መጥፎ ሊሆን እንደማይችል በመግለጽ ነው። ኦሪገን (ዓ.ም. 248) ከአኒቅያ በፊት ያሉ አባቶች ጥራዝ 4 ገጽ 308
አሁን ግን “የሚወድ ወይም የሚሮጥ አይደለም፥ ምሕረትን ከሚያደርግ ከእግዚአብሔር ነው እንጂ” የሚለውን አገላለጽ እንመልከት። ተቃዋሚዎቻችን እንደሚሉት፥ በፈቃዱ ላይ ወይም በሚሮጠው ላይ ሳይሆን፥ ምሕረትን በሚያደርገው በእግዚአብሔር ላይ የተመካ ካልሆነ፥ አንድ ሰው እንዲድን፥ ድኅነታችን በራሳችን ኃይል ውስጥ አይደለም። ተፈጥሮአችን ወይ መዳን ወይም አለመዳን የምንችልበት ነው፥ አለበለዚያ ድኅነታችን በሙሉ በእርሱ ፈቃድ ላይ ብቻ ያርፋል፥ እርሱም ቢወድ ምሕረትን ያደርጋል፥ ድኅነትንም ይሰጣል። አሁን በመጀመሪያ፥ እንደዚህ ያሉትን ሰዎች በረከቶችን መመኘት ጥሩ ወይስ ክፉ ተግባር እንደሆነ እንጠይቃቸው፤ እንደ መጨረሻ ግብ መልካምን መቸኮል ለምስጋና የሚገባ ነውን? እንዲህ ያለው አካሄድ ለውግዘት የሚገባ ነው ብለው ቢመልሱ፥ እነርሱ በእርግጠኝነት እብዶች ይሆናሉ፤ ሁሉም ቅዱሳን ሰዎች በረከቶችን ይመኛሉና ይከተሏቸዋል፥ በእርግጥም ሊወቀሱ አይችሉም። እንግዲህ፥ ያልዳነ ሰው፥ ክፉ ተፈጥሮ ያለው ከሆነ፥ በረከትን እንዴት ይመኛል፥ እንዴትስ ይከተላቸዋል፥ ነገር ግን አያገኛቸውም? እንግዲህ በረከቶችን መመኘትና መከተል ግዴለሽነት ሳይሆን በጎ ተግባር እንደሆነ ተረጋግጧል። ኦሪገን (ዓ.ም. 248) ከአኒቅያ በፊት ያሉ አባቶች ጥራዝ 4 ገጽ 321

X. መንግሥተ ሰማይን በኃይል የሚወስዱት

“ከመጥምቁ ዮሐንስ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ መንግሥተ ሰማይ ትሰቃያለች፥ ኃይለኛዎችም በኃይል ይወስዷታል።” ማቴዎስ 11:12
በውድድሩ እንደተሸነፉት ተከትለው ላልተጋደሉት ምን ዘውድ አለ? በዚህ ምክንያትም ጌታ መንግሥተ ሰማይ የ “ኃይለኛዎች” ክፍል እንደሆነ ተናገረ፤ እንዲህ ይላል፥ “ኃይለኛዎች በኃይል ይወስዷታል” ማለትም በብርታትና በጋለ ትጋት በቅጽበት ለመንጠቅ የሚጠባበቁት… ይህ ብቁ ታጋይ እንድንሸለምና ዘውዱን እንደ ክቡር አድርገን እንድንቆጥር፥ ማለትም በትግላችን የምናገኘውን፥ ለዘላለም ሕይወት እንድንታገል ያበረታታናል። እንግዲህ ይህ ኃይል ስለተሰጠን፥ ጌታም አስተምሮናል ሐዋርያውም እግዚአብሔርን የበለጠ እንድንወድ አዘዘን፥ እንድንጥርበት ይህን [ሽልማት] ለራሳችን እንድንደርስበት። ኢራኒዎስ (ዓ.ም. 180) ከአኒቅያ በፊት ያሉ አባቶች ጥራዝ 1 ገጽ 520

