Zemedkun Bekele (ዘመዴ)


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


"ይህ የቴሌግራም ቻናሌ ግንቦት1/2011ዓም የተከፈተ ነው። የእኔን የስልክ ወጪ ጨምሮ አገልግሎቴን መደገፍ የምትፈቅዱ ጓደኞቼ በ
👉🏿 https://donorbox.org/zemedemedia እና
👉🏿 https://www.paypal.com/paypalme/ZemedkunB በኩል ማገዝ ትችላላችሁ። በተረፈ ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክት ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


👆④✍✍✍ …

፲፦ በወላዲተ አምላክ የነገረ ድኅነት ሱታፌ ላይ በጳጳስ ደረጃ ሲቀለድ አይተን ዝም ልንል አንችልም። ከቅዱስ ሲኖዶስ ጠንከር ያለ ውሳኔ እንጂ ማስተባበያ አንጠብቅም። የተነቃነቀ ጥርስ ቀን ይጠብቃል እንጂ መውለቁ አይቀርም። እንደ ተራ ስኅተት ይቅርታ እንዲጠይቁም አንጠብቅም። ያስተማሩት የታሰበበት ክህደት ነውና የተብራራ መልስ ከቀኖና ጋር እንጠብቃለን። "የበራላቸው" ለመባል የብርሃን እናትን ሊጋርዱ የሚጥሩ ሰዎች ማላገጫ ሆነንም አንቀርም::

፲፩፦ ሙሴ ቤዛ በተባለበት መጽሐፍ ቅዱስ እያመኑ ድንግል ማርያም ቤዛ አትባልም ላሉት ጳጳስ ቅዱስ ሲኖዶስ ቤዛ ሲሆናቸው ማየት አንፈልግም:: ጠንከር ያለ ቀኖናዊ እርምጃ እንጠብቃለን::

ርጉመ ይኩን ዘይረግመኪ
ወቡሩከ ይኩን ዘይባርከኪ
ነገራተ ክልዔ ኢይርሳዕ ልብኪ

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ገሊላ ፳ኤል
ሚያዝያ 15 2017 ዓ.ም

"…ይላል የሄኒ የትናንቱ ሠይፈ ነበልባል ጦማሩ። የኢየሩሳሌም የቃና ዘገሊላ ወይን እንኮ አናጋሪ ነው። ያምሆነ ይህ አባ ገብርኤልም ደንግጧል። ከቤተ ክርስቲያኒቱ ሚዲያ ውጪ እነ መንክር ሚዲያን ጠርተው ለጊዜው ይቅርታ ጠይቀዋል። ቤዛ የሆናቸው መንግሥት እስካለ ድረስ ምንም አይሆኑም። ሲኖዶሱም ምንም አያመጣም። ዳንኤል ክብረትን ከፊት፣ እነ ብርሃኑ ጎበናን፣ እነ ዘበነ ለማን ከኋላ፣ እነ ቀሲስ ዮኒን፣ እነ አባ ፋኑኤልን ይዘው በአሜሪካስ ምን ይገጥመኛል ብለው ይፈራሉ? ኧረ ኤዲያ። 

"…ብቻ በአባ ገብርኤል ላይ የተመዘዘው ሰይፍ ከባድ ነው። ኅብረቱም ደስ ይላል። አሁን ከመሸ ስሰማም ባለሀብቱም በመጨረሻ ሚዲያውም፣ ማኅበሩም ታግዷል። ኪሳራ ነው የደረሰበት። ነገር ግን ይሄ የሊቃውንቱ ሰይፍ በትግራይም፣ በዐማራም፣ አሜሪካና የትም ቦታ ሆነው በቤተ ክርስቲያን ካባ ስር ተሸጉጠው የኑፋቄ መርዛቸውን በሚረጩት ላይ ሁሉ ይመዘዝ። የወደቀ ዛፍ ላይ ብቻ ምሳር አናብዛ። እንዲያውም በዚህ በደጀኔ ቶላ ኑፋቄ መነሻነት የእነ አባ ወልደ ትንሣኤም የኑፋቄ መርዝ ይነቀል። በዕለተ ስቅለት አርብ ቤተ ክርስቲያን መዋል የሚገባቸውን ምስኪን የድርጅቱን ሠራተኞች በባለፀጋ አዳራሽ ሰብስቦ ነጭ አስለብሶ ሲያስጨበጭቡ መዋል በራሱ ኑፋቄ ነው። ጥቁር በሚለበስበት የኀዘን ቀን ነጭ ለብሶ ሲዘሉ፣ ሲያጨበጭቡ፣ ቤተ ክርስቲያንን ሲዘልፉ፣ ድንግል ማርያምን ሲነቅፉ መዋልም ኃጢአት ነው። በደል ነው። አባ ወልዴ በዚህ ጾም እዚያ ተገኝተው ከሆነ ለፍልሰታ ቅዳሴ ሽሽት አሜሪካ ለቫኬሽን እንደሚሄዱት አባቶች እሳቸውም የስቅለት ዕለት በቤተ ክርስቲያን የሚፈጸመውን ሥርዓት ሽሽት ነውና ሊመረመሩ ብቻ ሳይሆን ሊወገዙም ይገባል። አለቀ።

"…የኢህአዴግ፣ የብልጽግናም የፓርቲዎቹ አባል መሆን የሚፈልግ ሰው በፓርቲው ማኒፌስቶ አምኖ የተጠመቀ መሆን ግድ ነው የሚለው። አቶ ልደቱ አያሌው የብልጽግና ፓርቲ ማእከላዊ ኮሚቴ አባል ሆኖ ሊመረጥ አይችልም። የብልፅግና ማእከላዊ ኮሚቴ የሚሆነው ሰው የበለፀገ ብልፅግና ብቻ ነው። የፓርቲው አባል የሆነ ሰው የፓርቲውን ውሳኔ እስከታች ድረስ ወርዶ የፓርቲውን ተልእኮ ይፈጽማል ያስፈጽማል። ፓርቲውን ወክሎ በምርጫ ይወዳደራል። ስለ ፓርቲው ይከራከራል። ብልፅግና ሆኖ ፓርቲውን መቃወም ከጀመረ ግን እንደ አቶ ታዬ ደንደአን ይሆናል። ይወገዛል። ይባረራል። ይታሠራል። የፓርቲውን መተዳደሪያ ደንብ ከጣሰ ስዬ አብርሃን ሆነ ማለት ነው ይታሠራል። ከፓርቲው ይባረራል። በአንድ ፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ ሆኖ ከፖለቲካ ፓርቲው ሕግና ደንብ ውጪ መንቀሳቀስ አይቻልም። በማንችስተር ማልያ ለአርሰናል መጫወትም አይቻልም። ሳይታወቅብህ አንድ ሁለቴ ልታጭበረብር ትችላለህ። ከዚያ በላይ ግን የቡድንህን ነጥብ እያስጣልክ የተቃራኒ ቡድን ደጋፊዎችን ጮቤ እያስረገጥክ በቡድኑ ውስጥ መቆየት አትችልም። ሕጋዊም አይደለም። ወንጀል ነው። በወታደር ቤት ሲሆን ደግሞ ያስረሽናል። ክህደትም ነው። አሁን እኮ ያሳቀኝ ከእኛ ይልቅ የተንገበገቡት ጴንጤዎች ናቸው። አንድ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ወዳጄ ቱግ ሲልብኝ ምንአገባህ እለዋለሁስ ጴንጤ ጴንጤ ሲጫወት አገኘሁት። መናፍቅ ነህ እንዴ ስለውም አዎ ብሎ አረጋገጠለኝ። ታዲያ አንተን በእኛ መሃል ምንአገባህ ስለው ጭራሽ ወበራብኝ። በመጨረሻ ነው እንግዲህ የጎንደር ዩኒቨርስቲ ሌክቸረሩ ወዳጄን በአባ ገብርኤል ምልንያት ጴንጤ መሆኑን ያረጋገጥኩት። ልኩን ነግሬው አፉን አስይዤዋለሁ።

"…እነ አባ ወልደ ትንሣኤንና አባ ገብርኤልን ከእኛ ይልቅ የሚወዷቸው፣ የሚያከብሯቸው፣ የሚያፈቅሯቸው እኮ ፕሮቴስታንቶቹ ናቸው። በአዳራሻቸው በፓስተሮቻቸው የሚሰሙትን ዲስኩር በእኛ ዐውደ ምሕረት ላይ ሲሰሙት ጮቤ ነው የሚረግጡት። ኢትዮጵያ አዋርዳ ገፍታ ያሽቀነጠረቻቸው ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ እኮ አይናቸውን ጨፍነው እያለቀሱ ሲጸልዩ እኛ ስንሸማቀቅ ሌላው መናፍቅ ግን ፓስተር በዳሳ ቆብ ደፍቶ የሚጸልይላቸው እኮ ነው የሚመስለው። ቀልብ፣ ወዝ፣ የሌላቸው፣ ወይ እንደፓስተሮቹ አያምርባቸው፣ እንዲሁ እንደቀላወጡ ሲልከሰከሱ ይታያሉ። ግእዝ እየጠቀሱ፣ ግእዝ እያነበነቡ ፓስተር ፓስተር መጫወት ልክ አይደለም። በእኛ ዐውደ ምሕረት ላይ መርዝ እየረጩ መናፍቅናን መፈወስ አይቻልም። ልክምከርሳቸው እየተሞላ፣ የቁስ ሰቀቀናቸው እየተሟላ አይደለም። ወንጀልም ነው። ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ እንዳለው ልሣን መናገር የቀራቸው ጳጳሳት በጊዜ ጥጋቸውን መያዝ አለባቸው። ከድሆች መቀነት በተሰበሰበ ሳንቲም የማንንም ደሀ አደግ የእኔቢጤ የቁስ ሰቀቀናም የመናፍቅ ቅጥረኛ የምንቀልብበት ምክንያት የለም። በኦርቶዶክስ ማልያ ለመናፍቃን መጫወት ልክ አይደለም።

"…ለምሳሌ ዲያቆን ምሕረት የተባለው አስደማሚ ክስተት የሆነ ልጅ የፕሮቴስታንት ፓስተሮቹን አንገት ሲያስደፋ አይተናል። ወዲያው ብዙዎች ወላጆቹ እነማናቸው ብለው ጥያቄ ጀመሩ። እኔም ጠየቄ ነበር። ከልጁ ምንም ስህተት አላገኘሁበትም። የልጁ አባት ግን ለዘመናት ቤተ ክርስቲያንን ሲያደማ የኖረ እኮ ነው። ቄስ መላኩ ማለት እነ አባ ዮናስን ያስጰነጠጠ፣ እነ ትዝታውን ያስካደ፣ ክህነቱ ራሱ አጠያያቂ የሆነ ሰው ነው። በልጁ ሰበብ አባ ወልደትንሣኤን እና አባ ጴጥሮስን ዩቲዩቡ ላይ ጋብዞ ሲውተረተርም እያየሁት እገረም ነበር። በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያደረሰውን ውድመት የሚያውቅ ያውቀዋል። ለማያውቅሽ ታጠኚ አለ ሰውዬው። ስህተት ባለገኝበትም እንዲያውም ልጁንም በጥርጣሬ እንዳየው ነው ያደረገኝ። ከፈረንጆቹ የሆነ ሴትአፕ ይኖር ይሆንን ነው ያስባለኝ። ጠርጥር ከገንፎም ውስጥ አይጠፋም ስንጥር አይደል የሚባለው?

• ይሄ ነው የዛሬው ርእሰ አንቀጼ።

•••

ሻሎም…!  ሰላም…!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ሚያዝያ 16/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።


👆③✍✍✍ …እነዚህን በግልጽ መታገል ይገባል። በፍልሰታ ደብረ ሊባኖስ፣ ደብረ ዳሞ ዋልድባ መሄድ ትቶ ወደ አውሮጳ አሜሪካ የሚሸሸውን መዋጋት ያስፈልጋል። በአሜሪካ ኑሮ ጳጳሱ መጡ ተብሎ ሴቶቹ ተራ ገብተው መቀለብ የለባቸውም። ይሄን የተራበ ጳጳስ በሌላ በምንም ወደመስመር ልታስገባው አትችልም።

"…በተመደቡበት ሀገረ ስብከት በራሳቸው ላይ በዘመዶቻቸው በኩል ተቃውሞ አስነሥተው አውሮጳና አሜሪካ ካልተመደብኩ የሚሉ እኮ ነፍ ናቸው። አዲስ አበባ ተቀምጠው ሀገረ ስብከታቸውን በሪሞት ኮንትሮል የሚያስተዳድሩ እኮ የትየለሌ ናቸው። ሀገረ ስብከታቸው ሄደው ጎብኝተውም የማያውቁም የትየለሌ ናቸው። መኖሪያቸውን አራት ኪሎ መንበረ ጵጵስና አድርገው የሀብታም ፍትፍት የሚያማርጡ እኮ ብዙ ናቸው። የተከፈተ አዲስ ሱቅ የሚመርቁ ጉደኞችን እኮ ነው እያየን ያለነው። ድህነትን ሸሽቶ የእነ ጸጋዬ ሮቶ ማዕድ ለመባረክ የጰጰሰን እንዴት አድርገህ ነው የድሆች አባት ሁን የምትለው? ድህነትን ለማሸነፍ ዋጋ ከፍሎ ሀብታም የሆነና ከሀብታሞቹ ጎራ ራሱን የመደበን አባት በምን ተአምር ነው የድሆች አባት የምታደርገው። ጭቅቅቱን፣ ቅጫሙን፣ አራግፎ በፈረንሳይ ሽቶ፣ በጣልያን ጫማ፣ በግሪክ ልብስ የተሽቆጠቆጠን ሊቀጳጳስ እንዴት አድርገህ ነው ተፈናቃዮችን፣ ስደተኞችን፣ ምስኪኖችን ጎብኝ፣ አባት ሆናቸው ብለህ የምትነዘንዘው? አይሰማህም። ከደሀ መቀነት ተፈትቶ በሚሰጥ ሙዳየ ምጽዋት ተንቀባርሮ እየኖረ ደሀን የሚጠየፍን አባት፣ ዘወትር በባለፀጋ ቤት ፀበል እየረጨ ደሀ ቤት ድርስ የማይልን፣  የምእመናንን እጅ የሚያይ ጳጳስ፣ ፈጣጣ ለማኝ የሚያስንቅ ስብእና የያዘን አስተዳደጉ ጫና የፈጠረበትን ምስኪን ምንአድርገህ ወደ መስመር ትመልሰዋለህ? ግርማ ወንድሙ፣ ሄኖክ ቅባቅዱሴ፣ ጆኒ ራጋም እኮ ጳጳሳት፣ ካህናቱን ጢባጢቤ የሚጫወቱባቸው አሳምረው ስለሚያውቋቸው ነው። ለገንዘብ ያላቸውን ፍቅር ስለሚያውቁ ነው የሚያዝረከርኳቸው። ጠቁር ራስን ግፋው ባለቆብን አስገባው የሚል የቆብ ዘረኛ ከባድ ነው። ፌደራል የተመደበለትን ጳጳስ ስለ መላእክት ጠባቂነት እንዲሰብክ መጠበቅ የዋሕነት ነው።

