️ ንስር አማራ🦅


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: не указана


የተቀደሰን ነገር በእግሩ ለሚረግጥ ፥ተመልሶም ያጎረሰውን እጅ ለሚናከስ ርኩስ መጫወቻ የማይሆን የነቃ ማህበረሰብ እስክንፈጥር ድረስ ብዕራችን አይነጥፍም።
አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ፥ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ።
💚💛❤️
እኛን በውስጥ ለማናገር @NISIREamhra2
@NISIREamhraa_bot 👈 ይችን አድራሻ ይጠቀሙ🦅
ንስር አማራ🦅
#የግፉአን_ድምፅ
t.me/NISIREamhra

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
не указана
Статистика
Фильтр публикаций


      🔥#5ኛ_ክፍለ_ጦር_የድል_ውሎ‼️

የአማራ ፋኖ በጎጃም የራስ ቢትወደድ መንገሻ አቲከም/5ኛ ክ/ጦር/ ውስጥ የሚገኙ ብርጌዶች ጠላትን ሲያስጨንቁት ውለዋል!!

    ፩ኛ ወርቅ አባይ ብርጌድ፦ጠላት ከሽንዲ እና ከእሁዲት የተንቀሳቀሰ ሲሆን የበርሃ ዘንዶወቹ ወርቅ አባይ ብርጌድ ጠላትን አምበር፣ፍሪ እና አየሁ አካባቢ ሲቀ*ጠቅ*ጡት የዋሉ ሲሆን በዚህም ሁለት ፓትሮል አስክ*ሬን ማምረትና ቁጥሩ በርከት ያለ የአልጋ ደምበኛ (ቁስ*ለኛ) ማድረግ ተችሏል::

፪ኛ ከሽንዲ ከተማ ከሌሊቱ 4:00 ሰዓት ጀምሮ ወደ ገጠር ቀበሌወች ሲንቀሳቀስ የነበረው ወራ*ሪ ሀይል ነበልባሎቹ የወምበርማ ብርጌድ ፋኖች ከ6 በላይ የአገዛዙ ጦር ሲሸ*ኙ ቁጥሩ የማይታወቅ ቁስለኛ ተሸክሞ በመፈርጠጥ ጠላ*ትን ወደ እሁዲት ከመሸገው ጠላት ጋር ተቀላቅሏል።

  ፫ ኛጓጉሳ ብርጌድ፡- ጠላት ከኮሶበር ፣አዘና አየሁ የመጣውን 4 ፖትሮል መከላከያ እና አድማ ብተና ጥምር ጦ*ር እና አንድ ኦራል አየሁ እርሻ ልማት ቡናው ላይ ወደ እሁዲት አምበር የተመታውን ለማገዝ በሚንቀሳቀስበት ሰአት ደፈጣ በመያዝ በከፈቱት ጥቃት ሙትና ቁስለኛ ያደረጉት ሲሆን ይህ ጠላት ወደ አዬሁ ከተማ በመመለስ ቀስለኛውን እና ሙቱን በማድረስ በድጋሚ  የተመለሰ ሲሆን አሁንም ውጥረቱ እንደቀጠለ  ነው።

አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!!
    ©የአማራ ፋኖ በጎጃም 5ኛ ክ/ጦር የሚዲያ ባለሙያ ፋኖ ዮሴፍ ሀረገወይን

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

27/06/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra


🔥የአማራ ፋኖ በጎጃም 3ኛ(ጎጃም አገው ምድር) ክፍለጦር  የግዮን ብርጌድ ከማክሰኞ ጀምሮ  3 ቀን የጨረሰ ጥልቅ የሆነ ግምገማ በማድረግ በዛሬው ዕለት የአመራር ሪፎርም በመስራት  አጠናቋል‼️

አዲስ የተመረጡ የብርጌዱ አመራሮች፡-
1. ሰብሳቢ ፋኖ 50 አለቃ ተፈራ ሁነኛው
2. ም/ሰብሳቢ የሻነህ ገድፍ
3. ጦር አዛዥ ፋኖ እንደሻው ጌታነህ
4.ም/ጦር አዛዥ ፋኖ ሀብታሙ ዋሴ
5.ጽፈት ቤት ሀላፊ ፋኖ ደሴ ነጋልኝ
6. ፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ አወቀ መላኩ
7.ህዝብ ግንኙነት ፋኖ የቻለ አድማሱ
8.ፋይናንስ እና ንብረት አስተዳደር ዳምጤ መላክ
9.አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ወርቅነህ ደሳለው
10.ቀጠና ትስስር እውቀት አለሙ
11.ዘመቻ መምሪያ ሻለቃ አላምነህ በለጠ
12.ም/ዘመቻ መምሪያ መቶ አለቃ ሙሉጌታ  አሳዬ
13 ስልጠና መምሪያ.አብርሀም ጋሻዬ
14.ወታደራዊ አስተዳደር መቶ አለቃ ደሴ ጋሻዬ
15.ጤና መምሪያ ደሳለው አድማስ
16.ሎጀስቲክስ በላይ አያሌው
17.ኦርዲናንስ ያየህ ንጋት
18.የሰው ሀይል አስር አለቃ ዳኛው አየለ
19.ወታደራዊ አማካሪ የሻምበል ዋሴ
20. መረጃና ደህንነት_
ሆነው የተመረጡ ሲሆን በክፍለጦሩ አመራሮች ቃለ መሀላ በመፈጸም እና ፎቶ በጋራ በመነሳት ፕሮግራሙ ተቋጭቷል።

