ኦርቶዶክሳዊ መጻሕፍት እና ጽሑፎች Tsegaye kiflu


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


በዚህ ቻናል ላይ አበው ያስረከቡንን መጻሕፍትን እንዲሁም መንፈሳዊያት ጽሁፎችን ለምዕመናን ተደራሽ ማድረግ ነው።
https://linktw.in/mejQ6H
ሰብስክራይብ ያድርጉ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri




በሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት ፶ አዳዲስ አማኞች በጥምቀት ከብረው የሥላሴ ልጅነት አገኙ።

የካቲት ፪/፳፻፲፯ ዓ/ም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

በሀዲያና ስልጤ ሀገረ ስብከት በአናሌሞ ወረዳ ቤተ ክህነት በወጎ ወጌላ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ፶ ኢ አማንያን በብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የሀዲያና ስልጤ ፤ የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በዛሬው ዕለት ተጠምቀው የሥላሴን ልጅነት አግኝተዋል ።

በዕለቱም ብፁዕነታቸውን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ሕይወት ንጉሤ ባወቀ ፣ የሀገረ ስብከቱ የሥራ ክፍል ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

©ብሕንሳ ሚዲያ


Church and Civil Laws, 13th Century A.D. page 6) (ሄኖክ ኃይሌ (ዲ/ን)፣ ተአምረ ማርያምና አንዳንድ ጉዳዮች)

- በራእየ ማርያም ውስጥ የዘረኝነት በሽታ የጸናበት አካል ያልኾነ ሥርዋጽ አስገብቷል። ራእየ ማርያም መጀመሪያ የተጻፈው በግሪክ ሲኾን ወደ ሀገራችን ከመምጣቱ በፊት ወደ ዐረብኛ ተተርጉሟል። ከ39 በላይ የራእየ ማርያም ቅጂዎች ይገኛሉ። ወደ አማርኛ የተተረጎሙ የ1961 የተስፋ ገብረ ሥላሴ ትርጉም ቀሲስ ዶ/ር አምሳሉ አላገኘኹትም ይላሉ። 1985 በተስፋ ገብረ ሥላሴ የተተረጎመ እና በ2007 በአክሱም ማተሚያ የተተረጎመ አመሳክረው ጥናት አቅርበዋል። (አምሳሉ ተፈራ (ቀሲስ፡ ዶ/ር)፣ ነቅዓ መጻሕፍት፣ 2011 ዓ.ም፣ ገጽ 294-302)

- "ማክሰኞና ሐሙስ እባብን የገደለ እንደ ዐርባ ቀን ሕፃን ይኾናል" የሚል ትምህርት የመጣው በደብረ አስቦ ለነበሩ ገዳማውያን ዋናዎቹ ፈተናዎች እባብና ዘንዶ ስለ ነበሩ ነው። በዚያ ዘመን ዕባቡንና ዘንዶውን መታገሥ፣ አልፎም ማጥፋት ጽናትን ማሳያ ነበርና። (ዳንኤል ክብረት፣ ኢትዮጵያዊው ሱራፊ፣ 2011 ዓ.ም፣ ገጽ 660፣ የግርጌ ማስታወሻ 1974)። ይህ አባባል በመጀመሪያ ቅጅ ላይ የለም፤ ሥርዋፅ ኾኖ የገባው ኋላ ነው። የገባው ግን ከላይ የተገለጸውን ሐሳብ ለማስጠበቅ ነበር። መናፍቃን ግን ይህን ለጥጠው "እባብን የገደለ ይጸድቃል" እያልን እንደ ኾነ ለማስቆጠር ይጥራሉ። ይህ ግን Straw man Fallacy (ያልተባለን ነገር እንደ ተባለ አድርጎ የማሰብ ስሕተት) ነው። ይህ አካሄድ ቅንነት የሌለው ጥላቻንና ማነወርን ማዕከል ያደረገ ስሑት አካሄድ ነው።

- በዚቅ ላይ ደግሞ "ኦ አምላክ መርቆሬዎስ ዘአሠርገውከ ሰማየ " የሚል ንባብ በሥርዋፅ ገብቶ መገኘቱን ልብ እንላለን። የተሐድሶ መናፍቃንም እንዲህ ብለን እንደማናምንና ይህ ሥርዋፅ እንደ ኾነ ቢረዱም የመስማት ፍላጎት የሌላቸውና እነርሱ የሚሉትን ብቻ እንድንቀበል የሚፈልጉ ስሑታን ስለ ነበሩ ያልኾኑ ነገሮችን ሲያራግቡ ተመልክተናል። ሌሎችም ይህን የመሰሉ ጉዳዮች ሊገኙ ይችላሉ። ያን ኦርቶዶክሳዊ በኾነ መንገድ በጉዳዩ ላይ በሥርዓትና በጥንቃቄ ጥናት ለሚያደርጉ በጉዳዩ ብዙ ለቆዩበት ለነ ቀሲስ ዶ/ር አምሳሉ ተፈራ ዓይነት ለቀቅ ብናደርግ መልካም ነው። በኹሉ ነገር ላይ ራስን አዋቂ አድርጎ ያውም በጉዳዩ ላይ ጥልቅ ንባብና ጥናት ሳያደርጉ ኦርቶዶክሳዊ ባልኾነ መንገድ አዋልድ መጻሕፍትን እያዩ ደረቅ ትችት ማቅረብ አግባብ አይደለም። ደረጃን እና አቅምን በመረዳት በማያውቁት ነገር በመሰለኝ ከማውራት እንቆጠብና ብዙ ዓመታትን በሥነ ድርሳናት ለቆዩት አካላት በአክብሮት ቦታውን ለቀቅ ብናደርግ መልካም ነው። በችኩልነትና በድርቅና የቤተ ክርስቲያን አረዳድ ኹሉ በኔ በር በኲል ሲያልፉ ነው የሚያገኙት ከሚያሰኝ አካሄድ ብንቆጠብ መልካም ነው።

የአዋልድ መጻሕፍት ምንነት፣ ዓይነት፣ ጥቅም ...! እንዳይሰፋ ትቼው እነሆ ይህን አቀረብኹላችሁ።

✍️ዲያቆን ዮሐንስ ጌታቸው እንደጻፈው


ይህ ማለት ግን ደጋግሜ እንዳልኹት በአዋልድ መጻሕፍት ላይ ያሉን በሙሉ ከዳር እስከ ዳር ምንም ችግር ስለሌ ተቀበሉ ማለት አይደለም። እንዲህም ያለ የለም፤ ያልተባለን ነገር እንደ ተተባለ አድርጎ ማቅረብም Straw man Fallacy ነው። ማን ነው እንዲያ ያለው? ማንም እንዲያ ሊል አይችልም። ሌላው ቀርቶ አንድ በሌላ ቤተ እምነት የቆየ ሰው ኦርቶዶክስ መኾን ሲፈልግ በአእማደ ምሥጢራት አምኖ ተምሮ ምሥጢራትን ፈጽሞ አካል ይኾናል እንጂ አዋልድ መጻሕፍትን በአጠቃላይ ትቀበላለህ አትቀበልም እየተባለ አይጠየቅም፤ እንዲያ እንዲጠየቅ የሚያዝ ሕግም ሥርዓትም የለም። በሌለበትና ባልተባለው በድፍረትና በምንአለብኝነት "ገድላት ድርሳናትን አልቀበልም ማለት ትችላለህ ችግር የለውም ዓይነት አካሄድ ከየት የመጣ ነው?" የሌለ ነገር እየተባለ እንዴት ውዝግብ ይፈጠራል? ይህን አካሄድ ብንተወውና ትክክለኛ በኾነውን መንገድ ትምህርቱን በሥርዓቱ ብናቀርብ መልካም ነው። ሌሎችም ያላሰቡትን ጥያቄ እየፈጠርን ባናደክማቸው መልካም ነው። በአዋልድ መጻሕፍት ውስጥ ስሕተት ሊኖር እንደሚችል ማሳያ በማቅረብ እንቋጭ።


አዋልድ መጻሕፍት እና አንዳንድ ስሕተቶች

1) የትርጒም ስሕተት ሊኖር ይችላል። ለምሳሌ አንቀጸ ብርሃን ላይ

«ወኢያኀትዉ ፡ ውስቴታ ፡ ማኅቶተ ።»

በዛሬው ጥቆማዬ ለማሳየት የፈለኩትና በብዙ ቦታ ያገኘኹት የመጀመሪያው የትርጕም ግድፈት፥ የቅዱስ ያሬድ ድርሰት በኾነው አንቀጸ ብርሃን ላይ ይገኛል። ክፍለ ጸሎቱም፥ በልሳነ ግእዝ፦ «አንቲ ፡ ውእቱ ፡ ተቅዋም ፡ ዘወርቅ ፡ ዘኢገብራ ፡ እደ ፡ ኬንያ ፡ ዘሰብእ ። ወኢያኀትዉ ፡ ውስቴታ ፡ ማኅቶተ ። አላ ፡ ለሊሁ ፡ ብርሃነ ፡ አብ ።» የሚለው ነው።