"…ወደ አባ ገብርኤል እንመለስ። ኦሮሞው አቡነ ገብርኤል ዐማሮቹን የጎንደር ተወላጅ ሊቃነጳጳሳት አቡነ ዮሴፍንና አቡነ በርናባስ ወይም በቀድሞ ስማቸው አባ ወልደ ትንሣኤን አስቀምጠው ነው ምንፍቅናቸውን የዘሩት። አሁን ግን የማየው ነገር ደስ አይልም። ለአቡነ ገብርኤል ምላሽ እየሰጡ ያሉት ሊቃውንት በሙሉ ትኩረታቸው ኦሮሞው ሰውዬ ላይ ብቻ ነው። የመናፍቅ ቆንጆ የለም። መናፍቅ መናፍቅ ነው። አባ ወልደ ትንሳኤን እየዘለልክ አባ ገብርኤል ላይ መደንፋት ልክ አይደለም። ኦሮሞዎቹም እየጠየቁ ነው። አባ ገብርኤል ከተሳሳቱ ልክ እንደ አባ ገብርኤል ያስተማሩት አባ ወልደ ትንሣኤም መጠየቅ አለባቸው እያሉ ነው። በኦርቶዶክስ ዘር የለም። ጎንደሬም፣ የሰላሌ ኦሮሞም ከመነፈቀ መነፈቀ ነው። ጎንደሬዎቹን ለይቶ ኦሮሞዎቹ ላይ መጮህ ልክ አይደለም። እኔ ሁለቱንም ነው የምቃወመው። የምለየው የለም። አይደለም ሁለቱን ሦስተኛውን የትግሬ መናፍቅ አባ ሰረቀንም ለይቼ አላየውም። ሚዛናችን ይስተካከል።

"…ወደ መጨረሻው ጦማሬ ስመጣ የዲያቆን ኃይሌ ጉዳይ ነው። ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌም በመጨረሻ ጊዜ፣ በመጨረሻው ሰዓት ላይ አቡነ ገብርኤል ላይ አደገኛ የተባለ ከባድ ሰይፉን አንሥቶ ታይቷል። የሄኖክ ኃይሌን የትናንቱን ጦማር ባደንቅም እኔ ግን በሄኖክ ኃይሌም ላይ ያለኝ ጥያቄ አልተነሣም። ሄኖክ ለእኔ ዘመናዊ አፈ ጮሌ የሃይማኖት ነጋዴ ነው። ሄኖክ ኃይሌ ያለ ቤተ ክርስቲያኒቱ ፈቃድ መዋቅሩ ውስጥ ሳይኖር ከሮም ካቶሊክ ጋር ያልተቀደሰ ጋብቻ የፈጸመ ሰው ነው። ሄኖክ ኃይሌ በግልጽ በአደባባይ ወጣቶችን አደረጃቶ የሀገሪቱን ሰንደቅ ዓላማ ያስገደ፣ ያዋረደ ሰው ነው። ዘረኛ እወደድ ባይ፣ አፍቃሬ ትግሬ ፀረ ዐማራ የሆነ ሰው ነው። ለትግራይ ጦርነት ብዕሩን ያነሣ፣ የተቃወመ፣ ለዐማራው ፍጅት ራሱን የደበቀ ሐዋርያ ለመምሰል በማስታወቂያ ብዛት፣ በዩቲዩበሮች ቤት በመንጦልጦል የራሱን የስብእና ካፒታል ለመገንባት የሚላላጥ ሰው ነው። በሄኖክ ኃይሌ ላይ ያለኝ ጥያቄ እስከአሁን አልተነሣም። በየትኛውም ጊዜ ለተነሡ አጽራረ ቤተ ክርስቲያን ምንም ዓይነት ሃይማኖታዊ የመከላለል ምላሽ ያልሰጠ ሰውዬ አሁን ምሳር የበዛበትን አቡነ ገብርኤል የተባለ ጳጳስ መውደቁን ሲያረጋግጥ አድቫንቴጅ ለመምታት ሲላላጥ ነው ያየሁት። የትግራይ መነኮሳት ቤተ ክርስቲያንን ገንጥለው ሲለፋደዱ እያየ እሱ የአዲስ አበባ ትግሬዎችን ሰብስቦ አብሮ ቢዝነስ እየሠራ ጮጋ ብሎ አንድ በግልጽ የሳተን የኦሮሞ ጳጳስ እንዲህ ጠንከር አድርጎ ስለተቃወመ አይደንቀኝም። አይገርመኝም። ተቃውሞውን ግን አልንቅም። አከብርለታለሁም።

"…ዲያቆን ሔኖክ ኃይሌ የጻፈውን የተቃውሞ መልእክት ሳይ እኔ ራሴ የጻፍኩት እስኪመስለኝ ነው የተደነቅኩት። እባጭ፣ ማድያታም፣ ከነንፍጡ፣ ምናምን ብሎ ሲጨርስ አሸበርቲው ዘመዴ ነኝ ከራየን ወንዝ ማዶ ብሎ የቋጨው ሁላ ነበር የመሰለኝ። ዘመድኩን ተሳዳቢ ነው። ዘመድኩን ኃይለ ቃል ይናገራል ሲሉኝ የከረሙ ሁላ ናቸው ሼር ሲያደርጉለት የዋሉት። ድፍረቱ የሌለ ገራሚ ነው። የጦማሩን ኤዲት ሂስትሪ ስቆጥር አብዝቶ መጨነቁንም ነው ያየሁበት። እስቲ ሄኖኬ የተጠቀማቸውን ቃላት እንመልከት። ይሄንን ድፍረት በእነ አኬም ላይ ያነሣ ይሆን? በእነ ወልደ ትንሣኤና በእነ አባ ሠረቀ ብርሃንም ላይ ያነሣ ይሆን? ለማንኛውም እንቁጠር።

፩፦ ፍኖተ ድድቅ የሚባል እባጭ ቤተ ክርስቲያን ላይ ከወጣ ጀምሮ አንዴ ዘፈን በሚመስል መዝሙሩ፣ አንዴ ምንፍቅናን በሚያገሣ ስብከቱ ምእመናንን ሲያወዛግብ ሰንበትበት ብሎ ነበር።

፪፦ ጌታ በወንጌል"ኀበ ሀሎ ገደላ ህየ ይትጋብዑ አንሥርት" "በድን ባለበት በዚያ አሞራዎች ይሰበሰባሉ" እንዳለው የፍኖተ ድድቅ ባለቤት ሙዳ ሥጋ ይጥላል ብለው ተስፋ ያደረጉ ሰዎች ዙሪያውን ስለከበቡት ላለፉት ጥቂት ዓመታት ቤተ ክርስቲያን ከነንፍጡ ካልወደደችው ብለው ሲሟገቱ ከርመዋል።

፫፦ በመሠረቱ ሁኔታው ሰውዬው ደሀ ቢሆን ኖሮ ገና ድሮ ተወግዞ ነበር እንድል ያደርገኛል።

፬፦ ሰሞኑን ደግሞ በፖለቲካ ቤዛነት የተሾሙ የሆኑ አንድ ጳጳስ ድንግል ማርያም ቤዛ አትባልም ብለው በፍኖተ ድድቅ አዳራሽ ሲያስጨበጭቡ ሰማን።

፭፦ ከንዑሰ ክርስቲያን ያነሰ እውቀት ያላቸው እኚህ ጳጳስ ሽልማት እንደሚጠባበቅ አዝማሪ ሰውዬውን ያስደስታል ብለው ያሰቡትን ሁሉ ሲዘባርቁ ነበር።

፮ ከቅርብ ዘመናት ወዲህ እንደ ፓስተር ለማውራት የሚጋጋጡ አባቶች ማየት ከጀመርን ሰነበትን። አይናቸውን አስሬ የሚጨፍኑ፣ (አቡነ ጴጥሮስ) በግድ እየጨመቁ ዕንባ ለማውጣት የሚታገሉ (አቡነ ጴጥሮስ) ከአሁን አሁን በልሳን ለፈለፉ ብለን በስጋት የምናያቸው (አቡነ በርናባስ)

፯፦ ምሁር ለመባል የቤተ ክርስቲያንን ነባር እሴቶች የሚያጣጥሉ የቤተ ክርስቲያን ማድያቶች (እነ አኬ፣ ራሱ ሄኖኬ) ብቅ ብቅ ካሉ ሰነበቱ።

፰፦ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተሹመው ተሸልመው ክህደት እያስተማሩ መቀጠል እንደማይቻል ለማሳየትና አንዴ ከጰጰሱ ምንም አይኮንም ዓይነት አመለካከትን ለማረም ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ዕድል ሊጠቀም ይገባዋል።

፱፦ በ3ኛው ክፍለ ዘመን ጳውሎስ ሳምሰጢ (Paul of Samosata) በአንጾኪያ ሲኖዶስ የተወገዘው ፣ ንስጥሮስ በ4ኛው ክፍለ ዘመን የተወገዘው ጳጳስ ከሆኑ በኋላ ነው። ቤተ ክርስቲያን መናፍቃንን ለመለየት ጵጵስናቸውን ፈርታ አታውቅም።…👇③✍✍✍


👆②✍✍✍ …ፓርቲው ኦህዴድኦነግ ከድርጅቱ መሪ ከፕሬዘዳንቱ አቢይ አሕመድ ጀምሮ እስከታች ድረስ ሽመልስ አብዲሳ፣ አዳነች አቤቤ ወዘተ ጴንጤዎች ናቸው። እናም ያን ካምፕ የግድ ማስደሰት አለባቸው። ከአቡነ ገብርኤል በፊት ጳጳስ የሆኑ ጓደኞቻቸው በአብዛኛው ደፋር፣ መናፍቅ የሚያስንቁ ሁላ እንዳሉ አቡነ ገብርኤል አሳምረው ያውቃሉ። ለእነዚህ ሰዎች ደግሞ መንግሥታዊ ከለላውንና ክብሩንም አሳምረው ያውቃሉ። ከአሜሪካ የሸኟቸው ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል እኮ ካህናቱን ሰብስበው "ምንድነው ልትፈርስ 50 ዓመት ለቀራት ቤተ ክርስቲያን እንዲህ መሻኮት?" እንዳሉ የሚነገርላቸው አባት ናቸው። ከልብስ ሰፊነት አውጥታ ሊቀጳጳስ ያውም በዜግነት አማሪካዊ እንደሆኑ የሚነገርላቸው ሰው ናቸው እኮ አቡነ ገብርኤልን መርቀው የሸኙት። እና ከእባብ እንቁላል የምን የዶሮ ጫጩት መጠበቅ ነው? ምንሼ?

"…አሁን የገረመኝ ነገር ግን እውነት ለመናገር አቡነ ገብርኤል ብቻ ናቸው ወይ የቤተ ክርስቲያኒቱን ዶግማና ቀኖና፣ መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ የናዱት? እርግጥ ነው በአቡነ ገብርኤል ላይ የትግሬ ሊቃውንትን አላየሁም እንጂ የኦሮሞና የዐማራ የጉራጌም ተወላጅ ሊቃውንት፣ መምህራን በአንድ ድምጽ ጠንከር ባሉ ቃላት ሲቃወሙአቸው እያየሁ ነው። ግሩም ነው። ነገር ግን ተቃውሞው መስመር እንዳይስት፣ ዱላው ደጀኔ ላይ ብቻ እንዳያርፍ በደጀኔ መስመር የነበሩትን በሙሉ መጠየቅ፣ ማካተት ያስፈልጋል። ያለበለዚያ እውነት ብንይዝም፣ ብትይዙም ውጤት አይኖረውም። አቡነ ገብርኤል ላይ የተነሣው የተቃውሞ ሰይፍ አባ ወልደትንሣኤን ለምንድነው የሚያልፈው? እነ አቡነ ሩፋኤልን ለምንድነው የሚያልፈው? እነ ብፁዕ አቡነ ማርቆስ ቅባቴውን ለምንድነው የሚያልፈው? ምንፍቅና ኦሮሞ ላይ ሲሆንና ዐማራ ላይ፣ ትግሬ ላይ ሲሆን ይለያያል እንዴ? አቡነ ባርናባስ አባ ወልዴ አማላጅ ያሉት ኢየሱስና አቡነ ገብርኤል ደጀኔ ቶላ አማላጅ ያሉት ኢየሱስ ይለያያል ወይ? ደጀኔ ቶላ ሲናገረው ውግዘት፣ ወልደ ትንሣኤ ሲናገረው እግዚአብሔር ይቅር ይበላቸው ማለትስ ተገቢ ነው ወይ? ሚዛናችን ትክክል ይሁን እላለሁ። አይጥ፣ ውሻ ብሉ የሚለውን አስቀምጦ በቤዛነት ላይ ተናገረ የሚባለው የቶላ ልጅ ላይ መደንፋቱ ትክክል አይደለም። ጎንደሬው አቡነ ባርናባስን ታግሰህ የሰላሌውን ኦሮሞ ነጥሎ ማብጠልጠሉ ፍትሓዊ አይደለም። ሁለቱንም እኩል ዳኙአቸው።

