አቡ መርየም አዳማ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


هدفنا الذب عن السنة.....................
ትክክለኛው እስላማዊ አስተምህሮ ከቁርአንና ከሐዲስ ከደጋግ ቀደምቶች አረዳድ ከታማኝ ዑለሞች የሚሰራጭበት ቻናል ነው። በተጨማሪም ተውሂድንና ሽርክን እንዲሁም ሱናንና ቢድአን እንዲሁም የቢድአ ሰዎችን ለሰዎች በፁሁፍና በሙሀደራ መልክ ግልፅ ማድረግ
https://telegram.me/abumerymadama

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


🟢 የአዛውንቱ ምስክርነት ከሌራው ዝግጅት መልስ

⏸ ድምፃቸውን የምትሰሙት አባት ከነበሩበት የሺርክና የቢድዐህ መንገድ ኮተት ወደ ተውሂድና ሱነህ ብርሃን በቅርቡ የገቡ የእድሜ ባለፀጋ አዛውንት ናቸው። አላህ ይጠብቃቸው።

ከሌራው ሀገር አቀፍ የዲን ድግስ ስንመለስ መጓጓዣ ላይ ተገናኝተን ከተናገሯቸው ጣፋጭ ቁምነገሮች ውስጥ፦

↪️ አህሉሱነህ ሰለፊዩች ማህበረሰቡን በአላህ ፈቃድ ከጥመት እያወጡ ነው።

↪️ ሀቅ ያልደረሰው ሀቅ ናፋቂ ማህበረሰብ እጅግ ብዙ ነው።

↪️ ኢኽዋኖች እና ሙመይዓዎች እንሚሞግቱት ሺርክን በስሙ በዝርዝር ማስጠንቀቅ ማህበረሰቡን የሚያስበረግግ ሳይሆን የሚያስደስት ኑር ነው።

↪️ የመጅሊሱ ባለስልጣናት በተውሂድ ዳዕዋ ላይ እያደረሱት ያለውን ጫና የገጠሩ ማህበረሰብ እንኳን አውቆታል።

↪️ አህሉሱናን የሚቃረናቸው ፣ የሚያንቆሽሻቸው ፣ የሚያሴርባቸው ሸረኛ ሁሉ አይጎዳቸውም ምክንያቱም አላህን ይዘዋልና።

↪️ ሁሌም ሀቅ ወደ ፊት ሁሌም ሀቅ ወደ ኸይር ነው !!

🤲"ከዚያ ጥመት አውጥቶ በዚህ ኒዕማ (ፀጋ) ላይ ያደረገኛ አላህ ሞቴንም በዚሁ ላይ ያድርገው!! " ይላሉ

አላህ ለሀቅ ይምራን እስከመጨረሻውም ያፅናን!