እንደሚታየው በእውነትም የተደበቀውን መልካም ነገር ማግኘት አስቸጋሪ ጉዳይ ነው፤ “ከምግባር በፊት ድካም አለ፥ ወደ እርሱ የሚወስደው መንገድ ረጅምና ቁልቁል ነው፥ በመጀመሪያውም አስቸጋሪ ነው፤ ነገር ግን ጫፉ ላይ ሲደረስ፥ [ከዚህ በፊት] አስቸጋሪ ቢሆንም ቀላል ነው።” “ጠባብና ቀጭን” በእውነት “የጌታ መንገድ” ነው። “የእግዚአብሔር መንግሥትም ለኃይለኛዎች ነውና።” ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ (ዓ.ም. 195) ከአኒቅያ በፊት ያሉ አባቶች ጥራዝ 2 ገጽ 410

እንዲህ ተብሏልና፥ “ለሚያንኳኳ ይከፈታል፥ ለምኑ፥ ይሰጣችኋልም።” “መንግሥትን የሚያስገድዱ ኃይለኛዎች” በክርክር ንግግሮች እንደዚያ አይደሉም፤ ነገር ግን በቀጣይነት ትክክለኛ ሕይወትና በማያቋርጡ ጸሎቶች “በኃይል ይወስዱታል” ይባላል፥ በቀድሞ ኃጢአታቸው የተተዉትን ነጥቦች እያጠፉ። ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ (ዓ.ም. 195) ከአኒቅያ በፊት ያሉ አባቶች ጥራዝ 2 ገጽ 448

መንግሥቱ በዋነኝነት የኃይለኛዎች ነው፥ ከምርመራና ከጥናትና ከዲሲፕሊን ይህን ፍሬ የሚያጭዱ፥ ነገሥታት የሚሆኑት። ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ (ዓ.ም. 195) ከአኒቅያ በፊት ያሉ አባቶች ጥራዝ 2 ገጽ 315

ጌታ ግን ይመልሳል፥ “በሰዎች ዘንድ የማይቻል በእግዚአብሔር ዘንድ ይቻላልና።” ይህ ደግሞ በታላቅ ጥበብ የተሞላ ነው። አንድ ሰው በራሱ እየሠራና ከፍላጎት ነፃ ለመሆን እየደከመ ምንም አይሠራም። ነገር ግን ይህን በጣም እንደሚፈልግና እንደሚጥር በግልጽ ካሳየ፥ የእግዚአብሔር ኃይል በመጨመር ያሳካዋል። እግዚአብሔር ከሚፈልጉ ነፍሳት ጋር ይተባበራል። እነርሱ ግን ቅንዓታቸውን ቢተዉ፥ በእግዚአብሔር የሚሰጠው መንፈስ ደግሞ ይቆማል። የማይፈልጉትን ማዳን የሚያስገድድ ሰው ሥራ ነውና፤ የሚፈልጉትን ግን ማዳን የጸጋን የሚያሳይ ነው። የእግዚአብሔር መንግሥትም ለተኛዎችና ለሰነፎች አይደለም፥ “ኃይለኛዎች ግን በኃይል ይወስዱታል።” ይህ ብቻ ነውና የሚመሰገን ኃይል፥ እግዚአብሔርን ማስገደድና ሕይወትን ከእግዚአብሔር በኃይል መውሰድ። እርሱም ጽኑዓን ወይም ይልቁንም ኃይለኛዎች ሆነው የሚጸኑትን አውቆ ይሰጣልና ያድላልም። እግዚአብሔር በእንደዚህ ባሉ ነገሮች በመሸነፍ ይደሰታልና። ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ (ዓ.ም. 195) ከአኒቅያ በፊት ያሉ አባቶች ጥራዝ 2 ገጽ 597

