ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ፍልስፍና  እውነትን በመፈለግ- ልማዳዊ እምነቶችን በመሞገት እና ጭፍን አመለካከቶችን በጥበብ በመመርመር ወደ ላቀ አሰተሳሰብ ያሻግራል።
በዚህ ቻናል አለም ላይ ያሉ ፍልስፍናዎች ፤ ርዕዮት አለሞች ፤  ሀይማኖቶች እና አስተሳሰቦች በነፃነት ይዳሰሳሉ።

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


2.ስለ ሁሉም ነገር ተሳስታችኋል (እኔም)

በአስራዎቹ የእድሜ ክልል ሳለሁ ለሁሉም ሰው፣ ለምንም ነገር ግድ እንደሌለኝ እናገር ነበር፡፡ እውነቱ ግን በጣም ለብዙ ነገር ግድ ያለኝ መሆኔ ነበር፡፡ ሌሎች ሰዎች እኔ ሳላውቅ የእኔን አለም ያዙበት ነበር፡፡ ደስታ እጣ ፈንታ እንጂ ምርጫ እንዳልሆነ አስብ ነበር፡፡ ፍቅር ዝም ብሎ የሚከስት እንጂ የምትሰራው እንዳልሆነ አስብ ነበር፡፡ አሪፍነት ራሳችን የምንፈጥረው ሳይሆን ከሌሎች ሰዎች የምንማረው እንደሆነ አስብ ነበር፡፡

ከመጀመሪያ የሴት ጓደኛዬ ጋር ሳለሁ እስከ ዘላለም አብረን እንደምንሆን አስብ ነበር፡፡ ከዚያ ግንኙነታችን ሲያበቃ፣ ስለ ሴቶች በፍፁም በድጋሚ በተመሳሳይ መንገድ እንደማይሰማኝ አስብ ነበር፡፡ ከዚያ ለሴት እንደገና ያን አይነት ስሜት ሲሰማኝ ደግሞ ፍቅር ብቻ በቂ እንዳልሆነ አስብ ነበር፡፡ ከዚያ ግን እያንዳንዱ ግለሰብ “በቂ” የሚለውን መወሰን እንዳለበትና ፍቅር ደግሞ እንዲሆን የፈቀድንለትን ሊሆን እንደሚችል ተረዳሁ፡፡

በመንገዴ በየትኛውም ደረጃ ተሳስቼ ነበር፡፡ ስለሁሉም ነገር ተሳስቼ ነበር፡፡ ህይወቴን ሙሉ ስለ ራሴ፣ ስለ ሌሎች፣ ስለ ማህበረሰቡ፣ ስለ ባህል፣ ስለ አለምና ስለ ሁሉም ተሳስቼ ነበር፡፡

እና በቀሪው ህይወቴም ሁኔታው ያው መሆኑ እንደሚቀጥል ተስፋ አለኝ፡፡ የአሁኑ እርማት የባለፈው እርማት የነበረውን እያንዳንዱን ግድፈትና ስህተት ወደ ኋላ ተመልሶ ሊመለከት እንደሚችል ሁሉ፣ የወደፊቱ እርማትም አንድ ቀን የአሁኑን ግምቶችና ተመሳሳይ ግድፈቶችን ወደኋላ የሚመለከት ይሆናል፡፡ እና ያ በጣም ጥሩ ነገር ነው፡፡ ምክንያቱም አድጌያለሁ ማለት ነው፡፡

ደጋግሞ ስለመውደቅ የሚገልፅ የማይክል ጆርዳን ጥቅስ አለ፡፡ እና ስኬታማ የሆነውም ለዚያ ነው፡፡ ጥቅሱ “ስለ ሁሉም ነገሮች ደግሜ ደግሜ እንደገና ደግሜ ተሳስቻለሁ ህይወቴ የተሻሻለውም ፤ለዚያ ነው” ይላል፡፡

ትክክል ህግ ወይም ፍፁም የሆነ የፖለቲካ ዘይቤ የለም፡፡ ያለው ነገር የአንተ ተሞክሮ ለአንተ ትክክል የሚሆነው የቱ እንደሆነ ያሳየህ ብቻ ነው፡፡ እና በዚህም ላይ ያ ልምምድ ራሱ ምናልባት በሆነ ሁኔታ ስህተት ሊሆን ይችላል፡፡ እና እኔ፣ አንተና ሁሉም ሰው የተለያዩ የግል ፍላጎቶች፣ የግል ታሪኮችና የህይወት ሁኔታዎች ያሉን በመሆኑ ሁላችንም ስለ ህይወታችን ትርጉምና እንዴት መኖር እንደሚገባን ወደተለያዩ “ትክክል” ወደምንላቸው መልሶች መምጣታችን የማይቀር ነው፡፡የእኔ ትክክለኛ መልስ አመቱን ሙሉ ብቻዬን ወደተለያዩ ቦታዎች መጓዝ፣ የተረሱ ቦታዎች ውስጥ መኖርና በራሴ ቀልዶች መሳቅ ያጠቃለለ ሊሆን ይችላል ወይም ቢያንስ እስከቅርብ ጊዜ የነበረኝ ትክክለኛ መልስ ይህ ነው፡፡ ያ መልስ ይለወጣል፣ ያድጋል፤ ምክንያቱም እኔም እያደግኩና ብዙ ልምዶች እያዳበርኩ ስመጣ እለወጣለሁ፣ አድጋለሁ፡፡ ምን ያህል የተሳሳትኩ መሆኔን እየሸራረፍኩ በየቀኑ ስህተቶቼን እያሳነስኩ እያሳነስኩ እመጣለሁ፡፡ ብዙ ሰዎች በህይወታቸው ሙሉ “ትክክል(ፍፁም)” ስለመሆን አጥብቀው ይጨነቃሉ፡፡ ግን በመጨረሻ አይሆኑም፡፡

አንዲት ሴት ያላገባችና ብቸኛ ናት፡፡ እናም አጋር ትፈልጋለች፡፡ ነገር ግን ከቤት አትወጣም፣ ግንኙነት ለመመስረት ምንም ነገር አታደርግም፡፡ አንድ ሰው ደግሞ በጣም ጠንክሮ እየሰራ በመሆኑ የደረጃ እድገት እንደሚገባው ያምናል፤ ግን ያንን በፍፁም ለአለቃው ተናግሮ አያውቅም፡፡

እነዚህ ሰዎች ሽንፈትን፣ አይሆንም መባልን እንዲፈሩ ተነግሯቸዋል ማለት ነው፡፡

ነገር ግን ያ አይደለም፡፡ እርግጥ ነው አለመፈለግ ይጎዳል፡፡ ሽንፈት ያስጠላል፡፡ ግን ለአመታት ለህይወታችን ትርጉም የሰጡ እሴቶች አድርገን የያዝናቸው ለመጠየቅ የመፍራት ወይም ነገሮችን የመተው እርግጠኝነቶች አሉ፡፡ ያቺ ሴት ከቤት ወጥታ ከወንዶች ጋር መገናኘት ስለ ራሷ ተፈላጊነት ያላትን እምነት ለመጋፈጥ እንድትገደድ ያደርጋታል፡፡ ያ ሰውም እድገት መጠየቅ ይፈራል፤ ምክንያቱም ባለው ክህሎት ራሱን በእርግጥም ዋጋ ያለው አድርጎ ከማመኑ ጋር መጋፈጥ ይጠበቅበታል፡፡

ስለዚህ እነዚያን እምነቶች ፈትኖ እውነቱን ከማወቅ ይልቅ ሰዎች ማራኪ ሆነህ ከማያገኙህ እና ተሰጥኦህን ሳያደንቁልህ ቢቀሩ ከሚሰማህ የሚያሳምም እርግጠኝነት ይልቅ መቀመጥ ቀላል ይሆናል፡፡እንደዚህ አይነት እምነቶች በኋላ ላይ ደስታችንንና ስኬታችንን በመያዣነት ይዘው አሁን መካከለኛ የሆነ ምቾት እንዲሰጡን የተነደፉ ወይም የተሰሩ ናቸው፡፡ እነዚህ አስቸጋሪ የረጅም ጊዜ ስልቶች ናቸው፡፡ ሆኖም እነርሱ ላይ ተጣብቀናል፡፡ ምክንያቱም ትክክል እንደሆንን እንገምታለን፡፡ ምክንያቱም ምን ሊከሰት እንደሆነ አስቀድመን እንደምናውቅ እንገምታለን፡፡ በሌላ አነጋገር ታሪኩ በምን አይነት ሁኔታ እንደሚያልቅ አስቀድመን እንገምታለን ማለት ነው፡፡
እርግጠኝነት የእድገት ጠላት ነው፡፡ ምንም ነገር ሆኖ እስኪገኝ ድረስ እርግጥ አይደለም፡፡ የዚያን ጊዜም እንኳን አከራካሪ ነው፡፡ የእሴቶቻችንን ፍፁም ያለመሆን በሚያጠራጥር አይነት መቀበል እየሆነ ላለው የትኛውም እድገት አስፈላጊ የሚሆነው ለዚያ ነው፡፡

ለእርግጠኝነት ጥረት ከማድረግ ይልቅ፣ ስለራሳችን እምነቶች፣ ስለራሳችን ስሜቶች እዚያ ደርሰን ራሳችን እስክንፈጥረው ድረስ የወደፊቱ ህይወታችን ለእኛ ስለያዘው ነገር ምንነት ሁሉ የማያቋርጥ ጥርጣሬ ሊኖረን ይገባናል።ሁልጊዜ ትክክል መሆናችንን ከማየት ይልቅ፣ ሁልጊዜ እንዴት የተሳሳትን እንደሆንን (ያለ ጥፋተኝነት ስሜት) መፈለግ አለብን።ምክንያቱም መሳሳትን ማወቅ ወደ መለወጥ ወደ መቻል ይወስደናልና።

📚The subtle art of giving a f*ck
Mark Manson

@zephilosophy


ስለ ሁሉም ነገር ተሳስታችኋል (እኔም)

አንዳንድ እጅግ መጥፎ ወንጀለኞች ስለራሳቸው በጣም ጥሩ ይሰማቸዋል፡፡ ይህ ስለራሳቸው የሚሰማቸው ጥሩ ስሜት፣ በዙሪያቸው ካለ እውነታ ይልቅ ሌሎችን ለመጉዳትና ላለማክበር ምክንያት የመደርደር ስሜት የሚያሳዩበት ነው፡፡

ሌሎች ሰዎች ላይ በሚያደርጓቸው አሰቃቂ ድርጊቶች ምክንያታዊ መሆናቸው የሚሰማቸው ግለሰቦች በራሳቸው ጻድቅነት፣ በራሳቸው እምነቶችና ያንን ማድረግ የሚገባቸው መሆን ላይ የማይነቃነቅ እርግጠኝነት የሚሰማቸው ናቸው፡፡ ዘረኞች፣ የዘረኝነት ስራ ይሰራሉ፡፡ ምክንያቱም ስለራሳቸው ዘር የበላይነት እርግጠኞች ናቸው፡፡ የኃይማኖት አክራሪዎች ራሳቸውን ይጎዳሉ ወይም ብዙ ሰዎች ይገድላሉ፡፡ ምክንያቱም በመንግስተ ሰማያት ሰማዕታት የመሆን ቦታ እንዳላቸው እርግጠኞች ናቸውና፡፡ ወንዶች ሴቶችን አስገድደው ይደፍራሉ ወይም ሴቶች ላይ ጥቃት ይፈፅማሉ፤ ይህንንም የሚያደርጉት በሴቶች አካል ላይ ባላቸው የበላይነት እርግጠኞች በመሆናቸው ነው፡፡ክፉ ሰዎች ክፉ መሆናቸውን አያምኑም፡፡እንዲያውም የሚያስቡት ሌላው ሁሉ ክፉ መሆኑን ነው፡፡

እዚህ ላይ ችግሩ እርግጠኝነት ሊደርስበት የማይቻል መሆኑ ብቻ ሳይሆን፣ በብዙ ጉዳዮች ላይ እርግጠኝነትን መከተል በአብዛኛው ወይም መጥፎ በሆነ ሁኔታ የማያስተማምን ነገርን የሚፈጥር መሆኑ ነው፡፡

ብዙ ሰዎች ስራቸው ላይ ባላቸው ችሎታ ወይም በሚያገኙት የደሞዝ መጠን የማይነቃነቅ እርግጠኝነት አላቸው፡፡ ያ እርግጠኝነት ግን መጥፎ እንጂ የተሻለ እንዲሰማቸው አያደርጋቸውም፡፡ ሌሎች ከእነርሱ በላይ እድገት ሲያገኙ ሲመለከቱ ትንሽነት ይሰማቸዋል፡፡ ያለመደነቅና እውቅና ያለማግኘት ስሜት ይሰማቸዋል፡፡

የወንድ ጓደኛሽን የፅሁፍ መልእክቶች በሚስጥር ማየት ወይም ሰዎችን ስለ አንቺ ምን እንደሚሉ ጓደኛሽን የመጠየቅ አይነት ቀላል ባህርያት እንኳን የሚነሱት ዋስትና ከማጣትና እርግጠኛ ለመሆን ካለን ከፍተኛ ፍላጎት የተነሳ ነው፡፡

ከዚያ ውስጥ ውስጡን ስለሚበላን ራስን ከፍ አድርጎ የማየት ስሜት ተጠቂ የምንሆነው በእነዚህ ዋስትና ማጣትና ጥልቅ ተስፋ መቁረጥ ጊዜያት ነው፡፡

ይህ ውስጥ ውስጡን የሚበላ የበላይነት ስሜት መንገዱን ለማግኘት ትንሽ ማጭበርበር እንደሚገባን፣ ሌሎች ሰዎች መቀጣት እንደሚገባቸው ፣ የምንፈልገውን አንዳንዴም በኃይል ማግኘት እንደሚገባን ማመን ናቸው፡፡
ይህ እንደገና ወደኋላ የመመለስ ህግ ነው፡፡ ያም ስለሆነ ነገር እርግጠኛ ለመሆን የበለጠ በሞከርን መጠን፣ የበለጠ እርግጠኛ ያለመሆንና ዋስትና ማጣት ይሰማናል፡፡

የዚህ ግልባጭም እውነት ነው፡፡ እርግጠኛ ያለመሆንና ያለማወቅን የበለጠ በያዝን መጠን የማናውቀውን ለማወቅ የበለጠ ፍላጎት ይሰማናል፡፡

እርግጠኛ ያለመሆን ሌሎች ላይ የምንሰጠውን ፍርድ  ያስወግድልናል፡፡ የሆነን ሰው በቴሌቭዥን፣ ቢሮ ውስጥ ወይም በመንገድ ላይ ስንመለከት የሚሰማንን አላስፈላጊ ኩረጃና አድልዎ ባዶ ያስቀርልናል፡፡ እርግጠኛ ያለመሆን በተጨማሪ ራሳችን ላይ ከመፍረድ  ያሳርፈናል፡፡ ተፈቃሪ መሆን አለመሆናችንን አናውቅም፣ ምን ያህል እርግጠኞች እንደሆንን ለማወቅ ብቸኛው መንገድ ስለእነዚህ ነገሮች እርግጠኛ ባለመሆን መቆየትና በልምምድ ለማግኘት ክፍት መሆን ብቻ ነው፡፡

እርግጠኛ ያለመሆን የሁሉም እድገትና መሻሻል ስር ነው፡፡ አሮጌው ብሂል እንደሚገልፀው ሁሉንም እንደሚያውቅ የሚያምን ሰው ምንም አይማርም፡፡ በመጀመሪያ የሆነ ነገር የማናውቅ መሆናችንን ካላወቅን ምንም ነገር ልንማር አንችልም፡፡ ምንም የማናውቅ መሆናችንን የበለጠ ባመንን መጠን፣ የበለጠ የመማር እድል እናገኛለን፡፡