ትርጕሙም፦ «የብልኻተኛ እጅ ያልሠራት፣ በውስጧም መብራት የማያበሩባት የወርቅ መቅረዝ አንቺ [ማርያም] ነሽ። የአብ ብርሃን ይበራባታል እንጂ፤» ወይም፦ «የብልኻተኛ እጅ ያልሠራት የወርቅ መቅረዝ አንቺ ነሽ። በውስጧም መብራት አያበሩባትም። እርሱ የአብ ብርሃን ይበራባታል እንጂ፤» ማለት ነው።

በዚኽ ክፍለ ጸሎት፦ «የማያበሩባት» መባል የሚገባው ቃል፥ በብዙ መጻሕፍት፦ «የሚያበሩባት» ተብሎ ተተርጕሟል። ግእዙ፦ «ወኢያኀትዉ» እያለ፥ «የሚያበሩባት» ብሎ መተርጐም አለማስተዋል ነው። ከቃሉም ባሻገር፦ «አላ ለሊሁ ብርሃነ አብ» የሚለው ሐረግ ራሱ ትርጕሙን ያመላክታል። ምሥጢሩም፦ ‹መቅረዝ› በተባለች እመቤታችን ማርያም ላይ፥ የእግዚአብሔር አብ ብርሃን [ወልድ] እንደሚበራባት እንጂ ሌላ መብራት እንደማያስፈልጋት ያጠይቃል። ‹የአብ ብርሃን› የተባለም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ነገር ግን ይኼን ምሥጢር በሚያፋልስ አገላለጽ፦ «የሚያበሩባት» ተብሎ ተተርጕሟል። (ኤፍሬም የኔሰው (ዲ/ን)፣ የትርጒም ግድፈቶች በጸሎት መጻሕፍት በሚል ካዘጋጀው ጽሑፍ የተወሰደ)

«ዘሠረፀ ፡ እምአብ ፡ ወእምወልድ ፡ ዘነሥአ ።»

በኀሙሱ ሰይፈ ሥላሴ፥ በግእዙ ጸሎት፦ «አአምን ፡ ሥልሰ ፡ በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ዘወፅአ ፡ እምአብ ፡ ወእምወልድ ፡ ዘነሥአ ፡ ከመ ፡ ይቀድሶ ፡ ለኵሉ ፡ ዐለም ።» የሚል ኀይለ ቃል አለ። ትርጕሙም፦ «ዐለሙን ኹሉ ይቀድሰው ዘንድ ከአብ በሠረፀ፣ ከወልድ በተሰጠ መንፈስ ቅዱስ አምናለኹ፤» ማለት ነው። እኔ ባየኋቸው አንዳንድ መጻሕፍት ላይ ግን፦ «.... ከአብ እና ከወልድ በሠረፀ (በወጣ) በመንፈስ ቅዱስ አምናለኹ፤» ተብሎ ተተርጕሟል። የዶግማ ተፋልሶን የሚያመጣ የተሳሳተ አተረጓጐም ነው። (ኤፍሬም የኔሰው (ዲ/ን)፣ የትርጒም ግድፈቶች በጸሎት መጻሕፍት በሚል ካዘጋጀው ጽሑፍ የተወሰደ)

-ግእዙ አንድ ባሕርይ የሚለውን ኹለት ባሕርይ ብለው መጽሐፈ ባሕርይ ላይ የተረጎሙት ንባብ አለ። ስሕተት ነው። ክሕደት ነውና።

- ንሕነሰ ነአምን ከመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኅቡራነ ህላዌ ወኅቡራነ መንግሥት ኅቡራነ ራእይ ወኅቡራነ መለኮት፦ እኛ ግን አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ 'በአካል አንድ' በመለኮት አንድ እንደ ኾኑ ..." ይላል። በዚህ መንባብ ውስጥ ሥላሴ በአካል አንድ መኾናቸውን የሚገልጽ የለም። ይህ ዳኅፅ ነው። ጠማማ ልቡና ያለው ያነበበው እንደ ኾነ አባ ጊዮርጊስን ባላሉት እንዳሉት አድርጎ ሊናገር ይችል ይኾናል።
(ኅሩይ ኤርምያስ (መ/ር፣ ተርጓሚ)፣ 2001 ዓ.ም፣ ምዕራፍ ስድስት የጥምቀት ምንባብ፣ ገጽ 73)።

2) ሥርዋፅ ኾኖ የገቡ አሉ። ለምሳሌ፦

- በሚያዝያ 10 በሚነበበው ስንክሳር ላይ የተቀመጠው ‘“ወሰብአ ኢትዮጵያሰ ኢይሲሙ ሊቀ እማዕምራኒሆሙ’ /የኢትዮጵያ ሰዎች ከሊቃውንቶቻቸው ጳጳስ አይሹሙ/ የሚልን በ318ቱ ሊቃውንት የተነገረ አንቀጽ በመተላለፋቸውና በንጉሥ ሐርቤ ዘመን ጵጵስናን በመጠየቃቸው ምክንያት ድርቅ መቅሠፍት ሆኖ ወረደባቸው’ የሚል የሐሰት ታሪክ አንዱ ነው፡፡ ይህንን የውሸት ታሪክ ግብፃውያኑ ሆን ብለው ኢትዮጵያን ለማስፈራራት የጨመሩት አንቀጽ ቢሆንም የ318ቱ ሊቃውንትን ቃል የምታከብረዋ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያንም ያለ ጥያቄ አምና ተቀብላው ኖራለች፡፡

የሚገርመው ግብፃውያኑ ይህንን የሐሰት ትርክት ሲጨምሩ ያበላሹት ሦስት መጻሕፍትን መሆኑ ነው፡፡ አንደኛው መጽሐፈ ስንክሳር ፣ ሁለተኛው ፍትሐ ነገሥት ሦስተኛው የኒቅያ ጉባኤ ድንጋጌ ነው፡፡ ይህንን ሥራ በወቅቱ ከነበሩት ጳጳስ ጋር ተስማምቶ የሠራው የፍትሐ ነገሥት አስተጋባኢ Safey Ibn Al-Assal (13 Ad) ነበረ፡፡ ይህንን ስኅተት የግንቦት 2009 ዓ.ም. ርክበ ካህናት ላይ የብፁዕ ዶ/ር አቡነ ገሪማን ቀደምት ጥናታዊ ጽሑፍ እንደማስረጃ በመጥቀስ ከስንክሳር እንዲወጣ ወስኖአል፡፡ በመጻሕፍት ላይ ‘በሊቃውንት ጉባኤ ታርሞና ተስተካክሎ የወጣ’ የሚል አንቀጽ በመጻሕፍት ላይ የምናገኘው ይህ በቤተ ክርስቲያኒቱ የኖረ አሠራር ስለሆነ ነው፡፡

የሚገርመው በእኛ ቤተ ክርስቲያን ይህ ውሳኔ ከመወሰኑና ከመታረሙ አስቀድሞ ግን የግብፅ ቤተ ክርስቲያን ባሳተመችው የፍትሐ ነገሥት አዲስ ቅጂ ላይ ‘ይህንን የኢትዮጵያ ሰዎች ከሊቃውንቶቻቸው ጳጳስ አይሹሙ’ የሚል አንቀጽ ስኅተት መሆኑን በመግለጽ አብራ እንደሚከተለው ከእርማት ጋር አሳትማዋለች :-

‘The Ethiopians are not to have a Patriarch from their scientists or by their own choice alone because their patriarch should be under the hand (authority) of the one on the chair of Alexandria’ [This again is wrong, because the council of Nicea did not have any knowledge of Ethiopia which did not have a bishop at the council and did not have a bishop until St. Athanasius ordained Fremenatous for them after the council of Nicea]

‘ኢትዮጵያውያን ከሊቃውንቶቻቸው መካከል በራሳቸው ምርጫ ብቻ ፓትርያርክን ሊሾሙ አይገባቸውም፡፡ ምክንያቱም ፓትርያርካቸው በእስክንድርያ መንበር ሥልጣን ሥር መሆን ይገባዋል’ [ይህም ዳግመኛ ስኅተት ነው ፤ ምክንያቱም የኒቅያ ጉባኤ በጉባኤው ወቅት ጳጳስ ስላልነበራት ኢትዮጵያ ምንም የሚያውቀው ነገር አልነበረም፡፡ ኢትዮጵያም ቅዱስ አትናቴዎስ ከኒቅያ ጉባኤ በኋላ ፍሬምናጦስን እስከሾመላት ድረስ ጳጳስ አልነበራትም] (Al Magmou Al-Safawy Le Ibn Al Assal – The Collection of


ምእመናን እንዲረዱ ማድረግ የሚገባን መሠረታዊውን የታምራትን አረዳድ ነው። ተአምር በቃ እንደ ተአምር የሚወስዱት መኾኑን ልብ ማለት ይገባል። መቼስ ተአምራትን እንደ ተለመደ ክስተት አድርገን ብቻ እንውሰዳቸው ካልን ትልቅ ችግር ውስጥ የምንገባ መኾኑን አንዘነጋም። አረዳዳችን ካልተስተካከለ ኦርቶዶክሳዊ መኾን አንችልም። ሕሊናችንን አበዋዊ ለማድረግ መጣር ይጠበቅብናል። የአበውን አረዳድ ትተን በኛ መጠን ልክ ብቻ ነገሮችን የምንቃኝ ከኾነ መጽሐፍ ቅዱስንም ቢኾን የመቀበል ዕድላችን አናስ ይኾናል። ስለዚህ በጣም በጥንቃቄ እና በእርጋታ በትሕትናም ኾኖ አካሄድን መመርመር ያስፈልጋል።