እኛ እንደ ጉባኤና እንደ ማኅበር እንሰበሰባለን፥ ለእግዚአብሔር ጸሎት በኅብረት ኃይል እያቀረብን፥ በምልጃችን ከእርሱ ጋር እንታገል። ይህን ኃይል እግዚአብሔር ይወዳል። ቴርቱሊያን (ዓ.ም. 198) ከአኒቅያ በፊት ያሉ አባቶች ጥራዝ 3 ገጽ 46
@WisdomOfTheFaith


“ለምን ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ ትሉኛላችሁ፥ እኔ የምላችሁንም አታደርጉም?” ይላል። “በከንፈሮቻቸው የሚወዱና ልባቸው ከጌታ የራቀ ሕዝብ” ሌላ ሕዝብ ነው፥ በሌላም የሚታመኑ፥ ራሳቸውንም ለሌላ በፈቃዳቸው የሸጡ፤ የጌታን ትእዛዛት የሚፈጽሙ ግን በእያንዳንዱ ተግባር እርሱ የሚፈልገውን በማድረግና የጌታን ስም በተከታታይ በመጥራት “ይመሰክራሉ”፤ በሚታመኑበት በእርሱም ለሚመሰክሩት በሥራ “ይመሰክራሉ”፥ እነርሱ “ሥጋን ከምኞቱና ከፍላጎቱ ጋር የሰቀሉት” ናቸውና። “በመንፈስ ብንኖር፥ ደግሞ በመንፈስ እንመላለስ።” ቀሌምንጦስ ዘእስክንድርያ (ዓ.ም. 195) ከአኒቅያ በፊት ያሉ አባቶች ጥራዝ 2 ገጽ 417