እሴቶቻችን ፍፁም ያልሆኑና ያልተሟሉ ናቸው፡፡ ፍፁምና የተሟሉ እንዲሆኑ አድርጎ መገመት ራስን ከፍ አድርጎ ማየትና ሀላፊነትን ችላ ማለትን የሚፈጥር በአደገኛ ሁኔታ  ግትር አስተሳሰብ  ውስጥ ያስቀምጠናል። ችግሮቻችንን ለመፍታት ብቸኛው መንገድ በመጀመሪያ እስከዚህ ነጥብ ድረስ ያሉት እርምጃዎቻችንና እምነቶቻችን የተሳሳቱ ሊሆኑ እንሚችሉ ማመን ነው፡፡

የትኛውም እውነተኛ ለውጥ ወይም እድገት እንዲካሄድ መሳሳታችንን ለማመን ግልፅነት መኖር አለበት፡፡ ወደ እሴቶቻችንና ቅድሚያ የምንሰጣቸው ነገሮች መመልከት ከመቻላችንና ወደተሻለና ጤናማ ልንለውጣቸው ከመቻላችን በፊት፣ በመጀመሪያ አሁን ስላሉት እሴቶቻችን እርግጠኛ አለመሆን ይገባናል፡፡ እሴቶቻችንን በመከፋፈል መመርመርና ስህተቶቻቸውንና ተፅዕኗቸውን ማየት፣ ከቀሪው አለም ጋር እንዴት እንደማይገጥሙ መመልከት፣ አላዋቂነታችንን ፊት ለፊት አፍጥጠን ማየትና ማመን አለብን፡፡

እድገት ማለቂያ የሌለው ተደጋጋሚ ሂደት ነው፡፡ አዲስ ነገር ስንማር፣ የምንሄደው ከ “ስህተት” ወደ “ትክክል” ሳይሆን ከስህተት ወደ አነስ ያለ ስህተት ነው፡፡ አንድ ተጨማሪ ነገር ስንማር አነስ ካለ ስህተት ከዚያ በመጠኑ አነስ ወዳለ ስህተት እየሄድን ነው፤ እንዲህ እንዲህ እያለ ይቀጥላል፡፡ ሁልጊዜ በፍፁም ወደ እውነትና ወደ ፍፅምና ባለመድረስ ወደ እውነትና ፍፅምና የመቅረብ ሂደት ላይ ነን፡፡ለራሳችን የመጨረሻውን “ትክክለኛ” መልስ ለማግኘት መፈለግ አይገባንም፡፡ በዚያ ምትክ ነገ ከዛሬ ይልቅ መሳሳታችን የቀነሰ መሆን እንድንችል ዛሬ ስህተት የሆንባቸውን መንገዶች ፈልገን ማግኘት ይገባናል፡፡

📚The subtle art of giving a f*ck
Mark Manson

ይቀጥላል....
@zephilosophy


አይኖቹን ከደነና ረሀብና ጥም በትነውት የነበረውን አሳቡን ሰበሰበ። ፈጣሪ ወደ አእምሮው መጣ:: አሁን ረሀብም ሆነ ጥም የለበትም:: ስለ ዓለም ድህነት (መዳን) አሰበ፡፡ “የጌታ ቀን የሚመጣው በፍቅር ብቻ ከሆነ እግዚአብሔር ሁሉን የሚችል አይደል? ስለምን ተአምር ፈጥሮ የሰዎችን ልብ እየነካ እንዲፈካ አያደርግም? በየአመቱ ግንዶች፣ አረምና እሾኾችስ እርሱ ሲነካቸው ይፈኩ የለ? ታዲያ ምናለ አንድ ቀን ሰዎች ሲነቁ ውስጣቸው ፈክቶ ቢያገኙት?”

ኒኮስ ካዛንታኪስ
የመጨረሻው ፈተና

@zephilosophy


ሰው እና ተፈጥሮ
___

"Life in all its forms is interconnected, and the song of a bird is as vital to the melody of existence as the hum of the stars."

___

ሳይንስ ስለ ምልዓተ ዓለሙ የሚተነትነውን ሃቂቃ ይዘን cosmic በሆነ መነጽር ብንመለከት ሰው የሕላዌ ማዕከል እንዳልሆነ ብቻ ሳይሆን ከዩኒቨርስ ስፋትና አይመጠኔ አነዋወር አንፃር ምድር ራሷ 'ብናኝ' ለማለት የሚደፍሯት እንደሆነች ይገባናል... 


በእኛ ጋላክሲ ውስጥ ያሉትን ጥቂት ፕላኔቶች እንደ ከረጢት ብንቆጥራቸው ኔፕቲዩን 57፣ ዩራነስ 63፣ ሳተርን 763፣ ጁፒተር 1321 እንዲሁም ጸሐይ 1.3 ሚሊየን ምድር በውስጣቸው መያዝ ይችላሉ... ይህ እንግዲህ ሌሎች በመቶ ቢሊየኖች የሚቆጠሩ ዓለማትን ሳይጨምር ነው... 


በእኛ ሶላር ሲስተም ውስጥ ያለችው ጸሐይ 1.3 ሚሊዮናት ምድር በውስጧ ማጨቅ በመቻል እጅግ ግዙፍ ትምሰል እንጂ እንደነ Betelgeuse፣ VY Canis Majoris፣ UY Scuti፣ እና Stephenson ካሉ ሌሎች ጸሐያት ጋር ስትወዳደር ከ 2 - 18 ያህል ጊዜ ስለምታንስ እርሷም ጢንጢዬ የመሆን ዕጣ ይወድቅባታል... [በእኛም ላይ 'አባይን ያላየ...' ታስተርትብናለች]


ከዚህ ሁሉ ግዝፈት አንፃር ታዲያ የሰው ልጅ ምንድነው?... ከብናኝ በታችስ ምን አለ?... 


[የከዋክብቱ ግዝፈት የእኛን ማንነት ያሳንሳል እያልኩ እንዳልሆነ ግን ልብ በሉልኝ... ትልቀታቸው ዝቅ አያደርገንም... ከራስ ባሻገር ላለ ሕላዌ ቦታ እንድንሰጥ ያደርጋል እንጂ... ከአንድ ዓይነት ንጥረ ስሪት የተገነባን አይደለን?...

አስትሮፊዚስቱ Neil deGrasse Tyson እንዲህ ይላል...

"We are part of this universe; we are in this universe, but perhaps more important than both of those facts is that the universe is in us... And for me, that is a deeply spiritual, inspiring experience."]


_

ዳር አልባ በሆነ ምልዓት ውስጥ ብቸኞች ነን ብሎ ማሰብ ከባድ ነው...

"We are not alone in the universe. We are members of a vast cosmic community, sharing the same atoms, stardust, and energy." – Carl Sagan


እኛ ብቻ የተመረጥን፣ እኛ ብቻ የተለየን፣ እኛ ብቻ ግዕዛን ያለን ብሎ መከራከርም ውሃ አይቋጥርም... ተፈጥሮን ጭብጣቸው አድርገው በተሰሩ በርካታ documentary ፊልሞች ውስጥ እጅን በአፍ የሚያስጭኑ የእንስሳትና ተክሎችን ባሕሪያት አይተናልና... 


"The smallest creature is a masterpiece of nature, as intricate and essential to the balance as the stars in the sky." – Anonymous


ደርሶ የሕላዌ ማዕከላዊ ጉዳይ (Center of existence) እኛ ብቻ ነን ብሎ ማሰብም አይከይፍም... ጉራ ይበዛዋልና... 


ሰው ሁሉ ከምድሪቱ ላይ ጠፍቶ ምድር ሌሎች ፍጡራንን አቅፋ፣ ተንከባክባ መኖር ግድ ቢላት ፈጽሞ የምትቸገር አይመስለኝም... ከአጥፊ ባህሪያችን አንፃር እንደውም ሳይመቻት አይቀርም... ግና ለጥቂት ቀናት ውሃ ቢርቃት ሕላዌን ድርቅ ሊያረግፋት ይችላል... እና ከውሃ አንፃር ሲታይ ሰው ምንድነው?... 


"In the grand orchestra of the universe, humanity is but one instrument, playing alongside countless others." – Anonymous


ደጉ ነገር ያለንበት Ecosystem ቅድሚያ የሚሰጠውም ሆነ የሚያበላልጠው ፍጥረት የለውም... ሁሉም ለእርሱ እኩል ነው፣ ሁሉም የተፈጥሮን ሚዛን አስጠባቂ ነው...


የሰው ልጅ የሃሳብ ጥመትና የእኔ እበልጥ ትርክት ግን ችግር ፈጠር መሆኑ አልቀረም...

___

እንዴት?... 

___


፩) ተፈጥሮን የምንቀርብበትን መንገድ የተሳሳተ አድርጎታል፤ በዙሪያችን ያሉ ተዋንያንን አስተዋጽዎ ከሰው አሳንሰን ስለምናይ የምንሰጣቸውን ቦታ ዝቅ አድርጎታል፤ ብዙ ተረቶቻችንን ተመልከቱ በእንስሳት ንቀት ላይ የተዋቀሩ ናቸው...

ንቀቱ ታዲያ እንስሳቱ ጋ ብቻ አልቆመም፣ ሰው የምንመዝንበትን ሚዛን አባይ አድርጎታል፤ 'ከራስ በላይ ንፋስ' የሚል ልክ አበጅቷል፤

፪) የርህራሔ ድንበር አፋልሷል፣ እንስሳቱን በጭካኔ እንገድላለን፣ ተክሎችን በግድየለሽነት እናወድማለን... 

"The greatness of a nation and its moral progress can be judged by the way its animals are treated." – Mahatma Gandhi

ይህ ልምምድ በአንፃሩ ሰውን የምናይበትን ዓይን አንሸዋሯል... ሞቱን አርክሶብናል...

፫) ጊዜያዊ ችግር ለመፍታት ዘላቂ ችግር እንፈጥራለን... ከእኛ ተርፎ ለልጅ ልጅ የሚሻገር ሃብት መፍጠር ሲገባን በስግብግብ ቅኝት ከመጪው ትውልድ አፍ ነጥቀን እንጎርሳለን...

"We do not inherit the earth from our ancestors, we borrow it from our children." – Native American Proverb

____

እንዲህም እንላለን... 

"Man is not the lord of all beings. He is a being among beings." – Martin Heidegger

@bridgethoughts
@zephilosophy




ነገረ መለኮት ከሌላ ማዕዘን...


እኔ እንደ በርትራንድ ረስል ‹‹ሐይማኖት የፍርሃት ውጤት ነው›› አልልም፡፡ ይልቁንስ ምንነቱን እና ከየትነቱን የማያውቁት በቅጡ ያልተደመጠ፣ ምላሽ ያልተሰጠው ናፍቆት ወደ ማመን እንደሚመራን አስባለሁ፡፡ በእርግጥ የሕይወት፣ የአምልኮ ነገር ሲጀመር አደራረጉ እንደሞኝነት መሆን አለበት፡፡

አጀማመሩ ልክ ከፏፏቴ እንማውጋት፣ ለጨቅላ እንደማንጎራጎር፤ ምናልባት ለነፋስ እንደማፏጨት ስሜት የማይሰጥ ከሚመስል መዳዳት ሳይሆን አይቀርም፡፡ ነገርግን መሰረታዊው ሰው የመሆን ቅጥም የተሰራው በዚህ የገርነት ቅኝት መሆን አለበት፡፡ ሰው የፍጥረት የበላይ (superior) የመሆኑን ቀቢጽ የሚሰብኩት ከራሱ መካከል ተከስተው ሙሉ በሙሉ ከተፈጥሮ ቅኝት እስኪነጥሉት ድረስ የንጽህና ልጅ ነበር፡፡

ለምሳሌ የላቲን አሜሪካ ቅዱስ ሕዝቦች ኮጊዎች (Kogi) የክርስቶስን አዳኝነት፣ የነብዩ መሐመድን መልዕከተኝነትን ለመስማት ለአንድ ሺህ ስድስት መቶ ዓመታት የቅኝ ገዥዎችን መምጣት መጠበቅ ነበረባቸው፡፡ ነገርግን ሰው መሆን አልጠፋባቸውም፡፡ እንኳን ለመሰላቸው ለመላው ግዑዝ ለሆነው ስነፍጥረት ሁሉ ይራራሉ፡፡ ለሺህ ዘመናት አማኞች ነበሩ፡፡ ለዚያውም የተፈጥሮን ሥሪት የተከሉ... ዛሬም ድረስ የጥንታዊ አያቶቻቸውን የአምልኮ እና አስተሳሰብ ዘይቤዎችን እያስቀጠሉ ዘመናዊውን የሰው ልጅ ሽሽት በኮሎምቢያ አይደፈሬ የተራራ ሰንሰለቶች ይኖራሉ፡፡

እነዚህ ሕዝቦች ለተፈጥሮ ካላቸው ጥንቁቅነት የተነሳ መንገድ ስንኳ ለመስራት አንዲትም ድንጋይ ከቦታዋ አያፈናቅሉም፤ አንዲትም ሀረግ አይነቅሉም፡፡ ሁሉንም ነገር የሚከውኑት የተፈጥሮን የልብ ምት በተከተለ መልኩ ነው፡፡ ሰሚ ባያገኙም ቅሉ ስህተተኛው ታናሽ ወንድማችን ለሚሉት ዘመናዊው የሰው ልጅ ተፈጥሮን ስለመጠበቅ አስፈላጊነት በተከታታይ መልዕክቶችን ይልካሉ፡፡
እንዲህ የንጽህና ልጅ በነበረ ጊዜ ሰው ጨካኝ በሚመስለው ነገር ግን ፍትህና ርትዕ ሚዛኑ በሆነው ስሙር የተፈጥሮ ሰሌዳ ላይ ጊዜያዊያነቱን፣ አላፊ ጠፊነቱን በጸጥታ የተቀበለ ስኩን ፍጥረት ነበር፡፡ ተፈጥሮን ለመግዛት ለመግራት በበላይነት ስሜት ከመቋመጥ ይልቅ ተፈጥሮን መልበስ፣ መዋረስ ሰው የመሆን ደመነፍስን ያሰለጥን የለምን?

ሁሉም ነገር ሲጀመር የሰው ልጅ የመሆንን ነገረ ውል ለመካን ሙዝን ልጦ የመበላት ጥበብ ማወቅ ብቻ ይበቃው ነበር፡፡ ሲፈጠርም ጀምሮ ስሪቱ የተፈጥሮ ነው፡፡ በእርግጥም ያኔ የሰው ልጅ ደመነፍስ እንደመላዕክት፣ እንደመለኮቱ ጉልህ ‹እኔነቱ በስግብግብ ምሪት ያልደበዘዘ ገር (simplistic) ነበር፡፡

ሊዮ ቶልስቶይ የጻፈው በብዙዎች ዘንድ ሊታወቅ የሚችል አንድ አስገራሚ ተረት አለ፡፡ አሳጥሬ ልተርከው..

በአንድ ደሴት በብህትውና የሚኖሩ ሦስት ጻድቃን ነበሩ፡፡ አኗኗራቸው ተርታ ነው፡፡ ቀስ በቀስ ስለቅድስናቸው በአጎራባቿ ከተማና በመላው ሀገሪቱ ዝነኞች ሆኑ፡፡ ሰዎች ወደ እነርሱ ይጎርፉ ጀመር፡፡

ይህ ያላስደሰተው የአጎራባቿ ከተማ የቤተክህነት አስተዳዳሪ አንድ ቀን ሊገበኛቸው በጀልባ ሄደ፡
እንደደረሰም ጠየቃቸው..

‹‹ዝናችሁ በከተማውና በሀገሪቱ ናኝቷል፡፡ ለመሆኑ ለቅድስና ያበቃችሁ የተለዬ የምትጠቀሙት ጸሎት አለን?

‹‹እውነቱን መናዘዝ ይኖርብናል፡፡ በሥላሶች፣ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ከማመናችን የተለየ ምንም የምናውቀው ፀሎት የለም፡፡ ይልቁንስ የምንፈልገው መናገር ነው።ይፈጸምልናልም፡፡››

እንግዳው የቤተክህነት ሰው ሳቀ፡፡ ያለ ጸሎት የሚሆን ነገር እንደሌለ አስረድቶ ፀሎቱን አስጠናቸው፡፡

‹‹እባክህ እኛ የተማርን ሰዎች ባለመሆናችን ጸሎትህ ረጅም ከመሆኑ የተነሳ ልናስታውሰው አልቻልንምና ድገምልን፡፡›› ባሉት ጊዜ እንደገና አስጠናቸው፡፡ ጸሎቱን ለሦስተኛ ጊዜ እንዲያጠኑት ረዳቸው፡፡

በአሸናፊነት ስሜት ወደ እናት ከተማው መመለስ ጀምሮ የሀይቁ መሀል ላይ ሲደርስ ግን ለማመን የሚከብድ ነገር ሆነ፡፡ ሦስቱ መናኒያን በውኃው ላይ በፍጥነት እየተራመዱ ተጠጉት...