በክፍለ ጦሩ ውሳኔ መሰረት አርበኛ ሻምበል ዋሴ የጦር መሪ አማካሪ ሆኖ ተመድቧል።

የቻለ አድማሱ የግዮን ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

27/06/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra


🔥መላው ህዝባችን እና ታጋዮቻችን ሁላችሁም በያላችሁበት ቦታ፤በያላችሁበት የግዜ አቆጣጠር እንደምን አላችሁ⁉️

የአማራ ህዝብ ትግል ከዛሬ ለነገ፣ ከነገ ለተነገ ውዲያ ከተነግ ወዲያ ወደዚያኛው ወደማይቀረው ድል እየገሰገሰ ይገኛል። ስለዚህ በትግሉ ውስጥ ላላችሁ የፋኖ አመራሮች፣ ተዋጊ ፋኖዎች ከጥንት ከአያት ቅድም አያቶቻችሁ የወረሳችሁትን ፍኖነት በማስቀጠል ላይ የምትገኙ እንደተርብ እየበረራችሁ ጠላትን እምታሽመደምዱ ጀግና የአማራ ልጆች በዚህ ሰአት በዚህ ግዜ ለአማራ ህዝብ የማይመጥን በሰፈር፣በመንደር፣በጎጥ፣የታጠረ ፋኖ መኖር የለበትም። የጭቁኑ ህዝባችንን ፊት ፈገግ የምናደርገው አንድ ስንሆን ነው። ለእውነት ለመሞትና ለእውነተኛ ትግል አንድነት ያስፈልጋል። አንድነት ውዴታ ሳይሆን ግዴታ ነው ።ስለዚህ ከዚህ በኋላ ሁላችንም አንድ መሆን አለብን። ለስልጣን ለቦታ ለሹም ለጥቅማጥቅም ሁኔታወችን ማመቻቸት መቆም አለበት።

አንድነት መብት አይደለም አንድነት ግዴታ ነው።በግድ ለማይቀረው ድልና ነጻነት ስንል አንድ መሆን አለብን።ሸዋ ላይ ያለው አንድ መሆን አለበት፤ በጎጃምና ጐንደር እንዲሁም በወሎ የመጣው አንድነት መቀጠል አለበት። አንድነታችን ነው የጎበጠው ህዝባችንን ቀና የሚያደርገው።አንድ ስንሆን ነጻ እንወጣለን።

እኛ የምንፈልገው ስልጣን ሳይሆን በሰቆቃ ለምትጮኸው ነፍስ መድረስ ነው፣የተጨቆነውን ህዝብ ማዳን ነው። በድሮን ቦንብ በተቀጠቀጠችው እናት ልብ ውስጥ መንገስ በቂ ነው የኛ ስልጣን እሱ ነው ፤ እርሻ ውሎ ሲገባ በመድፍ አንገቱ በተቆረጠው በአባታችን ነፍስ ውስጥ ያለው የንግስና ቦታ ለእኛ በቂ ነው። በብልፅግና አራጅ ሰራዊት ለሦስት ለአራት ለአምስት ለስድስት የተደፈሩት እህቶቻችን በእነሱ ነፍስ ውስጥ ከነገስን ለእኛ በቂ ነው፤ ወላሂ ከአሁን ቡኋላ አማራ አልሆንም ተውኝ ብላ ስትጮህ አንገቷ የተቀላው ህጻን ብላቴና በእርሷ ነፍስ ውስጥ ከነገስን ለእኛ ስልጣናችን እሱ ነው። ስለዚህ በሽኩቻ በጠብ አንድነታችን ሊፈርስ አይችልም። ከዚህ በኋላ አንድ መሆን ባለብን ልክ አንድ ሆነን መጠነ ሰፊ ወረራ እያደረገ ያለውን የፍሽስት ብልፅግና ሰራዊት መክተን በመመለስ የናቶቻችንን ፈገግታ እንመልሳለን።

የአማራ ህዝብ ጥያቄው ሊመለስ ይገባል። የአማራ ምሁር ፣ የአማራ ወጣት፣የአማራ ገበሬ ጥያቄው ሊመለስ ይገባል።አሁን እያደረግን ያለነው ትግል አትኖሩም እንኖራለን ነው።
አማራ በታሪኩ በእኛ ዘመን እንዲያፍር መፍቀድ የለብንም።

ስለዚህ አንድ ሆነን ክንዳችንን አፈርጥመን የመጣውን የብልፅግና ወንበዴ ሰራዊት አንገቱን እየቆረጥን እምንጥልበት ግዜው አሁን ነው። አሁን ያለንን ግዜ ተጠቅመን አንድ በመሆን ጠላታችንን በምንቀብርበት ሰአት ላይ ከፊት ሆነው ሊያግደን የሚሞክር ማንኛውም ኃይል በራሱ ግዜ ተኖ ይጠፋል ቀሪውም ይመነጠራል ። መሆን ባለበት ልክ ሁሉ የአማራ ህዝብን ክብር፣ልዕልና፣ሞራል በሚደግፍ መልኩ ወደፊት እንራመዳለን።

አንድነት ውዴታ ሳይሆን ግዴታ ነው!!
መገፋት መነሻችን ነጻነት መዳረሻችን!!

©የአማራ ፋኖ በሸዋ ምክትል ሰብሳቢ እና ወታደራዊ አዛዥ መቶ አለቃ ልመንህ ሻውል

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

27/06/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra




ከሁሉ አስቀድሜ   የትጥቅ ትግላችን ለተለኮሰበት 3ኛ ዓመት  ለዚች ቀን እንኳን አደረሳችሁ ለማለት እወዳለሁ።

  የትጥቅ ትግል ባልታሰበበት ማንም  ባልነቃበት ሁሉም በተኛበት የትጥቅ ትግል ባልተለመደበት በዚያ ጨለማ ጊዜ   የአማራን ሕዝብ ከጭቆና ለማላቀቅ  ሞጣና  አካባቢዋ  ወጣቶችን  አንቅቶና አደራጅቶ አሰልጥኖ  የትጥቅ ትግል በማስጀመር  የካቲት  27 _ 2014  አመተ ምህረት  የመጀመረያዋን  ጥይት  ወደ ካድሪ በመተኮስ   አርበኛ መዝገቡ ዋለልኝ የትግላችን ችቦ ለኳሽ ጀግና አርበኛ ነበር።  የመጀመሪያው የትጥቅ ትግል የጀመርን ዕለት በዚያች ቀን አርበኛ መዝገቡ ዋለልኝ ቢሰዋም 4 ባንዳዎችን በመቀንደሽ 9 ክላሽ   1 ጂም ስሪ በመማረክ ነበር በሞጣ ቀጠና የትጥቅ ትግሉን አሐዱ ብለን የጀመርን።   ልክ በዛሬዋ ዕለት  የካቲት 27-2014 የትጥቅ ትግሉን በይፋ የጀመርን ዕለት  አርበኛ መዝገቡ ዋለልኝ ከእኛ ቢለይም   ትግል ቅብብሎሽ በመሆኑ የእሱን አደራ ተቀብለን ከ እነ ተፈራ ዳምጤና  ከሌሎች ከተሰው  ጀግኖች ጋር ትግሉ ቀጣይነት እንዲኖረው  ትግሉ  ከሞጣ ቀጠና አልፎ   በመላ ጎጃም የትጥቅ ትግሉ  እንዲቀጣጠል አድርገናል።