መርሳት የሌለብን ነገር "አዳኛችንና አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ አምላክን ያለምንም እንከን የወለደች የአምላክ እናት እና ቅዱሳን የሚያደርጉትን ልዩ ተአምራት በንጽሕና፣ በፍጹም እምነት በፍጹም ነፍስና በፍጹም ልብ ኾነው የማይቀበሉ ነገር ግን ይህን ማድረግ አይችሉም በማለት የሚያሾፉ፣ በራሳቸውም ሐሳብ አጣመው የሚተረጒሙ፣ በራሳቸው ሐሳብ ብቻ የሚመዝኑ፣ ውግዘት የሚገባቸው መኾናቸውን የሚጠቁሙ ምንባባት ኹሉ አሉ። (The Synodikon of Orthodox)። በተአምረ ማርያም መቅድም ላይ ያለውንም ግዝት የምናውቀው ነው። ስለዚህ ስላልመሰለን ብቻ ቸኩለን ሌላ ባዕድ ነገር ለማምጣት ባንጥር መልካም ነው።

¤ በአዋልድ መጻሕፍት ውስጥ ያሉ ጸነን የሚሉ ምንባባት ይውጡን?

ጸነን የሚሉ ምንባባት ይውጡ ከማለት ይልቅ የሚሻለው አረዳዳቸውን ማወቅ ነው። ትክክል ቢኾኑ እንኳን ጸነን ስለሚሉ እያሉ በራስ የመረዳትና የማሰብ መጠን ልክ አድርጎ ማሰብ ወደ ከባድ ሌላ ስሕተት ሊወስድ ይችላልና። ኹሉን ነገር በራሱ መጠን ልክ አድርጎ ማሰብ የሚፈልግ ሰው እንዴት ኾኖ ኦርቶዶክስ ሊኾን ይችላል? ይህ ሰው ኋላ ሃይማኖትን በራሱ መጠን ልክ አድርጎ ወደ መረዳት እንደማይወርድ ማን እርግጠኛ ይኾናል? የአረዳድ መንገዱ ስሑት ከኾነ ያን አቅንቶ መሠረታዊ በኾነው የክርስትና ትምህርት መሠረት ላይ እምነቱን እንዲተክል ማድረግ ይገባል እንጂ እምነቱን በሥነ አመክንዮው ልክ አድርጎ እንዲያስብ የሚያደርግ በር መክፈት ተገቢ አይደለም።

ለምሳል "ፍጥረት ኹሉ እመቤታችንን ለማመስገን ተፈጠረ" የሚል ንባብ ያየ ሰው ኦርቶዶክሶች ቅድስት ድንግል ማርያም ያመልኳታል ከሚለው ቀድሞ በንጹሕ ልቡና አረዳዱን ይፈልጋል። አይ ይሄ ንባቡ ጸነን ይላልና ይውጣ ቢባል፤ ይህን አካሄድ የለመደ ሰው ምን ሊኾን ይችላል? ደረቅ ንባብ እያየ መልእክቱን ከመፈለግ ይልቅ ይጸናልና ይውጣ ወይም አልቀበልም ወደ ማለት አይወርድምን? እነ መርቅያንን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ቆነጻጽለው የሉቃስ ወንጌል ላይ ወስዶ የጣላቸው፣ እነ ሉተርን በሕሊናዬ ውስጥ ካለው ሐሳብ ጋር ይጋጫል ብሎ ከማሰብ የተነሣ የያዕቆብን መልእክት ገለባ መልእክት ለማለት የዳረገው ምን ኾኖ ኖሯል? ሌሎች ብዙ መናፍቃን እስካኹን ድረስ ውጭ አውጥቶ የጣላቸው ምንድን ነው? በራሳቸው ልክ መጥነው ማሰባቸውና የራሳቸውን አረዳድ እንዳለቀለት እውነት ማቅረባቸው አይደለምን?

ሊቁ አባ ጀሮም "መርቅያንና ባሲሊድስ፣ እና ሌሎችም መናፍቃን ኹሉ... የእግዚአብሔርን ወንጌል ገንዘብ አላደረጉም። ... ወንጌል ማለት ትርጒሙ (ሐሳቡ፣ መልእክቱ) ነው እንጂ ገጸ ንባቡ ነው ብለን አናስብም፤ በውጫዊ ቆዳው ሳይኾን በውስጣዊ ይዘቱ፣ በስብከቱ ቅጠሎቹ ላይ ሳይኾን በትርጒም ሥሩ ነው እንጂ። በዚህ ኹኔታ መጽሐፍ ቅዱስ ለሚያነቡትና ለሚሰሙት በእውነት የሚጠቅማቸው የሚኾነው ያለ ክርስቶስ የማይነገር ሲኾን ነው፥ ከአባቶች አስተምህሮና አረዳድ ሳይለይ የቀረበ ሲኾን ነው፥ የሚሰብኩት ሰዎች ያለ መንፈስ ቅዱስ የማይናገሩ ሲኾኑ ነው። ... የክርስቶስን ወንጌል በተጣመመ አተረጓጎም የሰዎች ወንጌል እንዳናደርግ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለ ጥንቃቄ መናገር ታላቅ አደጋ አለው።" እንዲል። (in Galat, I, 1. II. M.L. XXVI, c. 386) (ያረጋል አበጋዝ (ዲያቆን)፣ መድሎተ ጽድቅ ቅጽ 2፣ 2013 ዓም፣ ገጽ 176)። እንግዲህ አዋልድ መጻሕፍት የዐሥራው መጻሕፍት ልጆች ናቸው ካልን ልጅ አባቱን በሚመስልበት መንገድ እናየዋለን እንጂ በደረቁ ስሕተት ይገኝባቸዋልና እያልን ባላወቅነው ኹሉ በድፍረት መናገር ድፍረትም አለፈ ሲልም ነውርም ነው።

የአንድን ሰው አረዳዱን ኦርቶዶክሳዊ እስካላደረግነው ድረስ ምንም ያህል ዝቅ ብንል ላይረዳ ይችላል። ከዚያ ይልቅ ራሱን ብቁ ገምጋሚና አስተካካይ፤ የሃይማኖታዊ ጉዳይ ሚዛን በማድረግ ስሕተት ውስጥ እንዳይወድቅ ልንጠነቀቅለት ይገባል። መሠረታዊውን አስተምህሮ የተረዳ ነው፤ ምንም ነገር አያናውጸውም። የተኛውንም ንባብ ከወንጌል እውነታ አንጻር ነው የሚያየው እንጂ በውስጡ ባለ ምናባዊ ሥዕል ችግር አይፈጥርም። አምላክ ሰው ኾነ የሚለው እኛን የማይረብሸን ሙስሊሞችን ግን ለመቀበል የሚከብዳቸው በእነርሱ መጠን ውስጥ አድርገው ስለሚያስቡት ነው። የማስረጃ ዓይነት ቢጠቀስላቸው እንደ ተረት የሚቆጥሩት የተዘጋ አረዳድ ስላለ ነው። ይህን ዝግ የኾነ አረዳድ ካልከፈትንላቸው ነጻ ሊወጡ አይችሉም። ልክ እንዲሁም የኑፋቄ ዝናም ዘንቦባቸው፣ የክሕደት ጎርፍ ውስዷቸው ከእውነተኛው በረት ውጭ የነበሩ አካላትም መጀመሪያ ማጥራት ያለባቸው አረዳዳቸውን ነው። ንባብ ላይ ብቻ እየሄዱ መለጠፍን ማቆም አለባቸው። "ንባብ ይቀትል ወትርጓሜ የሐዩ ሕይወተ" ንባብ ይገድላል ትርጓሜ ሕይወትን ይሰጣል የሚለውን ልብ ይበሉት።