‹‹እባክህ ያስጠናኸን ጸሎት ረጅም ስለሆነ እኛም የተማርን ባለመሆናችን ተረስቶናል እና ብትደግምልን፡፡›› ተማጸኑት፡፡

በውኃ ላይ እንደቀላል መራመድ በሚያስችል ቅድስናቸው የተደነቀው እንግዳው ጎብኚ ግን በውኃ ላይ እስከመራመድ የሚያስችል የመብቃታቸውን ተዓምር ከተመለከተ በኋላ ...
«በፍጹም!   ትክክለኛው ጸሎት የእናንተው ስለሆነ በዚሁ ቀጥሉ ብሎ አሰናበታቸው፡፡››

የሰው ልጅ የንጽህና ልጅ በነበረ ጊዜ እንደነዚህ ሦስት ጻድቃን ነበረ፡፡ በዘመን ሂደት ቀስ በቀስ ሰው መሆንን ረስቶ አውሬነትን ተለማመደ፡፡ ሰው የመሆን ውሉ ሲደናገረው በመጽሐፍ ቅዱስ ‹‹ሰሎሞንስ ስንኳ በዚያ ሁሉ ክብሩ እንደነሱ አልለበሰም›› የተባለላቸው የሜዳ አበቦች ግን አበባ መሆን እንግዳ አልሆነባቸውም፡፡ አበባ ለመሆን ብዙ ምርምር፣ ላቦራቶሪ አላስፈለጋቸውም፡፡ የጽጌ ጌጥነታቸውን ለመቀዳጀት የንጽህና ልጆች መሆን ብቻ ይበቃቸዋል፡፡

የሰውን ልጅ ግን እናውቅልሃለን በሚሉ በራሱ በሰው ልጆች የመላው ፍጥረት የበላይ መሆኑን እየተጋተ ልጅነቱን ካደ፡፡ በሚያምነው ፊት ምንምን፣ ጊዜንም ቢሆን የማይፈራ የነበረውን ፍጥረት በሂደት ድንጉጥ አደረጉት፡፡ ድንጋጤው ጭካኔን ወለደ፡፡

ለራሱ ለመላው ስነፍጥረት ሁሉ ጭካኔን የሚነዛ አረመኔ ሆነ፡፡ ከጊዜና ከቦታ ጽንፍ፣ ከራስ መዳዳት በላይ አልፎ ማሰብ የማይችል ድኩማን...


በፍም እሳት ማቃመስ
ያዕቆብ ብርሀኑ

@Zephilosophy


የጠፋውን የሰው ልጅ ፍለጋ (Search for the lost human soul)

ዘመኑ 1950ዎቹ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ... ከሁለቱ የዓለም ጦርነቶች ስካር የባነነው ዓለም ለሌላ ዓይነት ባርነት ራሱን ሲያዘጋጅ ተገኘ፡፡ ሥልጣኔውም አገዘው፡፡ የሥልጣኔ ቀዳሚው ተልዕኮ የሰውን ልጅ እንሰሳዊ ደመነፍስ ማላመድ (taming human animalistic aggresion) ቢመስልም ውጤቱ ግን የተገላቢጦሽ ሆነ፡፡ ለኤሮፓዊ ፋውስታዊ የዛገ መዳዳቱ ስምረት ቴከኖሎጂው ረዳት ሆነለት፡፡

ዘመኑ ሰው ወደ አሻንጉሊትነት የሚያደርገውን የመምዘግዘግ ጉዞ አሀዱ ያለበት ሆነ፡፡ በአዲሱ ፈጠራ ቴሌቪዥን በመታገዝ "ፖፕ ከልቸር" ሰለጠነ፡፡ ሁሉም አብረቅራቂው ዘመን አመጣሽ ሳጥን ጋር ፍቅር ወድቆ ለአዲሱ ጊዜ ባርነት ራሱን አዘጋጀ፡፡ ዓመታት ተቆጠሩ፡፡ ቴክኖሎጂው በቀኝም በግራም እኩል ይመነደጋል፡፡ ቫይረሱ እና አንቲቫይረሱ፣ ሚሳኤሉና ጸረሚሳኤሉ እኩል ይበለጽጋሉ፡፡

ዛሬ ከሰባ ዓመታት በኋላ በዓለምአቀፍ ደረጃ ወደ ሁለት ቢሊዮን የሚጠጉ የቴሌቪዥኖች ዝግጅቶች ፣ ከ5 ቢሊዮን በላይ የሞባይል ስልኮች በሰው ልጆች እጆች ላይ ይገኛሉ። በአንጻሩ በሰው ልጆች የንባብ አትሮኖሶች ላይ እንደተዘረጉ የሚገመቱት መጻሕፍት ዓይነት ከ150 ሚሊዮን አይበልጥም፡፡

እነሆ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ሞታችን ረክሶ ‹ላይቭ ስናየው ስንኳ ማስደንገጡ ቀንሷል፡፡ እንበላለን፤ ግን አናጣጥምም፡፡ እንዋሰባለን፤ ግን ፍቅርን ረስተናል፡፡ አብረን ሆነን ለብቻችንን ነን፡፡ አብረን እየኖረን አንዳችን ለሌላችን በዓድ፣ ሩቅ ነን፡፡ ወዳጅነት፣ ሣቅ፣ ፈገግታ፣ መታመን፣ ፍቅር፣ ፍትወት... ሸቀጥ ሆነው በገበያ ዋጋ ይቸበቸባሉ፡፡

ሰብዓዊት የማይቀለበስበት አስፈሪ ውጥንቅጥ ውስጥ ገብቷል፡፡ አንዳንዶች ይህ አረዳድ ጭፍንነት ሊመስላቸው ይችላል፡፡ አንዳንዶች ሀዘኑ ቤታቸው እስኪገባ ድረስ የመቃብር ደወሉ በየዕለቱ ለእነርሱ እንደሚደወል ይረሱታል፡፡

እናስ ኤሪክ ፍሮም እንዳስጠነቀቀው የሚቀጥለው ዘመን ሮቦቶች ለመሆን ምን ያክል ይቀረናል? በዚያ ዘመን (በ195oዎቹ አጋማሽ) የተነሱት እንደ ኤሪክ ፍሮም ዓይነት የሰው ልጅ ዕጣ ያስጨነቃቸው አሰላሳዮች ሰው ስለመዳረሻው እንዲጠነቀቅ አብዝተው ቢወተውቱም ሁሉም ከአጥበርባሪ ሳጥኗ ጋር ሲወዛወዝ ሰሚ አልነበራቸውም፡፡ ኤሪክ ፈሮም በ1955 እ.ኤአ በታተመ The Sane Society› በተሰኘ መጽሐፉ ላይ እንዲህ አለ፡፡

‹የ19ኛው ክፍለዘመን ጥያቄ፣ ትርክት ‹‹እግዚአብሔር ሞቷል›› ነበር፡፡ የሀያኛው ክፍለዘመን ፈተና ግን የሰው ልጅ ሞቷል› ሆነ፡፡ በ19ኛው ክፍለዘመን ኢ-ሰብዓዊነት ማለት ጭካኔ ነበር፡፡ በ20ኛው ክፍለዘመን ግን ኢሰብዓዊነት ማለት መደንዘዝ፣ ስሜት ማጣትና መነጠል ሆነ፡፡ የትናንት ስጋታችን የሰውን ልጅ ወደ ባርነት እንዳይገባ ነበር፡፡ የነገ ስጋታችን ግን የሰውን ልጅ ከሮቦትነት የመታደግ ሆኗል፡፡››

‹‹ሁላችንም በዘመናዊው የምዕራብ ዓለም የምንኖር ሰዎች እብደት ውስጥ ነን፡፡ ራሳችን እያታለልን ላለመሆናችን ምን ዋስትና አለን?››

ዓለም መልክ የሌለው መገማሸር ውስጥ ገብታለች፡፡ ልክ አንደ ሁልጊዜው!... በዚህ ሂደት ሰው የመሆናችን ቀለም አጥተናል፡፡ ሰው የመሆናችን ውሉ በምን ይረጋገጥ? ከቅድመ አያቶቻችን የሚያስተሳስረን ፈትለነገር ከተቋረጠ ሺህ ዘመናት አልፈዋል፡፡ በሕንጻ ሰንሰለቶች መካከል እየተመላለስን ስንኳ ሕልማችን የተራራ፣ የሸንተረር፣ የአደን፣ የለቀማ ነው፤ እንደ ግዞተኛ ነን፤ ፊሊፒናዊ፣ ቼካዊ፣ ቱርካዊ... መሆናችን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ፣ የቅዱስ ቁርዓን፣ ወይም የማናቸውም ቅኝት ሥሪት መሆናችን እውነታውን አይቀይረውም፡፡

እኔ ግን የዓይኑ ቀለም ያላማራቸውን በጅምላ ኮንነው ሰልፊ እየተነሱ ዘቅዝቀው የሚሰቅሉ ሕዝቦች ሀገር ዜጋ ነኝ፡፡ ያ ሁሉ የሺህ ዘመናት ወንጌል፣ ሥነምግባር፣ ሀፊዝ፣ ሥርዓት፣ ትምህርት፣ ግብረገብነት በቅፅበት ውኃ በልቶት መቅላት፣ እስከነፍስ ማቃጠል፣ መደፍጠጥ፣ ማሳደድ... ሁሉም በሚያስደነግጥ ፍጥነት ሲከናወን አቅመቢስ ስዱድ፣ ዲዳ ሆኘ ተመልከቻለሁ፡፡ ታምሜያለሁ፡፡ ብዙ ኢፍትሃዊነት ባለበት ምንም ማድረግ ካለመቻል በላይ የሚያም ምንስ ነገር ይኖራል?

ለነገሩ በየትኛውም የዓለም ክፍል በሰብዓዊነት፣ በአጠቃላይ በስነፍጥረት ላይ የሚቃጣ በደል ካላመመኝ የስካሩ አካል ሆኛለሁ ማለትም አይደል? አንዳንዶች ለዚህ መድኃኒቱ ዜግነትን ማስረጽ፣ ሕገመንግስት መቀየር... ዓይነት _ ጨዋ ሐሳቦችን ሲሰነዝሩ እሰማለሁ፡፡ ምንኛ የዋሆች ሆነዋል ጃል! የታመመው በአጠቃላይ የሰው ልጅ (ሰብዓዊነት) መሆኑን ማየትስ እንዴት ይሳናቸዋል? ይህ የሰብዓዊነት ማሽቆልቆል፣ ስርዓት በመቀየር፣ ደንደሳም ዴሞክራሲ በማስረጽ፣ በአዋጅ በማስነገር፣ ኢትዮጵያን እንደ አሜሪካ በማበልጸግ ብቻ ሊሻሻል አይችልም፡፡ እንዲውም ሁላችንም ከጫፍ እስከ ጫፍ እንደ ሰው ካላሰብን አንተርፍም፡፡


ዘመናዊው የሰው ልጅ ከቅድመ አያቶቻችን አንጻር የሁሉም ነገር ውስጥ መትረፍረፍ ውስጥ ነው፡፡ ዛሬ የአንድ አሜሪካዊ ቤተሰብ አማካይ የመገልገያ ቁሳቁሶች ብዛት እስከ 300,000 ይገመታል፡፡ ከመቶ ዓመታት በፊት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር 5000% እጥፍ ተመንድጓል፡፡ ዘመኑ በሁሉም ነገር የመትረፍረፍ (Abundance) ቅዠት ውስጥ የሚዳክር ይመስላል፡፡ ነገርግን መትረፍረፍ መቅሰፍት ሆኖብን ምኞታችን፣ እውነታችን፣ የሕይወት ትርጉማችን አሳክሮብናል፡፡ ምንም የማይፈይድልን የመረጃ ናዳ ያጥለቀልቀናል፡፡ በተሳከረ የመረጃ ቱማታ ተዋክበን እውነታችን ራሱ ዋጋ አጥቷል፡፡

ዘመኑ እንደየትኛውም ግልብ ዘመን ነበርና ኤሪክ ፍሮምና መሰሎቻቸው አድማጭ አላገኙም፡፡ እንደየትኛውም ዘመን... ዛሬ ለስሙ እንሰዋለን የሚሉ ቢሊዮናት ተከታዮች ያሉት መሲሁ በቁርጡ ቀን ከመስቀሉ ፊት ለፊት ለብቻው እንደነበረበት ዘመን፡፡ የሚያሳዝነው ዘመን ልብ መግዛት ሲጀምር ዕድሎች ቁጭት ሆነው ከተፍ ማለታቸው እኮ ነው፡፡

የሰው ልጅ የለየለት ዕብደት ውስጥ ገብቷል፡፡ ነጠል ብሎ ለሚታዘብ ተመልካች የሚታየው የሚሰማው  ሁሉ  አጃኢብ ነው፡፡ ሥልጣኔው ሁሉ በየዕለቱ የሚያስመዘግበው መካን፣ መራቀቅ የአውዳሚነት መሆኑ ተስፋ ያስቆርጣል፡፡ ከጦር መሣሪያ ጋር ያልተነካካው ቴክኖሎጂያዊ ፈጠራ ስንኳ በየዕለቱ ሰብዓዊነትን የሚያኮሰምን የመሆኑ ነገር ያስደነግጣል፡፡

ተመራማሪዎች በቅርቡ ሰው በማይደርስባቸው አስፈሪ የአርክቲክ አካባቢዎች ሳይቀር ብዙ ሺህ ቶን የሚመዝን የማይበሰብስ ቆሻሻ አግኝተዋል፡፡ የሰው ልጅ አሁን በተያያዘው ግዴለሽ ጎዳና ከቀጠለ ሩቅ በማይባል ዘመን ሕይወት ከውቅያኖሶችና ባህራት ተጠቃልሎ ሊጠፋ ይችላል፡፡


በፍም እሳት መቃመስ
ያዕቆብ ብርሀኑ

ይቀጥላል
@Zephilosophy


ግለሰባዊነት

ምንጭ ፦ ከፍስሀ ጋር መወለድ (ኦሾ)
ትርጉም ፦ ዩሐንስ አዳም

ሰዎች የሚኖሩት ግለሰባዊ ባልሆነ ዓይነት ህልውና ውስጥ ነው:: እነርሱ የሚኖሩት እንደ በጎች ነው፡፡ ስለዚህ ስለ ግለሰባዊነቱ አመፁ ፣ ነፃነቱ ፣ የሚናገር ኢየሱስን ወይም ቡድሐን የመሰለ ሰው እዚያ ሲኖር መጠላቱ ወይም አለመወደዱ ተፈጥሯዊ ነው፡፡ ስብስቡ (መንጋው) ይፈራል መሰረታቸው ይነቃነቃል፡፡ ኢየሱስ ትክክል ከሆነ ከዚያም መላው የስብስቡ የህይወት ንድፍ መቀየር ይኖርበታል፡፡ ይህ ደግሞ በጣም ብዙ ስራን ይጠይቃል ሰዎች ደግሞ በባርነታቸው ላይ ብዙ ኢንቨስት አድርገዋል፡፡

የኢየሱስ መገኘት ወይም አሁናዊነት ሰዎችን የኪሣራ ስሜት እንዲሰማቸው ያደርጋል፡፡ ቡድሐን ባገኛችሁበት ቅፅበት ወደ በጣም አስቀያሚ ኢ-ሰባዓዊ ፍጥረት ዝቅ ትላላችሁ፡፡ ሁሉንም ክብር ታጣላችሁ፤ ኢ-ሰባዓዊ በሆነ መንገድ እንደታያችሁ ይሰማችኋል፡፡ ምጡቆች ከሆናችሁ የቡድሐን መገኘት እንደ ማንሠራሪያነት ትጠቀሙበታላችሁ፡፡ በአላዋቂነት ውስጥ፣ በእንቅልፍ ውስጥ ስትኖሩ እንደነበር የምታዩ ትሆናላችሁ:: እናም የቡድሐ መገኘት እና አሁናዊነት በጨለማው የነፍሣችሁ ሌሊት ውስጥ የብርሃን ጨረር እንደሆነ በመገንዘብ ለቡድሐ ታላቅ ምስጋናን ታቀርባላችሁ።