የትጥቅ ትግሉን ስንጀምረው  የብልጽግና ካድሬዎች አጥተው  ቸግሯቸው  ይሉን ነበር። አርበኛ መዝገቡ ዋለልኝም" እኛ የምንታገለው አጥተን አይደለም ለነጻነት ነው"  ሲል ነበር ።

ዛሬም  የምንታገለው  አጥተን ቸግሮን ገንዘብ ለማግኘት የሚመስላቸው አሉ።  ገንዘብ ሳይሆን ነጻነት አጥተን ነጻነትን ፍለጋ ወደ ጫካ ከወጣን እነሆ 3 ዓመታትን አስቆጠርን።

ጓድ ቀዳሚ ሰማዕት መዝገቡ ዋለልኝ  ለአማራ ነጻነትና ለአማራ አንድነት ሲል ሞጣ ከብት ገበያ  ከጎናችን ወድቋል። ጓዳችን ከተሰዋ በበነጋው  ጀምረን የተሰዋለትን ለአማራ ነጻነትና አንድነት  ለማምጣት እየታገልን እንገኛለን።

በትግላችንም  መጠነ ሰፊ ውጊያ በመክፈት የብልጽግና ሰራዊት ተቆጣጥሯቸው የነበሩ  ሰፊ ቀጠናዎችን ተቆጣጥረናል። የተቆጣጠርናቸውን ቀጠናዎችንም  ከውጊያ ጎን ለጎን የሲቪል አስተዳደር በማዋቀር ሕዝብ እያስተዳደርን እንገኛለን።
ወቅቱ በጠየቀው ትግል  ከጋንታ  እስከ ክፍለጦር  እየተዋጋን እስከዛሬ ያለውን አመርቂ  ድል አግኝተናል።  አሁን ላይ ግን ከጠላት አሰላለፍ አኳያ ይህ በአውራጃ  የተመሰረተ የፋኖ አደረጃጀት ወደ አንድ የአማራ ፋኖ ወታደራዊ ተቋም በማሳደግ  በወታደራዊ አንድነትና ቅንጅት ጠላቶቻችንን ደምስሰን ለሕዝባችን የመጨረሻዋን ድል ልናበስረው ይገባል እላለሁ።

አንድነት ኃይል ነው”  እንደሚባለው። የመጨረሻውን ድልና ግብ ለሕዝባችን ለማብሰር   አንድነት ፈጥሮ ተቀናጅቶ መዋጋት የደረስንበት የትግል ደረጃ   ይጠይቃል። ደካማ አገርና ትውልድ የሚወለደው አንድነትን በማጣት በመሆኑ  እንደ አማራ  አንድ  የአማራ ፋኖ  ወታደራዊ ተቋም ያስፈልጋል።

ጠላቶቻችን እኛን ለማጥፋት ለእኩይ ግብር ሕብረት ፈጥረው አማራን ለማጥፋት ወደ ሰፈራችን ሲመጡ እኛ  ለቅዱስ ዓላማ ለአማራ ፋኖ አንድነት ሲባል የግል ፍላጎትን ገርቶ ወደ አንድነት መምጣት አሸናፊነት  እንጂ ውርደት አይደለም ።
እንደ መብረቁ የትጥቅ ትግል ከጀመርንበት ከየካቲት 27- 2014 ዓ.ም  ጀምሮ  ከአርበኛ መዝገቡ ዋለልኝ መስዋዕትነት በኋላ የትግሉ አስቀጣይና የመብረቁ ፊታውራሪ የነበሩትን እነ ሻለቃ ተፈራ ዳምጤንና  ብዙ ጓዶችን በትግሉ ገብረናል። ጓዶቻችን የተሰ_ውት ደግሞ ለአማራ ነጻነትና ለአማራ አንድነት ሲሉ ነው።   ጓዶቻችን የተሰውለትን  ለአማራ ሕዝብ ነጻነትና  አንድነት   የሚከፈለውን መስዋዕትነት ሁሉ እየከፈልን የምናስፈጽም ይሆናል።

አዲስ ትውልድ
አዲስ አስተሳሰብ
አዲስ ተስፋ
(የአማራ ፋኖ በጎጃም )


🔥#ሰበር_ዜና_ጎንደር‼️

“60 የጠላት ኃይል ሲደመሰስ፣ 49 ክላሽንኮቭ መሳሪያ ማርከናል።” የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር

የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ቋራ ኦሜድላ እና አድዋ ክፍለጦር በምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ ጦር ጋር በተደረገ ውጊያ በጠላት ከፍተኛ ኪሳራ መድረሱን የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የቋራ ኦሜድላ ክፍለጦር ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ፋኖ አስቻለው አለባቸው ለኢትዮ 251 ሚዲያ በሰጠው ቃለመጠይቅ ገልጿል።

በዛሬው ዕለት የካቲት 27 ቀን 2017 ዓ.ም በምዕራብ ጎንደር ቋራ ወረዳ አልጣሽ ብሔራዊ ፓርክ ዙሪያ በተደረገ ውጊያ የምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ 60 ሰራዊት ሲደመሰስ፣ 49 ክላሸንኮቭ መሳሪያ ወደ ፋኖ ገቢ የሆነ ሲሆን በተጨማሪም ወደ አልጣሸ ብሔራዊ ፓርክ መደበኛ መኪና መግባት ስለማይቻል በትራክተር ተተኳሽና ስንቅ ለማሸጋገር ሲሞክር ትራክተሩ ከእነሙሉ ተተኳሽና ስንቁ በፋኖም እንደተማረከ ፋኖ አስቻለው አለባቸው ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጿል።