"…በረከታቸው ይደርብንና አባ ኃይለማርያም ኋላ አቡነ አረጋዊ ይደውሉልኛል። አባ በጣም ወዳጄ ነበሩ። ቤታቸው ሁላ የሚጠሩኝ፣ የሚያማክሩኝ አባት ነበሩ። ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ ቤት እየተጠራን አብረን ምሳም እንጋበዝ ነበር። ዘሪሁን ሙላትም ነበር። እናም እሳቸው ለጵጵስና ሲታጩ፣ ከየኔታ እዝራ ጋር ለውድድር ሲቀርቡ፣ የጎንደር ሎዛ ልጅ ሆነው ሳለ ለጵጵስናው ምርጫ ሲሉ የዓድዋ ተወላጅ ነኝ በማለት የትግሬ ማንነት ተላብሰው ሲተውኑ፣ በሰዓሊተ ምህረት ቤተ ክርስቲያን በመናፍቃኑ እጅ ሲቀቡ ሳይ አይቼ ዝም ማለት ስለሌለብኝ ከዕጩነት እንዲወጡ አጥብቄ ነበር የተቃወምኩት። ኋላ ላይ ከአንዲት እህቴ ጋር ቁጭብዬ ሳለሁ የእጅ ስልኬ ላይ ደጋግመው ይደውላሉ። ምንድነው አናግር እንጂ ትለኛለች። አይ የምቃወማቸው አባት ናቸው እላታለሁ። አናግራቸው ትለኛለች። አናገርኳቸው።

• አባ ኃይለማርያም፦ ዘመዴ እባክህ እባክህ ተወኝ። ስለወዳጅነታችን ተወኝ። የመነኩሴ የመጨረሻ ሕልሙ እኮ ጵጵስና ነው። እባክህ ስንት የደከምኩበትን እንቅፋት አትሁንብኝ። በማርያም፣ በወላዲተ አምላክ፣ በምትወዳት በእመቤቴ ይዤሃለሁ ልለምንህ።

~ እኔ፦ በዚህ መንገድ ያገኙት ጵጵስና ምን ያደርግሎታል? ደግሞስ ከሊቀ ሊቃውንት ዕዝራ ጋር ለውድድር ሲቀርቡስ ምን ይሰማዎታል? ይሄ ሁሉ የሚታይ ነቀፌታ እየተሰነዘረብዎ ቢሾሙስ ዕድሜ ይኖረኛል ብለው ያስባሉ? እኔ እስኪመረጡ ተቃውሞዬን አላቋርጥም። ከተመረጡ ግን አፌን አልከፍትም። ብዬአቸው ተለያየን። አባም አቡን ሆኑ። እኔም አቆምኩ። በሚዲያም ሁለታችንም ቀርበን እሳቸውም ልክ እንደነበርኩ በሺ ሰዎች ፊት መሰከሩ። ብዙም አልቆዩ ተሰቃይተው አረፉ።

"…አሁን ያሉት ጳጳሳት ሲሰብኩ አይታችኋል? እንደነ ብፁዕ አቡነ ጎርጎሬዎስ ዘመን ተሻጋሪ መጻሕፍት ጽፈው ሲያስደምሙን ዓይታችኋል? ፍሬ የሚያፈሩ አሉወይ? አንዳንዴ ማኅበራት ሰብከው የመለሷቸውን የዳር ሀገር ኢትዮጵያውያን የውኃ ጥምቀት ለማጥመቅ ለፎቶ መርሀ ግብር ከሚታዩ ሁለት ፍሬ አባቶች በቀር አሉ ወይ? የሉም። ለምን ያልን እንደሆነ በውትድርናው አገልግሎት ላይ የተቀላቀሉት ወታደሮች በፍላጎት፣ ሙያውን ወደው የተመዘገቡ ስላልሆነ ነው። ታፍሰው፣ ወይም ርቧቸው ለሆዳቸው፣ ለሥጋዊ ፍላጎታቸው ብለው የገቡ ስላሉ ነው። መስፈርቱን ስለማያሟሉ ነው። ተኩስ ሲጀመር፣ ውጊያ ሲጀመር፣ ጦርነት ሲጀመር በፍላጎት እንደዘመተው ወታደር ቆራጥ አይደሉም። ፈሪ፣ ቅዘናም፣ ቦቅቧቃ፣ ድንጉጥ፣ መስሎ አዳሪ ነው የሚሆኑት። ማንም ይማርካቸዋል። ለመኖር ስለሚጓጉ ባንዳነት ያጠቃቸዋል። እንደ ወታደር ፈንጂ ረግጠው፣ ፈንጂ ላይ ቆመው፣ እኔ ሞቼ እናንተ እለፉ የሚል ወኔ የላቸውም። የተቋሙን መስፈርት ሳያሟሉ የተመረጡ፣ ነፋስ አመጣሽ ናቸውና እንዲህ ነው የሚሆኖት። የአቡነ ጴጥሮስን፣ የአቡነ ሚካኤልን መንገድ ለመከተል እኮ ሙያውን ወደህ፣ የሙያው መስፈርት የሚጠይቀውን ሟሟለት አለብህ። አሁን እንኳን እንደ አቡነ ጴጥሮስ ሊኮን ይቅርና ሻሸመኔ ላይ የተዋሕዶ ልጆችን በታቦተ ሚካኤል ፊት ቆሞ አስጨፍጭፎ በክርስቲያኖች ደም ታጥቦ ፖለቲካው እና ዳንኤል ክብረት ስለሚፈቅዱለት ዓይኑን በጨው ታጥቦ ጳጳስ ሆኖ አሁንም የሚያቆርብ፣ የሚያጠምቅ ሆኖ ታገኘዋለህ። ቀደም ብሎ የጰጰሰውም አብዛኛው የግሩፑ አባል ስለሆነ ግድ የለውም።

"…አሁን አሁን ጳጳስም ሆነ አለቃ ሆኖ የሚሾመው የቁስ ሰቀቀን ናላውን ያዞረው ተመርጦ ነው። የድሀ ሀገር ጳጳስ መሆን ቪዛ በነፃ ስለሚያስገኝ የልመና ኮሮጆ ይዞ ዶላር፣ ፓውንድና ዩሮ ለመሸቀል የሚሮጠው ነው የሚበዛው። ታቦት 5ሺ ዶላር ለመቸብቸብ፣ በአሜሪካ ሕግ መሠረት የመጦሪያውን ሱቅ በደረቴ ቤተ ክርስቲያን ከፍቶ በበላይ ጠባቂነት ሙድ ቢዝነስ መሥራት፣ አስተማማኝ የኢኮኖሚ ለራሱ ለመገንባት ነው የሚሯረጠው። ጳጳስ ሆኖ አሜሪካ ሄዶ በየቡቲኩ የሴት ቦርሳ፣ የሕጻናት ጫማና ልብስ ሸምቶ የሚመለሰው ለእርዳታ ድርጅት እኮ አይደለም። እየተዋወቅን። ሃይ። አዎ ነውረኞች በዝተው ውርደታችን በዚያው ልክ በዛ። አይደለም ውዳሴ ማርያም ጸሎተ ሃይማኖትን የማይዘልቅ ጳጳስ አድርገህ መርጠህ፣ ሹመህ፣ ፍሬ ያፈራልኛል ብለህ መድከምህ ነው የሚያስቀኝ። ይትፍርህ እም እያለ የሚያላግጥ። ከዚህ በላይ መዋረድ ከወዴት ይምጣ? እናም ከተጀመረ አይቀር ጠንከር ያለ ፍትጊያ መፈጠር አለበት። ጠንከር ያለ። ጠላት ወኪሎቹን አጰጵሷል፣ የሲኖዶስ አባል አድርጓል። ውጊያው ቀላል አይሆንም። አሁን የተሾሙትም አብዛኛዎቹ ፍንዳታዎችና ጩጬዎች ናቸው። ገና የቁስ ሰቀቀን ያለቀቃቸው። መደብ ላይ ተኝተው ከርመው አሁን ሞዝቮልድ ላይ መተኛት የጀመሩ። የማይርባቸው፣ የማይጠማቸው። ሹፌር ተመድቦላቸው የሚንቀሳቀሱ። በአንዲት ስልክ ብፁዕ እገሌ ነኝ ብለው ባለሥልጣኑንም፣ ባለፀጋውንም የማዘዝ መብትና ሥልጣን ያገኙ። ፍልሰታን እንዳይጾሙ፣ ዕለት በዕለትም እንዳይቀድሱ ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካና ካናዳ፣ አውሮጳ የሚሸሹ። የሚያመልጡ። አሜሪካ ሄደው የባለትዳሮችን አልጋ፣ ወይ የልጆችን አልጋ ወርሰው፣ የባለ ትዳሮችን ፕራይቬሲ የሚሻሙ፣ የሚያደፈርሱ…👇②✍✍✍


"ርእሰ አንቀጽ"

"…የወደቀ ዛፍ ምሣር ይበዛበታል። በቀድሞው ደጀኔ ቶላ፣ ወይም በሣሕለ ማርያም ቶላ ወይም አሁን ምርጥ እና ንፁሕ ኦሮሞ ተብሎ በዘር ኮታ ጳጳስ ተደርገው ብፁዕ አቡነ ገብርኤል በተባሉት አባት ላይ ከጃፓን ሱናሚ፣ ከአሜሪካው ሄሪኬን የሚተካከል የተቃውሞ ማእበል ሲጎርፍባቸው እያየሁ እየተደነቅኩ ነበር። ጳጳሱ አስቀድመው ለሹመት ሲታጩ አይ አይሆንም ኧረ ንፅሕና ይቅደም። ሰውየውን በዘር መርጣችሁ ከመሾማችሁ በፊት ዞርዞር ብላችሁ ስለ ሰውየው ጠይቁ። የሁለት ልጆች አባት እንደሆኑ ይነገራልና አጣሩ። ባለቤታቸውም በሕይወት አለች ይባላልና አጣሩ። ሰውዬው በአልኮል ፆርም የተወጉ ናቸው። አሜሪካ ያሉትን ምእመናንም ጠይቁ። ምግባሩ የተበላሸ ሰው መነኩሴ ስለሆነ ብቻ ሊቀ ጳጳስ አታድርጉ ብዬ ስጮህ የሰማኝ አልነበረም። የእኔ ተቃውሞ ደግሞ ለዕጩነት የቀረበው ሰው እስኪሾም ድረስ ብቻ ነው። ከተሾመ በኋላ ግን የግድ ካልሆነ በቀር እንብዛም አፌን አልከፍትም። ከአሜሪካ ስቶሮች ቮድካ ጭኖ ወደ ሀገር ቤት የሚገባ መነኩሴ ጳጳስ አድርገህ እግዚአብሔር ያሳያችሁ።

"…ደጁ ላይ ተቃውሞ ሳቀርብ በኃይለኛው ተቃውሞ ያነሱብኝ በመጀመሪያ ደብረ ሊባኖስ አካባቢ ተወላጅ ነን። የሸዋ ሰው እንዳይሾም ከመፈለግ የተነሣ ነው እንጂ ለመጠጥ ለመጠጥማ የጉራጌው ሊቀጳጳስ አይበልጡም ወይ። ከመውለድ ለመውለድስ ብፁዕ አቡነ እገሌና ብፁዕ አቡነ እገሌ ጎረምሳ ልጆች አድረሰው የለም ወይ? ብፁዕ አቡነ እገሌ እመሆይ እገሊትን በጠራራ ፀሐይ ደፍሮ አይደለም ወይ ከክብርም አሳንሶ ያስወለዳት። ብፁዕ አቡነ እገሌ ከሞቱ በኋላ እንኳን በውርስ ጉዳይ ልጃቸው ፍርድቤት ከስሶ አባትነቱን ለማረጋገጥ ፍርድቤቱ ከሟቹ ሊቀጳጳስ አስከሬን ላይ ዲኤንኤ ተወስዶ ይመርመር እስኪባል ድረስ ተወስኖ ሟቹ ሊቀጳጳስ ትግሬ ስለሆኑ ብቻ አይደለም ወይ እነ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ተሟግተው የከረመው የሊቀጳጳሱ አስከሬን ምርመራው የቀረለት። ለምንድነው ደጀኔ ቶላ ላይ ሲሆን ተቃውሞ የሚበረታው? የፎን ሴክስ የሚፈጽሙት ሊቀ ጳጳስስ ወዘተ ብለው ወረዱብኝ። እኔ እነሱንም አልሰማሁም። ተቃውሞዬን ግን አጠናክሬ ቀጠልኩ። አቡነ አረጋዊ እስኪሾሙ፣ አቡነ ሩፋኤልም እስኪሾሙ ድረስ መረጃ እያቀረብኩ ስጋቴን ገልጬ በግልጽ በይፋ ተቃውሜአለሁ። ከተሾሙ በኋላ ግን ሲያበዙት፣ ልቅ ካልሆኑና መረን ካልለቀቁ በቀር ቁጥብ ነኝ። ከሹመት በፊት እንደነበረው እምብዛም አፌን አልከፍትም።