ዳሩ ያንን ያህል ምጥቀት ግን በጣም እያሰለሰ የሚገኝ ነው፡፡ ሰዎች ግትሮች እና ደደቦች ናቸው:: ወዲያውኑ ነው አፀፋ የሚሰጡት፡፡

ወደ ላይ ከማንሰራራት እና የቡድሐን (የነቃውን ሰው) ጫፍ ፈተና በመውሰድ ፋንታ ዳግም ማሸለብ ይችሉ እና ጣፋጭ ህልሞች ተብዬዋቻቸውን ያልሙ ዘንድ ቡድሐን፣ ኢየሱስን የመሰሉ ሰዎችን ያጠፏቸዋል፡፡

ለዚያ ነው ከእኔ ጋርም በተቃርኖ ውስጥ የሆኑት፡፡ እኔ የሆንኩኝ ረብሻ ዓይነት ነገር ነኝ፡፡ የእኔ መገኘት ችላ ሊባል አይችልም፡፡ አንድም ከእኔ ጋር መሆን አለባችሁ አልያም ደግሞ ከእኔ በተቃርኖ ውስጥ መሆን ይኖርባችኋል፡፡ የአንድን ሰው አሁናዊነት (መገኘት) ችላ ማለት ሣትችሉ ስትቀሩ መምረጥ ይኖርባችኋል፤ ታላቅ ትርምስም በፍጥረታችሁ ውስጥ የሚኖር ይሆናል - ምክንያቱም የትኛውም መምረጥ ቀላል አይደለም፡፡ መምረጥ ማለት ደግሞ መቀየር ማለት ነው::

ለሃምሣ ዓመታት በተወሰነ መንገድ ኖራችኋል እንበል፡- በነዚያ ዓመታት ውስጥ እነዚያ ልምዶች ሰምረዋል፡፡ አሁን በድንገት እኔ እዚህ ሆኜ እውነተኛ ህይወት ብላችሁ ታምኑበት ከነበረው መቃብራችሁ እየጠራኋችሁ ነው:: እኔ እዚህ ስትኖሩላቸው የነበሩት ሁሉንም ነገሮች፣ ሁሉም እሤቶቻችሁን፣ ግብረ - ገባዊነት ተብዬዎቻችሁ፣ ሁሉም ዕውቀቶቻችሁን፣ እየኮነንኩኝ ነው፡፡ በጣም ደፋር ሰዎች፣ በጣም የተመረጡ ሰዎች ብቻ ና፥ቸው በሁኔታው ማንሰራራት የሚችሉት እና ያላቸውን ሁሉንም ነገር ሊታይ ለማይችል ግን ዕምነትን ሊያሣድሩበት ለሚችል ነገር አደጋው ውስጥ ሊከቱ የሚችሉት፡፡ አሁን ይህ ለተራው መንጋ (ህዝብ) አስቸጋሪ ነው፡፡ ተራው መንጋ መወሰን የሚችለው ለታወቀ ነገር ነው፡፡ ኢየሱስ አንድ ያልታወቀ ነገር ነው፤ ቡድሐ ከባሻገሩ ያለ አንድ የሆነ ነገር ነው:: አሁን ጥያቄው አንድም የታወቀውን፣ አስተማማኙን፣ ምቹውን መምረጥ አልያም ይህንን ጅብዱ መምረጥ እና ካርታ ላይ ወዳልሰፈረው፣ ፈፅሞ እርግጠኛ ሊሆኑበት ወደማይችሉት መሆኑ አልያም አለመሆኑ ወደማይታወቅበት አንድ የሆነ ነገር
ውሥጥ ከቡድሐ ጋር መሄድ ይሆናል፡

ምናልባት ቡድሐ ራሱ ተሸውዶ ይሆናል ወይም ደግሞ ቡድሐ አታላይ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህንኛው፣ ያንኛው የሚል ምልዑ የሆነ እርግጠኛ የሆነ ምንም መንገድ የለም፡፡ አንድ ሰው በጥልቅ ማመንታቱ፣ በጥልቅ ግራ መጋባቱ፣ በጥልቅ መንገዳገዱ ከቡድሐ (ከነቃው ሰው) ጋር መሄድ ይኖርበታል፡፡ እስካሁንም ወጣቶች የሆኑቱ ፣ አዕምሯቸው አቧራዎችን ያልሰበሰበው፣ የተደሞ ብቃት ያላቸው፣ የህይወት አክብሮት ስሜት ያላቸው፣ ፍፁም ያልተዘጉ፣ ከህይወት ጋር ያላቸውን ጉዳይ ገና ያልጨረሱ፣ እስካሁንም ድረስ ያልሞቱ ...እነዚህ ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው ከእኔ ጋር፣ ከኢየሱስ እና ከቡድሐ ጋር መሄድ የሚችሉት፡፡ ሌሎቹ ከእኔ፣ ከኢየሱስ እና ከቡድሐ ጋር በተቃርኖ ውስጥ ሊሆኑ ግድ ነው::

በተጨማሪም ሌሎች ምክንያቶች አሉ ሰዎች የቡድኖች አባል መሆን ይፈልጋሉ፡፡ ቡድን አባል መሆን አንድ የሆነ በትክክለኛው መንገድ ላይ ነኝ የሚል መፅናናትን እና እርካታን ዓይነት ነገር ይሠጣል፡፡

እውነት በመንጋው ተቀባይነት ልታገኝ አትችልም፡፡ የዚህ ምክንያት ደግሞ መንጋው የሚኖረው በውሸቶች ውስጥ ስለሆነ ነው፡፡ እናም እነርሱ እነዚያ ውሸቶች ውሸቶች እስከማይመስሉ ድረስ ለረዥም ጊዜ ስለኖሩባቸው ውሸቶቹን የምር ያምኑባቸዋል፡፡ ከእነርሱ እምነቶች የተለየ ነገርን ስትናገሩ ግራ ይጋባሉ እናም ማንም ደግሞ ግራ እንዲገባው አይፈልግም፡፡ ውስጣዊ መነጋነግን ፣ ግራ መጋባትን በውስጣችሁ ትፈጥራላችሁ እናም ማንም ደግሞ በጥርጣሬ ውስጥ መሆንን አይፈልግም፡፡ እዚያ ግን ጥርጣሬ አለ፡፡ እውነትን አውቀው በነበር ምንም ፍርሃት አይኖርም ነበር፡፡ እነርሱ እውነትን አያውቁም፡፡ ብቻ ያምናሉ፡፡ በጥልቁ ነፍሣቸው ውስጥ ጥርጣሬ አለ፡፡ ስለዚህ ከእነርሱ በተቃርኖ የሚሄድ አንድ የሆነ በምትናገሩበት ጊዜ ጥርጣሬ ማንሰራራት ይጀምር እና ከላይ ቦታውን መያዝ ይጀምራል፡፡ እናም እነርሱ ደግሞ በጥርጣሬ ውስጥ መሆንን ይፈራሉ፡፡ እያንዳንዱ ሰው እርግጠኝነትን ይፈልጋል፡፡ ለምን? ምክንያቱም እርግጠኝነት በራስ መተማመንን ይሠጣችኋል፡፡ ጥርጣሬ እንድትንቀጠቀጡ ያደርጋችኋል፡፡

እናም እኔ ደግሞ ብዙ ጥርጣሬን በውስጣችሁ እየፈጠርኩኝ ነው - ምክንያቱም በራዕዬ ውስጥ ጥርጣሬ ውሸት የሆኑ እርግጠኝነቶቻችሁን ካላወደው በስተቀር እውነተኛውን እርግጠኝነት የመቀዳጀቱ ዕድል አይኖርም፡፡ እውነተኛው እርግጠኝነት ከዕምነት አይመነጭም፡፡ እርግጠኝነት የሚመጣው ከልምድ ነው ፤እርግጠኝነት የሚመነጨው በራሣችሁ ማወቅ ነው::

@Zephilosophy
@Zephilosophy



9.2k 0 62 51 62

ቁማርተኛው - ፓስካል

ሳንቲምን ወደ ላይ ብታፈናጥር፣ ሳንቲሙ ሰው ባለበት አልያም አንበሳ ገጽ ባለበት ይገለበጣል፡፡ እድሉም ሃምሳ ሃምሳ ነው፤ ሳንቲሙ ችግር ያለበት ወይም ጠማማ ካልሆነ በቀር። ሰው መረጥክ አንበሳ፤ ውጤቱ ላይ እኩል እድል ነው ያለህ:: የእግዚአብሔር ሃለወትስ? እግዚአብሔር ይኑር ወይም አይኑር እርግጠኛ ካልሆንክስ? በዚህ ሃሳብ መቋመር አለብህ? እግዚአብሔር የለም ብለህ ሕይወትህን እንዳሻህ ትመራለህ ወይስ በእግዚአብሔር መኖር አምነህ እንደሱ ፍቃድ ትኖራለህ? ብሌስ ፓስካል (1623-62) የተባለ ክርስቲያን ይህን ሃሳብ ተመራምሮበት ነበር፡፡

ፓስካል የአየር ግፊት መለኪያ የሆነውን ባሮ ሜትርን እና ሜካኒካል ካልኩሌተርን ፈልስፏል፡፡ ልክ እንደ ሳይንቲስትነቱ እና ፈላስፋነቱ ሁሉ፣ ፓስካል ግሩም የሂሳብ ሊቅ ነው፡፡ ከሂሳብ እሳቤዎቹ ውስጥም ይበልጥ የሚታወቀው በይሁንታ (probability) ሃተታዎቹ ነው፡፡ ፓስካል ፈላስፋ ብለን ከምንጠራው ይልቅ የስነ-መለኮት ጠቢብ ብንለው ይወዳል።

እናም ፓስካል በአመንክንዮ አስደግፎ በአምላክ መኖር ማመን እንዳለብን ያስረዳናል። ለእሱ በእግዚአብሔር ማመን የልብ ጉዳይ እንጂ የምክንያት ጉዳይ አይደለም፤ ምንም አይነት ማስረጃም ሊቀርብለት እንደማይችል ያስባል፡፡ እግዜርንም ማወቂያው መንገድ ልብ እንጂ ጭንቅላት አይደለም ይለናል።

እናም እግዜር አለ ወይም የለም በሚሉ ጥርጣሬዎች ሙግት ላይ የትኛው ጋ መቆም እንዳለብን የሚያሳይ አንድ ቁመራ ያሳየናል፡፡ ይህም ቁመራ ልክ እንደ ሳንቲሙ ሁሉ በእድል ላይ ይመሰረታል። አሪፍ ቆማሪ ከሆንክ፣ ሁሌም ቢሆን ከመቋመርህ በፊት ያሉህን እድሎች ትመረምራለህ፤ የሚያከስርህ ከሆነ አትገባበትም፡፡ እና በአምላክ መኖር ላይ እንዴት እንቋመር?
በአምላክ መኖር እርግጠኛ አይደለህም ብለን እናስብ፤ አሁን አማራጮች አሉህ።

ሕይወትህን አምላክ እንደሌለ እርግጠኛ ሆነህ መኖር ትችላለህ፤ እናም ልክ ከሆንክ እድሜ ልክህን ኃጢአት ሰራሁ አልስራሁ ሳትል እና ሳትጨነቅ ትኖራለህ፤ ቤተክርስቲያንም ሄደህ የሶስት ሰዓት ርዝማኔ ያለው ቅዳሴ ላይ የምታጠፋው ጊዜ አይኖርም፡፡ ሆኖም ይሄኛው ምርጫህ ልክ ካልሆነና በአምላክ ሳታምን ከሞትክ፣ ገነት የመግባት እድልህን ከማበላሸት በተጨማሪ ዘላለማዊ በሆነ እሳት ውስጥ ትማገዳለህ፡፡ በዚህ ምርጫህም የሚኖረው የመጨረሻ መጥፎ ነገር ሲዖል መግባት ይሆናል።

በሁለተኛው ምርጫህ፤ አምላክ እንዳለ አምነህ መኖር ትችላለህ። ትጸልያለህ፣ ቤተ-ክርስቲያን ትሄዳለህ፣ መጽሐፍ ቅዱስን ታነባለህ ወዘተ። እናም እድልህ ሆኖ አምላክ ከኖረ ዘላለማዊ የሆነ ሕይወትን ትሸለማለህ። ነገር ግን ባይሳካልህ እና አምላክ ባይኖር፣ የምትቃጠልበትም ሆነ ቅጣት የምትቀበልበት ሁናቴ አይኖርም፡፡ ከሞትክም ተሳስቼ ነበር ለማለት የሚሆን ጊዜ እንኳ አይኖርህም᎓᎓ ፓስካል ይህን ሃሳቡን እንዲህ ይለዋል “ካሸነፍክ ሁሉንም ታገኛለህ ፤ ከተሸነፍክ ሁሉንም ታጣለህ፡፡''

ፓስካል በአምላክ መኖር ካመንክ እነዚያን ጣፋጭ ኃጢአቶችን እንደምታጣቸው አልጠፋውም፡፡ ሆኖም ደስታን በሃብት እና በዝና ብቻ ማነው ይገኛል ያለው ታማኝ፣ ቅን፣ ትሁት አመስጋኝ፣ ለጋስ፣ መልካም ባልንጀራ እና እውነት በመናገር ውስጥም ደስታ ይገኛል፡፡

እናም የፓስካልን ቁመራ ስናጠቃልለው፤ በአንድ በኩል ያሉት ዘላለማዊ ሕይወት ወይም ገነትን ያገኛሉ፤ በሌላኛው በኩል ያሉት ደግሞ ዘላለማዊ ቅጣት ወይም ሲኦልን ያገኛሉ፡፡ የትኛው ይሻላል? የትኛውንስ ትመርጣለህ?
ፓስካልም፤ “ፈጣሪ የለም ብዬ ሲኦል ከምገባ፣ አለ ብዬ ባይኖር ይሻላል” ይለናል።

እናም ጥሩ ምክንያታዊ እና ጥሩ ቆማሪ ከሆንክ ምርጫህ አምላክ አለ ይሆናል ባይኖርም ምንም አትሆንም፤ ከኖረም ዘላለማዊ ሽልማት ይጠብቅሃል።

ሆኖም ይህ የፓስካል ቁመራ ልክ ነው? ምናልባትም ምርጫህን በአምላክ መኖር ላይ አደረግክ እንበል፤ ሆኖም ውስጥህ ባያምንበት ምን ይፈጠራል? አሁንም ገነት ትገባለህ? ገነትን ለመውረስ ምን ያህል እምነት በአምላክህ ላይ ሊኖርህ ይገባል? ፓስካል ይህን ሲመልስ፣ አንዴ በአምላክ መኖር ካመንክ በኋላ ወደ ትክክለኛው መንገድ ለመግባት መሞከር ይኖርብሃል። ቤተ-ክርስቲያን ሂድ፣ ጸልይ፣ አትስረቅ፣ አትዋሽ፣ ጠበል ተጠመቅ፣ የኃይማኖት አባቶች የሚሉህን ተከተል ወዘተ...። እናም እውነተኛዋን መንገድ ፍለጋ ስትኳትን፣ እምነትህ እየጠነከረ ይመጣል፤ ወደ አምላክህም ትቀርባለህ። ይህም ዘላለማዊ ሽልማትን የማግኛ እና ከቅጣት የመሸሺያ መንገድ ነው፡፡

ሁሉም ሰው በፓስካል እሳቤ ይስማማል ማለት አንችልም፤ ከፓስካል ቁመራ ካሉት ችግሮች አንዱ አምላክ ቢኖርም ምናልባትም አንተ የእሱ ሰው ላትሆን ትችላለህ። የሚኖረው አምላክስ የማን ነው? የክርስቲያን፣ የሙስሊም፣ የአይሁድ፣ የቡድሂስቶች ወይስ የማን? እንዲያውም የተሳሰተ አምላክን ስታመልክ ከርመህ ዘላለማዊ ሕይወትን ስጠኝ ብትለው፣ ይበልጥ የሚናደድብህ አምላክ ቢሆንስ? ወይም ደሞ ቢኖር እንኳ ሰዎች እንደሚሉት ስለተሳሳትክ ብቻ ሲኦል ውስጥ የሚዶልህ አምላክ ላይሆን ይችላል፡፡ የፓስካል ቁመራ መነሾ የእርሱ አምላክ ልክ እንዲሆን ከመመኘት ይነሳል፤ ሆኖም ለዚህ መልስ አይሰጠንም፡፡ አምነህም ልክ ባልሆነ አምላክ ካመንክ ሲኦል ትገባለህ፤ ወይም ያንተ አምላክ ውሸትን የሚጠላ ከሆነ እና አንድ ቀን ስቶህ ብትዋሽ ሲኦል ትገባለህ፡፡ ፓስካል እንዳሰበው ቁመራው ቀላል አይደለም፡፡

መፅሀፍ- የፍልስፍና ማዕድ
ደራሲ - ሰለሞን
@zephilosophy

11k 0 48 35 123

ተመስጦ (meditation)

ብዙ ሰው ከራሱ ጋር የግል ጊዜ ስለማይወስድ ሂወቱ የተረጋጋ አይደለም!