ውጊያው አሁንም እንደቀጠለ ሲሆን የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የቋራ ኦሜድላ ክፍለጦር አካል የሆኑት ዳግማዊ ቴዎድሮስ ብርጌድ፣ ነብሮ ብርጌድ እና የአድዋ ክፍለጦር አካል የሆነው ነብሮ ብርጌድ የጠላትን ኃይል ድባቅ እየመቱት ይገኛሉ፣ የጠላት ኃይል ከመደምሰስና ከመማረክ የተረፈው ወደ ገለጎ ከተማ እየፈረጠጠ ይገኛል ሲል የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር የቋራ ኦሜድላ ክፍለጦር ሕዝብ ግንኙነት ፋኖ አስቻለው አለባቸው ገልጿል።

© ኢትዮ 251 ሚዲያ

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

27/06/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra


🔥#ወርቅአባይ_ጠላትን_እየቀጠቀጠ_ይገኛል💪

የአማራ ፋኖ በጎጃም 5ኛ ክፍለ ጦር ወርቅአባይ ብርጌድ ጠላትን እያርበደበደው ይገኛል💪

አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!!
©የአማራ ፋኖ በጎጃም 5ኛ ክ/ጦር የሚዲያ ባለሙያ ፋኖ ዮሴፍ ሀረገወይን

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

27/06/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra

10k 0 3 9 112

🔥#ዳግማዊ_በላይ_ዘለቀ_በሸዋ_መርሐቤቴ‼️

ዐማራ ለአለፉት 50 ዓመታት በተሠራበት የሐሰት ትርክት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሲገደል፣ሲፈናቀል፣ሲሰደድ፣ሲረሸን፣እንደኖረ የአደባባይ ምስጢር ነው።

በተዘዋዋሪ ስንል የዐማራ ሴቶች በክትባት ሰበብ በየትምህርት ቤቶች የልጃገረዶች ክትባት በማልት እንዳይወልዱ በማድረግ ኦሮሞ ሦስት እጥፍ ቁጥሩ ሲጨምር የዐማራው 2.4 ሚሊዮን ሕጻን እንደ ዕቃ ጠፍቷል ተብሎ በሕዝብ ተወካይ በሚሉት የሕወሓት አሻንጉሊቶች ተነገረን።

በ2013 ዓ.ም የሕወሓት በሰሜኑ በኩል አስነሳው በተባለው ጦርነት የዐማራ ልጆች እንደቅጠል እንዲረግፉ የተደረገበትና ሸዋ ደብረብርሃን ድረስ እያወደመ እንዲመጣ አረንጓዴ መብራት እያበራለት ብልፅግና የዐማራን ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ጣቢያዎች፣ የአብነት ትምህርትም ቤቶች፣ የእምነት ተቋማቶችን አውድሞ ተመለሰ።

አሁን ደግሞ በቀጥታ ዐማራን የማጥፋት ዘመቻውን በይልቃል ከፋለ ፊርማ የተፈቀደለት ብልፅግና መጠነሰፊ የማጥፋት ዘመቻውን ያደረገበት አካባቢ አንዱ መርሐቤቴ አውራጃ ነው።

በዚህም አውራጃ የዐማራ መጨፍጨፍ ከመረራቸው የምኒልክ ልጆች፣ የራስ አበበ አረጋይ ተከታይ፣ የፋኖ ኢንጂነር ደሳለኝ ሲያስብሸዋ ትንፋሽ፣ የባዩ አለባቸው ወንድም አንዱ----------------------- ድሮ የፌጥራን ከተማ በሊቀመንበርነት ያስተዳድር የነበረና በሥራውም ለማኅበረሰብ ቀንአይ የሆነ አሁን ደግሞ የዐማራ ፋኖን በሸዋ የተቀላቀለ፤ ብልፅግና የዐማራን ሥነ ልቦና አጥንቼ ጨርሻለሁ ያለ ይመስልና ያወቀው ያክል የተሰማው፤ወደዚህ ጀግና ስልክ ደወለና፦
ሃሎ!
አቤት!
አቶ እከሌ!
አዎ!
ልጅና ሚስትህን ታፍነዋል በቶሎ እጅህን እስከ ሳምንት ካልሰጠህ እንገላቸዋለን!
አንተ ማን ነህ!?
እኔ! የመከላከያ ሠራዊት አዛዥ ነኝ!ይላል።
የሚገርመው ጀግናው ሚስትና ልጁን ጥሏቸው ሲሄድ ለዐማራ አንድያ ሕይወቱን ለመስጠት እንደሆነ ያልተረዳው የአቢይ አህመድ ቅጥረኛ ገዳይ ቡድን ያገኘው መልስ እጅግ ለጆሮ የሚሰቀጥጥ ነበር።

ስማ! አለ ጀግናው የበላይ ዘለቀ ትንፋሽ
አቤት!
"ሥስት ኪሎ ሽንኩርትና አምስት ሊትር ዘይት እልክልሀለሁ ቀቅለህ ብላቸው"
ይለውና ስልኩን ጆሮው ላይ ይጠረቅምበታል። ወዳጄ ዐማራ ከቤቱ ሲወጣ እንደብልፅግና በአጋጣሚ ስልጣን እንደተቆናጠጠውና ስልጣን ከያዘም በኃላ ሁሉ የኔ ነው እንደሚለው አካሄድ አይደለም ዐማራ ለትግል የወጣ። ሁሉም በእቅድ ነው የሚሠራው እንደአንዳንዶቹ በሆዳቸው እንደሚወድቁት አይነቶቹ አይደሉም ጫካ ያሉት። ዐማራ ላይጨርስ አልጀመረም!