መናዘዝ የክብር መጀመሪያ እንጂ የዘውዱ ሙሉ ዋጋ አይደለም፤ ምስጋናችንንም አያሟላም፥ ክብራችንን ግን ይጀምራል፤ “እስከ መጨረሻ የሚጸና እርሱ ይድናል” ተብሎ እንደተጻፈ፥ ከመጨረሻው በፊት ያለው ማንኛውም ነገር ወደ ድኅነት ጫፍ የምንወጣበት እርምጃ እንጂ የመውጣቱ ሙሉ ውጤት አስቀድሞ የተገኘበት የመጨረሻ ነጥብ አይደለም። መናዘዝን ያደረገ ነው፤ ከመናዘዙ በኋላ ግን አደጋው ይበልጣል፥ ጠላት የበለጠ ይበሳልና። ቄፕሪያን (ዓ.ም. 250) ከአኒቅያ በፊት ያሉ አባቶች ጥራዝ 5 ገጽ 428
VIII. የመጀመሪያዋ ቤተ ክርስቲያን ድኅነትን እንዴት ሰበከች
ነገር ግን በመጀመሪያ በደማስቆ፥ በኢየሩሳሌምም፥ በይሁዳም አገር ሁሉ፥ ከዚያም ለአሕዛብ ንስሐ እንዲገቡና ወደ እግዚአብሔር እንዲመለሱ ለንስሐ የሚገባ ሥራ እንዲሠሩ ነገርኳቸው። የሐዋርያት ሥራ 26:20
እንግዲህ ሐሳብህን ከቅድመ-ግምትህ ሁሉ አጽዳና የሚያታልልህን ልማድ አስወግድ፥ አዲስ መልእክት ልትሰማ እንደሆነ ከጅማሬው አዲስ ሰው ሁን። ለዲዮግኔጦስ የተላከ ደብዳቤ (ዓ.ም. 125-200) ምዕራፍ 2
ሁለት መንገዶች አሉ፥ አንዱ የሕይወት አንዱም የሞት፥ በሁለቱ መንገዶች መካከል ግን ትልቅ ልዩነት አለ። እንግዲህ የሕይወት መንገድ ይህ ነው፥ በመጀመሪያ፥ የፈጠረህን እግዚአብሔርን ትወዳለህ፤ ሁለተኛ፥ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ትወዳለህ፥ ለሌላውም በራስህ ላይ እንዲደረግ የማትፈልገውን አታደርግም። ከእነዚህም አባባሎች ትምህርቱ ይህ ነው፥ የሚረግሙህን ትባርካለህ፥ ለጠላቶችህም ትጸልያለህ፥ ለሚያሳድዱህም ትጾማለህ። ለሚወዱህስ ብትወድዱ ምን ዋጋ አለው? አሕዛብም እንዲሁ አያደርጉምን? የሚጠሉአችሁን ግን ውደዱ፥ ጠላትም አይኖርባችሁም። ከሥጋዊና ዓለማዊ ምኞት ራቁ። ቀኝ ጉንጭህን የሚመታህ ሌላውንም ወደ እርሱ መልስ፥ ፍጹም ትሆናለህ። አንድ ምዕራፍ የሚወስድህ ከእርሱ ጋር ሁለት ሂድ። ልብስህን የሚወስድብህ መጎናጸፊያህንም ስጠው። ያንተ የሆነውን ከሚወስድብህ አትጠይቅ፥ በእርግጥ አትችልምና። ለሚለምንህ ሁሉ ስጥ፥ አትጠይቅም፤ አብ ለሁሉም ከበረከታችን (ነፃ ስጦታ) እንዲሰጥ ይወዳል። ዲዳኬ (ዓ.ም. 80-140) ምዕራፍ 1
IX. መናፍቃን ድኅነትን እንዴት ሰበኩ
ግኖስቲኮች እንደሚሉት፣ ሥጋዊ ሰዎች በሥጋዊ ነገሮች ይማራሉ—በሥራቸውና ባልተሟላ እምነት ላይ የተመሰረቱና ፍጹም እውቀት የሌላቸው ሰዎች ማለት ነው። እኛ የቤተክርስቲያን ሰዎች፣ እነርሱ እንደሚሉት፣ እነዚህ ሰዎች ነን። ስለዚህም መልካም ሥራዎች ለእኛ አስፈላጊ እንደሆኑ ይናገራሉ፤ አለበለዚያ ድኅነት እንደማይኖረን ያምናሉ። ነገር ግን ስለ ራሳቸው፣ በመንፈሳዊ ተፈጥሮአቸው ምክንያት፣ በምግባር ሳይሆን በእርግጠኝነትና ሙሉ በሙሉ እንደሚድኑ ይናገራሉ።ኢራኒዎስ (ዓ.ም. 180) ከአኒቅያ በፊት ያሉ አባቶች ጥራዝ 1 ገጽ 324
ሌሎች [ግኖስቲኮች] ደግሞ፣ ሥጋዊ ነገሮች ለሥጋዊ ተፈጥሮ፣ መንፈሳዊ ነገሮች ደግሞ ለመንፈሳዊ ተፈጥሮ መቅረብ እንዳለባቸው በመናገር፣ በከፍተኛ ስግብግብነት ለሥጋዊ ምኞታቸው ይዳሉ። እነርሱ [ግኖስቲኮች] እኛ (ቤተክርስቲያን) ጸጋን ለጊዜያዊ ጥቅም ብቻ እንደምንቀበልና ስለዚህም እንደሚወሰድብን ይናገራሉ። ነገር ግን እነርሱ ራሳቸው ጸጋን ከላይ በማይነገርና በማይገለጽ መንገድ እንደተቀበሉትና እንደራሳቸው ልዩ ንብረት አድርገው ይቆጥሩታል፤ በዚህም ምክንያት ተጨማሪ ጸጋ እንደሚሰጣቸው ያምናሉ።ኢራኒዎስ (ዓ.ም. 180) ከአኒቅያ በፊት ያሉ አባቶች ጥራዝ 1 ገጽ 324