"…የአቡነ ገብርኤልም እንደዚያው ነው። ሰሚ ባይኖርም አፌን ሞልቼ ተቃውሜአለሁ። ያንጊዜ እኔ ስቃወም፣ የተቃውሞ ሓሳብ ሳቀርብ ከዳር ቆሞ ለዕጩው ሊቀ ጳጳስ ከሹመት በኋላ የሚያገኘውን ጥቅም እያሰበ የውዳሴ መዓት ሲያዥጎደጉድ የነበረ ሁላ፣ በአንጻሩ ዘመድኩን ተሳዳቢ ነው፣ ነቃፊ ነው፣ አባቶችን አዋራጅ ነው። በጦማሮቹም ሆነ በንግግር ዲስኮሮቹ ላይ የሚጠቀማቸው ቃላት የስድብ ናቸው። የዱርዬ ቃል ነው የሚጠቀመው፣ ምንም የቤተ ክርስቲያን ልጅ አይመስልም ብላብላ በማለት ከዳር ቆመው ሲደልቁኝ፣ ሲያሙኝ፣ ሲቦጭቁኝ ነበር የከረሙት። አቡነ ገብርኤል ደብረ ሊባኖስ የነበሩ መነኮስ ናቸው፣ ገድል ቤት ቀጥ ብለው ሲያገለግሉ የኖሩ አባት ናቸው። ነገር ግን ከጊዜ በኋላ ድቀት ሲገጥም እንደመደበቅ እንደ ነውር ጌጡ ደፋር የሆኑ ሰው ናቸው። በክርስትና ሕይወት ዕውቀት ሲያጥርና ንፅሕና ሲጎድልብህ በቀጥታ የምትሆነው መጥፎ ሰው፣ መናፍቅ፣ ክፉ፣ ጨካኝ፣ ለመንጋው የማይራራ አረመኔ ነው የምትሆነው። አንድ መነኩሴ ይሁን ቄስ ዲያቆን፣ ጳጳስ ይሁን ሰባኪ፣ ዘማሪ ሲመነፍቅ ካያችሁት የሥጋ ድቀት ሰልጥኖበታል ማለት ነው። ንስሀ ገብቶ እንደመመለስ በዚያው ነው ጨካኝ ሆኖ የሚቀረው። ለዚህ ነው አንዳንድ ነውረኞች የንስሐ ልጆቻቸውን የሚያነውሩት። ያውም ቃለ እግዚአብሔር እየጠቀሱ።

"…እነዚህ ነውረኞች ይደራጃሉ። እንደ አክስዮን፣ እንደ ሼር ሆልደር ነው የሚደራጁት። የጵጵስናውን መድረክ ጠቅልለው ሊይዙት እስኪችሉ ድረስ ነው የሚደራጁት። መጀመሪያ አንዱን መነኮስ ጓደኛቸውን በባሌም በቦሌም ብለው እንዲመረጥ ያደርጋሉ። ከዚያም ሁለት ሦስት ሆነው ተጠቃቅሰው ሊመረጡ ይችላሉ። አገዛዙ ለራሱ ፖለቲካ ማራመጃ የሚመርጣቸው፣ የሚያስመርጣቸው እንዳሉ ሆነው ከጓደኝነት ባለፈው በቤተ ዘመድ የሚመረጡም አሉ። በዘር የሚመረጡ አሉ። ራሳቸው መናፍቃኑም ኮትኩተው አሳድገው አስመርጠው የሚያስቀምጡት አሉ። ግብጽ እስላሞችን አሠልጥና ጳጳስ አድርጋ ልካልን 7 መስጊድ ሠርቶ ሄዶ የለም እንዴ? ጉድ እኮ ነው። ኢሉሚናቲውም፣ ግበረሰዶማውያንም ገንዘብ ስላላቸው ሊያስመርጡና ከውስጥ ወደ ውጭ ለመናድ ቦታ ሊያሲዙ ይችላሉ። የዘረኞች ግሩፕም፣ በፖለቲካም አመለካከት ታጭቶ የተመረጠው፣ በጓደኝነት፣ በጉቦ፣ በእጅ መንሻም የተመረጠው በሙሉ ከተመረጠ በኋላ ከእባብ እንቁላል የዶሮ ጫጩት እንደመጠበቅ ያለ ነው። ጥሪው ሰማያዊ አይደለም። ጥሪው ምድራዊ ነው። ምድራውያን ሆነው ለሰማዩ ጌታ ሠራዊተ ሰማይ ሆነው ለማገልገል በግድ ሳይወዱ በግድ የሚፈርሙ ትክክለኛ ወታደር፣ ትክክለኛ እረኛ ሊሆኑ አይችሉም። ውትድርና ፍላጎትን ይጠይቃል። ዓላማው ገብቶት፣ ለሀገር መሞት፣ ለወገን መስዋዕት መሆን ገብቶት ወዶና ፈቅዶ የውትድርና ተቋም ሄዶ የሚመዘገብ ወታደርና በግድ ታፍሶ፣ ተቀጥቅጦ፣ ተደብድቦ ወታደር የሚሆን ይለያያሉ። ርቦት አማራጭ አጥቶ ወታደር የሆነ ወታደር የሚጠብቀው ባንዳ መሆን፣ ሴት ደፋሪ፣ ዘራፊ፣ ገፋፊ፣ ፈሪ፣ የውትድርና ተቋሙን ስም የሚያቆሽሽ አለሌ ቦዘኔ ነው የሚሆነው። በቤተ ክርስቲያንም እንዲሁ ነው።

"…በጥሪ የተሾሙ። በመንፈስ ቅዱስ ፈቃድ የተሾሙ፣ ሕይወታቸው ታይቶ፣ ዕውቀታቸው ታይቶ፣ ንፅሕናቸው ተመስክሮላቸው የተሾሙ በሙሉ ፍሬ ያፈራሉ። ጉቦ፣ መማለጃ ሳይሰጡ ባዶ እጃቸውን ተጠርተው የተሾሙ በሙሉ ፍሬ ያፈራሉ። በመማለጃ፣ በጉቦ የተሾመ ሊቀጳጳስ ምን በወጣውና ነው ስለአንተ ፍሬ የሚጨነቀው። ከስንት ዘመድ፣ ከንስሐ ልጆቹ ተበድሮና ተለቅቶ፣ በአራጣ ተበድሮ የተሾመው ሰውዬ ስለአንተ መንፈሳዊ እድገት ያስብልህ ወይስ አናቱ ላይ ስለሚጮኸው ዕዳ። ዕዳውን እንዴት እንደሚከፍል፣ መቼ እንደሚከፍል ጭምር ነው የሚያስበው፣ የሚጨነቀው። አቡነ ሩፋኤል አሜሪካ ያለውን መነኩሴ አሾምሃለሁ ብሩን ግን በሹፌሬ በኩል ላከው ያለው ትዝ ይበላችሁ። ሥልጣነ ክህነት ያውም የጵጵስና ሹመት በገንዘብ ሲሆን አስቡት። መቅደሱ ይቆሽሻል፣ ቀኖና ይሻራል። መስዋእት አያርግም፣ በሀገር ላይ መከራ፣ ፍዳ፣ ራብ፣ ጠኔ፣ ችጋር፣ ጦርነት፣ መቅሰፍት ይበረታል። በኢትዮጵያ አሁን የምናየው ሁላ ችግር መነሻ ምክንያቱ እኔን ጨምሮ ቤተ መቅደሱ በማይገባ ሰዎች መሞላት ነው። እያንዳንዱን ሰባኪ፣ ዘማሪ፣ ቄስና ጳጳስ በብዛት ቀርባችሁ ብታወሯቸው እኮ የቁጭራ ሰፈር ልጆች ምንኛ ጨዋ ናቸው እኮ ነው የሚያስብላችሁ። እሾህ ይበዛል።

"…ወደ ሣህለማርያም ቶላ እንመለስ፣ ወደ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ማለት ነው። ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ለነውራቸው መሸፈኛ የግድ መደበቂያ መፈለግ ነበረባቸው። ያሾማቸውን አገዛዝ ፍላጎት ማሟላትም አለባቸው። አገዛዙ መናፍቅ ነው። የአሕዛብ ጥርቅምም ነው። ኦሮሞ ነኝ ካልክ ደግሞ የግድ ምርጫህን ማስተካከል አለብህ። በየትኛውም የሥልጣን እርከን ላይ ተቀመጥ ጴንጤንና እስልምናን ማስደሰት፣ ኦርቶዶክስን ማዋረድ አለብህ። ዐማራን መስደብ፣ ማዋረድ፣ ማንቋሻሽ ደግሞ አይደለም ለጵጵስና ለፕትርክናም ያሳጭሃል። አቡነ ገብርኤልም ያደረጉት ያንን ነው። የመረጣቸው እና ያስመረጣቸው የኦሮሚያ…👇①✍✍✍


መልካም…

"…እና ዘመዴ አሁን የዐማራ ፋኖ አንድነት በቅርቡ የለም ነው የምትለን? የሚል ጥያቄ መነሣቱ አይቀርም። እኔም ምላሼን ይዤ በነገው ርእሰ አንቀጼ ከች እላለሁ። እስከዚያው ድረስ በዛሬው ርእሰ አንቀጽ ዙሪያ እየተወያየን እንቆያለን። በማለት ነበር የትናንቱን ርእሰ አንቀጼን በይደር ያሳደርኩት። ይሄ የትናንት ነው።

"…ይሄን ቀጠሮ ወደ ነገ ዕለተ አርብ ርእሰ አንቀጼ አሸጋግረዋለሁ። ከቻልኩኝና ከደረሰልኝም በገደብ በሴራ በድሮን እንዲጨፈጨፉ ከተደረጉት ፋኖዎችና አመራሮች መካከል የተወሰኑትን ስም ዝርዝርም ይዤ ለመቅረብ እሞክራለሁ። በነገው ርእሰ አንቀጼ በሴራ ነው የተገደለው ተብሎ የሚታመነው ጌታዬ መንበሩም ለመገደሉ ምክንያት የሆነበትን ጉዳይ በስሱ እንዳስሳለን።

"…ለዛሬ ግን ከትናንት ጀምሮ እስከ አሁኗ ደቂቃ ድረስ በውስጥ መስመር እንደጉድ የሚጎርፍልኝና "ዘመዴ የዲያቆን ሄኖክ ኃይሌን ጦማር አላየኸውም እንዴ? እያሉ ፋታ እያሳጡኝ ላሉ ብዙ ፍሬ ሰዎች የሚሆን የማስተንፈሻ አጭር ርእሰ አንቀጽ እዚያው ጮቄ ላይ ሆኜ አዘጋጅቼላችኋለሁ። ስለሱ ልለጥፍላችሁ ነኝ።

• ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ አይደል?

18k 0 3 151 724

ሐሙስ፦ አዳም ሐሙስ ይባላል፦

"…ከጌታ ትንሣኤ በኋላ በአምስተኛው ቀን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አባታችን አዳም እና እናታችን ሔዋን ከትንሣኤው ጋር ተያይዞ ታስበው ይውሉ ዘንድ አዳም ወር በገባ በ6 ከኢየሱስ እና ከእነ ቅድስት አርሴማ ጋር አብሮ የሚከበር የወርሀዊ በዓል ሥርዓት የተሠራለት ቢሆንም የዛሬው ግን አባታችን አዳም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ፣ በሜዳህ ድኼ፣ በእንጨት ላይ ተሰቅዬ ከ5 ቀን ተኩል በኋላ አድንህሃለሁ ተብሎ የተሰጠው ተስፋና የተገባለት ቃል ኪዳን ተፈጽሞ አዳምና ልጆቹ ነጻ የወጣበትን አስበን የምንውልበት ዕለት ነው።

"…አባታችን አዳም በሦስት ነገር ወደቀ። በተዋሕዶ፣ በመብልና በእጽ ምክንያት ወደቀ። ሰይጣን ከቆንጆዋ እባብ ተዋሕዶ፣ እባብን መስሎ፣ እባብንም አሕሎ አዳምና ሔዋንን ሰብኮ፣ ጌታ እግዚአብሔር እንዳትበሉት፣ የበላችሁ ቀን የሞት ሞትን ትሞታላችሁ ብሎ የከለከላቸውን ዕጽ በልተው ሞቱ። በዚህ ምክንያት የሞቱትን አዳምና ሔዋንን ለማዳን እግዚአብሔር ወልድ ወደዚህ ምድር መጣ።

"…ሰይጣን በእባብ ገላ ተዋሕዶ እንዳዋረደው፣ ጌታም ከአዳም የልጅ ልጅ ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ሆኖ በተዋሕዶ ተገልጦ አዳነው። አዳም በዕፅ ምክንያት እንደ ሞተ የሚያውቅ ጌታም በዕለተ አርብ በ17 ክንድ ዕፀ መስቀል ላይ ተሰቅሎ አዳነው። በመብል ምክንያት የጠፋውን አዳም "ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ… ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ። ዮሐ፥ 6፥ 54-56 በማለት በመብል ምክንያት የጠፋውን አዳምን የራሱን ሥጋና ደም መብልና መጠት አድርጎ አደነው።

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግአዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍሥሐ ወሰላም።

28.1k 0 40 808 1.2k

መልካም…

"…አሁን ደግሞ 12ሺ ሰው አንብቦት 3 ፍሬ ሰዎች ብቻ ጓ 😡 ብው ወዳሉበት ወደዛሬው ርእሰ አንቀጻችን በእናንተ ወደማስተቸቱ እንገባለን። ከድሮው አንጻር ሲታይ አሁን አሁን ጓ😡 ብው የሚልብኝም ሰው እየቀነሰ መጥቶ በጣም ስጋት ላይ ወድቄአለሁ። ብዙዎች የተነፈሱ ይመስለኛል። ሃቅን መጋፈጥ አልቻሉም። እናም ጓ 😡 ብው የምትሉ ሰዎች ከፔጄ ባትጠፉ ዴየስስ ይለኛል።

"…ሌላው በአባ ደጀኔ ቶላ በብፁዕ አቡነ ገብርኤል አጀንዳ እንድታጠር የፈለጉ ቅባቴና መኔዎችንም አይቻለሁ። "አንተ የሚያምርብህ የሃይማኖት ጉዳይ ነው። እነ ሄኖክ ኃይሌ እንኳን ኃይለቃል መናገር ጀመሩ እኮ። መምህር ዘበነም ጓ ብሏል። ሲኖዶሱም ውይይት ጀምሯል እናም ዘመዴ እሱላይ ብትሠራ ያሉኝ አዛኝ ቅቤ አንጓቾችም ገጥመውኛል። እኔ ግን አልኳቸው እንኳን ይሄ ሁሉ ሊቅ ታክሎበት ለእመቤታችን ራሷ አታንስም። እኔ በዚህ ጉዳይ ላይ ብቻዬን የምጮህበት ዘመን አልፏል። ሞኝህን ፈልግ ብያአቸዋለሁ። አሁን የእኔ ትኩረት ጎጃም ነው። ጮቄ ተራራ።