ድል ለዐማራ ፋኖ!
ድል ለዐማራ ሕዝብ!
ድል ለጭቁኑ!
የካቲት 2//2017 ዓ.ም


@NISIREamhra


🔥የበረኸኛው ቀስተ ደመና ብርጌድ ትንቅንቅ#በደብረኤልያስ‼️

በዛሬው እለት ማለትም በየካቲት 26 ቀን 2017 ዓ.ም በበረኸኛው ቀስተ ደመና ብርጌድ እና በመከላከያ ሰራዊት መካከል ውጊያ ተደርጓል።

በብርጌዱ ዘመቻ መሪ በኮማንዶ አስር አለቃ አብርሃም ጸጋየ የተመራው የዛሬው ኦፕሬሽን አኩሪ ድል አስገኝቷል። በውጊያ ስልታቸው በጀግንነታቸው የተመሰከረላቸው ተናዳፊወቹ የቀስተ ደመና ፋኖ አባላት እንደሚያውቁበት የወንበዴውን ስብስብ በክላሽ ፣በብሬንና በስናይፐር
#ሲያጫውቱት አርፍደዋል ።

     ሌሊቱን ሲሳቡ ያደሩት ተናዳፊዎቹ የበረኸኛው ቀስተ ደመና ብርጌድ ፋኖዎች በወረዳችን ከደብረ ኤልያስ ከተማ ወጣ ብሎ ባለው በየቀጋት ቀበሌ በኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን ውስጥ የተደበቀውን ጠላት ምሽጉን በመክበብ ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ላይ መብረቃዊ ጥቃት በማድረግ እንደፈለጋቸው በመውቃትና ድባቅ በመምታት ሙትና ቁስለኛ አድርገውት ተመልሰዋል።በቆፈረው ምሽግ ቀብረውታል💪

   ይህ ራሱን መከላከያ እያለ የሚጠራው የአብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ የወንበዴ ስብስብ በዚህ ስፍራ ከ1 ወር በላይ መሽጎ እንደቆየ ይታወቃል ።የዛሬው ውጊያው ለ1 :30 ያህል የቆየ እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ የታየበት ነበር።ጠላትም የተናዳፊዎች ምት ሲበረታበት አድኑኝ ብሎ በጠየቀው መሰረት አዳረሩን ከጎዛምን ወረዳ ከማይ አካባቢ ሲጓዝ አድሮ ወደ ኤልያስ ከተማ የደረሰው ከ400 በላይ የሚሆን ሀይል ተጨምሮለት ሊታደገው ችሏል።

     እንግዲህ በዚህ አውደ ውጊያ ከጠላት ወገን 2 ፓትሮል እና 1ኦራል ሙትና ቁስለኛ አንስተዋል ሲሉ በአካባቢው ያሉ እማኞችም እስከ ረፋዱ 5:00 ድረስ በየጢሻው የወደቀውን አሰከሬን እና ቁስለኛ እየለቀሙ ነበር ሲሉ ገልፀውልናል።

     በቀስተ ደመናወቹ ከባድ ምት የተበሳጨው ጠላትም ወደ ጎፍጭማ ቀበሌ አሰሳ በመሄድ በመንደር በመግባት አንድ ንጹሀን ገበሬ መረሸኑን በአካባቢው ከነበሩ መረጃችን ለመረዳት ችለናል ሲሉ የዐፋጎ 6ኛ ክፍለ ጦር ቀስተደመና ብርጌድ ቃል አቀባይ ፋኖ ዘላለም ዘሪሁን ከንስር አማራ ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልፀዋል‼️


#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

26/06/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra


🔥የደብረኤልያስ ትንቅንቅ መረጃ‼️


🔥የዝያድባሬው አንበሳ ሜጨኛው ኮለኔል ታደሰ ሙሉነህ💪

ኮ/ል ታደሰ ሙሉነህ ከአባታቸው ከአቶ ሙሉነህ  እና ከእናታቸው ከወ/ሮ አዛለች ጥሩነህ በምእራብ ጎጃም መርዐዊ ከተማ በ1944 አ/ም ተወለዱ ።
የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምሕርታችውን ካጠናቀቁ በኋላ እናት አገራችውን በውትድርና ለማገልገል በነበራቸው ፅኑ ፍላጎት በኢትዮጵያ አየር ኃይል በአውሮፕላን አብራሪነት ሙያ እ.ኤ.አ. በ1971 ዓም ተቀጠሩ ።  በኢትዮጵያ አየር ኃይል የሚሰጠውን መሰረታዊ የወታደራዊ ስልጠና እና በሳብ ሳፋየር የመጀመሪያ ደረጃ በረራ ማሰልጠኛ አውሮፕላን የሚሰጠውን የበረራ ስልጠና በሚገባ በማጠናቀቅ ፤ በቀጣይ በቲ-28 ዲ አስመራ ፣ ቲ-33 ደብረ ዘይት እንዲሁም በአሜሪካን አገር ደግሞ ቲ- 39 እንዲሁም በቀድሞዋ ሶቪየት ህብረት የሚግ - 21 ስልጠናዎችን የተከታተሉ ሲሆን በ1974 ዓም በአገራችን በተፈጠረው የርእዮተ ዓለም ለውጥ ምክንያት የኢትዮጵያ አየር ኃይል የታጠቃቸውን ሩሲያ ሰራሽ ጀቶች በአጭር ጊዜ ተምሮ በማጠናቀቅ የአየር ኃይሉን ብቃት ወደ ነበረበት በመመለስ ለውጊያ ዝግጁ ከሆኑት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች መካከል ኮ/ል ታደሰ ሙሉነህ አንዱ ነበሩ ።
ዕብሪተኛውና ተስፋፊው የዚያድ ባሬ ጦር ያለ የሌለ ኃይሉን በማረባረብ የቀብሪ ዳሃር ከተማን ለመቆጣጠር የክብር ዘቡን ባንቀሳቀሰ ጊዜ የወራሪውን ኃይል ለመደምሰስ ግዳጅ በመቀበል የሶማሊያን የወራሪ ኃይል አከርካሪ ከሰበሩት የአየር ላይ ጀግኖች መካከል አንዱ ኮ/ል ታደሰ ሙሉነህ ነበሩ ። በዚሁ ግንባር በሚግ -23 ተዋጊ አውሮፕላን ወደ ምድር ዝቅ ብለው በመብረር የተመረጡ ኢላማዎችን በማደባየት ላይ እንዳሉ ከጠላት በተተኮሰ የአየር መቃወሚያ ያበሩት የነበረው አውሮፕላን ሲመታ እሳቸው በጃንጥላ በመዝለል ተርፈው በምድር በነበረው የወገን ሰራዊት እና በበራሪ ጓዶቻቸው ከፍተኛ ጥረት እንዲሁም በነበራቸው ወታደራዊ ብቃት ከጠላት አምልጠው የጦር ሜዳ ጀብዱ ሜዳይ ተሸላሚ ለመሆን በቅተዋል ።
ኮ/ል ታደሰ በሰሜን ግንባር በተደረገው ከፍተኛ ተጋድሎ አገራቸው የጠየቀቻቸውን መስዋእትነት ሁሉ ለመክፈል በተለያየ አውደ ውጊያ ላይ በመሰለፍ ግዳጃቸውን የተወጡ ጀግና ነበሩ ።  ከውጊያ ባሻገርም ብቃት ያላቸው ተዋጊ አብራሪዎችን ያፈሩ ስመጥር የበረራ አስተማሪም በመሆን ለትውልድ የሚተላለፍ ችሎታቸውን ለግሰዋል ።
በ1983 ዓም የህወሃት ዘረኛ ቡድን መላው አገሪቷን በተቆጣጠረ ጊዜ ኰ/ል ታደሰ ሙሉነህ እንደሌሎች የሰራዊቱ አባላት ሁሉ ወደ ባዕድ አገር ተሰደው የቆዩ ሲሆን ኤርትራ የራሷን አየር ኃይል ስታቋቁም ለ18 አመታት በበረራ አስተማሪነት አገልግለዋል ።