ይህን አካሄድ ትተን ይህን አልቀበልም ይውጣ ይጸናል ዓይነት አካሄድ ከጀመርን ለኔ የሚታየኝ መርቅያን ነው። ጌታችን "በኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ያደርጋል፤ ከእኔም የሚበልጥ ያደርጋል" ሲል ስናነብ ይህ በጣም ይጸናል፤ ተገላበጠ እኮ! ፍጡር ፈጣሪ የሚያደርገን እንዴት ያደርጋል? ከዚያም ብሶ ፈጣሪ ከሚያደርገው በላይ ያደርጋል ይባላልን? ኧረ ይሄስ ይውጣ ሊባል ነውን? "ሰላምን ላመጣ የመጣው አይምሰላችሁ ሰይፍን እንጂ" ሲል ስናነብ እንዴ ጨካኝ ነው ማለት ነውን? ይህን እንዴት ያደርጋል ልንል ነውን? "ከኔ አብ ይበልጣል" ሲል ታዲያ ከአብ የሚያንስ ከኾነ እንዴት ልናመልከው እንችላለን? ይህ ንባብ ያሰናክላልና በሌላ ግልጽ ንባብ ይቀየርልን ልንል ነውን? ጌታ በወንጌል "ነገር ግን እነዚያን በላያቸው ልነግሥ ያልወደዱትን ጠላቶቼን ወደዚህ አምጧቸው በፊቴም እረዱአቸው" ሉቃ 19፥27 ስላለ ግድያን እየበረታታ ነውና ይህ ምንባብ ይውጣ ይባላልን?
መዝ 136፥9 "ሕፃናቶችሽን በዓለት ላይ የሚፈጠፍጥ ብፁዕ ነው" ይላል። ይህ ንባብ ጸነን ያለ ነውና ለመረዳት ስለሚያስቸግር ይውጣ ሊባል ነውን? "ኀጥእ የጻድቅ ቤዛ ነው፤ በደለኛም የቅን ሰው ቤዛ ነው፡፡" ይላል መጽሐፍ ቅዱስ፡፡ ምሳ 21፡18፡፡ ኀጥእ እንዴት የጻድቅ ቤዛ ነው ይባላል? ስንኳንስ ኀጥእ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ጻድቃን ስንኳን ቤዛ አይባል ይሉ የነበሩ ይህን ንባብ እንዴት ሊቀበሉ ይችላሉ? እንግዲህ እንዲህ እያልን ከሄድን የሚቀረን ምንድን ነው? የምንደርሰውስ ወዴት ነው? ስለዚህ ጭንቀታችን መኾን ያለበት ንባብ ላይ ሳይኾን አረዳድ ላይ ነው ሊኾን የሚገባው።


+#አዋልድ_መጻሕፍት_ለሃይማኖት_ማስረጃ_ኾነው_አይጠቀሱምን?+++

[] የሚጠቀሱ አሉ፤ የማይጠቀሱም አሉ!

አንዳንዴ ገድላትም ሃይማኖታዊ ጉዳይ ለማስረዳት ይጠቀሱ ይኾናል።

ለምሳሌ በሃይማኖተ አበው " ቅዱስ ባስልዮስ ... ስለ ቦሊጣ ሰማዕት በተናገረው ድርሳኑ ስለኛ እግዚአብሔር በሰው መካከል ተገለጠ፤ ብሉይ ሥጋን ለማደስ ቃል ሥጋ ኾነ፤ ባሕርያችንንም ገንዘብ አደረገ፤ የኃጢአት ምርኮኞችን ነጻ የሚያወጣቸው፥ ከበደለኞች ጋር ተቈጠረ፤ በጨለማ ውስጥ ለነበሩ ሰዎች እውነተኛ ፀሐይ ወጣላቸው፤ የማይታመመው በመስቀል ላይ ታመመ፤ ሕይወት እርሱ ሞተ፤ ብርሃን በሲኦል ተገለጠ፤ የተቀበሩትን የሚያነሣ እርሱ ከሙታን ጋር ተቈጠረ ብሎ ተናገረ" ይላል። (ሃይ ዘባስልዮስ ምዕ 96፥42)።

- "የቤተ ክርስቲያን ዐምድ ቅድስ ባስልዮስም ስለ ኢየሉጣ ሰማዕት በተናገረው ድርሳኑ አምላክ ስለኛ ሰው ኾነ፤ በሰው መካከል ተመላለሰ፤ ከተገፉት ጋር የሚገፋ ኾነ፤ የተጎዱትን ያድን ዘንድ ረዳት ለሌላቸውም ረዳት ይኾናቸው ዘንድ ይህን ኹሉ ሠራ፤ ቀድሞ ሥጋ ያልነበረው ዛሬ ሥጋን ተዋሐደ፤ ተሰቀለ፤ ሕይወት እሱ በሥጋ ሞተ፤ ብርሃን እሱ ወደ ሲኦል ገባ፤ ይህም ኹሉ የኾነው አዳምና ልጆቹም ስለ ተጎዱ ነው አለ" እንዲል። (ሃይ ዘዮሐንስ (የአንጾኪያ፣ የሶርያ፣ የባቢሎን ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሐንስ) ምዕ 114፥20)።

- አድማሱ ጀንበሬ በአጽንዖት የሚሉን አለ፦ "ሃይማኖተ አበው፣ አፈወርቅ፣ ቄርሎስ፣ ፍትሐ ነገሥት፣ 14ቱ ቅዳሴያት፣ ፊልክስዩስ፣ ማር ይስሐቅ፣ አረጋዊ መንፈሳዊም ሠለስቱ ምዕት በፍትሐ ነገሥት ከቈጠሯቸው ጋር አንድ ኾነው ይቆጠራሉ። ቅዱሳት መጻሕፍት ይባላሉ።" ይላሉ። (አድማሱ ጀንበሬ፣ ኰኵሐ ሃይማኖት፣ 2012 ዓ.ም፣ ገጽ 176)። ለአበው የትርጓሜያት መጻሕፍትና ሥርዓተ አምልኮትን የሚፈጸምባቸው የሥርዓት መጻሕፍትን እንዲሁም ኅብስትና ወይን ቀርቦ ወደ አማናዊው ቅዱስ ሥጋና ደም (ቅዱስ ቍርባን) የሚለወጥበት ጸሎት የሚከወንበትን የቅዳሴያት መጻሕፍት እንዴት በጥንቃቄ እንደ ጠቀሷቸው ልብ እንበል። እነዚህን አዋልድ መጻሕፍት እንደ መሠረታዊ መጻሕፍት አድርገው መጥቀሳቸውን ልብ ማለት ይገባል። ከዚህ በተጨማሪ በጒሜ ትምህርት የሚሰጥበትን የምንኲስናን ሕይወት ማዕከል አድርጎ የተዘጋጀውን መጽሐፍም ትልቅ ቦታ እንዳለው ይጠቁሙናል። አድማሱ ጀንበሬ ፕሮቴስታንታዊውን መናፍቅ "... እንግዲህ የእግዚአብሔርን አምላክነት ከሚናገሩት መጻሕፍት ውስጥ ይህ ሰው የጻፈው ነው፤ ይህም አዋልድ ነው፤ አልቀበልም ማለት የተሳሳተ ንግግር መኾኑን ትረዳ ዘንድ ..." ይላሉ። (እንደ ላይኛው ገጽ 168)። እንዲሁ በመሰለን ተነሥተን ይሄን አልቀበልም፣ ይህን እቀበላለሁኝ እያልን በመጻሕፍት ተጽፈው ለተቀመጡ ምንባባት የራስን አእምሮ መጣኝ ወይም መዛኝ ከማድረግ ስሑት አካሄድ እንድንወጣ ይመክሩናል። ማንኛውንም ሃይማኖታዊ ጉዳይ በራስ መረዳት ልክ አድርጎ መጓዝ ኦርቶዶክሳዊ አካሄድ ካለመኾኑም በተጨማሪ መዳረሻው በትዕቢት እሾህ ተወግቶ በክሕደት ገደል ውስጥ መግባት ነው።

አድማሱ ጀንበሬ መልክአ ማርያምን ጠቅሶ ለሚተቸው ፕሮቴስታንት ሲመልሱ "ከዚህ ከፍ ብሎ በሚገኘው መሥመር መጻሕፍት ማታለያ አዋልድ የተባሉ ልብ ወለድ መነኰሳቱ ሰበኩት ብለህ አዋልድ መጻሕፍትን ስትነቅፍ ተናግረህ ነበረ። እኛ ከጸሎት በቀር ለሃይማኖትና ለምግባር ምስክር አድርገን የማንጠቅሳቸውን መልካ መልኮችን በቂ ምስክሮች አድርገህ ከጠቀስክልኝ ከላይ የተናገርከውን አዋልድ መጻሕፍት ማታለያ መባላቸው ቀርቶ ባንተው ቃል ተሠይመው ለምስክርነት የበቁ እውነተኞች መጻሕፍት መኾናቸውን ማረጋገጥህን አስተውል። እንግዲህ አንተ የጠቀስካቸውን አዋልድ ምናልባት እኔ የጠቀስኩልህ እንደ ኾነ ቅር እንዳይልህና ሰው እንዳይታዘብህ አደራ" ይላሉ። (እንደ ላይኛው ገጽ 85-86)። ይህ ደግሞ በአንድ በኩል እንደ መልካ መልኮች ዓይነት መጻሕፍት የተዘጋጁበትን ዓላማ የሚያሳስብ ነው በሌላ በኩል አዋልድ መጻሕፍትን አልቀበልም የሚሉ መናፍቃን ያን አናምንበትም ያሉትን መጻሕፍት ጠቅሰው የመሞገት ሥልጣን እንደ ማይኖራቸው አመልካች ነው። እንግዲህ መጻሕፍትን ባልተጻፉበት ዐውድ መገምገም ፍጹም ስሑት የኾነ አካሄድ መኾኑን ልብ ከማለት ጋር አዋልድ መጻሕፍትን የማይቀበሉ መናፍቃን ለማዘናጋት የሚሄዱበትን መንገድ መለየት ያስፈልጋል።