✏️ ሰውየው "ሀጂ ሀሚድ" ሲሉ አሸይኽ ዐብዱልሀሚድ አለተሚይ ነው።

http://t.me/Abuhemewiya


[ኢብን ሽፋ - Ibn Shifa] dan repost
ድካ የደረሰች በገንዘብ የማትተመን ግሳፄ!!
———
ሱፍያን አስ-ሰውሪ (ረሂመሁላህ) ወደ ወንድሞች በላኩት ግሳፄ እንዲህ አሉ:-
“እራሴንም አንተንም አላህን በመፍራት እመክራለሁ!!። ካወቅከ በኋላ አላዋቂ ከመሆን እንድትጠነቀቅ፣ ዓይንህን ከፍተህ ሀቁን መመልከት ከቻልክ በኋላ እንዳትጠፋ፣ መንገዱ ግልፅ ከሆነልህ በኋላ እንዳትተወው አስጠነቅቅሃለሁ!!።
የዱኒያ ሰዎችም ዱኒያን በመፈለጋቸው፣ ለእርሷም በመጓጓታቸውና እሷንም በመሰብሰባቸው እንዳትታለል። ይህም በጣም ከባድ የሆነ አስፈሪ፣ አደገኛና በቅርበት የሚከሰት ነገር ነው።
ወደ አኼራ ከመወሰድህ በፊት አንተ ወደ አኼራ ተጓዝ፣ የጌታህን መልክተኛ ተቀበል፣ ውሳኔ ተወስኖብህ ከምትፈልገው ነገር ሳትለያይ በፊት ሽርጥህን ጠበቅ አድርግ።
በእርግጥ እራሴን በገሰፅኩበት ነገር ነው የገሰፅኩህ፣ መግጠም ከአላህ ነው የመገጠም መክፈቻው ደግሞ ዱዓ፣ ወደ አላህ መተናነስና ከወንጀል ተፀፅቶ መመለስ ነው።
ከዚያም ስራህን ከሚያበላሽብህ ነገር እንድትጠነቀቅ እመክርሃለሁ!፣ ስራህን የሚያበላሽብህ ነገር ለይዩልኝ (ሪያእ) መስራት ነው፣ ከይዩልኝ ብትርቅ እንኳን በነፍሲያህ በመደነቅህ ነው፣ ከወንድምህ በላይ እንደሆንክ እስኪያስመስልህ ድረስ በራስህ እንድትደነቅ ያደርግሃል። ምናልባትም በራስህ ስትደነቅ የተሻልከው የመሰለህ ሰው ከአንተ የተሻለ በስራው የገጠመና ምንዳ የሚያገኝበት ከባድ ስራ ይኖረው ይሆናል፣ ከአንተ በበለጠ መልኩ አላህ እርም ካደረገው ነገር የተሻለ ጥንቁቅ ሊሆንና በስራ ጥራትም ከአንተ የተሻለ ሊሆን ይችላል።
በራስህ ባትደነቅ እንኳ አደራ በሰዎች መወደስን ከመውደድ ተጠንቀቅ!፣ መወደስህ በስራህ እንዲያከብሩህ እንድትወድና በልባቸው ልዩ ደረጃ እንዲሰጡህ፣ አለያም በጉዳይህ እንዲቆሙልህ እንድትፈልግ ያደርግሃል። ይልቅ በስራህ የአላህን ፊት እና የመጨረሻይቱን ቀን ፈልገህ እንጂ ሌላን ፈልገህ መሆን የለበትም!።
ሞትን በብዛት በማስታወስ፣ ከዱኒያ ቸልተኛ በመሆን ለአኼራ ተነሳሽነት (ፍላጎት) ይኑርህ! ምኞትህ ረዝሞ ፍርሃትህ በማነሱና ወንጀልን በመዳፈርህ ተጠንቀቅ!፣ እውቀት እንጂ ስራ የሌላቸው የሆኑ ሰዎች በእለተ ትንሳዔ በመቆጨታቸውና በመፀፀታቸው ተመከርበት።” [ሂልየቱ'ል አውሊያእ አል-አስበሃኒ]
✍🏻ኢብን ሽፋ (t.me/ibnshifa)
#Join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


የ ሸይኽ ሙሐመድ ሀያት ቻናል dan repost
👉➤ተውሂድን ተማሩ

ከሰዎች ብዙዎቹን ተውሂድ ምንድን ነው
ብለህ ብጠይቃቸው መልስ አይሰጡህም 
ምክኒያቱም  ትርጉሙ እሱን በአምልኮ
ብቸኛ ማድረግም እንደተፈለገበት
አልተማሩም.......
تعلموا التوحيد..... الكثير من الناس
إذا سألتهم ماهو التوحيد لا يجيبك

 
🎙الشيخ صالح الفوزان حفظه الله

ሌሎችን ተጨማሪ ትምህርቶችን ለመከታተል⤵️
https://t.me/SheikMohmmedHyatHara


ሙሀመድ አል―ወልቂጢይ dan repost
👉 የሌራን ኮንፈረንስ ልዩ የሚያደርገው ምንድነው ?

የሌራ ሀገር አቀፍ ኮንፈረንስ ከሌሎች ለየት የሚያደርገው ብዙ ነገር ቢኖርም በዋነኝነት 3 ነገሮችን ልጥቀስ : –
1 – አስገራሚ ማኔጅመንት
ፕሮግራሙ በጣም አስገራሚ በሆነ ሁኔታ ማኔጅ ተደርጎ ነበር ። ለዚህ ትልቁን ድርሻ የወሰደው ወንድማች ዐ/ሀዲ ሲሆን አላህ ይጨምርለትና በሚገርም ሁኔታ ፕሮግራሙን ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ ማኔጅ አድርጎታል ። እንግዶቹን የተቀበሉበትና ያስተናገዱበት ሁኔታ አስደማሚ ነበር አላህ ይቀበላቸው ።