"…እኔ ዘመዴ ከጎጃም አልወጣም። ከጮቄም አልወርድም። የነገውን ርእሰ አንቀጽ እስክጽፍላችሁ ድረስ የዛሬውን እንዴት አያችሁት? ደፈር ብላችሁ ምከሩ፣ ተነጋገሩ፣ ተከራከሩ።

• ተንፒሱ…ጻፉ…✍✍✍

39.1k 1 16 321 1.2k

👆③✍✍✍ …የዘር ማጥፋት የሚጠቅማትን ፕሮፓጋንዳ ሠራላቸው። ቲክቶክ፣ ፌስቡክ፣ ዩቲዩብ፣ ቴሌቭዥኑ ሁሉ አሥረስ መዓረይ ሆነ። የጀግና ዐማራ ፋኖ በጎጃም ጀግኖችም በድሮንና በስናይፐር መርገፍ፣ መውደቃቸውን ቀጠሉ።

"…ይሄን ጊዜ ነው እኔ ጎጃም መግባቴን ያወጅኩት። ጎጃም መግባቴን እንደሰማ በመጀመሪያ ከተደጋጋሚ የስልክ ቅጥቀጣ በኋላ አላነሣውም ያልኩትን የአስረስ መዓረይን የሥልክ ጥሪ አንሥቼ ማነጋገር ጀመርኩ። እሱ ጠበቃ ስለሆነ አመጣጡ እኔን ቅርጽ ሊያሲዘኝ ነበር። በፍርድ ቤት የለመደውን እኔ ላይ ለመተግበር ነበር አመጣጡ። አስረስ ብልህ ነው። ሲጀምር እንኳ ያለኝ "ዘመዴ አንተ ግን ዋጋህን ታውቀዋለህ? አንዳንድ ሰዎች ዋጋቸውን አያውቁም። አንተ ማለት ቀላል ሰው አይደለህም። መሬት ላይ እኮ ገበሬው ሳይቀር ዘመዴ ምን አለ ነው የሚለው። እናም ዋጋህ ውድ ነው ነበር ያለኝ። አሁንም ደጋግሜ ስሰማው ይገርመኛል። አላልኩም ካለ አስረስ ይናገርና እኔ ልፈርበት። ሌሎቻችሁ በማታውቁት አትዘባርቁ። ውሸት ማለት ያለበት ባለቤቱ ነው። የመጀመሪያው ቀን የስልክ ውይይታችን በመግባባት ነበር የተቋጨው።

• አስረስ፦ ሃሎ መምህር ዘመድኩን እንደምን አለህ። እንኳን ወደ ጎጃም ምድር ለጉብኝት መጣህ። እንደው በጾሙ ባይሆን መልካም ነበር…

~ዘመድኩን፦ ሃሎ ጠበቃ አስረስ እንዴት ነህ?

• አስረስ፦ እንዴ እንዴት ስልኬን ልታውቅ ቻልክ? ተደዋውለን እኮ አናውቅም።

~ ዘመድኩን፦ አዎ እርግጥ ነው ተደዋውለን አናውቅም። ነገር ግን እኮ ከአለቃህ መልእክት እየተቀበልክ የምታደርሰኝ በዚሁ ስልክ ነበር። እኔ ለአንተ አልመልስልህ እንጂ ስልክህንማ ሴቭ አድርጌ እኮ ይዤዋለሁ።

• አስረስ፦ በፍጹም እኔ ጽፌልህ ዐላውቅም።

~ ዘመድኩን፦ ቆይ ጠብቀኝማ። ስክሪንኮፒ አድርጌ ላኩለት።

• አስረስ፦ ኦ ያያ ልክ ነህ፣ ይሄኛው ያኛው ስልኬ ነው። ረስቼው ነው። ይቅርታ።

~ ዘመድኩን፦ ምንም አይደል።

"…እንዲህ ነው የተጀመረው የእኔና የአስረስ ግኑኝነት። እኔም ከመጣህማ ማርያም ታምጣህ ለመጠየቅ፣ ለመመርመር ፈቃደኛ ነህ? አልኩት። አዎ አለኝ። አስረስን በፈቃዱ መረመርኩት፣ ጠየቅኩት። ቃሉን ተቀበልኩት። 9 ጥያቄ ሲቀረኝ ደንብሮ፣ ደንግጦ ጠፋ። አላስተረፍኩትም። በውስጤ ያለውን ሁላ ነው የጠየቅኩት። ሴራውን ሁላ ነው ያስለፈለፍኩት። አንድነቱ በጎጃሞች እንደዘገየ የነገረኝ፣ ያመነልኝ ራሱ አስረስ መዓረይ ነው። እነ ዝናቡ ናቸው ወታደራዊ አዛዥነቱም ለጎጃም መሰጠት አለበት ብለው ትንሽ ያስቸገሩን እንጂ ሠራዊቱ ራሱ መውጫ መግቢያ ነው ያሳጣን ያለኝ ራሱ አስረስ መዓረይ ነው። እኔ ዘመነ ካሤ እስከተመረጠ ድረስ ዘመነ ስለማይተወኝ፣ ስለማይከዳኝ ችግር የለብኝም ብሎ በቃሉ የነገረኝ ራሱ አስረስ ነው። ውይይታችንን ደጋግሜ ሳዳምጠው አሁንም ድረስ እገረምበታለሁ። እኔ ከሰው ሰምቼ አይደለም። በይሆናልም አይደለም የምጽፈው። እኔ ከፈረሱ አፍ የሰማሁትን፣ በመረጃና በማስረጃ የያዝኩትን ነው የማወራው። ግርማ አየለንና አልማዝ ባለጭራዋን "እነሱን ሰው አድርገህ፣ ከሰው ቆጥረህ" ያለኝ አስረስ ራሱ ነው። የእኔን የዘመዴን ዋጋም ውድነት በአፉ የገለጸልኝ አስረስ መዓረይ ነው። መጀመሪያ ክዶኝ ኋላ ላይ የነገረኝ ማርሸት ነው ስለው ትንፋሽ አጥሮት ሲንተባተብ ብትሰሙት ትደነቃላችሁ። የሆነው ሆኖ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ባወቀ አስረስን ከቤቴ አምጥቶ በቤቴ ያስለፈለፈውም ራሱ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ነው ብዬ ነው የማምነው።

"…አሁን የተያዘው ሴራ አክራሪ የዐማራ ብሔርተኛ እና የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ፍጹም አማኝ የሆኑ የጎጃም ጀግኖችን ማስወገድ ነው በጎጃም የተያያዙት። ለምሳሌ በቀደም በድሮን ገደብ ላይ የተፈጁትና ያለቁት በሙሉ ምርጥ ምርጥ የዐማራ ታጋይ የጎጃም ፋኖዎች ናቸው። በየትኛውም የምረቃ ሥነ ሥርዓት ላይ የማይጠፉት እነ አስረስ መዓረይ፣ እነ እሸቱ፣ እነ ማርሸት በዚያ የኮማንዶ ምረቃ ላይ አልተገኙም። ሠልጣኞቹም ከመዋቅር ውጪ ነው የሠለጠኑት። የሥልጠናውም በጀት ከዐማራ ፋኖ በጎጃም የፋይናንስ ቋት የተገኘም አይደለም። አንድ ባለሀብት ነው ገንዘቡን የሰጠው። የብርጌዱ መሪ እና ኋላ እሱም ከጀርባ እንደተመታ የሚነገረለት ሻለቃ መንበሩ ጌታዬም ይሄን አካሄድ በጽኑ መቃወሙን ነው አሁን ጮቄ ላይ ሆኜ እየሰማሁ ያለሁት። በድሮን የተጨፈጨፉትን ከጭፍጨፋው በፊት በአካባቢው ድሮን እየታየች ነውና ልጆቹ ይበተኑ እያሉ የዐማራ ፋኖ በጎጃም የቴሌግራም አክቲቪስቶች አብዝተው ቢጮሁም ምላሽ አላገኙም። ኋላ ላይ ግን ልጆቹ ጭዳ ከሆኑ በኋላ የአዞ እንባ "ጅግና ይሞታል፣ ትግል ይቀጥላል" ብላ ብላ ዲስኩር ከጫካ ውስጥ ተሁኖ ተለፈፈ። ይሄ ልክ አይደለም።

"…አሁን በጎጃም የዐማራ ፋኖ በጎጃም ትልቅ ፈተና ውስጥ ነው ያሚገኘው። የዐማራ ፋኖ አንድነት ይመጣል ተብሎ የሚለፈፈውም በእነዚሁ የዐማራ ፋኖ በጎጃምን እግር ተወርች አስረው ቀፍድደው በያዙት አካላት አማካኝነት ነው። ማርሸት ፀሐዩ በቃል አቀባይነቱ ዕድል አግኝቶ በቅርቡ የምሥራች ጠብቁ የሚለውም ፍጹም ውሸት ነው። እነ አስረስ እያሉ የዐማራ ፋኖ አንድነት የማይታሰብ ነው። ሞጣ እንኳ በአንድ ቪድዮው ላይ አስረስን ሲያስቀር ዘመነን ጨምሮ በሙሉ ፋኖዎችን ባንዳ የሚል ማዕረግ ሰጥቶ ሲያከናንብ ነበር የሰማሁት። ሞጣ የምሥራቅ ጎጃም ፀረ ኦርቶዶክስ መናፍቅ ቅባቴ ነው። በሴራው በምሥራቅ ጎጃም የሚገኙ የተዋሕዶ ጀግኖችንም እየተቀረጠፉ ነው። ማርሸት ፀሐዩ ከግንባሩ ገንዘብ ያዥ ከወሮ ሕይወት ጋር በስልክ ባደረገው ቃለመጠይቅ ላይ በግልጽ የነገራት "ዐማራ ጄኖሳይድ ተፈጸመበት የሚባለው ውሸት ነው። ጭፍጨፋው የዓለም አቀፍ የጄኖሳይድ መመዘኛን አያሟላም" ብሎ የተሟገተ የዐማራ ነፃ አውጪ ፋኖ ቃልአቀባይ ነው። ድሮኗ እነሱን አትነካም። የጎጃም ዐማራ ጀግኖች ግን ተራ በተራ እየተለቀሙ ነው። ጎጃም ጥቁር ከል እየለበሰች ነው። የጀግና መፍለቂያ ሀገር በአመራር ቅሽምና እመቀእመቃት እየወረዱ ነው። ፉከራ፣ ቀረርቶ፣ ሽለላ ብቻውን ለጎጃም ዐማራ ረብ አያመጣለትም። በጎጃም ዶክተሮች በተጠና መልኩ አየተረሸኑ ነው። እየተሰደዱም ነው። መምሕራን እየተጨፈጨፉም፣ እየተሰደዱም ነው። ደንቆሮ፣ ማይም፣ ያልተማረ ትውልድ ጎጃም ላይእንዲበቅል እየተደረገ ነው። ነጋዴና ንግድ ቀዝቅዟል። ያልተማረ ማይም ትውልድ ደግሞ ባርያ ከመሆን የዘለለ ስፍራ አያገኝም። ይሄ ሲነገር ለመፍትሄው ከመራወጥ ይልቅ ለምን ተተቸን እያለ የሚያለቃቅሰው፣ የሚነስረው፣ የሚያንዘረዝረውን መንጋ ማየቱም ያሳቅቃል። ያሳቅቃልም። በጣም ነው የሚያሳፍረው። ቤተሰብህ፣ ትውልድህ በሴራ እያለቀ ነውና መፍትሄ ፈልግ ስትለው ለምን በአደባባይ ተነገረኝ ብሎ ኮሬንቲ ካልጨበጥኩ ብሎ የሚፎገላውን ሳስብ እደመማለሁ። ኩራት እራት አይሆንም እኮ።

"…እና ዘመዴ አሁን የዐማራ ፋኖ አንድነት በቅርቡ የለም ነው የምትለን? የሚል ጥያቄ መነሣቱ አይቀርም። እኔም ምላሼን ይዤ በነገው ርእሰ አንቀጼ ከች እላለሁ። እስከዚያው በዛሬው ርእሰ አንቀጽ ዙሪያ እየተወያየን እንቆያለን።

• ዘመዴ ሚዲያ መጥቷል። አየር ላይም ውሏል።

• የባንዳና የሾተላይ መርዝ ይሽራል።
• የባንዳና የሾተላይ እሾህም ይነቀላል።
• የዐማራ ፋኖ በጎጃምም ከሕመሙ ይፈወሳል።
• ዐማራም እንደ ሕዝብ ድል ያደርጋል።

~ይደፈርሳል…ግን ደግሞ ይጠራል…✊

•••

ሻሎም…!  ሰላም…!