የሰው ልጅ ዕለት ተዕለት በሚኖረው ኑሮ ውስጥ ሲደክመው ዕረፍት ማድረግን ፤ የሰውነት ክፍሎቹን ለማፍታታት መንጠራራትንና ማፍታታትን ፤ የድብርት ስሜት ሲሰማው ማፋሸግንና ሲጨንቀው ስሜቱን ለማረጋጋት ዓየር በደንብ ወደ ውስጥ አስገብቶና ወደ ውጭ በረጅሙ መተንፈስን በተፈጥሮ የታደላቸው ገጸ በረከቶች ናቸው፡፡ ከፍ ሲልም መንፈሱን ወደ ትልቁ ማማ ሰማየ ሰማይ በመውሰድና በመመሰጥ አእምሮውንና መንፈሱን ያድስበታል፡፡

ተመስጦ ሰዎች ከጥንት ጊዜ ጀምሮ አእምሯቸውንና ህይወታቸውን የሚቆጣጠሩበት እንዲሁም እራሳቸውን ፈልገው የሚያገኙበት የአእምሮ ፤የአካልና የመንፈስ እንቅስቃሴ ነው፡፡ በተጨማሪም ተመስጦ ሰዎች አእምሯቸውን እንደ ኤሌክትሪክ ማብሪያና ማጥፊያ ባሻቸው ሰዓት ማሰብ የሚፈልጉትን እንዲያስቡ ማሰብ የማይፈልጉትን ደግሞ ከአእምሮአቸው ውስጥ በቀላሉ የሚያጠፉበት ተፈጥሯዊ የአእምሮ ቁልፍ ነው፡፡

በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ በዓለም ላይ በሚገኙ ባህሎች ውስጥ ተመስጦና መመሰጥ አለ፡፡ ነገር ግን ተመስጦ በተደራጀና በተዋቀረ መልኩ የተጀመረው በሂንዱ ሸለቆ ውስጥ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ5000 እስከ 3500 ዓመተ ዓለም አካባቢ መሆንኑን የአርኪዮሎጂ ጥናቶችና ግኝቶች ያስረዳሉ፡፡ በሂንዱ ሸለቆች የተገኙ የግርግዳ ላይ ስዕሎች ከላይ ከተጠቀሰው ዓመተ ዓለም ጀምሮ ሰዎች ቁጭ ብለው እግራቸውን አመሳቀለው ተመስጦን ሲያከናውኑ እንደነበር ማስረጃዎች ያስረዳሉ፡፡ እንዲሁም በህንድ መጻሕፍት ውስጥ ከ3000 ዓመታት በፊት የተመስጦና መመሰጥ ዘዴዎች ተመዝግበው እንደሚገኙ የታሪክ ድርሳናት ያሳያሉ፡፡

ሁሉም ሃይማኖታዊ ክንዋኔዎች በውስጣቻው ተመስጦን ይዘው ይገኛሉ፡፡ በሃይማኖታዊ ስርዓት ምዕመናን ሲጸልዩ ፤ ሲያመሰግኑና ሲሰግዱ ወደ አምላካቸው ይመሰጣሉ፡፡ ነገር ግን አብዛኛውን ጊዜ ስለተመስጦና መመሰጥ ሲነሳ ሰዎች ወደ አእምሮአቸው የሚመጣው የቡድሃ ወይም የሂንዱ እምነት ነው፡፡ ምንም እንኳን እነኚህ ሃይማኖቶች በሃይማኖታዊ ክንዋኔአቸው ለተመስጦ ትልቅ ትኩረት ቢሰጡም በዘመናዊው እይታ ተመስጦና መመሰጥ ከየትኛውም ሃይማኖት ጋር አይያያዝም አልያም ዘውትር መመሰጥንና ተመስጦን ማከናወን የቡድሃ ወይም የሂንዱ እምነት ተከታይ መሆን ማለት አይደለም፡፡ ለመነሻ ያህል ይህን ካልን የመመሰጥና የተመስጦን ጥቅም ከብዙ በጥቂቱ እንመለከታለን

1.ውጥረትን ይቀንሳል

መመሰጥና ተመስጦ ከማንኛውም አካላዊ እንቅስቃሴ በላይ ውጥረትን የመቀነስ አቅሙ ከፍተኛ ነው፡፡ መመሰጥ ውጥረትን መቀነስ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ በነርቭ ስርዓት ላይ ውጥረትን የሚያመጣውን ኮርቲሶል የሚባለውን ኬሚካል በመቀነስ በምትኩ ሰዎች ጥሩ ስሜት እንዲሰማቸው የሚያደርገውን ሴሮቶኒን የተባለውን ኬሚካል አንጎላችን እንዲያመነጭ ያነሳሳል፡፡

2.ጤናን ያሻሽላል

ተመስጦ የበሽታ መከላከል ኃይልን በማደርጀት፤ የደም ግፊትና የኮለስትሮል መጠንን  በመቀነስ ጤናን ያሻሽላል፡፡ በተለይ በማይድን ጽኑ ህመም የሚሰቃዩ ሰዎች ህመማቸውን ለማስታገስና ለማገገም ከተመስጦ ብዙ ጥቅም ያገኛሉ፡፡ በእርግጥ ተመስጦን ለመጠቀም የግድ ጽኑ ህሙማን መሆን አይጠበቅብንም ከጉንፋንና እራስ ምታት ለመታቀብና ለመዳን ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡

3.ለእንቅልፍ

በስራ ጫና ብዛትና በውጥረት ምክንያት አንዳንድ ጊዜ ሰዎች እንቅልፍ ላይዛቸውና በቶሎ በመተኛት ከድካማቸው ፋታ ለማግኘት ይቸገራሉ፡፡ ይህ በሚሆንበት ወቅት መመሰጥት ችግራቸውን  ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ በቀላል እንዲፈቱ ይረዳቸዋል፡፡

4.እርጅናን ይከላከላል

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት አዘውትረው የሚመሰጡ ሰዎች ከማይመሰጡት ጋር ሲወዳደሩ ቀናቸውን በተመስጦ የሚያሳልፉ ሰዎች ከዕድሜቸው አንጻር ቶሎ የማያረጁና ረጅም ዕድሜ የሚኖሩ ሆነው ተገኝተው፡፡ ይህም የሚሆንበት ምክንያት መመሰጥና ተመስጦ እርጅና የሚያስከትሉ ቲሹዎችንና በሽታዎችን መግታት በመቻሉ ነው፡፡

5. ለውስጠ ስሜት መረጋጋትና አወንታዊ አስተሳሰብ

መመሰጥ ጭንቀት ውስጥ ለገቡ፤ በቶሎ ለሚናደዱ፤ ስሜታቸውን መቆጣጠር ለሚቸገሩና ድብርት ለሚያጠቃቸው ሰዎች እንደ ተፈጥሯዊ መከላከያ መድኃኒት ተደርጎ በባለሙያዎች ይታዘዝላቸዋል፡፡ በተጨማሪም መመሰጥ የአሉታዊ አስተሳሰቦችንና ስሜቶችን ከሰዎች አእምሮና አካላት ውስጥ አጥርቶ በማውጣት በአወንታዊ አስተሳሰብ እንዲገነቡ ትልቅ ሚና ይጫወታል፡፡ በአጠቃላይ ከጭንቀትና ተያያዥ ጉዳዮች ባሻገር ተመስጦን የሚያዘወትሩ ሰዎች ጥሩ ስሜት የሚሰማቸውና ደስተኞች ናቸው፡፡

ለተመስጦ የሚረዱ ጥቆማዎች

.ዘውትርና በተመሳሳይ ሰዓት መመሰጥን ልምድ ማድረግ ይመከራል

.ከመመሰጥ በፊት የማነቃቃት ባህሪይ ያላቸውን ትኩስ ነገሮች አለመውሰድ

.ከምግብ በኋላ አለመመሰጥና በቀን ውስጥ ሙሉ ኃይል የለኝም ብለው በሚያስቡበት ሰዓት መመሰጥ

.መመሰጥ የሚፈልጉበትን ስፍራ ማዘጋጀትና በቂ ዓየር እንዲገባው መስኮት መክፈት

.በጣም ደማቅ ብርሃን የሌለውን ስፋራ መምረጥና ሰፋ ያለ ልብስ መልበስ

.ጸጥ ያለ አካባቢን መምረጥና በተመስጦ ጊዜ ሊረብሹ የሚችሉ ነገሮችን እንደ ስልክ ፤ ሬዲዮ ፤ ቴሌቪዥንና የመሳሰሉ ነገሮን ድምጽ ማጥፋት

.በረጅሙ ዓየር ወደ ውስጥ ማስገባት

.ያስገቡትን ዓየር ለጥቂት ሰከንዶች ሳይተነፍሱ ማቆየት

.ከዚያም በረጅሙ መተንፈስ

.በሚተነፍሱበት ወቅት ለሚሰማዎት ስሜት ትኩረት መስጠት፤ ዓየር በአፍንጫ ቀዳዳዎ ሲገባ ፤ ዓየሩን ለተወሰኑ ሰከንዶች ሲይዙት በመላ አካላቶ እየተሰራጨ እንደሆነና ሰውነቶን አዝናንቶ በአፍዎ እንደሚወጣ ማሰብ በቀላሉ የተረጋጋ ስሜትንና መዝናናትን አእምሮአችንና አካላችን እንዲሰማው ያደርጋል፡፡

@Zephilosophy
@Zephilosophy


#Moral_Philosophy
በዚህ ዓለም ላይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ጥሩ የሆነ ነገር ምንድን ነው?
___
#Repost

በሥነ
ምግባር የፍልስፍና ታሪክ ውስጥ እንደ አብሪ ኮኮብ ሆነው ከሚታዩ ፈላስፋዎች መካከል አንዱ ጀርመናዊው ፈላስፋ ኢማኑኤል ካንት ነው። በዚህ የፍልስፍና ዘውግ ውስጥ "ደስታ" እና "ጥቅም" ለረጅም ጊዜ የህልዮቱ ማንፀሪያዎች ሆነው አገልግለዋል።

ካንት ግን በ18ኛው ክ/ዘ መጨረሻ ላይ አዲስ የሥነ ምግባር ማንፀሪያ ይዞ መጣ። ይሄንንም ማንፀሪያ ለማሳየት በቅድሚያ አንድ ወሳኝ የሥነ ምግባር ጥያቄ ያነሳል፤ እንዲህ የሚል፦

"በዚህ ምድር ላይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ (ያለምንም Qualification) ጥሩ የሆነ ነገር ምንድን ነው?"

እስቲ እንገምት መልሱ ምን ሊሆን ይችላል?

#ገንዘብ!? አይደለም፤ ገንዘብ ጥሩ የሚሆነው ለጥሩ ነገር ስናውለው እንጂ ገንዘብ በራሱ በተፈጥሮው ጥሩነት የለውም፡፡

#ዕውቀት!? ዕውቀትም አይደለም፤ እውቀት ጥሩ የሚሆነው መልካም ሰው ሲያገኝ ነው፡፡

#ጉብዝና (Courage)!? እሱም አይደለም፤ ጉብዝና ጥሩ የሚሆነው ለጥሩ ዓላማ ሲሆን ነው፡፡ ለምሳሌ፣ ሂትለር ጎበዝ (Couragous) ነው፡፡ ሆኖም ግን፣ የእሱ ጉብዝና መጥፎ ጉብዝና ነው፡፡

እና ታዲያ ምንድን ነው? ለካንት መልሱ ቀላል ነው - በዚህ ዓለም ላይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በራሱ መልካም የሆነ ነገር አንድ ብቻ ነው፤ እሱም "ቅንነት/Good will" ነው፡፡ ዕውቀት፣ ገንዘብና ጉብዝና ቅንነት ላይ ካላረፉ አደገኛ ይሆናሉ፡፡

ይሄም ማለት በካንት የሥነምግባር አስተምህሮ
(Deontological Ethics) መሰረት አንድ ነገር ጥሩነቱ የሚለካው በውጤቱ (ጥቅም ወይም ደስታ ስለሚሰጥ) ሳይሆን በዓላማው (በሞቲቩ) ነው፡፡ እስቲ አንድ ምሳሌ እናንሳ፦

#ለምሳሌ፣ ኤልሳ የምትባል ልጅ ዋና እየተለማመደች እያለች ውሃ ውስጥ ስትሰምጥ ሄለን አየቻት፡፡ ወዲያውም ሄለን የኤልሳን ህይወት ለማዳን ውሃው ውስጥ ዘላ ገባች፡፡ ውጤቱ ግን በጣም የሚያሳዝን ሆነ ― ኤልሳ በሄለን እጅ ላይ ሞተች፡፡ ይሄንን የሄለንን ተግባር በምንድን ነው የምንመዝነው/ የምንዳኘው?