2 – የአካባቢው ሴቶች ተሳትፎ
በጣም በሚገርም መልኩ የአካባቢው ሴቶች ኮሚቴው ካዘጋጀው መስተንግዶ ውጪ ለእንግዶች መቀበያ እንዲሆን አዋጥተው አንድ ሰንጋ ገዝተው በመስጠት ኮሚቴውን ካስደነገጡ በኋላ ላጠቃላይ በሺዎች ለሚቆጠረው እንግዳ ቁርስ አዘጋጅተው አብልተዋል ። ይህ በጣም የሚገርም የሴቶቹ ተግባር አላህ በመልካም ስራ መዝገባቸው ላይ አስፍሮ ለጭንቁ ቀን ስንቅ ያድርግላቸው የሚል ዱዓእ እንዲደረግላቸው አድርጓል ።

3 – የኻዲሞቹ ቅንጅት
በርግጥ በዚህ ነጥብ ላይ የጉንችሬና የሓራ ኻዲሞች የሚጋሩዋቸው ቢሆንም የእነርሱን ለየት የሚያደርገው አንድ ነገር አለ ። እሱም ሌሎቹን ሳይጨምር የወጥ ቤት ኻዲሞች ብቻ አዋጥተው ለወላኢታ ዩንቨርሲቲ ተማሪዮች ለመድረሳ ኪራይ ድጎማ 11 ሺህ ብር ለግሰዋል ። እነርሱንም አላህ ይቀበላቸው እንላለን ።
ባጠቃላይ ፕሮግራሙ ልዩ ትዝታ በሰለፍዮች አእምሮ ላይ ጥሎ አልፏል ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ የተገባ ይሁን ።

http://t.me/bahruteka


القناة التعليمية الرسمية للدعوة السلفية في الحبشة dan repost
.
.
ለሶስት ተከታታይ ቀናት በሌራ ከተማ በኢማሙ አሕመድ መስጂድ ሲሰጥ የነበረው የዳዕዋና የኮርስ ፕሮግራም የማይረሳ፣ ተናፋቂ እና ትልቅ ሥራ ሆኖ በሚገርም ሁኔታ በሰላም ተጠናቋል። ለሁሉም መሻይኾች፣ ኡስታዞች እና ወንድሞች አላህ ረጅም እድሜ በሐቅ ላይ ከመፅናት ጋር እንዲሰጣቸው በያላችሁበት ዱዓ አድርጉላቸው!!!

🔎 አሏህ እንደዚህ አይነት የዳዕዋና የኮርስ ፕሮግራሞችን ያብዛልን።

@AbuYehyaAselefy


ሙሀመድ አል―ወልቂጢይ dan repost
✅ የባሕሩ አባት ሰልሟል ወይ ላላች ወንድምና እህቶች

በአልከሶና አካባቢዋ ሰለፍዮች ግሩፕ ላይ አንድ ወንድም ባሕሩ ተካ ( አሕመድ ) ብሎ ፅፎ አሕመድ ማን ነው ? የአባቱ ስም ነው ወይ ? ወይስ ሌላ ባሕሩ ነው ? ባሕሩ ተካ ከሆነ አባቱ ሰልሟል ወይ የሚሉ ጥያቄዎች ተደጋግሞ አይቻለሁ ። ይህ ጥያቄ በብዙዎች አእምሮ ሊኖር ስለሚችል ለወንድምና እህቶች ቤተሰቦቼ በሙሉ የሰለሙ መሆኑን ላሳውቃቸው ወደድኩ ። መስለማቸው ብቻ ሳይሆን ሁሉም ቤተሰቦቼ ሰለፍዮች መሆናቸውንም አውቃችሁ ዱዓእ እንድታደርጉላቸው ላስታውሳችሁ እወዳለሁ ።
ምስጋና ለአለማቱ ጌታ የተገባ ይሁንና ከአጎቴቼ ውስጥ አብዛኞቹ ከነቤተሰቦቻቸው ሰልሟል ። የተወሰኑት ደግሞ ልጆቻቸው ሰልሟል ። አላህ ሁላችንንም ፅናቱን ይስጠን ።

http://t.me/bahruteka




🔸 አዲስ ሙሀደራ

🔊 "ስለ ተውሒድ፣ አስማእ ወሲፋት እና ኢስቲዋእ!!”