የመናፍቃን] ጽሑፎች እንዲህ ይላሉ፡ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱና ለሐዋርያቱ በምስጢርና ለብቻቸው ይናገር ነበር። እነርሱም የተማሩትን ለሚገባቸውና ለሚያምኑ ሰዎች ለማስተላለፍ ፈቃድ ጠየቁና ተፈቀደላቸው። ድኅነት በእምነትና በፍቅር የሚገኝ ቢሆንም፣ ሌሎች ነገሮች በባህሪያቸው ግድ የለሾች ሲሆኑ፣ በሰዎች አስተያየት አንዳንዶቹ ጥሩ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ክፉ ተብለው ይወሰዳሉ። በእውነቱ በባህሪው ክፉ የሆነ ነገር የለም።ኢራኒዎስ (ዓ.ም. 180) ከአኒቅያ በፊት ያሉ አባቶች ጥራዝ 1 ገጽ 351
እግዚአብሔር ሊፈራ አይገባም ይላሉ፤ ስለዚህ ሁሉም ነገር በእነርሱ እይታ ነፃና ያልተገደበ ነው። እግዚአብሔር የማይፈራው ግን ከየት ነው? እግዚአብሔር በሌለበት። እግዚአብሔር በሌለበት ደግሞ እውነትም የለም። እውነት በሌለበት ደግሞ በተፈጥሮ እንደነርሱ ያለ ዲሲፕሊን አለ። ቴርቱሊያን (ዓ.ም. 198) ከአኒቅያ በፊት ያሉ አባቶች ጥራዝ 3 ገጽ 264-265
ማርሲዮን አምላኩን ከባድና ፈራጅ አድርጎ ከማየት አስወግዶታል። . . ምንም የማይቆጣ፣ የማይናደድ፣ የማይቀጣ፣ በገሃነም እሳትና በውጭኛው ጨለማ የጥርስ መፋጨት ያላዘጋጀ የተሻለ አምላክ ተገኝቷል! እርሱ ሙሉ በሙሉ ጥሩ ነው። በደልን በቃል ብቻ ይከለክላል። እርሱን እንደምታከብሩ ለማሳየትና ለማስመሰል ብቻ ክብር ልትሰጡት ከፈለጋችሁ እርሱ በእናንተ ውስጥ ነው፤ ፍርሃታችሁን ግን አይፈልግም። ስለዚህ የማርሲዮናውያን በእንደዚህ ዓይነት ማስመሰል ስለሚረኩ፣ አምላካቸውን በጭራሽ አይፈሩም።ቴርቱሊያን (ዓ.ም. 198) ከአኒቅያ በፊት ያሉ አባቶች ጥራዝ 3 ገጽ 291-292
“አትታለሉ፣ እግዚአብሔር አይዘበትበትም።” የማርሲዮን [የግኖስቲክ መናፍቅ] አምላክ ግን ሊዘበትበት ይችላል፤ እንዴት እንደሚቆጣ ወይም እንዴት በቀል እንደሚወስድ አያውቅምና።ቴርቱሊያን (ዓ.ም. 198) ከአኒቅያ በፊት ያሉ አባቶች ጥራዝ 3 ገጽ 438
በዚህ ምክንያት እነርሱ [የቫለንቲኑስ መናፍቃን] ለራሳቸው ሥራ አስፈላጊ እንደሆኑ አድርገው አይመለከቱም፥ ወይም ማንኛውንም የግዴታ ጥሪ አያከብሩም፥ በምንም ዓይነት ምክንያት በምኞታቸው በሚስማማ ማንኛውም ሰበብ የሰማዕትነትን አስፈላጊነት እንኳን ያስወግዳሉ። ቴርቱሊያን (ዓ.ም. 198) ከአኒቅያ በፊት ያሉ አባቶች ጥራዝ 3 ገጽ

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.