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
አሸበርቲው/አስነቀልቲው
ሚያዝያ 15/2017 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።


👆②✍✍✍ …ቡድን ነው። የጎጃሙ ግን ይለያል። ከዶክተር ሙሴ ጀምሮ አሁንም ከጎጃም ውጪ ወደ ውጪ የሚሉ አካላት ትግሉን ተቆጣጥረው ይዘውታል። ፋይናንስ ደግሞ ዘጭ ነው። እናም የጎጃሙ ከበድ የሚለው ለዚህ ነው።

"…ለዚህ ፕሮጀክት ሲባል ከ30 ዓመት በላይ ከታች ከ1ኛ ደረጃ ጀምሮ ተመልምለው እየተረዱ፣ እየተደገፉ አድገው ዩኒቨርሲቲም ሲገቡ ወጪ ተችሎላቸው ተመርቀው ሥራ ተመድበው ተኮትኩተው ያደጉ ልጆች አሁን የዐማራ ፋኖ በጎጃምን ወታደራዊና ቦለጢቃዊ የአመራር ቦታውን ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ተቆጣጥረውት ይገኛሉ። የጎጃሙ ቋጠሮ በቶሎ የማይፈታው ለዚህ ነው። ከባድ ነው። እንደ ጎንደርና እንደ ወሎ አጀንዳ አራማጆቹ ከዐማራ ፋኖ ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራር ውጪ አይደሉም። ራሳቸው አመራር ናቸው። የጎጃሙ ሴራ አደገኛነቱ ለራሳቸው ለጎጃም ዐማራ ፋኖዎች ጭምር ነው። ሴራውን የማያውቁ፣ በምልመላው ውስጥ ያልነበሩ። ነገር ግን ጎጃም መወለዳቸው፣ ዐማራ መሆናቸው፣ መከራው ገፍቶ ወደ ትግሉ የቀላቀላቸው። በንፁሕ ዐማራነት መንፈስ የሚታገሉቱ በተለይ ኦርቶዶክሳውያኑ ምሁር ጀግና ፋኖዎችም፣ ከሕዝብም መካከል እየተለቀሙ በሙሉ እየተወገዱም ነው። ከተሰመረው ቀይ መስመር የሚያልፍ የጎጃም ዐማራ ፋኖ ጀግና ከጀርባ በመቺ ኃይል ይመታና ይወገዳል አልያም በድሮን በጥቆማ በጅምላ ይጨፈጨፋል። አለቀ።

"…የጎጃሙ ኃይል የሚዲያ የበላይነት አለው። የአክቲቪስቶችም የበላይነት አለው። የጋዜጠኞችም የበላይነት አለው። የቴሌግራም ገጽ ላይ የተከፈቱ አብዛኛው ፔጆች የጎጃም ልጆች ፔጅ ነው። ቴሌግራም ላይ በየቤቱ ድምጻቸው ጎላ ብሎ የሚሰማውም የእነሱ ድምፅ ነው። ነገሩ የገባቸውም ያልገባቸውም አክቲቭ ሆነው ነው የሚንቀሳቀሱት። ሚዲያውን በሰበር ዜና የሚያጨናንቁትም እነዚሁ አካላት ናቸው። ግንብ አያፈርሱም እንጂ እንደ ኢያሪኮው ሠራዊተ እስራኤል በጩኸት የሚተካከላቸው የለም። እናም ይሄን አስኳል ሰብሮ ገብቶ ነገርየውን ለመጋፈጥ የፈጣሪ ጥበቃና ርዳታ ከሌለህ ከባድ ነው። አደገኛም ነው። አብዛኛው ሰው ነገርየው አልገባውም። ነገርየው እጅግ ረቂቅ፣ ውስብስብና የተጠላለፈ ነው። በጎጃም ጉዳይ ትንታኔ የሚሰጡ ጋዜጠኛ በለው ወላ ቦለጢቀኛ የነገሩን 1% እንኳ ዐውቆ አይደለም የሚንቀሳቀሰው። አልገባቸውም ባይ ነኝ። በጎጃም ሀብቱ አለ። ገንዘቡ አለ። መሣሪያው አለ። የሰው ኃይሉ በሽ ነው። ግን ትግሉ ከላይ ተጠልፏል። ተጠልፏል ሲባል እንዲህ በዋዛ በፈዛዛ የሚነገርና የሚታለፍ ተጠልፏል አይደለም። ከባድ ጥልፍ ነው። እሱን መጋፈጥና ማስተካከል ካልተቻለ ዓይናችሁ እያየ ጎጃም ዱቄት ይሆናል። አንድ ዐማራ ብቻ ነው የሁሉም መዳኛ። እኛ ብቻ ብሎ ተገንጣይ፣ ጠቅላይ ሓሳብ ማራመድ አደገኛ ነው። አጥፊ አውዳሚም ነው።

"…አሁን በጎጃም ያለው የዐማራ ፋኖ በጎጃም 95% ቱ አመራር አጠቃላይ የዐማራ አንድነት እንዲፈጠር አይፈልግም። 5% ቱ ብቻ ነው አንድነት ፈላጊው። የሚበልጠው ስግብግብ፣ ተረኛ ገዢ ለመሆን የቋመጠና ካልተሳካ ጎጃምን ክልል ወይም ሀገር ማድረግ የሚፈልግ ጎጠኛ ነው። መስከረም ላይ አንድነቱ ሊመጣ ሲል ጎንደር የሚገኘው የዐማራ ፋኖ በጎንደር የእነ አርበኛ ባዬ ቡድን በእስክንድር ነጋ ተጠልፎ ከነበረው የእነ አርበኛ ኃብቴ ቡድን ጋር ንግግር ላይ ስለነበረ አንደነቱ ሳይበሰር ተራዘመ። በመሃል ግን በእኛ ምክንያት አንድ ባለመሆናችን የዐማራን ሕዝብ መከራ ከሚያራዝም ብለው ጎንደሮች በቃ አንድነቱ ይፍጠን፣ የእኛና የእነ ሀብቴም ንግግር ከሰመረ እና ከተሳካ ከአንድነቱ በኋላ አስፈላጊውንና ተገቢውን ሥፍራ እንሰጣለን በመላት ከሸዋም፣ ከወሎና ከጎጃም ጋር መክረው ወሰኑ። በውሳኔውም መሠረት ከብዙ ክርክርና ውይይት በኋላ የአንድ ዐማራ ፋኖ መሪዎች፣ የሥልጣን ድልድሉም ተወስኖ አለቀ። ሁላቸውም በተስማሙበት መሠረት አርበኛ ዘመነ ካሤ የዐማራ ፋኖ አንድነቱ ጊዜያዊ መሪ እንዲሆንም ወሰኑ። ወሰኑና ወደ አፈጻጸሙ፣ ወደ ማወጁ ሊሄዱ ሲሉ የጎጃሞቹ ተወካይ ጠበቃ አስረስ መዓረይ ሳንካ መፍጠር ጀመረ። ጭራሽ ከውይይቱ ስፍራ ጠፋ። እልም ብሎም ጠፋ። እንደ ድንገት ሲገኝም ሳንኳ እየፈጠረ ያለቀ የደቀቀውን ጉዳይ እንደገና እያመሰው ይረብሽ ጀመር።

"…አስረስ መዓረ የዘመነ ካሤን መሪነትን በተለይ ጎንደሮች ተቀብለናል ማለቱ አስደነገጠው። ተሸበረም። ቋሚ ትርክት፣ እንደ ፍልስጤምና እስራኤል፣ እንደ ሰሜንና ደቡብ ኮሪያ፣ እንደ ሕንድና ፓኪስታን ይተያይ ዘንድ ሰኔ 15 የተባለ መርዛማ ጎንደር፣ ሸዋና ወሎን መከፋፈያ ገዳይ ትርክት ደምስሶ የሚያስቀር ውሳኔ ነበር በጎንደሮች በኩል በወሎም የተወሰነው። ይሄ ነገር ለእነ አስረስ መዓረይ ቡድን አልተዋጠም። የዚያን ሰሞን አስረስ መዓረይ ጠፍቶ ሳለ በጎጃም የድሮን ጥቃቱ የትየለሌ ሆነ። በተለይ የአርበኛ ዘመነ ካሤ ቀኝ እጅ ናቸው የሚባሉት የጎጃም ዐማራ ጀግኖች በሙሉ እየተለቀሙ ተደመሰሱ። ተበሉም። በጎን ደግሞ እነ ይሄነው የሸበሉ፣ እነ አማኑኤል አብነት፣ እነ በላይነህ ሰጣርጌ ግሩፕ፣ እነ አልማዝ ባለጭራዋ፣ እነ ሞጣ ቀራንዮ የተባሉ የምሥራቁ ጎጃም የእነ አስረስ መዓረይ የሳይበር ሠራዊት አርበኛ ዘመነ ካሤን በጥበብ በስውርም፣ በግልጽ በገሀድም፣ በቅኔ፣ በአግቦ፣ በአሽሙርም በማዋረድ፣ በማንቋሸሽ ቀጣዩ የዐማራ ፋኖ በጎጃም መሪ የሚሆነው ሰው ጠበቃ አስረስ መዓረይ መሆኑን ማወጅ ጀመሩ። መጻፍም ጀመሩ። "ዘመነ አስረስን የሚበልጠው ብረት በመጨበጥ እንጂ ሁለቱም በንባብ እኩል ናቸው።" ብለው በድፍረት መጻፍ ሁላ ጀመሩ። ድሮኗ ዘመነ ካሤ ላይ አነጣጥራ መቆም ጀመረች። ያኔ ነው እኔ ዘልዬ ነገር ሳይበላሽ ወደ ጎጃም የገባሁት።

"…የዐማራ ፋኖ በጎጃም የታችኛው አመራሮች ጥያቄ ማንሣት ጀመሩ። ለምንድነው አንድነቱ የሚዘገየው? ምንድነው ችግሩ በማለት እነ አስረስ እና እነ ዘመነ ላይ ጥያቄ ያዥጎደግዱ ጀመር። ሕዝባችን እያለቀ ነው። ከጎንደር፣ ከወሎና ከሸዋ ወንድሞቻችን ጋር በቶሎ አንድ ካልሆንና ጎንደር ችግር ሲገጥመው እኛ ሄደን፣ እኛ ችግር ሲገጥመን ሌላው ጋር ሄደን ካልተዋጋን እንዴት ማሸነፍ እንችላለን። አንድ ካልሆን ማሸነፍ አንችልም። በየሰፈራችን ሆነን በየተራ እያለቅን ነው። ምንድነው ችግሩ? ከእናንተ ነው ወይስ ከጎንደሮች፣ ከወሎና ከሸዋ? በማለት መጠየቅ ጀመሩ። ወተወቱም። እንዲያውም አንዳንዶቹ ጎንደር፣ ሸዋ፣ ወሎም እየደወሉ ምንድነው ችግሩ በማለት ይጠይቁ ያዙ። ተጠያቂዎቹም ለጠያቂዎቹ ምላሽ ይሰጡ ጀመር። "እኛ ሁሉንም ጨርሰን የምንጠብቀው የጎጃምን ውሳኔ ነው። መሪውንም ከጎጃም መርጠናል። የጠፋው የእናንተ ተወካይ አስረስ ማረ ነው" በማለት ይመልሱላቸው ጀመር። በዚህ የተበሳጩት ምስኪን ነገሩም ያልገባቸው የጎጃም ዐማራ ፋኖዎች እነ አስረስን ወጥረው መያዝ ጀመሩ። ዘመነ ካሤም ኧረ ይሄ ነገር እንዴት ነው በማለት በለሆሳስ መጠየቅ ጀመረ።

"…ቀደም ብሎ በዲፕሎማሲው፣ በፖለቲካው ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ ሀገራት የራሱን የፖለቲካ ካፒታል የገነባው አስረስ መዓረይም የእኔ መዓት እንደሚዘንብበት ሳያውቅ፣ ሳይረዳ ለብቻው ይዳክር፣ ይፈነጥዝ ያዘ። የበፊት የኢሣት ጋዜጠኞች እነ መሳይ መኮንን፣ እነ ወንድምአገኝ፣ አነ ደረጄ ሁላ የአስረስ መዓረይ ልሣኑ ሆኑ። አፍቃሬ ወያኔዎቹ ኢትዮ ፎረሞችና እነ በቃሉ አላምረው ሁሉ፣ እነ ኦሮምቲቲው ተብታቤ ሞገስ ዘውዱም ሁሉ ቤተኛው ሆኑ። ትሪፕል ኤዎችም ፈረንጅ ጋዜጠኛ ሁላ ላኩለት። ከጋዜጠኛው ጋር በነበረው ቃለ መጠይቅ ላይም ትግሬዋ ወያኔ በወልቃይት በማይካድራ ለጨፈጨፈችው…👇②✍✍✍


"ርእሰ አንቀጽ"

"…ዘንድሮ በ2017 ዓም ከጎንደር መልስ ነበር ከገና ከበዓለ ልደት በፊት ወደ ጎጃም የገባሁት። መጀመሪያ አገባቤ እስከ በዓለ ጥምቀት በዚያ ለመቆየት ነበር አስቤ፣ አልሜ፣ አቅጄ ወደ ጎጃም የሄድኩት። ጎጃም ገብቼ ነገርየውን ሳየው ግን ሓሳቤን ቀይሬ አይደለም በጥምቀት በልደት ልመለስ ዐቢይ ጾምን በዚያው በጎጃም አሳልፌ እስከ ትንሣኤ ድረስ ለመቆየት ወሰንኩ። በዚህ የውሳኔ ሓሳቤም ልጸና አልቻልኩም። በጎጃም ያለው የደነደነ ነገር አይደለም እስከ ትንሣኤ ፋሲካ እስከ ነሐሴ ጾመ ፍልሰታ ድረስም ብቆይ የማይቀረፍ መሆኑ ገባኝ። እሱንም አራዝሜ እስከ መስከረም 1/2018 ዓም እስከ ቅዱስ ዮሐንስ በዓል አስከ እንቁጣጣሽ ድረስ እንደምቆይ ገለጥሁ። መጀመሪያ መርጡለ ማርያም፣ ከዚያ ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሰነበትኩ በኋላ ነው አሁን በዓቴን ወዳጸናሁበት ጎጃም ጮቄ ተራራ ላይ ከትሜ የቀረሁት። ከመረጃ ቴቪ ጋር ስንነጋገር እሺ ጎጃምስ መግባቱን ግባ፣ እስከመቼ ነው የምትቆየው? ነበር የተቋሙ ጥያቄ። እስከ መስከረም ድረስ ነው የምቆየው የሚለው የእኔ መልስ አስደንጋጭ ነበረ። አሁን ላይ ሳየው መስከረምም ከጎጃም የምወጣ አይመስለኝም። ማርያምን በጣም አስፈሪ፣ በጣምም ከባድ ነው የጎጃም ነገር። እንደሚወራው አይደለም። ጀግንነት፣ ወንድነት ሳያንሳቸው ነገር ግን ተተብትበዋል አይገልጻቸውም።