🎙በሸይኽ አቡ ዐብዲል ሀሊም ዐብዱል ሀሚድ ያሲን አል-ለተሚይ (ሐፊዘሁላህ)

🕌ሌራ ኢማሙ አህመድ መስጂድ የተደረገ

https://t.me/abdulham
https://t.me/abdulham
https://t.me/abdulham


Bahiru Teka dan repost
👉 ሌራ ተረኛዋ የተውሒድ ጮራ አሰራጭ

በምእራብ ስልጤ ዞን የምትገኘው ሌራ ከተማ ተረኛዋ የታደለች የተውሒድ ጮራ አሰራጭ ሆናለች ። የሌራ አል – ኢማሙ አሕመድ መስጂድ የተውሒድና ሱና መሻኢኽና ኡስታዞችን እንዲሁም ዱዓቶችና እንግዶችን ለመቀበል አንፀባራቂ በለበሱ የሱና ኻዲሞች ተውቦና አምሯል ። መስጂዱ ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች በተመሙ መሻኢኾችና ኡስታዞች እንዲሁም ዱዓቶች የተውሒድ ዘር እየተዘራበትና የብርሃኑ ጮራ እየፈነጠቀ ይገኛል ።
ሰው ምን ይለኛልን በማይፈሩ የቁርጥ ቀን ዑለሞችና መሻኢኾች ነጭ ነጩ እንቅጭ እንቅጩ እየተነገረ ነው ። የተውሒድ ሚስጢር እየተገለፀ የሽርክ ቫይረስ ላይ አጥፊ መድሃኒት እየተረጨ ነው ። ሐቅን ደብቆ አንድነት የለም, ሐቅን ደብቆ ስምምነት የለም ሐቁ ይነገራየጠላ ይጠላል የወደደ ይወዳል ። ስለተውሒድ ለተበሩክ ሳይሆን ሽርክን ለማጥፋት ማስተማር ነብያዊ ተልእኮ ነው ። በመሆኑም ሽርክን በጥቅሉ ሳይሆን በዝርዝር እየአንዳንዱ በስሙ ሌራ ላይ እየተነገረ ይገኛል ።
የሌራ ከተማ በተውሒድና ሱና መአዛ ታውዳለች ። መንገዶቿ ፣ መንደሮቿ ፣ ጋራ ሸንተረርዋ ተውሒድ ተውሒድ ይሸታሉ ። ጎዳናዎቿ የሱና አበባ ተነስንሶ ላየ ጤነኛ ልቦና ባልተቤት የደስታ ሲቃ ያሲዛል ።
ለዚህ ታላቅ ፕሮግራም መሳካት የከተማዋ የፖሊስ የፀጥታና የድርጅት ሀላፊዮች የተጣለባቸውን ህዝብን የማገልገል ሀላፊነት በቅንነት መወጣት አላህን ከማመስገን በኃላ ሊመሰገኑ ይገባል ። በቅርቡ አሊቾ ወረዳ ላይ ያየነውና አሁን ምእራብ አዘርነት በርበሬ ሌራ ወረዳ ላይ ያለው ሁኔታ የእነዚህ የሴክተር መ/ቤቶች ያሳዩት ሀላፊነትን በአግባቡ መወጣት የስልጤ ዞንን ገፅታ የሚቀይርና እሰይ የሚያሰኝ ሌሎችም ሊከተሉት የሚገባ የሚደነቅ ተግባር ነው ።

http://t.me/bahruteka


አዲስ ሙሃዶራ

ርእስ:- ከቢድዓ ባለቤቶች ጋር ከመቀማመጥ ማስጠንቀቅ ከአህሉ ሱና መሰረቶች መካከል አንዱ ነው!!

🎙በሸይኽ መህቡብ አስ’ሳንኩሪይ (ሐፊዘሁላህ)

በሌራ ሀገር አቀፍ ፕሮግራም የተደረገ

#join ⤵️ ቴሌግራም ቻናል
https://telegram.me/IbnShifa
https://telegram.me/IbnShifa


ሙሀመድ አል―ወልቂጢይ dan repost
📙 ከሙብተዲዖች ጋር መቀማመጥ ያለው አደጋ!