በተጨማሪም የህውሃት ስርዓት አገራችን ላይ እያደረሰ ያለውን የጥፋት ተልዕኰ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ የአርበኞች ግንባርን በመቀላቀል ከ1993 ዓም ጀምሮ ግንባሩን የመሩ ሲሆን በኋላ ግን በእነ ዶክተር ብርሀኑ ነጋ ሴራ ከሻቢያ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት  ምክንያት በኤርትራ መንግስት በቁጥጥር ስር ውለው እስከ ቅርብ ጊዜ ለስምንት አመታት በግዞት እስር ላይ በመቆየታቸው ሳቢያ ጤናቸው በመታወኩና ቀስ በቀስም ለህይወታቸው አደገኛ ደረጃ ላይ በመድረሱ ከእስር ተለቀው ለሚወዷት እናት አገራቸው አፈር በቅተዋል ። ይሁን እንጂ የጤናቸው ጉዳይ በሚያሳዝን ሁኔታ እያሽቆለቆለ የመጣ ሲሆን በአገር ውስጥና በህንድ አገር ህክምናቸውን ሲከታተሉ ቆይተው ጥር 27 ቀን 2011 ዓም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል ።
ኮ/ል ታደሰ ሙሉነህ አገር ወዳድ ፣ ላመኑበት ነገር ፈጽሞ ወደኋላ የማይሉ ፣ በስራቸው ትጉህ ፣ እጅግ ትሁትና ሰውን አክባሪ የነበሩ ሲሆን ባለትዳር እና የስድስት ልጆች አባት ነበሩ ።
የቀብራቸውም ስነ- ስርዐት በትውልድ ስፍራቸው ምእራብ ጎጃም መርዓዊ ቅ/ማሪያም ቤ/ክርስቲያ  ጓደኞቻቸው ወዳጅ ዘመዶቻቸውና እና በርካታ የቀድሞው የኢትዮጵያ አገር መከላከያና የፖሊስ ሰራዊት አባላት በተገኙበት በታላቅ ስነ - ስርዐት ተፈጽሟል ።
ኮ/ሎ ታደሰ ሙሉነህ ! ሞት ለሰው ልጆች የማይቀር እዳ ነውና ፤ ትውልድ የማይረሳው አኩሪ ጀግንነትና በጐ ስራህ  ምንግዜም ሲታወስ ይኖራል ።

ለዚህም የጀግኖቿን ውለታ የማትረሳው፣ ጥንትም ጀግና የማይነጥፍባት የጎጃሟ ፈርጥ መራዊ ከተማ መሰናዶ ትምህርት ቤቷን "ኮሎኔል ታደሰ ሙሉነህ 2ኛ ደረጃ መሰናዶ ት/ቤት" እንዲሁም የአማራ ፋኖ በጎጃም የሜጫውን ወኪል "ኮለኔል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ" በጀግናው ስም ሰይማለታለች !

#ታሪክ ጠባቂ ፣ ታሪክ ሰሪ ነን‼️

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

26/06/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra




🔥የፋኖን ይዞታ ለመንጠቅና ለመደምሰስ ተንቀሳቅሶ የነበረው ጠላት አስከሬኑን አዝረክርኮ ተመልሷል፣ ዝርዝር መረጃውን youtube ይመልከቱ‼️

https://youtu.be/6vQi8kF6cUE


🔥#ነበልባሎቹ_ታላቅ_ጀብዱ_ሰሩ🔥

የአማራ ፋኖ በሸዋ ከሰም ክፍለ ጦር የነበልባል ብርጌድ በቀን 24/6/2017ዓ.ም አመሻሽ ላይ የብርጌዱ ሺአለቃ ሶስት ፋኖች ባልጪ ከተማ ገብተው ከተማዋን ከአገዛዙ ነፃ አድርገው ለህዝብ ደህንነት ሲሉ ንጋት ላይ ከተማዋን  በጠዋት ነበልባሎቹ እንደ አቦ ሸማኔ የሚወረወሩት የሺአለቃ ሶስት ፋኖች ከተማዋን ለቀው ሲወጡ በየአቅጣጫው የተበታተነው የአገዛዙ ግብስብስ ሰራዊት በመሰባሠብ ተመልሶ ወደ ባልጪ ከተማ በመግባት በከተማው ያሉ የአገዛዙን ወንበር አስጠባቂ ሆድ አደር የደም ነጋዴዎች ሚኒሻና ፖሊስን ለፍተሻ አሰማርቶ ህዝብ በኬላ ሲያስበዘብዝ እሳቶቹ በቀጠናው የሚንቀሳቀሱት ጀብደኞቹ ሺአለቃ ሶስት እረመጦቹ ጠላትን በያዙት ነፍጥ የሚያናግሩት ቀጫጭኖቹ ፋኖች በኬላ ሰልተው በመጠጋት ጠላት በፍተሻ ኬላ ሳለ በከፈቱበት የጨበጣ ተኩስ አምስት ሚሊሻና ፖሊስ ከዚህ ምድር እሰከወዲያኛው በፋኖ ጥይት የተሸኙ ሲሆን አራት መቁሰላቸውን ከቦታው መረጃ የደረሰን መሆኑን እና ጀብደኞቹ ክንደ ብርቶቹ የሺአለቃ ፋኖች ግዳጃቸውን በሚገባ ፈፅመው ወደ ነፃ ቀጠና ወጥተዋል። የሟቾችን ስምና ፎቶ እንደደረሰን የምናቀርብ መሆኑን እናሳውቃለን።