ሌላው እዚህ ጋር ልብ ማለት የሚገባን የጸሎት መጻሕፍት ኹሉ ለሃይማኖት አስረጅ ተደርገው አይጠቀሱም ግን አይባልም። ለምሳሌ ውዳሴ ማርያም፣ 14 ቅዳሴያት፣ ... ሊጠቀሱ ይችላሉና። በኦርቶዶክስ የምናምነውን እንጸልያለን የምንጸልየውንም እናምናለን የሚለውን መሠረታዊ ሐሳብ ቸል የምንል አይደለምና። ዶግክትሪናችንን በራሱ እንደምንጸልየው ልብ ማለት ይገባልና። ጸሎተ ሃይማኖት ብለን የምንጸልየውም ለዚህ ማሳያ መኾኑ ግልጽ ነውና። መሠረታዊ ዓላማቸው ግን ርእሰ ጉዳያቸውን ማዕከል ያደረገ መኾኑን ልብ ማለት ይገባል። የተለያዩ ዓይነት አዋልድ መጻሕፍት አሉ ማለታችንም ከርእሰ ጉዳያቸው አንጻር ነው። ዋና ጉዳይ ያደረጉትን ትተን ወደ ሌላ ወስደን ቸኩል ድምዳሜ ውስጥ መግባት አይጠበቅብንም።

በቦሩ ሜዳ ላይ ሦስት ልደት የሚል ከመጻሕፍት ምንጭ አምጣ ሲባል "በደብረ ብርሃን በሚገኝ ተአምረ ማርያም ላይ አለ" ማለቱ ትችትን ያመጣበት ተአምረ ማርያምን አንቀበልም ለማለት ወይም አያስፈልግም ለማለት ሳይኾን ሃይማኖታዊ ዶክትሪንን ለማስተማር ታቅዶ የተጻፈ አይደለም ለማለት ነው። የተአምር ማርያም ዋና ዓላማው እግዚአብሔር በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አድሮ ያደረገውን መክራት ማሳየት እንጂ ትምህርተ ቤተ ክርስቲያንን ማስተማር አይደለምና። ብዙ ጊዜ Missing the point Fallacy (ነጥቡን የመሳት ስሕተት) ይሠራል። አዋልድ መጻሕፍት ሲጠኑ ከተጻፉበት መሠረታዊ ሐሳብ አንጻር ይገመገማሉ እንጂ ወደ ሌላ ዘወር ተደርገው ሊገመገሙ አይገባም። ተአምር የሚታየው ከታምር አንጻር ነው፤ ገድልም ከገድል አንጻር፤ ሌላውም ከዚያ አንጻር እንጂ ገድልን ሃይማኖተ አበው፥ ሃይማኖተ አበውንም ገድል አድርጎ ማሰብ መሠረታዊውን ነጥብ መሳት ነው። የቦሩ ሜዳው ጒባኤ አዋልድ መጻሕፍት ብዙም ጥቅም እንደሌላቸው አስረጅ ሳይኾን እንዲያውም እጅጉን ጠቃሚ መኾኑን ጠቋሚ ነው። ኹለት ልደት የሚለው በዋነኛነት ትክክል መኾኑ የተረዳው በሃይማኖተ አበው ባሉ ምንባባት ነውና። ሃይማኖተ አበው ደግሞ ቍጥሩ ከአዋልድ መኾኑ ግልጽ ነው። ከዚያ ውጭ ያልተባለን ማለት አግባብ አይደለም። ይህም ማለት ተአምረ ማርያምን ሃይማኖተ አበው አድርጎ ከማሰብ ነጥብን ከመሳት ስሕተት መጠበቅ ይገባል።

ታምራትን በተመለከተ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ የቅድስት ማክሪንን ሕይወት ሲጽፍ የሰጠው ጠቃሚ አስተያየት አለ። ይኸውም፦ "በጣም ትንሽ እምነት ያላቸውና በእግዚአብሔር ስጦታ የማያምኑ ሰዎች ወደ መጎዳት እንዳይመጡ፥ በዚህ ምክንያት ታላቅ ታምራትን መጻፍ ትቼያለሁኝ፤ ስለዚህ እንደማስበው ከኾነ አስቀድሜ ያልኹት የማክሪንን ታሪክ መጽሐፍ ለመፈጸም በቂ ነው።" ይላል። (The Life of SAINT MACRINA BY Gregorry, BisHop of Nyssa /Translated, with introduction and notes, by Kevin Corrigan p.54)። ይህ እንግዲህ አስተውሎት ያለበት ጥንቃቄ ነው። ይህን ሊቁ ማለት በፈለገበት መንፈስ ብቻ ኾነን የምንረዳው እንጂ ታላላቅ ታምራት በዐሥራው መጻሕፍት ውስጥ ተጽፈው ስለምናገኝ




ስለ ገድላት ማስተዋል የሚሹ ጉዳዮች
--
#አስፈላጊነታቸው፡- ለድርድር አይቀርብም፡፡ የክርስትና ሕይወት በሞት አይቋረጥም ለሚለው አቋማችን ምስክሮች ናቸው፡፡ በአስፈላጊነታቸው ላይ የሚሰጥ የማርያም መንገድ የለም፡፡ ገድላት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን የተቀደሱ የአገልግሎትና የጸሎት መጻሕፍት መካከል ናቸው፡፡

#ይዘታቸው፡- የገድልት ይዘት ‹‹ገድል›› ነው፡፡ በጠባዩ የሃይማኖት መግለጫ፣ የታሪክ ሰነድ፣ ግለታሪክ፣ የሕይወት ታሪክ፣ ቀኖናዊ መጽሐፍ (መጽሐፍ ቅዱስ)፣ ወዘተ. አይደለም፡፡ ገድል ነው! ገድል አንድ የቤተ ክርስቲያን የሥነ ጽሑፍ ክፍል ነው፡፡ መነበብም ሆነ መመዘን ያለበት፣ መቃናትና መታረምም ያለበት፣ መጠናትም ያለበት በዚያ መንገድና ዐውድ ነው፡፡

#ፈራጁን_ጠርጥሩ፡- ገድላት ከሥነ ጽሑፍና ከቅጂ አንጻር ውጫዊ የሆነ ጥናት በፊሊዮሎጂ ይጠናሉ፡፡ በነገ መለኮት ኮሌጆች ግን የሚገባውን ያህል እየተጠኑ አይመስለኝም፡፡ በጉባኤ ቤት ውስን ድርሳናት እንደየአጥቢያው በተማሪው ይነበባሉ፡፡ ገድል ሕይወት በተግባር የተተረጐመበትን ታሪክ ስለያዘ እንደ ገቢራዊ ማሳያ ይጠቀሳል፡፡ መጥቀስና ማጥናት ተቀራራቢ አይደሉም፡፡ ዳኝነት ለመስጠት አያበቁም፡፡ ስለዚህ ገድላት ላይ ከውስጥም ቢሆን የሚሰጡ አስተያየቶች በተገቢው ንባብና ጥናት መመርኮዛቸው ላይ ጥርጣሬ አለን፡፡ ትልልቆቹ የሀገራችን የጥናት ሰዎች እነ ፕ/ር ጌታቸው፣ ፕ/ር ታደሰ፣ ከውጪም ስቴፈን ካፕላንና የመሳሰሉ አጥኚዎች ገድላትን በስፋት አጥንተዋል፡ ጥናታቸው ግን በሃይማኖት ዐይን አይደለም፡፡ በታሪክና በሥነ ድርሳን መነጽር ነው፡፡ በእነሱ መነጽር ገድላትን እንዲህ ናቸው ማለት ሃይማኖትን በታሪክና በሥነ ድርሳን ሕግጋት መዳኘት ይሆናል፡፡ በአጭሩ ገድላት ተገቢውን ኦርቶዶክሳዊ የጥናት ዐይን ይፈልጋሉ፡፡ በዚህ ረገድ ቀሲ ዶ/ር አምሳሉ ተፈራ (የነቅዐ መጻሕፍት ደራሲ) ደስ ብሎኝ እጠቅሳቸዋለሁ፡፡ የፕ/ር ጌታቸው ‹‹ስለግዕዝ ሥነ ጽሑፍ የተሰበሰቡ አንዳንድ ማስታወሻዎች›› የተሻለ ሃይማኖታዊ መነጽር አለበት (‹‹ከግዕዝ ሥነ ጽሑፍ ጋራ ብዙ አፍታ ቆይታ›› ከሚለው በተለየ)፡፡

ለሰማዕያንና አንባብያን ያለን ምክር፡- አብዛኛው የውስጥም ሆነ የውጭ ተናጋሪ ስለገድላት ሲናገር ንባቡን ጠርጥሩ! ግምቱን ነው ወይስ ንባቡን? ቁንፅል ዕውቀቱን ነው ወይስ ጥናቱን? ሥራዬ ብሎ ውሎበታል አልዋለበትም? የሚለውን ጠርጥሩ! ብዙ ፈትነን ያረጋገጥነው ምክንያታዊ ጥርጣሬ ስለሆነ! የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ ማስመስከር ወይም የሥነ መለኮት ምሩቅ መሆን ስለገድላት በሥልጣን ለመናገር መብት እንደሚሰጥ ተደርጎ መታመኑ መበረታታት ያለበት ተግባር ሆኖ አይታየንም፡፡