* በውጤቱ ይሆን?! ውጤቱማ ሄለንን ወንጀለኛ ያደርጋታል፡፡

* በዓላማው (በሄለን ሞቲቭ) ማለትም "ነፍስ የማዳን" ዓላማ ይሆን?! ይሄ ጥሩ መለኪያ ይመስላል፡፡ ሆኖም ግን፣ በዚህ የሄለን ዓላማ ላይ ራሱ ጥያቄዎች ይነሳሉ፦

የሄለን "ነፍስ የማዳን" ዓላማ (motive) መነሻው ምንድን ነው?! ለካንት ወሳኙ ጥያቄ ይሄ ነው፡፡ የአንድን ድርጊት ጥሩነትና መጥፎነት የምንለካው በውጤቱ ሳይሆን በሐሳቡ/ በዓላማው ቢሆንም፣ የዓላማውስ መነሻ ምንድን ነው?! የሚለው ጥያቄ በጣም ወሳኝ ነው፡፡ ስለዚህ፣ የሄለን "ነፍስ የማዳን" ዓላማ (motive) መነሻው ምንድን ነው?! አራት መላምቶችን እናስቀምጥ፦

* የሄለን "ነፍስ የማዳን" ዓላማ ኤልሳን ስለምታውቃት (የጎረቤት ልጅ ስለሆነች ወይም የብሄሯ ልጅ ስለሆነች) ከሆነ፣ የሄለን ተግባር መልካም ሥራ አያስብለውም፤ ያ "የሞራል ተግባር" አያስብለውም፡፡ ምክንያቱም፣ የሞቲቩ መነሻ Inclination ነው፡፡

* የሄለን "ነፍስ የማዳን" ዓላማ መነሻው "ማንኛውም ሰው በሞት አፋፍ ላይ ያለን ሌላ ሰው የመርዳትና የማዳን ግዴታ አለበት" የሚለውን የመንግስት ህግ ለማክበር ከሆነ፣ አሁንም የሄለን ተግባር መልካም ሥራ አያስብለውም፡፡ ምክንያቱም፣ የሞቲቩ መነሻ ውጫዊ (in accordance with Duty) ነው፡፡

የሄለን "ነፍስ የማዳን" ዓላማ መነሻው "ባልንጀራህን እንደራስህ አድርገህ ውደድ" የሚለውን ሃይማኖታዊ ህግ ለማክበርና ገነት ለመግባት ከሆነ፣ አሁንም የሄለን ተግባር መልካም ሥራ አያስብለውም፡፡ ምክንያቱም፣ የሞቲቩ መነሻ አሁንም ውጫዊና ቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

የሄለን "ነፍስ የማዳን" ዓላማ መነሻው "በሞት አፋፍ ላይ ያለን ሰው የመርዳትና የማዳን ውስጣዊ የሞራል ግዴታ አለብኝ" ከሚል ከሆነ ትክክል ነች፤ ይሄም ሄለንን "መልካም ሰው" ያስብላታል፡፡ ምክንያቱም፣ የሞቲቩ መነሻ ምንም ዓይነት ቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመረኮዘ ንፁህ ውስጣዊ የቅንነት ግዴታ (motive from Duty/the moral law within) ስለሆነ፡፡

ካንት በዚህ ቅንነት (Good Will) ላይ በተመሰረተው ውስጣዊ የሞራል ግዴታ አብዝቶ ይመሰጣል፡፡ ለዚህም ነው ካንት እንዲህ በሚል ንግግሩ ይበልጥ የሚታወቀው፦

"ሁልጊዜ በህይወቴ የሚያስደምሙኝ ሁለት ነገሮች አሉ፤ እነሱም ከላይ በከዋክብት የተንቆጠቆጠው ሰማይና በውስጤ ደግሞ ያለው የሞራል ህግ the moral law within me!! ናቸው።"

@Zephilosophy
@Zephilosophy

9k 0 77 5 111

ራስን ከፍ አድርጎ የማየት ኢጎ

በህይወት ስቃይ ና ችግሮች ውስጥ  ስንሆን  በችግሮቻችን የበለጠ አቅመቢስነት የሚሰማን እንሆናለን፡፡ በዚህም ከእነዚያ ችግሮች ለማምለጥና ያንን ለማካካስ ራሳችንን ከፍ አድርጎ ማየት እናዳብራለን፡፡ ይህ ራስን ከፍ አድርጎ ማየት ከእነዚህ በአንዱ መንገድ ይሰራል፡፡

1. እኔ በጣም አሪፍ ነኝ ሌሎቻችሁ ግን ደባሪዎች ናችሁ ስለዚህ የተለየ እንክብካቤ ያስፈልገኛል፡፡
2. እኔ የምረባ አይደለሁም ሌሎቻችሁ
ግን አሪፎች ስለሆናችሁ የተለየ እንክብካቤ ያስፈልገኛል የሚሉ ናቸው፡፡

እነዚህ ሀሳቦች በውጪ ሲታዩ ተቃራኒ አስተሳሰብ፣ ውስጡ ግን ተመሳሳይ ራስ ወዳድነት ያለባቸው ናቸው፡፡ በእርግጥ ራሳቸውን ከፍ አድርገው የሚያዩ ሰዎች በሁለቱ መካከል ሲዋዥቁ ይታያሉ፡፡ ወይ እነርሱ ከአለም ሁሉ በላይ ናቸው አለዚያም ደግሞ አለም ሁሉ ከእነርሱ በላይ ነው፡፡ ይህም መዋዠቅ የሚከሰተው የሆነ ቀን ወይም ያለባቸውን ሱስ እያስታገሱ ባሉባት ቅጽበት ይሆናል፡፡

ብዙ ሰዎች ከንቱ በሆነው ለራሳቸው በሚሰጡት ከፍተኛ ክብር የተነሳ በራሳቸው ፍቅር የወደቁ እንዲሁም በጣም ለፍላፊ በመሆናቸው ከሌላው ሰው በቀላሉ መለየት ይችላሉ።በቀላሉ መለየት የማይችሉት ለራሳቸው ከፍተኛ ክብር የሚሰጡ ሆነው ነገር ግን ዝቅተኛ እንደሆኑና ለአለም የማይጠቅሙ እንደሆኑ የሚሰማቸውን ነው፡፡

በሕይወት ውስጥ ሁሉም ነገር አንተን ለመጉዳት የሚደረግና ያለማቋረጥ ተጠቂ የሚያደርግህ አድርጎ መተርጎም ልክ ተቃራኒውን እንደማድረግ ያህል ራስ ወዳድነት ነው፡፡ አንደኛው ምንም አይነት ችግር የሌለበት ሆኖ አንደኛው ደግሞ ሊቀረፍ የማይችል ችግር አለበት የሚል እምነት ማዳበር የዚያኑ ያህል በከፍተኛ ደረጃ ከንቱ የሆነ ራስን ከፍ አድርጎ የማየት ነገር ይፈልጋል፡፡ እውነታው በሕይወት ውስጥ የግል ችግር የሚባል ነገር አለመኖሩ ነው፡፡ የሆነ ችግር ካለብህ፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሌሎች ሰዎችም ከዚህ ቀደም የዚያ አይነት ችግር ነበረባቸው ወይም አሁን አለባቸው አለበለዚያም ወደፊት ይኖርባቸዋል፡፡ የዚያ ችግር ተጠቂዎች ምናልባትም አንተ የምታውቃቸው ሰዎች ሊሆኑም ይችላሉ፡፡ ይህ መሆኑ ግን ችግሩን አያሳንሰውም ወይም የሚጎዳ የመሆኑን መጠን አይቀንሰውም፡፡ ይህ ማለት በአንዳንድ ሁኔታዎች ተጠቂ ላትሆን ትችላለህ ማለትም ሳይሆን ይህ ማለት አንተ የተለየህ አይደለህም ማለት ነው፡፡

በአብዛኛው ችግሮችን ለመፍታት የመጀመሪያውና በጣም አስፈላጊ የሆነው እርምጃ፣ አንተና የአንተ ችግሮች በችግሮቹ ከባድነት ወይም በሚያስከትሉት ስቃይ ተጠቃሚዎች አለመሆናችሁን መረዳት ነው፡፡

ራስን ከፍ አድርጎ የማየት ችግር

አንድ ጊዜ ሰዎች በዙሪያቸው የሚከናወነው ሁሉ ራስን ትልቅ አድርጎ የሚያሳይ እንደሆነ ያለማቋረጥ እንዲገምቱ የሚያደርግ አስተሳሰብ ካዳበሩ፣ እነርሱን ከዚያ ውስጥ ሰብሮ ማውጣት በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ እነርሱን ለማስረዳት የሚደረግ ሙከራ ሁሉ ለእነርሱ የእነርሱን ታላቅነት፣ ምን ያህል ጎበዝ፣ ተሰጥኦ ያላቸው፣ መልከ መልካሞችና ስኬታማ መሆናቸውን መሸከም ባለመቻል የሚመጣ ጥቃት ተደርጎ ይታያል፡፡

ራሳቸውን ከፍ ያሉ እንደሆኑ የሚሰማቸው ሰዎች፣ በሕይወት ውስጥ ያሉት ሁኔታዎች ሁሉ ለእነርሱ ታላቅነት ወይ አድናቆት ወይ ጥቃት የተሰሩ ናቸው ብለው ያምናሉ፡፡ የሆነ ጥሩ ነገር ካጋጠማቸው እነርሱ በሰሩት አሪፍ ነገር ምክንያት ነው፡፡ መጥፎ ነገር ካጋጠማቸው የሆነ ሰው ቀንቶ ሊጎዳቸው ሞክሮ ነው፡፡ ራስን ከፍ አድርጎ ማየት ዘላቂነት የለውም፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች የእነርሱን የበላይነት ስሜት በሚያጠናክር በየትኛውም ነገር ራሳቸውን ያሞኛሉ፡፡ ምንም ያህል ዋጋ ቢያስከፍልም፣ አንዳንድ ጊዜ በዙሪያቸው ላሉ ሰዎች አካላዊና ስሜታዊ ጉዳት የሚያስከትል ቢሆንም የአእምሮ እይታቸውን ይከላከላሉ፡፡

ለራሳቸው ከንቱ የሆነ ከፍተኛ ግምት የሚሰጡ ሰዎች  ለራሳቸው ችግሮች በግልፅና በታማኝነት እውቅና መስጠት ስለማይችሉ ህይወታቸውን ዘላቂ ወይም ትርጉም ባለው ሁኔታ ማሻሻል አይችሉም፡፡ እንደዚህ ያሉ ከፍተኛ ክህደት እያሳደዱና ታላላቅ የክህደት ደረጃዎች እያከማቹ ለመኖር የተተው ናቸው፡፡

ግን በመጨረሻ እውነቱ ይወጣና የተቀበሩት ችግሮች ሁሉ እንደገና ራሳቸውን ግልፅ ሲያደረጉ ከባድ የህይወት ምስቅልቅል ውስጥ ይገባሉ።

📚- The subtle art of not giving a f*ck
✍️ - Mark manson

@Zephilosophy


ደስታ

ምንጭ ፦ ከፍስሀ ጋር መወለድ (ኦሾ)
ተርጓሚ፦ በዩሐንስ አዳም

መደሰት አስቸጋሪ የሆነው ደስታ መጥፋት እንዳለበት ስለሚታሰብ ነው፡፡ መደሰት የሚቻለው ራሳችሁን ሳትሆኑ ነው፡፡ አናንተ እና ደስታ በአንድ ላይ ልትኖሩ አትችሉም፡፡ ደስታ እዚያ ሲኖር አናንተ ቀሪ ናችሁ፡፡ አናንተ እዚያ ስትኖኑ ደስታ ቀሪ ይሆናል፡፡ ደስታ እና አናንተ ልክ እንደ ብርሃን እና ጨለማ ናችሁ፡፡ ሁለታችሁም ተመሳሳይ ቦታ ላይ መከሰት አችትሉም፡፡

በዚህ ምክንያት የተነሳ መደሰት አስቸጋሪ ነው፡፡ ደስታ ቀላል አይደለም፤ ምክንያቱም መሞት አስቸጋሪ ነው፡፡ እናም በእያንዳንዷ ቅፅበት እንዴት መሞት እንዳለባቸው የሚያውቁ ብቻ ናቸው እንዴት መደሰት እንዳለባቸው የሚያውቁት፡፡ ብዙ የመሞት ብቃት በኖራችሁ ቁጥር ደስታችሁ የጠለቀ፣ የፍስሃችሁ ነበልባልም በጣም ታላቅ ይሆናል፡፡

መደሰት አስቸጋሪ ነው ፦ ምክንያቱም መከረኛ ሆናችሁ እንድትቀሩ የሚያደርጉ በጣም በርካታ ኢንቨስትመንቶች አሉ ይህንን ሁኔታ ካላያችሁት በስተቀር ለመደሰት መሞከራችሁን መቀጠል ብትችሉም ቅሉ በጭራሽ ደስተኛ አትሆኑም፡፡ እነዚህ በመከራችሁ ውስጥ የሚያገኙት ኢንቨስትመንቶቻችሁ መወገድ አለባቸው፡፡ እናም እያንዳንዱ ሰው ከልጅነቱ ጀምሮ መከራ ሊከፍል የሚችል መሆኑን ተምሯል፡፡ አናንተ ደስተኛ እና ጤነኛ ከሆናችሁ ማንም ስለ አናንተ ደንታ የለውም፡፡ ጥሞናን አታገኙም፤ እናም ጥሞና የእኔነት ዋናው እስትንፋስ ነው፡፡ ልክ አካል ኦክስጂን እንደሚያስፈልገው እኔነት ጥሞና /ትኩረት/ ያስፈልገዋል፡፡

ጤነኛ ፣ ደስተኛ ስትሆኑ ሰዎች ጥሞና አይቸሩዋችሁም፡፡ ጥሞና አያስፈልግም፡፡ ዳሩ ስትታመሙ፣ መከረኛ ስትሆኑ፣ ስታለቅሱ፣ ስታስቡ ግን ሁሉም ቤተሰብ ወደ ፍላጎቶቻችሁ ትኩረትን ይሰጣሉ፡፡ ልክ ድንገተኛ አደጋ እንደ ደረሰባችሁ ስራቸውን ያቆማሉ፡፡ እናት ከማዕድ ቤት እየሮጠች ትመጣለች ፤ አባትም ጋዜጣውን ያሽቀነጥራል፡፡ እናም ሁሉም ሰው ትኩረቱን ከእናንተ ጋር ያደርጋል፡፡ ይህ ሁኔታ ታላቅ የእኔነት እርካታን ያጎናፅፋል፡፡ እናም ቀስበቀስ የእኔነትን መንገድ ትማራላችሁ፡፡ መከረኛ ሆኖ መቅረት... እናም ሰዎች ለእናንተ ጥሞና ይሰጣሉ፡፡ መከረኛ ሆናችሁ ቅሩ እናም እነሱ ለእናንተ ያዝኑላችኃል፤ ደስተኛ ስትሆኑ ማንም ያንን ስሜታችሁን አይካፈልም፡፡ ለዚያ ነው ሰዎች ለባህታዊዎች ትኩረትን የሚሰጡት፡፡ አንድ ሰው ይፆማል እናም ሰዎች ተመልከቱት እንዴት ያለ ቅዱስ ነው" ይላሉ፡፡

ክብረ በዓልን ብታከብሩ ማንም ያንን ስሜት ከአናንተ ጋር አይቋደስም:: ከአንድ ሰው ጋር በፍቅር ውስጥ ብትሆኑ ማን ነው ከአናንተ ጋር ስሜታችሁን የሚጋራው? በተቃራኒው ሰዎች በጣም ቀናተኛ ይሆናሉ፡፡ አናንተ ተወዳዳሪ ሆናችኃል፡፡ እነዚህ ሰዎች አንድ ዓይነት ሰውን ለራሳቸው ይፈልጋሉ፤ አናንተ ጠላት ናችሁ።

እኛ የተወለድነው ከፍስሐ ጋር ነው፤ ፍስሐ የኛ ዋናው ፍጥረት ነው፤ ደስተኛ ለመሆን ምንም ነገር አያስፈልግም፤ አንድ ሰው ዝም ብሎ ብቻውን በመቀመጥ ደስተኛ መሆን ይችላል፡፡ ደስታ ተፈጥሯዊ ሲሆን - መከራ ደግሞ ተፈጥሮዊ ያልሆነ ነው:: ግን መከራ ትርፋማ ያደርጋል፡፡ እናም ደስታ ዓላማ - ቢስ ነው፡፡ ማንኛውንም ትርፍ አያመጣላችሁም፡፡

ስለሆነም አንድ ሰው መወሰን መቻል አለበት፡፡ ደስተኛ መሆንን ከፈለጋችሁ ተራ ሰው መሆን መቻል አለባችሁ፡፡ ይህ ነው እንግዲህ ውሳኔው፡፡ ደስተኛ መሆን ከፈለጋችሁ ማንንም ያልሆናችሁ መሆን ይኖርባችኃል፡፡ ምክንያቱም እንዳችም ጥሞና አታገኙም፡፡ በተቃራኒው ሰዎች ቅናት ይሰማቸዋል። ሰዎች ከእናንተ
በተቃራኒ ውስጥ ይሆናሉ፡፡ ሰዎች አይወዱአችሁም፡፡ ሰዎች የሚወዱአችሁ በመከራ ውስጥ ከሆናችሁ ብቻ ነው:: ከዚያም ያዝኑላችኃል፤ ችግራችሁን ይካፈሏችኃል፤ በሁኔታው የእናንተ እኔነት ይረካል፤ እናም የእነርሱም እኔነት ጨምሮ ይረካል፡፡ ከአንድ ሰው ሀዘኑን ሲጋሩ እነሱ የበላይ እናም አናንተ የበታች ናችሁ፡፡ እነርሱ ወሳኝ እጆች ናቸው፡፡ የመተዛዘን የበላይነት ጨዋታ ደስ ያሰኛቸዋል፡፡