ነፃነታችንን በተባበረ ክንዳችን እናስከብራለን።

ዘላለማዊ ክብር ስለነፃነት ለተሰው ሰማዕታት።

©የአማራ ፋኖ በሸዋ ከሰም ክፍለ ጦር የነበልባል ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ኢንጂነር ታደሠ ወንድሙ

  
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

26/06/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra


በዛሬው እለት ጠላት በሌሊት በመጎዝ  የአማራ ፋኖ በጎጃም 1ኛ ክ/ጦር ባህርዳር ብርጌድ  የጊዬወን ሻለቃን ለማፈን የተደረገውን ሙከራ በክንደ ብርቱወቹ እቅድ እንዲከሽፍ ተደርጎል ።
  የአውሬው የአብይ አህመድ ቡችሎች በተለያዩ ሁለት አቅጣጫወች ከጭንባ እና ባህርዳር በመውጣጣት ብዛት ያለው ሀይል በማጎጎዝ  ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሰፊው የተለመደውን በአውደ ውጊያወች ሽንፈት ሲደርስበት ሰራዊቱ የህዝቡን ንብረቶች በመዝረፍ ላይ መሰማራቱ ይታወቃል ይኸን ተግባር ለመፈፀም ሲሯሮጥ የነበረውን የጠላት ስብስብ ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት የጀመረው ትንቅንቅ ለ5 ሰዓት ያህል ውጊያ በማድረግ ሁለቱ የ1ኛ ክ/ጦር ሻለቆች በጠላት ላይ ክንዳቸውን አሳይተዋል ።

ለወገን ኩራት ለጠላት እራስምታት የሆነው የ አማራ ፋኖ በጎጃም 1ኛ ክ/ጦር የባህርዳር ብርጌድ ጊዬወን ሻለቃ እና የአማራ ፋኖ በጎጃም 1ኛ ክ/ጦር የጣናው መብረቅ ብርጌድ ዘጌ አራራት ሻለቃ በጋራ አስገራሚ ጥምረት በመፍጠር በሌሊት ለማፈን እና ለመዝረፍ የመጣውን የአብይ አህመድ ቡችሎችን በጋራ እንደ እባብ  ሲቀጠቅጥት ውለዋል ።

© የአማራ ፋኖ በጎጃም 1ኛ ክ/ጦር ባህርዳር ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት ፋኖ ሐብታሙ የሱፍ
       
#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

26/06/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra


🔥#የ1ኛ_ክፍለ_ጦር_ትንቅንቅ💪

የአማራ ፋኖ በጎጃም ፩ኛ ክፍለ ጦር 4ኛ ተከታታይ አውደ ውጊያ አደረገ።የአማራ ፋኖ በጎጃም ፩ኛ ክፍለ ጦር ባህር ዳር ብርጌድ አካል የሆነችውን ጊዮን ሻለቃን ለማፈን ከባህር ዳርና ከጭንባ ተውጣጦ የሄደውን ዘራፊ ሀይል የሁለቱ ወንድማማች ብርጌድ ሻለቃዎች የአማራ ፋኖ በጎጃም ፩ኛ ክፍለጦር ባህር ዳር ብርጌድ ጊዮን ሻለቃና የአማራ ፋኖ በጎጃም ፩ኛ ክፍለ ጦር ጣናው መብረቅ ብርጌድ ዘጌ አራራት ሻለቃ ሲወቃ ውሏል። በየቀኑ ከከተማ የሚወጣው ጠላት ከከተማ ሚወጣበትን ቀን እየረገም አስክሬኑን ሳይሰበስብና ቁስለኛውን አዝረክርኮ ሚመላሰው የብርሀኑ ጁላ ዘራፊ ሀይል ዛሬም በለሊት ወደ ቀጠናው ቢገባም የገባበትን ቀን እየረገመ ይገኛል። አሁን ላይ ነበልባሎቹ ሁለቱ ሻለቃዎች ይሄን የዘራፊ ቡድን ከፍተኛ የሆነ ሙትና ቁስለኛ አድርገው እያስፈረጠጡት ይገኛሉ ሲሉ ፋኖ ሙሉሰው የኔአባት የአማራ ፋኖ በጎጃም ፩ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ለንስር አማራ ገልፀዋል‼️

አዲስ ትውልድ! አዲስ አስተሳሰብ! አዲስ ተስፋ"
©ፋኖ ሙሉሰው የኔአባት የአማራ ፋኖ በጎጃም ፩ኛ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

26/06/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra


🔥#የአደረጃጀት_ዜና‼️
የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አማራ) ልጅ እያሱ ኮር የጁ ክፍለጦር ተመስርቷል።

የክፍለ ጦሩ ሙሉ መግለጫ    
ቀን  26/6/2017 ዓ/ም

በአማራ ህዝብ ላይ የከፈተዉን የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለመቀልበስ የህልዉና ትግል ዉስጥ የገባዉ የአማራ ፋኖ ከጊዜ ወደ ጊዜ ወታደራዊ እና ፖለቲካ አደረጃጀቶችን በብቃትና በጥራት እያሻሻለ አሁን ካለበት ደረጃ መድረስ ችሏል።

በዚህም መሰረት ዛሬ የካቲት 26/2017ዓ/ም  በይፉ የተመሰረተዉ የጁ ክፍለ ጦር በስሩ የተለያዩ አደረጃጀት መሪዎችን ሰራዊቱ መርጧል።