#የመሥዋዕቱ_ማሳረጊያ፡- የቤተ ክርስቲያን ዋነኛ የአምልኮ መፈጸሚያ ቅዳሴው ነው፡፡ በቅዳሴ ውስጥ የሚነበቡት መጻሕፍት ከመጽሐፍ ቅዱስ የተመረጡ 4 ምንባባት (ከመልእክታት፣ ከሐዋ.ሥራና ከወንጌል) ብቻ ናቸው፡፡ ገድል በቅዳሴ አይነበብም (የቅዳሴውን አንድምታ ትርጓሜ ገጽ 96 ማየት ይቻላል)፡፡ የመሥዋዕት ማሳረጊያው ቅዱስ መጽሐፍ ነው፡፡ ገድላት ከቅዳሴ በኋላ ወይም በፊት ለማጽኛና መጽናኛ ይነበባሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ለቅዱስ ወንጌል በምትሰጠው ቦታ ላይ ብዥታ የለም፡፡

#ገድላትና_ድርሳናት_ለሃይማኖት_ማስረጃነት፡-

(1)ገድላትና ድርሳናት በቤተ ክርስቲያን ለቅዱሳት መጻሕፍት መተርጐሚያና ማብራሪያነት ይጠቀሳሉ፡፡ በነገረ ሃይማኖት ረገድም በቀደሙት አበው ዘንድ ገድላትና ድርሳናት ለሃይማኖት ማስረጃነት ሲጠቀሱ እናያለን (ሃይ.አበ.ዘባስልዮስ ም.96፡42 እና ዘዮሐንስ 114፡20)፡፡ በቦሩ ሜዳ ጉባኤ ሦስት ልደቶች ከደብረ ብርሃኑ ተአምረ ማርያም መጥቀሳቸው የተነቀፈበት ዐውድ መለጠጥ የለበትም፡፡

(2)መጀመሪያ ወደ ምንጭና ሥልጣን ወዳለው ንባብ ክርክር የተሔደው ያላስማማ ኃይለ ቃል ስላለ ነው፤ የተአምሩ አስፈላጊነት ላይ ክርክር የለም፤ ቦሩ ሜዳ ክርክርና ጥያቄ ሲነሣ በበላይነት መምራት ያለበትና ልንከተለው የሚገባው ዋነኛው የበላይ ገዢ የክርስትና ሕግ መጽሐፍ ቅዱስ ነው በሚል የተነገረበት ነው፤ ጥያቄ በማይነሣባቸውና በትርጉም ባላከራከሩ ነጥቦች መጠቀሱ ይቀጥላል፤ ማረም ቢያስፈልግ የደብረ ብርሃኑ ተአምረ ማርያም የሦስት ልደቶችን በመደገፍ የተጻፈው ክፍል ተለይቶ ይታረማል እንደማለት ነው፡፡ እናስተውል! ገድል ቀኖናዊ መጽሐፍ (Canonical Book) አይደለም! አዳዲስ ተአምራት ሲፈጸሙ ተጨምረው ይጻፋሉ፤ የተፋለሱ ምንባባት ይቃናሉ፡፡

(3)የቦሩ ሜዳ ጉባኤ ውሳኔ የቤተ ክርስቲያን የዶግማ መግለጫዎችን በምንረዳበት ጊዜ ስለሚኖረን የምንጮች ተዋረድ(Hierarchy of sources)ና ምንጮች ሲያከራክሩ በስተመጨረሻ በየትኛው ፍጹማዊ መስፈሪያ እንደሚፀኑ (በሕግ validity requirement እንደሚባለው) በሚያስታውቅ ዐውድ የተነገረ መሆኑን መረዳት ይገባል፡፡ በጉባኤው ‹‹ሁለት ልደት›› ተብሎ የተወሰነው በዋናነት በሃይማኖተ አበው ምንባባት ነው፤ ሃይማኖተ አበው ቁጥሩ ከድርሳን ነው፡፡ እዚህ ላይ ድርሳን የሚለው የግእዝ ቃል የመጽሐፍ ማብራሪያን (Homily) እና የመላእክት/ቅዱሳን ድርሳንን (Encomium) ስለሚጠቅልል ዐውዱ እንዳያሳስተን፡፡
--
የመልእክቱ ጭብጥ፡- በገድላት ጉዳይ የማርያም መንገድ ለመስጠት አንፋጠን!

ሦስት ነገሮች ይቅደሙ፡-
(1)የገድላቱን አስፈላጊነት አምኖ መነሣት፣
(2)በሃይማኖታዊ መነጽር ማጥናት፣
(3)ማቅናት፣ የቀናውን ማጽናት፡፡
--
በቀናች ሃይማኖት አጽንቶ ከቅዱሳኑ ይደምረን! አሜን!!!
✍️ደብተራ በአማን ነጸረ እንደጻፉት






ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የ2017 ዓ.ም የጾመ ነነዌ የሰላምና የጸሎት አዋጅ መግለጫ
ሙሉ መልእክት የሚከተለው ነው፡፡

ጥር 29 ቀን 2017ዓ.ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>>
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተላለፈ የምህላ ሱባዔ፡-
‹‹ቀድሱ ጾመ ወስብኩ ምህላ አስተጋብኡ ሕዝበ ሊቃውንተ ሕዝብ፤ ጾምን ቀድሱ፣ጉባኤውንም አውጁ፤ሽማግሌዎችንና በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ወደ ኣምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ቤት ሰብስቡ፤ ወደ እግዚአብሔርም ጩኹ (ኢዩ ፩÷፲፬)

ሁላችንም እንደምናውቀው ያለንበት ዓለም የመከራ ዓለም ነው፣ መከራው በኛ ስሕተትና ክፋት የመጣና እየሆነ ያለ መሆኑም ይታወቃል፤ እኛ የምንፈጽመው ጥቃቅንና ትላልቅ ግብረ ኃጢአት እግዚአብሔርን እንደሚያስቈጣ በቅዱስ መጽሐፍ ተረጋግጦ ያደረ ነው፤ ለዚህም ከነነዌ ነዋሪ ሕዝብ የበለጠ ማስረጃ የለንም፤ የነነዌ ከተማ ነዋሪዎች በፈጸሙት ግብረ ኃጢአት እግዚአብሔርን አስቈጥተዋል፤ ድርጊታቸው እግዚአብሔርን የሚያስቆጣ ቢሆንም እሱ ምሕረቱን ማስቀደም ስለፈለገ በዮናስ በኩል አስጠንቅቆአቸዋል፤ የነነዌ ነዋሪዎችም በዮናስ በኩል የደረሳቸውን የንስሓ ጥሪ ወዲያውኑ ተቀብለው በምህላ፣ በጾም፣ በጸሎት ንስሓ ስለገቡ እግዚአብሔር ፍጹም ይቅርታ አድርጎላቸዋል፤

• የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያን ልጆቻችንና ወገኖቻችን !

እኛ ሰዎች ዛሬም በየሰዓቱ ብቻ ሳይሆን በየደቂቃው እግዚአብሔርን የሚያስቆጣ አበሳ እንደምንፈጽም ማወቅ ኣለብን፣ አበሳውና ኃጢኣቱ ሲበዛ እግዚአብሔር እውነተኛ ዳኛ ነውና ወደ ዳኝነት ተግባሩ ይገባል፤ይህ ደግሞ በሰብአ ትካት በሰዶምና በጎሞራ ያስተላለፈውን ዳኝነት ያስታውሰናል፤ አሁን ያለንበት ዘመን ዓመተ ምሕረት በመሆኑ እግዚአብሔር ለጊዜው ቢታገሠንም በኃጢኣታችን የምንጠየቅበት ጊዜ አዘጋጅቶአል፤ ዛሬም ቢሆን የማናስተውለው ሆነን ካልሆነ በስተቀር እግዚአብሔር ተግሣጹን ማስተላለፍ አላቆምም፤ በምድራችን ላይ በምናደርሰው የተዛባ ተግባር በጐርፍ፣ በድርቅ፣ በመሬት መንቀጥቀጥና በአየር መዛባት እየገሠጸን እንደሆነ ማስተዋል አለብን፤

እግዚአብሔር ከጥንቱ ከጠዋቱ ጀምሮ ምድርን እንድንከባከባት፤ እንድናበጃት፣ እንድናጠብቃትና እንድናለማት አዞናል፤ ሆኖም ይህን ትእዛዙን ገሸሽ አድርገን በኬሜካልና በመርዛም ጋዝ ምድርን በመበከል፣ደንዋን በመመጠርና ራቁቷን በማስቀረት በምናደርገው ድርጊት አበሳ እየፈጸምን እንደሆነ ያወቅነው አይመስልም፤ በዚህም ምክንያት በጐርፍ፣ በድርቅ ለሰው ልጆች በማይመች የኣየር ፀባይ ወዘተ . . . ስጋት ውስጥ እየወደቅን ነው፤