ዝም ብላችሁ ታዘቡ-አናንተም ራሳችሁ እነዚህን ታደርጋላችሁ፡፡ አንድ ሰው የእሾህ አልጋ ላይ ቢተኛ ሰውየው ለሰው ልጅ የተወሰነ ደስታን ይዞ የመጣ ይመስል፣ ታላቅ ድርጊትን የፈጸመ ይመስል- ወዲያውኑ ትሰግዱለታላችሁ፡፡ እሱ እኮ ዝም ብሎ ራሱን ማሰቃየት የሚወድ ሰው ነው፡፡ ነገር ግን ትወዱታላችሁ ፤ ታከብሩታላችሁም፤ አክብሮታችሁ ግን ጤናማ ያልሆነ ነው፡፡ ይህ ሰው የአናንተን ጥሞና ይፈልጋል፡፡ እናም ይህ መንገድ ደግሞ የአናንተን ጥሞናን ለማግኘት በጣም ቀላሉ መንገድ ነው፡፡ የእርሱ እኔነት ይሟላል፤ ይረካል፡፡ ስለዚህ በእነዚያ እሾሆች ላይ ለመተኛት እና ለመሰቃየት ዝግጁ ነው፡፡

ይህ ነገር ሁሉም ቦታ በትንሽም ሆነ በትልቅ መጠን እየተከሰተ ነው፡፡ ልብ በሉት! ይህ በጣም ጥንታዊ ወጥመድ ነው፡፡ እናም ከዚያ በኋላ መደሰት ትችላላችሁ፡፡ ከደስታ በቀር ምንም የለም፤ ማንንም ላለመሆን ዝግጁ ከሆናችሁ፣ የሌሎችን ጥሞና የማትሹ ከሆነ ከናካቴው ምንም ዓይነት ችግር አይኖርም ደስተኛ መሆን፣ ዘና ማለት ትችላላችሁ፡፡ በጣም ትናንሽ ነገሮች የሚቻለውን ታላቅ ፍስሐ ሊሰጡአችሁ ይችላሉ፡፡

@Zephilosophy
@Zephilosophy


ኢጎ እና የአሁኑ ቅፅበት

የአሁኑ ቅፅበት ወዳጅህ አድርገህ መወሰን የኢጎ ፍፃሜ ነው። ኢጎ በአሁኑ ቅፅበት ማለትም ከህይወት ጋር አንድ መሆን አይችልም። ምክንያቱም የኢጎ ተፈጥሮ እራሱ አሁንን ቸል የማለት፣ የመቃወምና፣ ዋጋ ያለመስጠት ነው። ኢጎ የሚኖረው በጊዜ ውስጥ ነው። ኢጎ ብርቱ ከሆነ፣ በህይወት ውስጥ ብዙ ጊዜ ይወስዳል። እናም አብዛኛው የምታስበው ሃሳብ ካለፈው ጊዜ እና ከመፃኢው ጊዜ ጋር የተገናኘ ይሆናል። በዚህም የማንነት ስሜትህ፣ ማንነትህን ካለፈው ጊዜ ይቀዳል። ሙላትህን ደግሞ ከመፃኢው ጊዜ ይጠብቃል። ፍርሀት፣ ድብርት፣ ጥበቃ፣ ቁጭት፣ ፀፀት፣ ንዴት በጊዜ የተገደበው ህላዌ ብልሹነቶች ናቸው።

ኢጎ የአሁኑን ቅፅበት የሚያስተናግድበት ሶስት መንገዶች አሉት። እነዚህም፣ ለሆነ ግብ እንደ መረማመጃ፣ እንደ እንቅፋት ወይም እንደ ጠላት ናቸው። እነዚህ ልምዶች ሲነሱ እንድታስተውልና መልሰህም መወሰን እንድትችል፣ እያንዳንዳቸውን እንፈትሻቸው።

1.ለኢጎ የአሁኑ ቅፅበት የተሻለ ከተባለ፣ ሊሆን የሚችለው ለሆነ ግብ እንደ መረማመጃ ሲሆን ነው። ምንም እንኳን መፃኢ ጊዜ እራሱ በአእምሮ ውስጥ ከሃሳብነት ያልዘለለ፣ ሲመጣም የአሁን ቅፅበት ሆኖ ከመምጣት ውጪ መሆን የማይችል ቢሆንም፣ የአሁኑ ቅፅበት ግን በጣም አስፈላጊ ተደርጎ ለሚወሰደው መፃኢ ጊዜ እንደመረማመጃ ተደርጎ ይወሰዳል። በሌላ አገላለፅ ሌላ ጊዜ ላይ ለመሆን በጣም ከመጣደፍ የተነሳ፣ አሁንን በደንብ መኖር አትችልም።

2.ይህ ልምድ እጅግ ሲጎላ ደግሞ (የተለመደም ነው) ፣ የአሁኑ ቅፅበት ሊቀረፍ እንደሚገባ እንቅፋት ተደርጎ ይወሰዳል። በዘመናችን አኗኗር፣ በየሰው የእለት ኑሮ ውስጥ ጥድፊያ፣ ሰቀቀን እና ጭንቀት የሚነሱትና መደበኛ ሁኔታ የሆኑትም ለዚሁ ነዉ። ህይወት ማለትም አሁን እንደ "ችግር" ታይቷል፣ እናም ከመደሰትህ፣ በትክክል መኖር ከመጀመርህ በፊት ልትፈታቸው የሚገቡ ብዙ ችግሮችን ማኖር ትጀምራለህ። ችግሩ ግን ፣ አንድ ችግር በፈታህ ቁጥር ፣ ሌላ ችግር ደግሞ ብቅ ይላል። የአሁኑ ቅፅበት እንደ እክል እስከታየ ድረስ፣ ችግሮች ፍፃሜ አይኖራቸውም።

3.ሌላው በጣም የከፋና በጣም የተለመደው ደግሞ፣ የአሁኑን ቅፅበት እንደ ጠላት ማየት ነው። የምትሰራውን ስራ ስትጠላ፣ አካባቢህን ስታማርር፣ የሚከሰተውንና የተከሰተውን ነገር ስትረግም፣ ወይም ከራስህ ጋር የምታወራው ነገር በነበርና ባልነበር ሲሞላ፣ ስትወቅስና ስትወነጅል፣ ከሚከሰተው ነገር ጋር ስትጣላ፣ ሁሌም ቢሆን ከዚያ ውጪ መሆን ከማይችለው ክስተት ጋር ስትጣላ፤ ህይወትን ጠላት እያደረክ ነው፤ ህይወትም "የምትፈልገው ጦርነት ነው፣ የምታገኘውም ጦርነት ነው" ትልሀለች።

ከአሁኑ ቅፅበት ጋር ያለህን ብልሹ ግንኙነት እንዴት መቀየር ትችላለህ? በጣም አስፈላጊው ነገር፣ ራስህን፣ ሃሳቦችህንና ድርጊቶችህን መመልከት ነው። በምትመለከትበት ጊዜ፣ ከአሁን ጋር ያለህ ግንኙነት ብልሹ እንደሆነ በምታስተውልበት ጊዜ፣ ህላዌህ ውስጥ ነህ። ተመልካቹ፣ በውስጥህ የሚያንሰራራው ህላዌ ነው። ብልሹነቱን ባየህበት ቅፅበት፣ ብልሹነቱ መክሰም ይጀምራል።

👉 ከወሰን ባሻገር መሆን

ንቁ ከሆንክ፣ ትኩረትህ በአሁን ላይ ብቻ ከሆነ፣ ያ ህላዌ በምትሰራው ስራ ላይ ይፈስና ለውጥ ይፈጥራል። በዚያ ውስጥ ጥራትና ሀይል አለ። የምትሰራው ነገር፣ በዋናነት ለሆነ ግብ (ገንዘብ፣ ክብር፣ አሸናፊነት) መረማመጃ ካልሆነ፤ ይልቁንም በራሱ ምሉዕ ከሆነ፣ በምትሰራው ላይ ሀሴት እና ህያዉነት አለ፤ በህላዌህ ውስጥ ነህ። እንዲሁም ከአሁኑ ቅፅበት ጋር ወዳጅነት ካልፈጠርክ በቀር፣ ህላዌ ውስጥ አትሆንም። የተፈጠርነው ገደብን ለመኖር ብቻ ሳይሆን ከገደብ ባሻገር በመጓዝ በሕላዌያችን እንድናብብ ጭምር ነው።

መፅሀፍ፦ አዲስ ምድር
ደራሲ፦ ኤክሀርት ቶሌ

@Zephilosophy
@Zephilosophy


እውነተኛ ማንነትን ማግኘት

ህይወታቸውን ሙሉ በኢጎ የተያዙ፣ የማያስተውሉና የማያስተውሉ ሆነው የቀሩ ሠዎች፣ ስለማንነታቸው ሲያወሩ ወዲያውኑ ስማቸውን፣ ስራቸውን፣ ግላዊ ታሪካቸውን፣ የሰውነታቸውን ቅርፅና ሁኔታ፣ ሌሎች ሊዛመዷቸው የሚችሉትን ሁኔታዎች ይነግሩሀል። ሌሎች ደግሞ እራሳቸውን ዘላለማዊ ነፍስ ወይም ህያው መንፈስ አድርገው እንደሚያስቡ በመናገር የተሻሉ መስለው ሊቀርቡ ይሞክራሉ። ነገር ግን በእውነት እራሳቸውን አውቀውት ነው ወይስ በአእምሮአቸው ውስጥ መንፈሳዊ-ቀመስ ፅንሰ ሐሳብ እየከተቱ ነው? እራስን ማወቅ፣ የተወሰኑ ሃሳቦችን ወይም እምነቶችን ከመቀበል በላይ ጥልቅ ነው። መንፈሳዊ ሃሳቦችም ሆኑ እምነቶች ጠቋሚ ቢሆኑ እንጂ፣ የሰው አእምሮአዊ ቅኝት አካል የሆነውን ቀድሞ የተገነባውን ጠንካራ የማንነት ፅንሰ ሃሳብ የሚያመክን ሃይል እምብዛም  የላቸውም። እራስህን በጥልቀት ማወቅ፣ በአእምሮህ ዙሪያ ከሚመላለስ ምንም አይነት ሃሳብ ጋር፣ አንዳች ግንኙነት የለውም። እራስን ማወቅ፣ እራስህን በአእምሮህ ውስጥ ከማጣት ይልቅ፣ በህላዌህ ውስጥ መትከል ነው።

👉ማንነቴ ብለህ የምታስበው ማንነት

የማንነት ስሜትህ በህይወትህ ያስፈልገኛል የምትለውንና ቦታ የምትሰጠውን ነገር የሚወስን ይሆናል። ለአንተ ቦታ ያለው ነገር ደግሞ፣ ሊረብሽህም ሆነ ሊያበሳጭህ አቅም አለው። እራስህን ምን ያህል በጥልቀት እንደምታውቀው ለመመዘንም፣ ይኽንኑ መስፈርት ልትጠቀም ትችላለህ። ቦታ የምትሰጣቸው ነገሮች የሚገለፁት በምትናገረውና በምታምነው ብቻ ሳይሆን በድርጊቶችህና በምትወስዳቸው አፀፋዊ ምላሾች ላይ አስፈላጊ እና ቁምነገር መስለው የሚገለጡትንም ያካትታል። እራስህን እንዲህ 'የሚያበሳጩኝና የሚረብሹኝ ነገሮች ምንድን ናቸው?' ብለህ ልትጠይቅ ትችላለህ። ትንንሽ ነገሮች አንተን የመረበሽ አቅም ካላቸው ማንነትህ በትክክል እንደዛ ነው፤ ትንሽ ነህ። ሳታስተውል የምታምነውም ይህንን ነው።

የምር የምትፈልገው ነገር ሰላምን ከሆነ፣ ሰላምን ትመርጣለህ። ከምንም ነገር በላይ ቦታ የምትሰጠው ለሰላም ከሆነ እና እራስህን ከትንሽ " እኔነት" ይልቅ መንፈስ እንደሆንክ በእውነት የምታውቅ ከሆነ፣ ከፈታኝ ሰዎች እና ሁኔታዎች ጋር ስትገናኝ ፍፁም አስተዋይና የረጋህ ሆነህ ትቆያለህ። የተፈጠረውን ሁኔታ ወዲያው ተቀብለህ፣ እራስህን ከማግለል ይልቅ ከሁኔታው ጋር አንድ ታደርጋለህ። እና ከዚያ አርምሞ ውስጥ የሚመጣ መልስ ታገኛለህ። መልሱን የሚሰጠውም ማንነትህ (ጥልቁ ተፈጥሮህ) እንጂ፣ ማንነቴ ብለህ ያሰብከው (ትንሹ እኔ) አየሸደለም። ምላሹም ሀያልና የተሳለጠ ሲሆን፣ የትኛውንም ሠውም ሆነ ሁኔታ ጠላት አያደርግም።

አንተ ኢጎህን አይደለህም፤ ስለዚህ በውስጥህ ያለውን ኢጎ ስታውቅ እራስህን አወቅክ ማለት ሳይሆን፣ ማንነተህ ያልሆነውን አወቅክ ማለት ነው። ነገር ግን በትክክል እራስህን ለማወቅ እንዳትችል ያደረገህን ትልቅ መሰናክል የምታስወግደው ማንነትህ ያልሆነውን ስታውቅ ነው።

ማንነትህን ማንም ሊነግርህ አይችልም። ማንነትህ ምንም አይነት ሀሳብ አይፈልግም። እንዲያውም እያንዳንዱ እምነት መሰናክል ይፈጥርብሀል። ምክንያቱም ሲጀመር የተፈጠርከውን ነህ። ነገር ግን መረዳት ከሌለ፣ ማንነትህ ወደ አለም ብርሀን መምጣት አይችልም።

👉  መትረፍረፍ

የምትረፍረፍ ምንጩ በውጪ የለም። የማንነትህ አካል ነው እንጂ። ነገር ግን ውጪ ያለዉን መትረፍረፍ በማወቅና በማመስገን መጀመር ትችላለህ። በዙሪያህ ያለውን የህይወትን ሙላት ተመልከት። ምነም እንኳን መትረፍረፍ ከተሰማህ ነገሮች ወደ አንተ መምጣታቸው አይቀሬ ቢሆንም፣ መትረፍረፍ እንዲሰማህ፣ ንብረት መያዝ አይጠበቅብህም። መትረፍረፍ፣ ላለው የሚመጣ ነገር ነው። ይህ የዩኒቨርስ ህግ ነው። መትረፍረፍም ሆነ ጎዶሎነት የሚገለጡ የውስጥህ እውነታዎች ናቸው።

👉 መልካም አና መጥፎ

ብዙ ሰዎች በህይወታቸው የሆነ ወቅት ላይ ከመወለድ፣ ከማደግ፣ ከስኬት ከመልካም ጤንነት፣ ከእርካታ እና ከማሸነፍ በተጨማሪ እጦት፣ ውድቀት፣ ህመም፣ እርጅና፣ መጃጀት፣ ስቃይና ሞትም እንዳለ ያውቃሉ። እነዚህም በስምምነት "መልካም" እና "መጥፎ" ፣ "የሰመረ" እና "ያልሰመረ" ተደርገው ይወሰዳሉ። የሰዎች ህይወት "ትርጉም" የሚኖረው መልካም ከተባለው ጋር ሲያያዝ ሲሆን፣ ይህም መልካም የተባለው ነገር ደግሞ ሁልጊዜ የመንኮታኮት፣ የመሰባበር፣ የመበጥበጥ አደጋ ይጋረጥበታል። ህይወት ትርጉም ስታጣና የሚገልፃት ነገር ሁሉ ስታጣ፣ ትርጉም የለሽና መጥፎ በሆነው አደጋ ውስጥ ገብታለች። ፈጥኖም ሆነ ዘግይቶ፣ የትኛውንም የኢንሹራንስ ፖሊሲ ብንገባ ህይወትን የሚያምስ ነገር መምጣቱ በማንም ላይ አይቀሬ ነው። አመጣጡ፣ በእጦት ወይም በአደጋ፣ በህመም፣ በአካል ጉዳት፣ በእርጅና ወይም ሞት ሊሆን ይችላል። ነገር ግን በሰውየው ህይወት ውስጥ የመጣው እክል እና ይሄን ተከትሎ የሚፈጠረው አእምሮ የፈጠረው ትርጉም መንኮታኮቱ፣ ለመለኮታዊው ስርአት በር ከፋች ሊሆን ይችላል።