በዚህም መሰረት
1. አርበኛ አምሳ አለቃ ሞላ አባተ የክ/ጦሩ ዋና አዛዥ
2. አርበኛ ቢኒያም ሰኢድ የክ/ ጦሩ ምክትል አዛዥ
3. አርበኛ ተገኘ ስጦት የክፍለ ጦሩ ዘመቻ መሪ
4. መምህር አማረ ተገኘ የክ/ጦሩ አስተዳደርና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ
5. አርበኛ ሀሰን ሙሄ ህዝብ ግንኙነትና ኦዲተር ኃላፊ
6. አርበኛ ተስፋየ አለባቸዉ የፋይናንስ ኃላፊ
7. አርበኛ ግዛዉ ሰለሞን ሎጅስቲክ ሀላፊ
8. አርበኛ ዮናስ አሉላ የክፍለ ጦሩ ፐርሶኔል ኃላፊ ሆነዉ ተመርጠዋል።

ከላይ በተዘረዘሩት አደረጃጀቶች መሰረት ህዝባችንን ከጥቁር ጣሊያን የአፓርታይድ ማነቆ ስርዓት ለማዉጣት በሚደረገዉ የህልዉና ትግል በፅናት ለመስራት ቃል እየገባን በዚህ ትግል የሚመለከታችሁ ሁሉ በምትችሉት ከጎናችን እንድትቆሙ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

ድል ለፋኖ!!!
ድል ለአማራ ህዝብ!!!
©የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ-አማራ)

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

26/06/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra


🔥የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ተጋድሎ መረጃዎች‼️

የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ከደብረ ታቦር እስከ ባ/ዳር ያካለለ አውደ ውጊያ እያደረገ ነው:: አውደ ውጊያው የአለም ሳጋ አጋቾችን: የብልፅግና ሚሊሻ: አድማብተና: ካድሬና የብርሃኑ ጁላን ወራሪ ሰራዊትን ኢላማ ያደረገ ነው::

ለዛሬ የካቲት 26/2017 አም አጠባባብ ከንጋት 10:00 በጀመረው በዚህ እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር:- የሜጀር ጄኔራል ውባንተ አባተ ኮር በታቀደ መልኩ እየተከናወነ ሲሆን በስርአቱ ጦር ላይ ቁሳዊ: አካላዊ: የህይወት መስዋእትነትና ስነ ልቡናዊ ስብራት ደርሶበታል:: በተለይ ደግሞ የአለም ሳጋው: የአለም በሩ እና የወጅው ድል ጠላት ሙሉ ለሙሉ የተደመሰሰበትና ካድሬ እስከውዲያኛው የተሸኘበት መሆኑን ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል::

በሌላ መረጃ የ አማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር:- ዞዝ አምባ ንጉስ ክ/ጦር: ጥቁር አንበሳ ብርጌድ: ነብዩ አሳምነው ብርጌድ በቅንጅት ሚካኤል ደብርን ለመቆጣጠር የመጣን ወራሪ ሰራዊት ሲበትኑት ውለው በመጣበት እግሩ ፈርጥጦ ተመልሱዋል::

ሌላው መረጃ ወደ በለሳ ያለው የጀግኖቹ ትንቅንቅ ነው:: የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ንስር በለሳ ቅጣው እጅጉ ክ/ጦር ጉሃላ: ስላሬ: አርባያና ሌሎችም ቀጠናዎች ላይ ጠላትን ሙትና ቁስለኛ አድርጎታል::

ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!
©የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር

#ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️
#ምረር_አማራ💪
#ድል_ለአማራ_ፋኖ💪
#ድል_ለአማራ_ህዝብ💪

26/06/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra


የአማራ ፋኖ በጎጃም የ5ኛ ክ/ጦር ከፍተኛ አመራሮች ከክፍለ ጦሩ ተወርዋሪ ሀይል ጋር በቀጣይ በቀጠናው ላይ በሚፈፀሙ ተልዕኮዎች ዙሪያ መክረዋል!!

   አዲስ ትውልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!!
©የአማራ ፋኖ በጎጃም 5ኛ ክ/ጦር የሚዲያ ባለሙያ ፋኖ ዮሴፍ ሀረገወይን


የካቲት 26/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra


🔥የካራማራ ጦርነት የተካሄደው ከዛሬ አርባ ሰባት (47) ዓመታት በፊት የካቲት ሃያ ስድስት (26) ቀን ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰባ (1970) ዓመተምህረት ነበር‼️

#ዝክረ_ታሪክ

ከአርባ ሰባት (47) ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ዕለት ታሪክን የኋሊት!!

የሶማሊያ ጦር በምስራቅ በኩል ሰባት መቶ ኪሎ ሜትር በደቡብ በኩል ደግሞ ሦስት መቶ ኪሎ ሜትር የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ ገብቶ ነበር። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ ጦር ወራሪውን የሶማሊያን ሰራዊት ከኢትዮጵያ ግዛት በማባረር ካራማራ ተራራ ላይ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ አውለበለበ።

ቀደምት አባቶቻችን ለኛ እና ለኢትዮጵያ ነፃነት እና ክብር ሲሉ ለማመን የሚከብዱ ከባድ ተጋድሎዎችን አድርገው ነፃ አገር ለኛ ለተተኪው ትውልዶች አውረሰውናል እኛ ተተኪ ትውልዶች ግን ያንን ታሪክ ማወቅ አልፈለግንም ይባስ ብለን በብሔርና በሃይማኖት ተከፍፋለን አገር ለማፍረስ ታጥቀን እየሰራን ነው። የሰማዕታቱ መስዋትነት ባከነ የካራማራ ድልም የዚህ አሳፋሪ እጣ ፋንታ አንዱ አካል ሆነ፡፡

ክብር እና ሞገስ ለዚህ ድል መሰዋት ለሆኑ ጀግኖች አባቶቻችን ይሁን!!

#የኋላው_ከሌለ_የለም_የፊቱ‼️
#ይህ_የኛ_የኢትዮጵያውያን_ታሪክ_ነው‼️

የካቲት 26/2017 ዓ.ም

@NISIREamhra

Показано 20 последних публикаций.