"…ከመረጃ ቲቪ እንደለቀቅኩ ለዘመድ ቴቪ ምሥረታ ወደ ራየን ወንዝ ማዶ በዓቴ ለጥቂት ጊዜ ብቅ ጥልቅ እያልኩ ከመመለሴ በቀር ከወርሀ ታህሳስ አጋማሽ ጀምሮ አብዛኛውን ጊዜዬን እያሳለፍ የምገኘው በዚያው በጎጃም ነው። እኔ ጎጃም በመግባቴ መጠነኛም ቢሆን ሚጢጢዬ ለውጥ መምጣቱ በሁሉም ዘንድ የሚታመን ነው። ለውጡ መሠረታዊ ለውጥ ግን አይደለም። የጎጃም ጉዳይ በጣም ውስብስብ ነው። የጎጃም ጉዳይን ከባድ የሚያደርገው የገንዘብ ጉዳይም ስላለበት ነው። የውጭ ኃይሎች የፖለቲካ ኢንቨስትመንት አለበት። የጎጃም ጉዳይ የማንነት ጥያቄና እጅግ አደገኛው የሃይማኖት ጉዳይም አለበት። ጎጃም የታላቁ ወንዝ የዓባይ ውኃ መገኛም ስለሆነ የብዙዎች ዓለም አቀፍ ኃይሎች ትኩረት ሰጥተው በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚፋተጉበት ስፍራ ነው። የፖለቲካ ምእመናን እንደሚያስቡት ጎጃም በአርበኛ ዘመነ ካሤና በጠበቃ አስረስ መዓረይ ምናምን ተብሎ በቀላሉ የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም። እጅግ እጅግ አደገኛና ከባድ ነገር ነው በጎጃም ያለው። መለኮታዊ ጣልቃ ገብነት ከሌለ በቀር ጎጃም ብቻ ሳይሆን ዐማራ በጎጃም ጉዳይ ከባድ ዋጋ ይከፍላል። ከባድ ኪሳራንም ያስተናግዳል።

"…እኔ ዘመዴ ጎጃም ከገባሁ ወዲህ ተለቅመው በሴራ ከተገደሉት ከአርበኛ ዮሐንስና ከአርበኛ ሃይማኖት በቀር በጎጃም ጋብ ብሎ የነበረው የድሮን ጭፍጨፋ እና ጀግናን ከጀርባ ነጥሎ የመምታቱ ነገር ጋብ ብሎ ቆሞ የነበረ ቢሆንም ሰሞኑን ግን በጊዜ የለንም መንፈስ ይመስላል ሴረኞቹ የሴራ ሰንዱቃቸውን ከፍተው እንደገና በድጋሚ አገርሽተው ጎጃምን በተለየ መልኩ ማስጨፍጨፋቸውን ጀምረው ታይተዋል። ጎጃምን ወያኔ ትፈልገዋለች። ሻአቢያም ይፈልገዋል። ኦህዴድ ኦነግም እንዲሁ ሴል አስገብቶ ተቀምጧል። በጎጃም የጎንደር ስኳድም እጁን ነክሯል። የጦር መሪ ሁላ አለው በጎጃም። በጎጃም አገው ሸንጎ ወታደራዊ ቁመናው ከፍ ያለነው። በጎጃም የቅባትና የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ፉክቻም ይንፀባረቃል። ብአዴን በሁሉም የዐማራ ፋኖ ትግል ውስጥ ገብቶ ቢታይም እንደ ጎጃም ዐማራ ፋኖ የተቆጣጠረው ግን አለ ማለት አይቻልም። አሕፋድ እስክንድር ነጋ እንኳ የአባቴ ሀገር ነው ብሎ የራሱ ሴል አለው ጎጃም ላይ።

"…ነገርየውን ስጽፈውም፣ ስናገረውም ይመርራል። ያንገሸግሻልም። ነገር ግን ደፍሮ፣ ጨክኖ ለመፍትሄው ካልተንቀሳቀሱ በቀር የጎጃም ኪሳራ በትውልድ እንኳ በቶሎ አይመለስም። ማርያምን እንደቀላል አትዩት። ሰሞኑን ጮቄ ከመግባቴ በፊት በጎጃም ጉዳይ ራሳቸው ጎጃሜ የሆኑ የጎጃም ዐማሮችን ለማግኘትና ለመወያየት ሞክሬ ነበር። ሁላቸውም የሚነግሩኝ ነገር እጅግ ከባድ ነው። በጣም ከባድ ነው። አገዛዙ ራሱ ዐማራን እያደቀቀ ያለው ሁለቱን ጎጎ ዎችን ግራና ቀኝ ገዝቶ ይዞ ነው። ጎጃምና ጎንደርን። የወያኔም የኘሆነ የኦሮሙማው ኃይላት አብዛኛው የብአዴን ባለ ሥልጣናት የሚመረጡት ከጎጃምና ከጎንደር ነው። አሁንም በፋኖ አንድነት ላይ ውዝግብ እየፈጠሩ የሚገኙት ሁለቱ ጎጎ ዎች ናቸው። ከዚያ አካባቢ ባለው እርስ በእርስ መናናቅ፣ መገፋፋት ምክንያት ዐማራ ከባድ ዋጋ እየከፈለ ነው። ሰኔ 15ን እንደ ቤንዚን እየተጠቀሙበት ሁለቱ ዝሆኖች ሲራገጡ ምስኪን ሳር ዐማራው እየተጨፈለቀ፣ እየተደፈጠጠም ነው። ይሄን ማስተካከል በቀላሉ የሚቻል አይመስለኝም። አገዛዙም ይሄን በሚገባ ስለሚያውቅ ነው ደረቱን ነፍቶ እያላገጠባቸው የሚገኘው።

"…የታመመ ሰው መድኃኒት ነው የሚታዘዝለት። መድኃኒት ደግሞ በባህሪው መራር ነው። ይጎመዝዛል። ያንገሸግሻልም። የኮሶ መድኃኒት የሚጠጣ ሰው ዶሮ ማታ፣ ዶሮ ማታ እየተባለ ከመድኃኒቱ በኋላ ሲፈወስ የዶሮ ፍትፍት እንደሚጠብቀው እየተነገረው ነው ያን ሆምጣጤ፣ ሬት የተጨቀጨቀ የሚመር የኮሶ ፍሬ እየተንዘፈዘፈ፣ እየተንገሸገሸ የሚጠጣው። የሚጋተው። ያለበለዚያ የኮሶን ትል አይስክሬምና የፍራፍሬ ጭማቂ ጁስ አይፈውሰውም። የዐማራም ትግል ለደረሰበት በሽታ መፍትሄው ዶሮ ማታ ዶሮ ማታ እያለ ጥርሱን ነክሶ ጎምዛዛውን መድኃኒት መርጦ ጨክኖ መዋጥ ብቻ ነው። የዐማራ ትግል እንዲፈወስ መፍትሄው እንዲያ ማድረግ ነው። አሁን የሚታየው የትግሉ አያያዝ ግን ለዐማራም፣ ለራሳቸው ለታጋዮቹም ምንም አይጠቅማቸውም። ጠብ የሚል ነገርም አያመጣላቸውም። ትግሉም ፈቀቅ አይልም። አንዳንድ የፋኖ መሪዎች፣ በእገታ፣ በኮንትሮባንድ፣ በቀረጥና ታክስ ስብሰባ፣ በመሳሪያ ሽያጭ፣ በግብርና ሥራ ላይ እየተሳተፉ ስለሆነ ትግሉ እንዲቋጭ ፈጽሞ አይፈልጉም። ሴረኞችና ሴራ ራሱ የሚመራው የዐማራ ትግል ትርፉ መጪው ትውልድ ራሱ ቀና የማይልበትን ስብራት ጥሎ ማለፍ ብቻ ነው የሚሆነው። እናም ከወዲሁ በፍጥነት የዐማራ ፋኖን ትግል ፍቱን መድኃኒት በመስጠት ከደረሰበት ስብራት መፈውስ ያስፈልጋል። ማርያምን ጊዜ የለም። እኔ ይሄን እየጻፍኩ የዐማራ ፔጆችን ዞር ብላችሁ ስታነቡ በብርጌድ ሰበር ዜና ድብልቅልቁ ወጥቶ ስለምታዩ ግራ መጋባታችሁ አይቀሬ ነው። ግን ጨክናችሁ መድኃኒቱን ዋጡት። የሚሻለው የእኔ የዘመዴ ምክር ነው።

"…እንደነገርኳችሁ ነው። አሁን የዐማራ ዋነኛው የችግሩ ቋጠሮ የሚገኘው ጎጃም ውስጥ ነው። ሰንኮፉ የሚገኘው ጎጃም ውስጥ ነው። ችግር ሸዋም አለ። ጎንደርም ወሎም አለ። የሚፀንነው ችግር ያለው ግን ጎጃም ነው። የጎጃም ዐማራ ችግር ደግሞ አሁን ዝም ብዬ ሳየው በምክክር፣ በውይይት፣ በንግግር የሚፈታም አይመስለኝም። ሥር የሰደደ፣ ቀድመው የተዘጋጁበት ኃይሎች የላይኛውን ወሳኝ ስፍራ የተቆጣጠሩት ስለሚመስለኝ ነገርየውን ከባድ ያደርገዋል። ለምሳሌ ከሸዋ በቀር ጎንደርን፣ ወሎን ክልል የማድረግ እንቅስቃሴ በሰፊው ነው ያለው። ሁሌም ሲናገሩ ነው የምትሰሟቸው። ነገር ግን በአፍ ይነገር፣ ይመከር፣ ፕሮፓጋንዳም ይሠራበት እንጂ በወሎም፣ በጎንደርም አፍቃሬ መንግሥት የሆነ አካል የሚያወራው እንጂ ነገርየው በሠራዊቱ ውስጥ ሰርጾ የገባ አይደለም። የነገርየው የክልልነት አራማጆቹም ከሠራዊተ ፋኖ ውጪ ያሉ አካላት ናቸው። በጎንደር የፖለቲካው ቅማንት የትግሬ ዲቃላ ስኳዶች እና የዐብን ብአዴን አባላት ሲሆኑ፣ በወሎ ደግሞ አፍቃሬ ኦሮሙማው እዚህ ግባ የማይባል የወሃቢይ እስላም…👇①✍✍✍


መልካም…

"…እኔ ዘመዴም በአዲስ አበባ የነበረኝን ቆይታ አጠናቅቄ በሰላም ጎጃም ጮቄ ተራራዬ ላይ ደርሻለሁ። በአዲስ አበባ የጎጃሙንና የሸዋውን የድሮን ጭፍጨፋ አጀንዳ ለማስቀየር በአባ ደጀኔ ቶላ ወይም በአቡነ ገብርኤል አማካኝነት በፀጋዬ ሮቶ የሠራተኛ ማኅበር አዳራሽ በእመቤታችን ላይ የተዘራውን የምንፍቅና ትምህርት መስመር ያስያዙ ሊቃውንት ትምህርት ስኮመኩም ውዬ ነው እነሱ ወደማይነኩት አጀንዳ ወደ ጮቄ ተራራ ተጋድሎዬ የተመለስኩት። ጮቄ እኮ ነፍስ ነች።

"…ወደ ጮቄ ተራራ ስሄድ በቦሌ አየር መንገድ በኩል ነበር ያለፍኩት። በዚያም ሳልፍ የቀድሞው ግራኝ አሕመድ ረዳት፣ የአሁን ዳግማዊ ግራኝ አሕመድ አጋዥ ቱርክ በቦሌ አየር መንገድ በሦስት ግዙፍ አውሮጵላኖች የተጫኑ የዐማራ መጨፍጨፊያ ቦንብና ጥይት እያራገፉ ነበር የተመለከትኩት። ይሄን የቱርክን ጭካኔ ያየው የተመለከተው የዐማራ አምላክ ደግሞ ቱርክ በዛሬው ዕለት በመሬት መንቀጥቀጥ እያራገፋት መሆኑን ከአልጀዚራ ዜና እያየሁ ስደነቅ ነበር። ባለፈውም እንዲሁ በኢትዮጵያ ጉዳይ እጇን ስታነሣ ዱቄት አድርጓት ነበር። አሁንም ገና ምን ዓይተው።

"…አሁን ጮቄ ተራራ በአቴ ደርሻለሁ። የተከመረ የቤት ሥራ ነው የጠበቀኝ። እንደ አዲስ የሚነሣብኝ የተለየ አዋራ ባይኖርም ነገር ግን ከበፊቱ የከፋ ሴራ አለና እሱን ሴራ ወደማፍረሱ እገባለሁ። በድፍረት እናገራለሁ ጎጃም አደጋ ውስጥ ነው። ባለድርሻ አካላትና ይመለከተናል የምትሉ በሙሉ በጊዜ መፍትሄው ላይ ካልተረባረባችሁ መጪው ጊዜ ከባድ ነው። የአንድነት ዘመቻ ብላብላ ፉገራውን ለጊዜው አቁማችሁ የምር አንድ ካልሆናችሁ እመኑኝ ደም እንባ ብታለቅሱ የማትወጡት አዘቅት ውስጥ ነው የምትዘፈቁት። መዝግቡልኝ። ተናግሬ የቀረ የለም አይደል? እደግመዋለሁ መዝግቡልኝ።

• እናሳ ርእሰ አንቀጹን ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ…?