በሌላም በኩል በምናወሳስበው የአስተዳደር ርእዮትና መሳሳብ የእግዚአብሔር ገንዘብ የሆነውን ሕዝብ እርስ በርሱ እንዲጋጭና ያላስፈላጊ አደጋ ላይ እንድወድቅ እያደረግን ነው፤ በዚህም ጠንቅ ሰላም እየደፈረሰ፣ ፍቅርና አንድነት እየላላ የሃይማኖት ክብርና ልዕልና እየተነካ ራሳችንንም እየጐዳን ነው፤በዚህ ሁሉ ተግባራችን እግዚአብሔርን እያሳዘንን ነው፤ ይህ ሊገባንና ሊቈረቁረን ይገባል፤
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት
ለችግሮች ሁሉ መፍትሔ አላቸው፤ መፍትሔውም የሚገኘው ከእግዚአብሔርና ከእኛ ነው፤ ከእኛ በንስሓ ተመልሰን ከልብ እግዚአብሔርን ይቅርታ መጠየቅና ከክፉ ተግባራችን በእውነት መጸጸት ይጠበቃል፤ እግዚአብሔር ደግሞ ይህንን ዓይነቱ ንስሓ ከኛ መኖሩ ሲመለከት ምሕረትና ይቅርታን ይለግሰናል፤በዚህም መፍትሔና ፈውስ ይገኛል፤ ከዚህ አንጻር በአሁኑ ጊዜ ለሀገራችንና ለዓለማችን ስጋት የሆኑ የጦርነት ክሥተቶች፣ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ የአየር መዛባት፣የድርቅ መከሠት፣የጎርፍ መጥለቅለቅ የሰላም መደፍረስ፣ የሰላማውያን ወገኖች መጎዳት፣ የፍቅርና የአንድነት መላላት ወዘተ. . . . ከምድራችን ተወግደው ፍጹም ምሕረትና ሰላም እናገኝ ዘንድ በኃጢኣታችን ተጸጽተን በምህላ ንስሓ መግባት አለብን፤

ከዚህ አኳያ ከጥንት ጀምሮ በቤተክርስቲያናችን ቀኖናዊ ሥርዓት መሠረት በየዓመቱ የሚጾመው ጾመ ነነዌ ለዚህ አመቺ ጊዜ ስለሆነ ከየካቲት ፫ ቀን ፳፻፲፯ ዓመተ ምሕረት ጀምሮ ለሦስት ቀናት ከልኂቅ እስከ ደቂቅ ሁላችንም ጠዋትና ማታ በየቤተክርስቲያኑ ዐውደ ምሕረት እየተገኘን በንስሓ በዕንባ በጸሎት በምህላ የእግዚአብሔርን ምሕረትና ይቅርታ እንድንጠይቅ፤ እንደዚሁም በሀገራችንና በውጭ ያላችሁ ሊቃውንተ ሕዝብ ቀኖናውን ጠብቃችሁ ይህንን በማስፈጸም ምህላውን በቀኖናው መሠረት እንድታከናውኑ በእግዚአብሔር ስም አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን፤

እግዚአብሔር አምላካችን ምሕረቱን ይቅርታውንና ሰላሙን ለሀገራችንና ለዓለማችን ይስጠን፤ ምህላችንንም ይቀበልልን፤
“እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ” ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!!
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስምወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት
ጥር ፳፱ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
ፎቶ መልአከ ሰላም አባ ኪሮስ ወልደአብ




እየው ስሙር ሲያሰምረው

ሲሆን ሲሆንማ የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ማለት እንደ ደጉ ሳምራዊ ወንበዴዎች በተባሉ አጋንንት ተደብድበው ወድቀው መስማት መልማት ያልቻሉትንም አይቶ ማዘን፣ አዝኖ መቅረብ፣ ቀርቦ ቁስላቸውን ማጠብ፣ ወይንና ዘይት አድርጎ ማሠር፣ ማንሣት መሸከም የእንግዶች ማረፊያ ወደተባለች ቤተ ክርስቲያን አምጥቶ ማዳን ነበረ። አሁን ያለው ግን በግልባጭ ነው። ወደ ቤተ ክርስቲያን ማቅረብ ሳይሆን ድካም ያለበትን አውጥቶ ለመጣል መድከም፣ የወደቀ ማንሣት ሳይሆን የሚፍገመገመውን ለመጣል መታገል ነው። ይህም ሆኖ ደግሞ ራሳችን ችለን ያልቆምን ሰዎች የቆምን መስሎን መድከማችን ያሳዝናል። ቅዱስ ጳውሎስ "ማንም የቆመ የመሰለው ቢኖር እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ" ያለውም ትዝም አይለንም። እግዚአብሔር ልቡና ይስጠን።
ለሁሉም ስሙር የሆነ አሳብ ነውና ያስምርልን።

✍️ዲያቆን ብርሃኑ አድማስ




የተሰበረ ጽዋዕ
እዚኽ ፎቶ ውስጥ በአካል የማውቀው ዘማርያምን ብቻ ነው፡፡ ሌሎች ግን በማኅበራዊው ሚዲያ መልስ ሲሰጡና ሲጠይቁ አያቸዋለሁ እንጂ ፊት ለፊት ተገናኝተን አናውቅም፡፡በወንድሞቻችን ፊት ፕሮቴስታንት ሰባክያን ምላሳቸውን ሲተሳሰር ብዙ ጊዜ አይቻለኹ፡፡ ሌላ ጊዜ ደግሞ "ከኦርቶዶክስ ወንድሞች ጋር እንዳትከራከሩ" የሚል አዋጅ ሲያውጁ ሰምቻለኹ ጰንጤዎቹ፡፡
በአጭሩ፥ እኒኽ ወንድሞቻችን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቅዱሳን መላእክትና ሰዎችን ታመልካለች የሚለውን ፕሮቴስታንታዊ የድር ምሽግ ሲበጣጥሱ ተመልክቻለኹ፡፡ ከዐይን ያውጣችኹ አልላችኹም፡፡ ዐይንም ጆሮም ውስጥ ናችኹና፡፡
ጽንዑ ወኀይሉ፡፡ ለማለት ነው አመጣጤ፡፡
ከእኒኽ ወንድሞች መኻል አንዱ ወይም ኹሉም ሊሳሳቱ የሚችሉ ናቸው፡፡ የቀለም ሠረገላ የማያሰናክለው የለምና፡፡
ደግሞም እኔ እንኳ የሰማኋቸው የሚታረሙ ስሕተቶች አሉ፡፡የሚታረም ነገር ተገኘ ማለት ግን፥ ሙሉ እርሻው አረም ነውና አያስፈልግም የሚል ቧልት መናገር ግን ቅንነትና ወንድማዊ ፍቅር ይጎድለዋል፡፡
በአንድ ወቅት፦
አንድ እጅግ የተከበሩ ሊቅ ከአንዲት ሴት ጋር ድቀት አገኛቸው፡፡ እኒኽን ሊቅ ብዙ ሰው ያውቃቸዋል፡፡ በዚኽኛው ታሪክ ግን ሰፊው ሕዝብ ስለማያውቃቸው ስማቸውን ልለፈው፡፡
ይኽን ድቀታቸውን የሰማ ደብተራ አንድ ቀን ማሕሌት ውስጥ አገኛቸው ሊቁን፡፡"ደግሞ አንተ እዚኽ ምን ልታደርግ ገባኽ?"
ሲል በፍና ተሣልቆ አፌዘባቸው፡፡ እርሳቸውም "እኔኮ የተሰበርኩ ጽዋዕ ነኝ" ብለው አንጀት የሚበላ መልስ ሰጡት፡፡
የተሰበረ ጽዋዕ ሰባራ ስለኾነ አይጣልም፡፡ንዋይ ቅዱስ ነውና በክብር ከዕቃ ቤት ይቀመጣል እንጂ፡፡
እንደዚያ ደብተራ ለቤተክርስቲያን የቀናን እየመሰለን ጥቂት ሸራፋ ያገኘንባቸው ጽዋወችን ኹሉ አውጥተን እንጣል ማለት እጅግ የከፋ በደል ነው፡፡ክርስቶሳዊውን መንገድ የረሳ ነውና፡፡ "ድኅረ ተሰብረ አጽንዖ ለሰብእናነ ልሕኵት፥ ለብሓዊ ክርስቶስ በማየ ሐዲስ ጥምቀት" የምትል ድንቅ የንጉሥ ጉባኤ ቃና አለች፡፡ ግርድፍ ትርጉሟ፦ ገላ'ችን ከተሰበረ በኋላ ሸክላ ሠሪው ክርስቶስ በአዲስ የውኀ ጥምቀት እንደገና ሠራው፡፡ ማለት ነው፡፡ ቤተክርስቲያን ከጌታዋ የተማረችው የተሰበረን መጠገን ነው፡፡
ችግሩ፥ መጠገን እንደመስበር ቀላል አይደለም፡፡ ለመጠገን ዕውቀትና ቅንነት ያስፈልጋል፡፡ ለመስበር ግን ኦርቶዶክሳዊ የዘብነት ቀለም የተቀባች ምላስ በቂ ናት፡፡
ወንድሞች በጎ ሲሠሩ እናበርታ፡፡ሲስቱ እንክርዳድ ከስንዴ እየለየን በፍቅር እናርም፡፡አልታረምም የሚል ካለ ደግሞ የቤክርስቲያን ቱንቢ ያርመዋል፡፡እንደ ግለሰብእ እኔ ነኝ ቱንቢው ማለት ግን የስሕተት ስሕተት ነው፡፡
በየሚዲያው ሌሎች ጥሩ ወንድሞችም አሉ፡፡ ነገር ግን በልዩ ልዩ የቤተክርስቲያን አገልግሎት የተገለጡ ናቸውና ተውኳቸው፡፡
ሊቀ ሊቃውንት ስሙር አላምረው እንደጻፉት


መድኃኔዓለም ለእኛ!

