ማስታወቂያ…
• ጌዴዎናዊነት አሸናፊነት ነው።
"…ዛሬ ምሽት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ "ነጭ ነጯን ከዘመዴ ጋር" የተሰኘው ዝነኛ መርሀ ግብራችን በቴሌቭዥን እስክንከሰት በቲክቶክ ይዤላችሁ እቀርባለሁ።
• ከእውነት ጋር በቁርባን በቃልኪዳን ተጋቡ። ከእውነት ጋር ከተጋቡ በኋላ መፋታት ነውር ነው። ኃጢአትም ነው።
"…ሥራ ልሥራ ካላችሁ አንዲት የስልክ ስታንድ፣ አንዲት ቀላል ስልክ እና የኢንተርኔት ኔትውርክ ካለ በቂ ነው። ከአጠገብህ ምስለ ፍቁር ወልዳ፣ መጽሐፍ ቅዱስ፣ ድርሳነ ሚካኤል፣ በኩባያ ውኃ፣ የማስታወሻ ደብተር ትይዛለህ ከዚያ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንደበትህ ላይ ሆኖ እንዲናገር መፍቀድ፣ ኃይሉን፣ ጽናቱን፣ ብርታቱንም፣ ዕወቀትንም ይገልጽልህ ዘንድ መማጸን ነው። ከዚያ ከዚያማ እርሱ ሥራውን ሲሠራብህ ማየት ነው።
• እውነት እግዚአብሔር ነው። እግዚአብሔር ደግሞ አሸናፊ ነው።
"…የ EBC, FANA, WALTA, EBS, ወዘተ ሚዲያዎች ዓመታዊ በጀታቸው ከፍያለ፣ ካሜራዎቻቸው ውድ፣ የሰው ኃይላቸው ብዙ፣ ከማስታወቂያ ገቢ ያገኛሉ። የሠራተኞቻቸው ደሞዝ የማይቀመስ ነው።
"…ወደ እኔ ወደ ዘመዴ ስቱዲዮ ስንመጣ ግን ወፍ የለም። የስቱዲዮ ካሜራ፣ መብራት፣ ኮምፒዩተር፣ ኤዲተር፣ ዳይሬክተር፣ ሹፌር፣ ጸሐፊ፣ አርታኢ፣ በጀት፣ ደሞዝ፣ ቦነስ ብሎ ነገር የለም። እንደ ሶምሶን ብቻህን ትቆማለህ እግዚአብሔርን ይዘህ ግን ሺ ዉን በአህያ መንጋጋ።
• ጌዴዎናዊነት ደ አሸናፊነት ነው።
"…እንደ አማሪካው FOX ተለቭዥን ጣቢያ ያለ ተቋም መገንባት፣ በ300 የጌድዮን ሠራዊት ብቻ ምድያማውያንን ማሸነፍ ይቻላል። አንተ ፈቃደኛ፣ ታዛዥ፣ ከእውነት የተጣበቅህ ሁን እንጂ እግዚአብሔር ልሥራብህ ካለ አለ ነው አንዱን አንተ ብዙ አድርጎ ይሠራብሃል።
• አይደለም እንዴ…?