ታላቁ የየመኑ ሊቅ ሙሀመድ አሽ’ሸውካኒይ ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦

«قال الله تعالى "وَإِذَا رَأَيْتَ الَّذِيْنَ يَخُوْضُوْنَ فِيْ آيَاتِنَا فَأَعْرِضْ عَنْهُمْ حَتَّىٰ يَخُوْضُوْا فِيْ حَدِيْثٍ غَيْرِهِ" الأنعام: ٦٩

አላህ ጀለ ወዓዘ እንዲህ አለ "እነዚያንም በአንቀጾቻችን የሚገቡትን ባየህ ጊዜ ከእርሱ ሌላ በኾነ ወሬ እስከሚገቡ ድረስ ተዋቸው፡፡" አንዓም 68

وفي هذه الآية موعظة عظيمة لمن يتسمح بمجالسة المبتدعة، الذين يحرفون كلام الله، ويتلاعبون بكتابه وسنة رسوله صلى الله عليه وسلم ويردون ذلك إلى أهوائهم المضلة وبدعهم الفاسدة، فإنه إذا لم ينكر عليهم ويغير ما هم فيه فأقل الأحوال أن يترك مجالستهم، وذلك يسير عليه غير عسير.

በዚች አንቀፅ ውስጥ እነዚያ የአላህን ንግግር የሚያንሻፍፉ፣ በመፅሀፉ እና በመልእክተኛው መንገድ የሚጫወቱ፣ ያንን ሁሉ ወደ አጥማሚ ስሜታቸው እና ወደ ተበላሸ ፈጠራቸው የሚመልሱ የሆኑትን ሙብተዲዖችን በመቀማመጥ ለሚተሻሽ ሰው ሁሉ ትልቅ ምክር አለ። እሱ ካልተቃወማቸው እና እነሱ ያሉበትን ሁኔታ የማይቀይር ከሆነ፤ ያለበት ትንሹ ሀላፍትና እነሱን መቀማመጥ መተው ነው። ይህም ደግሞ በሱ ላይ ቀላል ነው ከባድ አይደለም።"

وقد يجعلون حضوره معهم مع تنزهه عما يتلبسون به شبهةً يشبهون بها على العامة ،فيكون في حضوره مفسدة زائدة على مجرد سماع المنكر.

ሰውዬው ከነሱ ቢድዓ የጠራ ከመሆኑም ጋር ከነሱ ጋር መቀማመጡን በተራው ማህበረሰብ ላይ የሚያወዛግቡበት ብዥታ ሊያደርጉት ይችላል። ስለዚህ እነሱ ጋር በመቀማመጡ መጥፎን ነገር ከመስማት በሻገር ተጨማሪ ውድመት ይከሰታል።

وقد شاهدنا من هذه المجالس الملعونة ما لا يأتي عليه الحصر، وقمنا في نصرة الحق ودفع الباطل بما قدرنا عليه، وبلغت إليه طاقتنا.

በርግጥ ከነዚህ የተረገሙ መቀማመጦች የማይገደቡ በርካታ ነገራቶችን አይተናል። ሀቅን በመርዳት እና ባጢልን በመገፍተር የቻልነውን ልክ እና አቅማችን በደረሰችው ቆመናል።

ومن عرف هذه الشريعة المطهرة حق معرفتها، علم أن مجالسة أهل البدع المضلة فيها من المفسدة أضعاف أضعاف ما في مجالسة من يعصي الله بفعل شيئ من المحرمات

ይቺን ንፁህ የሆነችዋን ሸሪዓን ተገቢ የሆነን መገንዘብ የተገነዘበ ሰው የአጥማሚ ፈጠራ ባለቤቶችን መቀማመጥ ከአደጋ ሆኖ በውስጡ ከክልክሎች አንዱን በመስራት አላህን የማመፅ ባልተቤቶችን መቀማመጥ ውስጥ ካለው አደጋ የእጥፍ እጥፍ እንደሆነ ያውቃል።

ولاسيما لمن كان غير راسخ القدم في علم الكتاب والسنة فإنه ربما ينفق عليه من كذباتهم وهذيانهم ما هو من البطلان بأوضح مكان، فينقدح في قلبه ما يصعب علاجه ويعسر دفعه فيعمل بذلك مدة عمره ويلقى الله به معتقدا أنه من الحق ،وهو من ابطل الباطل وأنكر المنكر.