ቤዛችን
አዳኛችን
ታዳጊያችን
የፀጋ አባታችን
የሕይወት ውሃችን
የጸናንበት ግንዳችን
የዘላለም ሕይታችን
የማይናወጽ ዓለታችን
የቤተ ክርስቲያን ራሳችን
አንድ ጊዜ የተሰዋ በጋችን
በሥጋ የተገለጠ ምላካችን
የማይታክት ትጉህ እረኛችን
ለክርስትናው አኗኗር አርአያችን
በአምሳሉ የፈጠረን ፈጣሪያችን
ሌባ የማይሰርቀው መዝገባችን
በጨለማ ውስጥ ያለ ብርሃናችን
መስዋዕቱን አቅራቢ ሊቀ ካህናችን
ከራሱ ጋር ያስታረቀን አስታራቂያን ነው።


መማር ጥሩ ነው ወዳጆቼ




አመ ፳ወ፯ ለጥር – በእንተ ሰማእታት ዘምድረ ሻሸመኔ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አመ ፳ወ፯ ለጥር በዛቲ ዕለት ውኅዘ ደመ ሰማእታት በምድረ ሻሸመኔ በመዋዕሊሁ ለዐቢይ አህመድ ወውእቱ ንጉሥ ኮነ ዘያሌዕል ርእሶ እምኩሉ ሰብእ ወይብል አንሰ ባህቲትየ አአምሮ ለኲሉ ነገር ወበመዋዕሊሁ ኮነ አቢይ ስደት በቤተክርስቲያን ወተቀትሉ ምእመናን ወምእመናት ዘየአምኑ በክርስቶስ ዘእንበለ ሙስና ዳእሙ በእንተ ኃይማኖቶሙ

ወተንስኡ ፫ቱ ጳጳሳት ተላውያነ ንጉሥ እንዘ ይብሉ ንህነሰአ ኢንትዌከፍአ ትእዛዘ ቅዱስ ሲኖዶስ ወንሠይምአ ኤጲስ ቆጶሳተአ እምነገደ ዚአነአ ወእሙንቱሰአ እምድኅረ ተሠይሙአ ይረድኡነአ ከመ ናማስናአ ለቤተክርስቲያንአ ወንሬሲአ ስዒረ ሲኖዶስአ ወንጉሥሰአ ሀሎአ ምስሌነአ መኑአ ይከልአነአ ወዘንተ ብሂሎሙ ኃረዩ መነኮሳተ ዘይትኤመሩ በብዙኅ ነውር ወቦ እምኔሆሙ ዘአውሰበ ብእሲተ ወቦ እምኔሆሙ ዘኢየአምን በክርስቶስ ወቦ እምኔሆሙ ሰራቂ ወቦ እማእከሎሙ ዘማዊ ወሰራቂ ወተማከሩ ምስለ መሳፍንተ ሀገር ወሤምዎሙ በህቡዕ ዘእንበለ ሥርዓት ወህግ ወወሀብዎሙ አስማተ ቅዱሳን ክቡዳተ ዘኢይደሉ ለግብሮሙ

ወሶበ ሰምዑ ሊቃነ ጳጳሳት ተጋብዑ ፍጡነ በጉባዔ ሲኖዶስ ወአውገዝዎሙ ለእልክቱ አማሳንያነ ሥርአት ወህግ ወሶበ ሰምዐ ንጉስ ተምአ ጥቀ ላእለ ቤተክርስቲያን ወላእለ አበው ወተናገረ እንዘ ይብል አነ ብዙኃ ሠናየ ነገረ ገበርኩ ለቤተክርስቲያን ወበእንተዝ ስምዑኒ ወተዐረቁ ፍጡነ ምስለ ሠዐርያነ ሲኖዶስ ወተወከፍዎሙ ለዘተሠይሙ ወሶበ ሰምዑ ዓበው ጳጳሳት ብህሉ ከመዝ ንህነሰ ኢተፃባእነ ምስለ አሀዱ ሰብእ ባህቱ ሐሎነ ህግ ወሥርአት ዘተወከፈሰናሁ እምሐዋርያት ወእምሊቃውንት ወለእመ ተመይጡሰ በህግ ወበሥርአት ንትዌከፎሙ በንስሀ ወበትእዛዘ ንጉሥሠ ኢንገብሮ ለዝንቱ ዳእሙ በትእዛዘ አምላክነ።

ወንጉሥሠ ተቆጥአ ወይቤሎሙ ለመኳንንቲሁ ኢትግበሩ ምንተኒ ግብረ ሶበ ይመጽእ ሀውክ ላዕለ ቤተክርስቲያን ወእምድህረ ዝንቱ ዕለት በዝኀ መከራ ላዕለ ቤተክርስቲያን ወእሙንቱ ጳጳሳተ ሐሰት ገብሩ ብዙኃ ኃጢአተ ወሞቅህዎ ለአባ እስጢፋኖስ ወሰደድዎ እመንበሩ ዘትሠመይ ጅማ ወለአባ ያሬድኒ ከማሁ ሰደድዎ እመንበሩ ዘስማ አርሲ ወቦኡ በኃይል ምስለ መንገኒቅ ኃበ መንበረ ጵጵስናሆሙ ለአባ ናትናኤል ወለአባ ሩፋኤል ወመዝበሩ ብዙኃ ንዋያተ ቅዱሳተ ዘቤተክርስቲያን ወወኃብዎሙ ለሐራ ንጉሥ ወሖሩ ኃበ ሻሸመኔ ከመ ያብዕዎ ለአሀዱ ጳጳሰ ሐሰት ዘስሙ ገብረ እግዚአብሔር ወግብሩ እኩይ ወሰብአ ሻሸመኔሰ ከልሁ እንዘ ይብሉ አሐቲ ቤተክርስቲያን አሐዱ ሲኖዶስ ወአሐዱ መንበር ወመጽአ ተአጊቶ በብዙኅ ሰራዊት ኃበ ሻሸመኔ ወሖረ ሐበ ቤተክርስቲያኑ ለቅዱስ ሚካኤል ወብዙኃን ሰብእ ሐለዉ እንዘ ይፄልዩ ወይዜምሩ ወሶበ በጽሐ ዝንቱ እኩይ ኃበ ከኒሳ ወከልእዎ ምእመናን ከመ ኢይባእ እንዘ ይጠቅዑ መጥቅዐ ወሶቤሀ ተምዑ ወዐልያነ ንጉሥ ላእለ ህዝበ ክርስቲያን ወቀተልዎሙ ለምእመናን በመንገኒቅ ወብዙኃን ኮኑ ሰማእተ ወኃበ ቤተክርስቲያኑ ለተክለሃይማኖትኒ ከማሁ ቀተልዎሙ ወአቁሰልዎሙ ለክርስቲያን ወሰማእተ ኮኑ በእንተ ጽድቅ ወበእንተ ክርስቶስ በረከቶሙ ተሀሉ ምስሌነ ወኪያነሂ ይምሀረነ በፀሎቶሙ ለሰማዕታት ወየሀብ ሰላመ ለቤተክርስቲያን ለዓለመ ዓለም አሜን

ሰላም ሰላም ለሰማዕታት ኩሎሙ
በእንተ ከኒሳ ቅድስት እለ ከአዉ ደሞሙ
ሶበ መጽአ ሐሳዊ ሀበ ሻሸመኔ ምድሮሙ
ኢፈርህዎ ለመንገኒቅ ወተወክፍዎ በፍጽሞሙ
እንዘ ይኄልዩ ገነተ ርስቶሙ

በመሪጌታ Birhanu Tekleyared የተዘጋጀ

✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥

ጥር 27 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

1. ቅዱስ ኄኖክ ነቢይ (ወደ ብሔረ ሕያዋን ያረገበት)
2. ቅዱስ ጢሞቴዎስ ሐዋርያ (ፍልሠቱ)
3. ቅዱስ አባ ቢፋሞን ሰማዕት
4. ቅዱስ ሰራብዮን ሰማዕት
5. ቅዱስ ሱርያል ሊቀ መላዕክት (ከሰባቱ ሊቃናት አንዱ)

ወርኀዊ በዓላት

1. መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ
2. አቡነ መባዐ ጽዮን
3. አባ መቃርስ ርዕሰ መነኮሳት
4. ቅዱስ ገላውዴዎስ ሰማዕት (ንጉሠ ኢትዮጵያ)
5. ቅዱስ ፊቅጦር ሰማዕት
6. ቅዱስ ያዕቆብ ዘግሙድ
©ጴጥሮስ አሸናፉ



20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.