ሃሳብ፣ ሁኔታዎችና ክስተቶች ልክ የግላቸው ተፈጥሮ ያላቸው ይመስል፣መልካም እና መጥፎ እያልን እንሰይማቸዋለን። በሃሳብ ላይ ባለን ቅጥ ያጣ አመኔታ ምክንያት እውነታ ይሰነጣጠቃል። ይህ መሰነጣጠቅ ወዥንብር ቢሆንም፣ በውዥንብሩ እስከተጠመድክ ድረስ ግን እውነት ይመስላል። ቢሆንም፣ ዓለም ግን እርስ በእርሱ የተሳሰረ፣ አንድም ነገር የብቻው ህልውና የሌለው፣ የማይከፋፈል ህብር ነው። የሁሉም ነገሮችና ክስተቶች በጥልቀት መተሳሰር የሚያመለክተውም "መልካም" እና "መጥፎ" የሚባሉት አእምሮአዊ ስያሜዎች፣ በተጨባጭ ውዥንብር እንደሆኑ ነው። እጅግ የተገደቡ ምልከታዎች ሲሆኑ እውነት መሆን የሚችሉትም በአንፃራዊነትና በጊዜያዊነት ነው። ይሄ በሎተሪ እጣ ውድ መኪና በገዛው አስተዋይ ሰው ታሪክ ውስጥ ውብ ሆኖ ተብራርቷል። ጓደኞቹና ቤተሰቦቹ ስለርሱ ተደስተው በዚያውም ደስታውን ለማክበር መጡ። "በጣም አይገርምም!። እድለኛ ነህ" አሉት። ሰውየውም ፈገግ ብሎ "ይሆናል" አለ። መኪናዋን በመንዳት የተወሰኑ ሳምንታት አጣጣመ። አንድ ቀን ግን፣ የሰከረ አሽከርካሪ በመንገድ መገናኛ ላይ ገጨውና በከፍተኛ ጉዳት ሆስፒታል ገባ። ጓደኞቹና ቤተሰቦቹ ሊጠይቁት መጡ " እንዴት አይነት ክፉ አጋጣሚ ነው?" አሉ። ሰውየው በድጋሚ ፈገግ ብሎ "ይሆናል" አለ። በሆስፒታል በነበረበት ጊዜም፣ በምሽት የመሬት መንሸራተት ተከስቶ መኖርያ ቤቱን ባህር ውስጥ ከተተው። እንደገና በሚቀጥለው ቀን ጓደኞቹና ቤተሰቦቹ መጥተው " ሆስፒታል ውስጥ በመሆንህ እድለኛ አይደለህም ታዲያ?" አሉት። እርሱም መልሶ "ይሆናል" አላቸው።

የአስተዋዩ ሰው "ይሆናል" የሚለው አባባል፣ የሚከሰተውን ሁሉ ለመፈረጅ አለመፈለጉን ያመለክታል። ከመፈረጅ ይልቅ፣ የሆነውን ሁሉ በመቀበል ከመለኮታዊዉ ስርዓት ጋር ንቁ አንድነት ይፈጥራል። ተራ የሚመስል ክስተት በህብሩ ሸማ ውስጥ ምን አይነት ስፍራ ሊኖረው እንደሚችል አእምሮ በፍፁም እንደማይረዳ አውቋል። ነገር ግን ድንገተኛ የሚባል ክስተት የለም፤ በራሱ እና ስለራሱ ብቻ በብቸኝነት የሚኖር ክስተትም ሆነ ሁኔታ የለም። አካልህን የገነቡ አተምች በውስጥህ የሚገኙ ከዋክብት ይመስላሉ፤ እናም የትንሽ ክስተት መንስኤው ወሰን የለሽ እና በማይጨበጥ መልኩ ከህብሩ ጋር የተሳሰረ ነው። የማንኛውንም ክስተት መነሻ ወደ ሗላ ሄደህ መመርመር ከፈለግክ፣ እስከ ፍጥረት መጀመሪያ ድረስ መጓዝ ይኖርብሀል። 

ምንጭ ፦ አዲስ ምድር
ፀሀፊ :-ኤካሀርት ቶሌ

✍ይቀጥላል✍

@Zephilosophy
@Zephilosophy

11k 0 42 2 63

[የሕሊና ጸሎት]
___
ደምስ ሰይፉ

'አንዳንዶች' ሆይ...
.
.
.
'ሕዝብ' 'ሕዝብ' በሚለው አንደበታችሁ ውስጥ በሕዝብነት ስፍር በምላሳችሁ የምላመጥ ስም የለሽ መሆኔን...
___
ልባችሁ ቅንጣት ፍቅር ሳይኖራት ስለኔ መሰዋታችሁን በመለፈፍ በስሜ የምትነግዱ መሆኑን...
___
ከገዛ ክፋታችሁ አገዛዝ ነፃ ሳትወጡ 'ነፃ አውጭ ነን' ስብከታችሁን በየ አጋጣሚው ስትሰብኩ የማያቀረሻችሁ መሆኑን...
___
ወገኔ ሰው ነው ብዬ ከምኖርበት ቀዬ በመንደርተኛነት ጥንወት ታውራችሁ እንደ አውሬ አሳዳችሁኝ ስታበቁ ስለ ሰብዓዊ መብት ስታወሩ የማያቅለሸልሻችሁ መሆኑን...
___
'ዲሞክራሲ' በማስፈን ስም አገዛዝ ለማንበር እንደምታሴሩና ለዚህ ክፋታችሁ እኔኑ ጭዳ ከማድረግ የማትመለሱ መሆኑን...
___
ያለፈውን 'ጨለማ' የምትተቹት የተሻለ ቀን ለማምጣት ሳይሆን የተረኝነት አዙሪት ለማንበር መሆኑን...
___
ከሰላሜ ይልቅ ወንበራችሁ እያስጨነቃችሁ እንኳ 'የዜጎች መብት ይከበር' የምትሉት በአስመሳይነት መሆኑን...
___



.
.
.





.
.
.
ግና
.
.
.
ዛሬም ተስፋ ሳልቆርጥ የፍትህ ጸሐይ እስክትወጣ የምጠብቀው "የማይነጋ ለሊት የለም" ያሉኝን አምኜ ነው...
___

@Zephilosophy
@Zephilosophy


ቅናት

ምንጭ ፦ ነፃ ስሜቶች (ኦሾ)
ትርጉም፦ ዩሐንስ አዳም

ቅናትውድድር/ንጽጽር ነው፡፡ እንድናወዳደር እና እንድናነጻጽር ተምረናል፡፡ ሁሌም እንድናነጻጽር ተገርተናል፡፡

አንድ ሰው የተሻለ ቤት አለው፡፡

አንድ የሆነ ሰው ያማረ አካል አለው፡፡

አንድ ሌላ ሰው ብዙ ገንዘብ አለው፡፡

አንድ ሰው ማራኪ ሰብእና አለው፡፡

ራሳችሁን ከአላፊ አግዳሚው ጋር አነጻጽሩ እናም ታላቅ ቅናት የሚያንሰራራ ይሆናል፡፡ ቅናት የንጽጽር መገራት ውጤት ነው፡፡ ንጽጽርን እና ውድድርን የምታስወግዱ ከሆነ ቅናት ይጠፋል፡፡ ከዚያም ራሳችሁን እንደሆናችሁት ብቻ ታውቁታላችሁ፡፡ እናንተ ማንንም አይደላችሁም፡፡ ማንንም መሆን አያስፈልጋችሁም፡፡ ራሳችሁን ከዛፎች ጋር አለማወዳደራችሁ ጥሩ አለበለዚያ በእነሱም ቅናት ይሰማችሁ ነበር፡፡ ለምን አረንጓዴ አልሆናችሁም? ለምን ይሆን እግዚአብሔር የጨከነባችሁ? ለምን አበባዎችን
አልሆናችሁም? ራሳችሁን ከአዋፋት ፣ ከወንዞች ፣ ከተራሮች ጋር አለማወዳደራችሁ ጥሩ ነው፡፡ አለበለዚያማ ትሰቃዮ ነበር። የምትወዳደሩት ከሰው ልጆች ጋር ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም እንድትወዳደሩ የተገራችሁት ከሰዎች ጋር ብቻ ስለሆነ ነው፡፡ ከፒኮኮች እና ከበቀቀኖች ጋር አትወዳደሩም፡፡

አለበለዚያማ ቅናት በጣም እና በጣም ይጨምር እና መኖር እስከሚያቅታችሁ ድረስ የቅናት ሸክም ይጫናችሁ ነበር፡፡ ውድድር እና ንጽጽር በጣም ቂላቂል አመላካከት ነው ምክንያቱም እያንዳንዱ ሰው ልዮ እና የማይነጻጸር በመሆኑ ነው።

ይህ ግንዛቤ አንድ ጊዜ በውስጣችሁ ከሰፈነ ቅናት ይጠፋል፡፡

እያንዳንዱ ሰው ልዮ እና የማይወዳደር ነው፡፡

እናንተ ራሳችሁንብቻ ናችሁ፡፡

ማንም ፈጽሞ እናንተን አይመስልም፡፡

እናንተ ፈጽሞ ማንንም መምሰል አትችሉም፡፡

አንድን ሰው/ሴት በምትወዱ ጊዜ ወደሌላ ሴት/ሰው ዘንድ ሊሄድ/ልትሄድ እንደማይችል/ትችል ታምናላችሁ፡፡ ግን ከሄደ/ከሄደች ምንም ማድረግ አይቻልም፡፡ ፍቅር ይህንን ግንዛቤ ያመጣል፡፡ ምንም ቅናት አይኖርም፡፡ ስለሆነም ቅናት የሚኖር ከሆነ ፍቅር እንደሌለ ጠንቅቃችሁ እወቁ፡፡ ቅናት ባለበት ግንኙነት ውስጥ ካላችሁ ጨዋታ እየተጫወታችሁ ነው ፤ ከፍቅር በስተጀርባ ወሲብን እየደበቃችሁ ነው ማለት ነው፡፡ ፍቅር ምንም ሳይሆን የተቀባ/ያጌጠ ቃል ብቻ ነው ማለት ነው፡፡

ቅናትን በጣም በቅርበት ተመልከቱት፡፡ ቅናት ምንድን ነው? ቅናት ማለት በውድድር ውስጥ መኖር ማለት ነው፡፡ አንድ ከእናንተ የበላይ የሆነ ሰው አለ፡፡ ከእናንተ በታች የሆነ ሰው አለ፡፡ እናንተ ሁሌም የመሰላሉ መሃል ላይ ናችሁ፡፡ ምናልባትም መሰላሉም ማንም መጨረሻውን የማያገኘው ክብ ሊሆንም ይችላል፡፡ እያንዳንዱ ሰው መሃል ላይ ተወስኖ ቀርቷል፡፡ እንዳንዱም ሰው መሃል ላይ ነው፡፡ መሰላሉ በክብ የሚሽከረከር ይመስላል፡፡

አንድ ሰው ከበላያችሁ ነው- ያ... ይጎዳል፡፡ ያም በጦርነት፣ በትግል ፣ በሚቻለው የትኛውም መንገድ ትንቀሣቀሱ ዘንዳ ያደርጋችኋል፡፡ ምክንያቱም የሚሳካላችሁ ከሆነ በትክክለኛው ይሁን በተሣሣተው መንገድ ማንም ግድ አይኖረውም፡፡ ስኬት ትክክለኛ ያደርጋችኋል፡፡ ውድቀት የተሣሣታችሁ እንደሆነ ያረጋግጣል፡፡ ስለዚህ ዋናው ጉዳይ ስኬት ነው፡፡ ስለዚህ ለስኬት የትኛውም መንገድ መጠቀም ይቻላል፡፡ መጨረሻው መንገዱን ትክክል ያደርገዋል፡፡ ስለዚህ ስለ መንገዱ ምንም መጨነቅ አያስፈልጋችሁም፡፡ ማንም ስለ መንገዱ ማንም አይጨንቀውም፡፡ መላው ጥያቄ እንዴት ነው መሰላሉን መውጣት የሚቻለው የሚለው ጥያቄ ነው፡፡ ግን የመሰላሉ መጨረሻ ላይ ፈጽሞ መምጣት አትችሉም፡፡ እናም ከእናንተ በላይ የሆነው ሰው ቅናትን በውስጣችሁ ይፈጥርባችኋል፡፡ እሱ ተሳክቶለታል
እናንተ ወድቃችኋል፡፡

@Zephilosophy
@Zephilosophy


ሟች ከመሆንህ እውነታ ጋር መጋፈጥ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ምክንያቱም ሁሉንም የማይረቡ፣ አቅም የሌላቸውና ጥልቀት የሌላቸውን እሴቶች ሁሉ ጠራርጎ የሚያስወግድ ነገር ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ቀኖቻቸውን ተጨማሪ ገንዘብ ወይም ትንሽ ተጨማሪ ዝናና ትኩረት ወይም ትክክል ወይም ተወዳጅ በመሆናቸው ትንሽ ተጨማሪ ማረጋገጫ በማሳደድ ሲያሳልፉ፣ ሞት ግን ሁላችንንም በጣም በሚያሰቃይና አሰፈላጊ ጥያቄ ያፋጥጠናል፡፡
"ውርስህ ምንድነው? አንተ ስትሞት አለም የተለየችና የተሻለች የምትሆነው እንዴት ነው? ምን አሻራ ትተሀል? ምን ተፅእኖ ታመጣለህ?"

@Zephilosophy


የትኩረት መዛባት

በዚህ ማህረሰብ ውስጥ  “ተመልከት የእኔ ሕይወት ከአንተ ሕይወት የበለጠ ያማረ ነው” በሚሉ በማህበራዊ ድረ- ገፆች በሚተላለፉ መልዕክቶች በኩል ጭንቀት፣ ፍርሃት፣ የጥፋተኝነት ስሜት ወዘተ... የመሳሰሉት አሉታዊ ልምዶች ያሉት ትውልድ እየፈራ ነው፡፡

ሰዎችም ሆነ የቲቪ ማስታወቂያዎች የመልካም ሕይወት ቁልፉ አሪፍ ስራ ማግኘት፣ ወይም ዘናጭ መኪና ወይም ቆንጆ ሴት ጓደኛ ያለህ መሆን እንደሆነ እንድታምን ይፈልጋሉ፡፡ አለም ያለማቋረጥ የሚነግርህ ነገር፣ የተሻለ የሕይወት መንገድ የሚባለው ብዙ መግዛት፣ ብዙ ማግኘት ፣ ብዙ መዋብ እንደሆነ ነው፡፡ ስለዚህ ሁልጊዜ በተደጋጋሚ ስለሁሉም ነገር ግድ እንዲኖርህ በሚነገሩ መልዕክቶች ስለምትጨናነቅ ያለማቋረጥ አዲስ ቅንጡ ነገሮችን ስለመግዛት፤ የእረፍት ጊዜህን ውድ በሆኑ ቦታዎች ስለማሳለፍ የምታስብ ትሆናለህ ወይም ፋሽን ልብሶች እና ኮስሞቲክሶችን ስለመግዛት የምታስቢ ትሆኛለሽ።

  እነዚህ ነገሮች ከባድ የበታችነት እና የጭንቀት ስሜት ከመፍጠራቸውም በላይ በማይገባ አይነት የማይረቡና የውሸት ከሆኑ ነገሮች ጋር የተጣበቅክ እንድትሆንና ሕይወትህን ሙሉ የማይጨበጥ ደስታና እርካታ ስታሳድድ እንድትኖር ያደርግሃል፡፡ የመልካም ሕይወት ቁልፍ ስለ ብዙ ነገሮች መጨነቅ ሳይሆን፣ ስለ ትንሽ ለዚያውም እውነት፣ አስቸኳይና አስፈላጊ ስለሆነው ነገር ብቻ መጨነቅ ነው፡፡

Mark Manson

@zephilosophy

20 last posts shown.