በተለይ ደግሞ በቁርአን እና ሀዲስ እውቀት እግሩ ያልጠለቀ ለሆነ አካል! ምናልባትም ከመዘባረቃቸው እና ከመዋሸታቸው የሆነ በጣም ግልፅ በሆነ ደረጃ ያለ ባጢል ሊደበቅበት ይችላል። ከዚያም መታከሙ የሚያስቸግር እና መገፍተሩ የሚከብድ የሆነ ነገር በልቡ ላይ ይጫራል። እድሜ ልኩ በዚያ ባጢል ይሰራ። በጣም ግልፅ ከሆኑ ውሸቶች እና በጣም ግልፅ ከሆኑ መጥፎዎች የሚቆጠር ሆኖ ሳለ ሀቅ ነው ብሎ ያሰበ ሲሆን አላህን በዛ ባጢል ይገናኛል።»

اهـ فتح القدير سورة الأنعام: الآية ٦٩.

ዛሬ ዛሬ ግን በርካታ ከመንሀጅ የተፍረከረኩ የሆኑ አካላት ከቢድዓ ባልተቤቶች ጋር በመስለሀ ስም አድርገው የሚቀማመጡ፣ የሚጓዙ፣ የሚሳሳቁ፣ የሚወዳደሱ፣ የሚሿሿሙ፣ የሚተጋገዙ፣ እና የሚተሻሹ በርካታ ናቸው። በጣም የሚያሳዝነው እነሱን አይቶ የሚፍረከረከው በበርካታ የሚቆጠር ወጣት ክፍል ነው። አላህን የሚፈሩ ቢሆኑ እዛ የሚገኝ የሆነን ያልተረጋገጠ ጥቅም አይኖች ከሚያዩት ግዙፍ ግዙፍ መፍሰዳዎች ጋር ባላወዳደሩ ነበር። በርግጥ ለኡማው መስለሀ በሚል ይቀባቡት እንጂ የሚፈልጉት የግል ጥቅምን ነው። ስልጣን፣ ገንዘብ፣ እውቅና እና ክብር ፈልገው እንደሆነ እያየን ነው። አላህ ሁሉንም ቀናውን መንገድ ይምራው።


✍ በወንድም፡ ሙሀመድ አል-ወልቂጢይ

t.me/abuzekeryamuhamed
t.me/abuzekeryamuhamed


አቡ አዒሻ العلم نور dan repost
📢ዳዕዋ ዳዕዋ ዳዕዋ!!

የዳዕዋ ፕሮግራም ጥሪ
📢

🔰ታላቅና በአይነቱ ለየት ያለ የዳዕዋ ፕሮግራም
ዝግጅት ተሰናድቷል የፊታችን ጁሙዓ
ማለትም የካቲት ቀን/14/06/2017/እለተ/ጁሙዓ  ይጠብቃችኋል

🌎በሰሜን ወሎ ዞን  በራያ ቆቦ ወረዳ ቀበሌ
(022) ልዩ ቦታ ተካሪ ከአላ ውሃ ከፍ ሲሉ
የገጠር ድቅድቅ ታዳጊ መንደር ነች

🕌 መስጂደል አቡበክር  ተካሪ

♻️ስለሆነም በቆቦና እሮቢት ጉራ ወርቄ
ጎብየና ደሮ ግብር ቆርኬ ወረጋራ ጥልፍና ሀሮ
እንድሁም ሀራ የምትገኙ ውድ ሰለፍያ
ወጣቶች ሆይ እነሆ የፊታችን ጁሙዓ
ከጧቱ 2:30 ጀምሮ እስከ አሱር ሶላት
ድረስ የሚዘልቅ የዳዕዋ ዝግጅት ስላለን
ሁላችሁም ታድማችኋል እሰቡበት

🪑ተጋባዥ እንግዶቻችነን እነሆ ብለናል↩️

🎙1.ሸይኽ ሙሀመድ ሀያት ሀራ حفظه الله
🎙2.ሸይኽ ሁሴን አባስ ጉራ ወርቄ حفظه الله
🎙3.ሸይኽ ሁሴን  ከረም ሀራ حفظه الله
🎙4.ሸይኽ ሰኢድ ሙሐመድ  ሀራ حفظه الله
🎙5. ኡስታዝ ሙሐመድ ሰልማን ሀራ حفظه الله