35.1k 0 7 149 1.3k

ረቡዕ፦ አልዓዛር ይባላል።

"…የማርታና የማርያም ወንድማቸው አልአዛር መሞቱን ተከትሎ ከተቀበረ ከ4 ቀን በኋላ ጌታ በሕዝቡ ሁሉ ፊት መግነዝ ፍቱለት መቃብሩንም ክፈቱለት ሳያስብል እንዳስነሣው እያስበን የምናከብርበት ዕለት ነው። “…ኢየሱስም፦ ትንሣኤና ሕይወት እኔ ነኝ፤ የሚያምንብኝ ቢሞት እንኳ ሕያው ይሆናል፤” ዮሐ 11፥25 የሚለውን ወርቃማ የትንሣኤ ትምህርት ያስተማረንም በዚሁ በአልአዛር መቃብር ላይ ቆሞ ነበር።

"…በእርግጥ አልአዛር የሞተው በዚህ ዕለት አልነበረም። አልአዛር የሞተው ከበዓለ ሆሣዕና በፊት በነበረው ረቡዕ ሲሆን አራተኛ ቀኑ የሚሆነው ቅዳሜ የሆሣዕና ዋዜማ ላይ ነበር። ጌታም ያስነሣው በዚሁ በዕለተ ቅዳሜ መጋቢት 17 ቀን ነበር። በዚሁ ቀን መታሰቢያ እንዳያደርጉለት የግርግር ወራት ሆነ። በ22 ሆሳዕና ሆነ። በ23ም ርግመተ በለስ አንጽሖ ቤተ መቅደስ ሆነ፣ ደግማሞ የአልዓዛር ትንሣኤ ከሞት ወደ ሞት እንጂ ለሕይወት ያልሆነ፣ ከጊዜም በኋላ ተመልሶ የሚሞት ትንሣኤንም ጠባቂ ስለነበር በዚህ ምክንያት የትንሣኤው በኩር የክርስቶስ ትንሣኤ ካለፈ በኋላ በዛሬው ዕለት እንዲከበር ሥርዓት ሠርተውልናል።

"…ለምሳሌ ጌታ የወይን ጠጁን ወደ ውኃ የቀየረው የካቲት 23 ነበር። ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ግን ሥርዓት ሲሠሩልን የካቲት 23 በዐብይ ጾም የሚውል ሆነው ቢያገኙት በዚህ ዕለት ሀሴት፣ ደስታ ማድረግን ከልክለው የየካቲት 23ን የቃና ዘገሊላ በዓል ወደ ጥር 12 አምጥተው ከበዓለ ጥምቀት በኋላ የውኃ በዓል ከውኃ ጋር ይከበር ይውል ዘንድ እንደወሰኑት ሁሉ የአልአዛርንም ትንሣኤ ከትንሣኤ ጋራ እንዲውል ነገር ግን ከጌታ ትንሣኤ በኋላ በዛሬው ዕለት እንዲከበር አደረጉልን።

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግአዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍሥሐ ወሰላም።

39.7k 0 35 806 1.3k

"…የምርኮኛ አያያዝ በምሥራቅ ጎጃም…

"…እነኝህ ወጣቶች ሃይማኖት በቀለ፣ መሰረት አሳዬ እና ድንበሩ ሽታ ይባላሉ። ከሰሞኑ ከወራሪው ሠራዊት ካምፕ በመውጣት የወገንን ኃይል የተቀላቀሉ የ33ኛ ዙር አድማ መከላከል የብርሸለቆ ምሩቃን ናቸው። የአረጋ ከበደን "ሙሴዎች" እየተቀበልን ነው። በነገራችን ላይ ብርሸለቆ ከተመረቀው 5,500 የአድማ መከላከል አባላት መካከል ግማሽ ያህሉ ከነ ትጥቃቸው ፋኖን ተቀላቅለዋል ይላል የአስረስ የፌስቡክ ልጥፍ።

"…በጦርነት ሕግ ምርኮኛ ከነ ሙሉ ዝናሩ፣ ካርታ ሙሉ ጥይቱ ክላሹን ሞልቶ በአንድ ጊዜ ዋነኛውን የጦር መሪ እንደ አጃቢው አክት እየደረገ አጠገቡ ተደርድሮ ፎቶ ሲነሣ የማየው እዚያው ምሥራቅ ጎጃም አስረስ መዓረይ ጋር ብቻ ነው።

"…እኔ በየትኛውም ዓለም እንዲህ ዓይቼ አላውቅም። ምርኮኛ ጫማ ያወልቃል፣ ትጥቅ ያስረክባል። ከዚያ ወደማረፊያ ቦታ ሄዶ የሥነ ልቦና አገልግሎት ያገኛል። ጎጃም እነ አስረስ መዓረይ ጋር ግን ይሄ የለም። ከፋኖ ይልቅ ምርኮኛ ነው ክብር ያለው። እንዴት ሰው ለራሱ አይሰጋም? ምርኮኞቹ የተለየ ተልእኮ ይዘውስ ከሆነ የመጡት? ወይስ አገዛዙ ነው ጠባቂ ብሎ የሚልክለት? ቀሽም።

"…ይሄን ዓይነቱ ዝርክርክ ነገር ወሎ ላይ አላይም። ጎንደር ላይም አልመለከትም። ሸዋም ላይ እነ መከታው ጋር እንጂ እነ ደሳለኝ ጋር አላይም። የሚያልቀው፣ የሚጨፈጨፈውም የጎጃም ፋኖና የጎጃም ሕዝብ ነው። የምርኮኛ እንክብካቤም ያለው ደግሞ እዚያው ጎጃም በተለይም ምሥራቅ ጎጃም እነ አስረስ መዓረይ ጋር ነው። አልገብቶኝም።

"…አሁን እኮ ይሄን የመሰለ ጮማ ምርጥ ምክሬንም በክፉ የሚያይ ሰው አይጠፋም። ወዳጄ አትቀልዱ። የፎቶ ቦለጢቃው ምንም ጠብ የሚል ነገር የለውም። ወሬም፣ ፕሮፓጋንዳም ቢሆን የሚያሳምንና የሚመስል በልክም ሲሆን ነው የሚያምረው።

• ዘመዴ ነኝ ከጮቄ

43.3k 1 14 194 1.6k

መልካም…

"…6 ፍሬ ሰዎች የተበሳጩበት ርእሰ አንቀጻችን ተነብቧል። አሁን ደግሞ የእናንተ ሓሳብ የሚደመጥበት መርሀ ግብር ይከተላል። ጻፉ። አስተያየታችሁን ጻፉ።

"…በነገራችን ላይ ካልቀደምናቸው በቀር ሲኖዶሱ ራሱ የተጠለፈ ነው የሚመስለኝ። አባ ደጀኔ ቶላ፣ አቡነ ገብርኤል የመነፈቀ ቃል የዘሩት ብቻቸውን ተደብቀው መስለውኝ ነበር። ለካስ አባ ወልደ ትንሣኤ ከጉባኤው በደስታ ጮቤ ረግጠው ተቀምጠዋል። አህያ ብሉ፣ እየሱስ አማላጅ ነው፣ ታቦት ላይ ያፌዙት ሊቀጳጳስ በዚያ አሉ።

"…በተሃድሶነት ተከስሶ በስንት አማላጅ ተንበርክኮ እግር ላይ ወድቆ ይቅርታ ጠይቆ የነበረው አቶ ፀጋዬ ሮቶም በዚያው በጉባኤ ላይ ይታያል። ደጀኔ ቶላ አባ ገብርኤል እመቤታችንን አዋርዶ በተሳደበ ጊዜም እጁ እስኪላጥ ሲያጨበጭብ ይታያል። አደጋ ደርሶባቸው አንጎላቸው ተከፍቶ ከተሰፋ በኋላ አፍቃሬ መናፍቅ የሆኑት አባ ወልደተንሣኤም በድል አድራጊነት ስሜት ተኮፍሰው ይታያሉ።

"…በዚያው ጉባኤ ላይ "አትደንግጡ፣ አትፍሩ" የተባሉት የአቶ ፀጋዬ ሮቶ ሠራተኞችም ሲያጨበጭቡ ይታያሉ። ማኅበረ ቅዱሳን ስቱዲዮው የተገነባው በፀጋዬ ሮቶ ብር ነው። የቤተ ክህነቱም የቴሌቭዥን ጣቢያ ስቱዲዮም የተገነባው በዚህ ባለፀጋ ገንዘብ ነው። ፓትርያርኩን ጨምሮ ባለሀብቱ ቤቱ ጠርቶ እጅ መንሻ ያልተሰጠው ሰው የለም። የገንዘቡ ምንጭ ሮዳስ ቀለምና ሮቶው ብቻ አይመስልም። የሆነ የታቀደ ነገር እንዳለ ይሸተኛል።

"…እደግመዋለሁ ከውጭ ማፍረስ ያልቻሏትን ቤተ ክርስቲያን ከውስጥ ለማፍረስ ግርርር ብለው የገቡ ይመስለኛል። ሰዶማውያን መብት እንዲኖራቸው በስሱ የሚሞግቱ፣ ለመናፍቃን ተቆርቁረው የሚሞግቱ ጉዶችን እያየን ነው። ይላላጣሉ እንጂ ምንም አያመጡም።

• በነገራችን ላይ ደጀኔም ብፁዕ አይባልም። የአረቄያም ሁሉ መጫወቻ ሆነን እንቅር በማርያም።

42.9k 1 31 177 1.4k

👆⑤ ✍✍✍ …ሕዝቡን ሊምር ሲሻ ለሙሴ ላጠፋ ነኝ እንዳለው አሁንም የእናቱን ርኅርኂትነት ያውቃልና ማርልኝ እንድትለው በሲኦል ያሉትን ነፍሳት አሳያት። ስለዚህም  እርስዋ መሪር እንባን አለቀሰችና "ቅትለኒ በእንተ ቤዛሆሙ- እኔ ስለ እነርሱ ልሙትና ማርልኝ ስትል ለምነዋለች፣ ጌታም ቅዱሳኑ ሁሉ ሰብስቦ ወርዶ ነፍሷን ታቅፎ ታይቷልና አስተርእዮ ተብሏል። ሥጋዋን አቃጥላለሁ ያለውን ታውፋንያን እጆቹን ቆርጦ የእናቱን ሥልጣን የገለጠበት ቀን ነው።ሥጋዋን ያቃጥል ዘንድ በድፍረት የመጣውን ይቀጠልለት ብላ ቤዛ ሁናው ተቀጥሎለታል።  ስንዴ መሬት ላይ ስትወድቅ ብዙ ታፈራለች። ካልወደቀች ግን ብቻዋን ትኖራለች(ዮሐ፲፪፥፳፬) የድንግል ማርያም መሞት ብዙ ሰማዕታትና መናንያን ሊቃውንት ይፈሉ ዘንድ የቤተክርስቲያን ቤዛ ነው! ያለ ድንግል ማርያም ድኅነት የለም መባሉም መሬት ላይ ካልወደቀች ፍሬ የለም ብቸዋን ትኖራለች እንጅ እንዳለው ነው። የድንግል ማርያም፦ ልደቷ ጥቅም፣ ልኅቀቷ ጥቅም፥  መፅነሷ ድኅነት፥መውለዷ ድኅነት፥ መሰደዷ ድኅነት ፥መመለሷ ድኅነት፥ ማሳደጓ ድኅነት፥ መሪር እንባዋ ድኅነት፥ ድንጋጼዋ ድኅነት፥ ጸሎቷ ድኅነት፥  መሞቷ ድኅነት፥ ማረጓ ድኅነት ነው፡፡ ፷፬ቱ እድሜዋ ሁሉ የደረሰባት እያንዳንዱ መከራዋ ለሰው ድኅነት ስለሆነ እድሜዋ ራሱ ቤዛችን ነው። ፷፬ መቁጠሪያ የምንጸልየው ፥ ፷፬ሰላም ለኪ የምንማጸነው ስለዚህ ነው።

"…ነገሬን በወዳጇ በአባ ጊዮርጊስ ሰዓታት ልጠቅልል" ንትፈሣሕ ኩልነ በዝክረ ስምኪ ጥዑም፤ ወበደመ አስካልኪ መዓድም፥ ቅድስት ማርያም ቤዛዊተ ኩሉ ዓለም- ድንግል ማርያም ሆይ በሚጣፍጠው ስምሽ ደስ ይለናል፥ ጥዑም በሆነው በማኅፀንሽ ፍሬ በክርስቶስ ደምም ሐሴትን እናደርጋለን፥ ዕንዕት ክብርት ንጽሕት ልዩ እመቤታችን ሆይ አንቺ ቤዛዊተ ዓለም ነሽ!" ሁላችን እንዲህ እንል ዘንድ የልቡናችንን አውታረ መሰንቆ መንፈስ ቅዱስ ይቃኝልን! አሜን።
    
"…መዝግቡ። አሁን የአገዛዙ ካድሬ ሰባኪያነ ወንጌል ተብዬዎች ስለዚህ ነገር አይተነፍሱም። ስለ ዶሮ ብልት 12 ሁለት መሆን የሚያመሰጥሩት በሙሉ አሁን የሉም። እንዲህ ዓይነቱ ኑፋቄ ሲዘራ ድምጻቸው አይሰማም። ብዕራቸው አይነበብም። አንዴ ቴዲ አፍሮ ሚስት ጋር፣ አንዴ ሌላ ቦታ፣ በየዩቲዩቡ ራሳቸውን የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተጠያቂ ሊቅ አድርገው የሾሙ፣ አፈ ጮሌ ሸቃጭ ነጋዴ ሰባክያን አሁን የሉም። ትንፍሽ አይሉም። ወዳጄ ሆድና እምነት ይለያያል። በአንጻሩ እንዳልኩት ነው። የመናፍቃን በኃይለኛው በውስጥም በውጭም ማፍላት ሊቃወንተ ቤተ ክርስቲያንን ያበዛል፣ ያስነሣል። የአሕዛብ ሰይፍ ቅዱሳን ሰማእታትን ያበዛል፣ ያስነሣል። ሳይማሩ፣ ሳይጠነቅቁ በብር፣ በጉቦ፣ በፓርቲ ፍላጎትና በደብዳቤ በብሔር ኮታ መሾም፣ አባ፣ ብፁዕነትዎ መባል ብቻውን ከማስከበሩ ይልቅ በሥጋም ያዋርዳል፣ መሳቂያ፣ መሳለቂያ ያደርጋል ያስቀስፋልም። በነፍስም ያስቀስፋል። ዕድሜ ነው የሚያሳጥረው። የእነ አባ ደጀኔም መነሣት እንዲሁ ነው። ለዛሬ አበቃሁ።

ነይ ነይ እምዬ ማርያም
ነይ ነይ በዛዊት ዓለም
የአማኑኤል እናት የመድኃኔዓለም

• ዘመዴ ነኝ ከቤዛዊት ማርያም

15 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.