ርዕስ"✅
በቦታው ላይ በእለቱ የሚገለፅ ሲሆን

🕰 የሚጀመርበት ሰአትና ወቅት ከጧት 2:30 ስለሆነ በጧት ተገኝተው
የዳዕዋው ተካፋይና ተቋዳሽ ይሁኑ

⚙የፕሮግራሙ አዘጋጅና ጋባዥ የተካሪ
ሰለፍያ ጀመዓዎች

🗓የካቲት ቀን/14/06/2017/እለተ/ ጁሙዓ

https://t.me/hussenhas


🔸 አዲስ ሙሀደራ

🔊 "ስለ ተውሒድ ማስተማር ከሺርክ ማስጠንቀቅ!!”

ክፍል አንድ 01

🎙በሸይኽ አቡ ዑበይዳህ ባህሩ ተካ (ሐፊዘሁላህ)

ሌራ ኢማሙ አህመድ መስጂድ የተደረገ

t.me/abuzekeryamuhamed
t.me/abuzekeryamuhamed


Muhammed Mekonn dan repost
ኮርስ ተጀምሯል።

📚 شُروطُ الصَّلاةِ وَواجِباتُها وَأركانُها
📚 የሶላት መስፈርቶች ማዕዘናቶቿ እና ግደታዎቿ
📝
للشـيخ محمد بن عبد الوهاب النجدي
🎙 በሸይኽ አብዱልሐሚድ ብን ያሲን አል`ለተሚይ

🏝           ➘➘➘➘➘➘

👇
https://t.me/AbuImranAselefy?livestream=5ac234d0514db83d97


Muhammed Mekonn dan repost
መነሻው ከዚህ ነው ተከታተሉ ባረከሏሁ ፊኩም።




Abu abdurahman dan repost
ፋዒደህ


🎙ከሸይኽ አብዲልሐሚድ ሙሓደራ የተወሰደ

أَخْبَرَنَا أَبُو زَكَرِيَّا بْنُ أَبِي إِسْحَاقَ الْمُزَكِّي، أنبأ أَبُو الْحَسَنِ أَحْمَدُ بْنُ مُحَمَّدِ بْنِ عُبْدُوسٍ الْعَنَزِيُّ، قَالَ: سَمِعْتُ أَبَا سَعِيدٍ عُثْمَانَ بْنَ سَعِيدٍ الدَّارِمِيَّ، يَقُولُ: سَمِعْتُ إِسْحَاقَ بْنَ إِبْرَاهِيمَ الْحَنْظَلِيَّ، يَقُولُ: قَالَ سُفْيَانُ بْنُ عُيَيْنَةَ، عَنْ عَمْرِو بْنِ دِينَارٍ، قَالَ: «أَدْرَكْتُ النَّاسَ مُنْذُ سَبْعِينَ سَنَةٍ يَقُولُونَ: اللهُ الْخَالِقُ، وَمَا سِوَاهُ مَخْلُوقٌ، وَالْقُرْآنُ كَلَامُ اللهِ عز وجل»
السنن الكبرى للبيهقي

https://t.me/abuabdurahmen?livestream=4680edf02ac34cd9de




Muhammed Mekonn dan repost
ኮርስ ተጀምሯል።

📚 شُروطُ الصَّلاةِ وَواجِباتُها وَأركانُها
📚 የሶላት መስፈርቶች ማዕዘናቶቿ እና ግደታዎቿ
📝
للشـيخ محمد بن عبد الوهاب النجدي
🎙 በሸይኽ አብዱልሐሚድ ብን ያሲን አል`ለተሚይ

🏝           ➘➘➘➘➘➘

👇
https://t.me/AbuImranAselefy?livestream=5ac234d0514db83d97


🔸 አዲስ ኮርስ

🔊 “ሹሩጡ ሶላቲ ወአርካኑሃ

✅ ኮርስ ክፍል 01

✍ አዘጋጅ፦ ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ዐብዲል ወሀብ (ረሒመሁላህ)

🎙በሸይኽ አቡ ዐብዲልሀሊም ዐብዱልሀሚድ አል-ለተሚይ (ሐፊዘሁላህ)

https://t.me/abdulham
https://t.me/abdulham
https://t.me/abdulham

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.