አማርኛ አባባሎች


Гео и язык канала: Эфиопия, Английский
Категория: Другое


Contact Us: @YaadafiGaaffii_bot
Contact me: @Getu_Abera

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Английский
Категория
Другое
Статистика
Фильтр публикаций


#41 ✍️

1. ድንኳን ገልጦ ዙፋን ረግጦ
2. ያላዋቂ ቆራሽ ማእድ አበላሽ
3. ነቢይ ባገሩ አይከበርም
4. ያላስደጉት ውሻ ቤት ዘግተው ቢመቱት ዞሮ ይናከሳል
5. ሳይጠሩት አቤት የሰይጣን ጎረቤት

@amharic_proverb


Репост из: SPEAK ENGLISH
❤️ ✍️ "Miira jaalalaa namatti dhaga'amu parsantiin 70% maal akka ta'e beektuu?...." ➡️ As tuquun dubbisaa.

🔜 See More
See More


#40 ✍️

1. ድንኳን ገልጦ ዙፋን ረግጦ
2. ያላዋቂ ቆራሽ ማእድ አበላሽ
3. ነቢይ ባገሩ አይከበርም
4. ያላስደጉት ውሻ ቤት ዘግተው ቢመቱት ዞሮ ይናከሳል
5. ሳይጠሩት አቤት የሰይጣን ጎረቤት

@amharic_proverb


#39 ✍️

1. ለብልህ አይነግሩ ላንበሳ አይመትሩ
2. ቁም እንዳላማ ጥልቅ እንደጫማ
3. የሚያጠግብ ቂጣ ከምጣዱ የሚወጣ ጥጃ ከገመዱ ያስታውቃል
4. ሚስቱ ክፉ ባቄላ እራቱ ብሳና እንጨቱ ሀዘን ነው እቤቱ
5. ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ

@amharic_proverb


#38 ✍️

1. ያልዘሩት አይበቅልም
2. መልኳ ባያምር አመሏ ይመር
3. ጆሮ ካያት ያረጃል
4. እውነት ትዘገያለች እንጂ አትቀርም
5. የልቡን ሲነግሩት የኮረኮሩትን ያህል ይስቃል

@amharic_proverb


#37 ✍️

1. እኩሉ በዶሮ እኩሉ በሽሮ
2. አማርኛ አባባሎች:
3. እጅና አፍ አይተጣጡም
4. የማይመለስ ማር ሹመኛ ይበደረዋል
5. ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም

@amharic_proverb


#36 ✍️

1. ሁለት እግር አለኝ ብሎ እሁለት ዛፍ አይወጣም
2. የሞኝ ዘፈን ሁልጊዜ አበባዬ
3. የሚበጀውን ባለቤት ያውቃል
4. ክረምትን የፈጀ በጋ እዳውን የፈጀ ዜጋ
5. ለሰው ብሎ ሲያማ ለእኔ ብለህ ስማ

@amharic_proverb


#35 ✍️

1. ቀን ከጣለው ሁሉ ይጥለው
2. ሳይተርፋት አበድራ ሳትቀበል ሞተች
3. ያሉሽን በሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ
4. ዘር ልትበደር ሂዳ እህል ሲሸት መጣች
5. በቆፈሩት ጉድጓድ መቀበር አይቀርም

@amharic_proverb


#34 ✍️

1. ያልሰጡት ተቀባይ ያልጠሩት አቤት ባይ
2. የላጭን ልጅ ቅማል በላው ያናጢን ልጅ ጅብ በላው
3. እከክን ያመጣ ጥፍርንም አላሳጣ
4. ሞኝ ሲስቁበት የሳቁለት ይመስለዋል
5. ያልቆረጠ እግብ አይደርስም

@amharic_proverb


#33 ✍️

1. ለእባብ እግር የለው ለሞኝ መላ የለው
2. ተልባ በጥባጭ እያለች ጎመን ቀንጣሹዋን ምች መታት
3. ቢጠሩሽ አትሰሚ ቢጠቅሱሽ አታዪ ረጋ ብለሽ ሂጂ ብር ብር አትበዪ
4. ሆዱ ፈሪ እግሩ ዳተኛ አዳም ሲዋጋ እርሱ ይተኛ
5. ከምድር ውስጥ ልቃቂት አይወጣም

@amharic_proverb


#32 ✍

1. በእጅ ያለ መዳብ እንደወርቅ ይቆጠራል
2. ፍየል በልታ በበግ አበሰች
3. ሂድ ካገር ኑር ካገር
4. ቅንድብ ለአይን ጥቅሻ አስተማረች
5. ፈሪ ቢሸፍት እስከ ጓሮ

@amharic_proverb


#31 ✍️

1. የምላስ ጦር ቢታከም አይድንም
2. እውር ምን ይሻል ብርሀን ነጋዴ ምን ይሻል መዳን
3. ነገር ከመጀመሪያው እህል ከመከመሪያው
4. ያወቀ ዘለቀ ያላወቀ አለቀ
5. ዳኛ ሲቆጣ ማር ይዞ ከደጁ

@amharic_proverb


#30 ✍️

1. ቀን ሲደርስ አምባ ይፈርስ
2. የማይጣሉ መላእክት የማይታረቁ አጋንንት
3. ፈጣሪን የሚያህል ጌታ ገነትን ያህል ቦታ
4. ጠርጥር በገንፎ ውስጥ እንዳለ ስንጥር
5. ደስታና መከራ ቀኝና ግራ

@amharic_proverb


#29 ✍️

1. የደላው ወርቅ ያስራል
2. ለሀጥአን የወረደ ለጻድቃን ይተርፋል
3. ካልደፈረሰ አይጠራም ካልጠራ አይጠጣም
4. ጥጋበኛ ከርከሮ የነፍጠኛ ጎጆ ይታከካል
5. የሚያፈስ ቤት ጨቅጫቃ ሚስት

@amharic_proverb


#28 ✍️

1. ዱባ ባገሩ ጋን ያህላል አሉ
2. ደካማ ቀበሌ በአህያ ይወረራል
3. ተይዛ ትዘፍን ጦጣ
4. እንኳንስ ዘንቦብሽ እንዲየውም ጤዛ ነሽ አሉ እትዬ ዘነቡ
5. ያለ ጎረቤት ቡና ያለ ሙያ ዝና

@amharic_proverb


#27 ✍️

1. እውር ተመሪው ሞኝ ተመካሪው ይጣላል
2. ያጣ ሰው ያገኝ አይመስለውም
3. የማይነጋ መስሏት እቋቱ ላይ አራች
4. እንደ ገና ይመታል በገና
5. ተፈጣሪ ሙርጥ ጫሪ

@amharic_proverb


#26 ✍️

1. የማታ ማታ እውነት ይረታ
2. ሁለተኛ ግፌ ጫንቃዬን ተገርፌ ልብሴን መገፈፌ
3. እዛም ቤት እሳት አለ
4. የልጅ ብልጥ እየቀደመ ይውጥ
5. ቁርጥማት ቢያብር አልጋ ላይ ያማቅቃል

@Amharic_Proverb


#25 ✍️

1. የሽማግሌ ፍቅር እና የክረምት አበባ አንድ ነው
2. ሽታና ግማት ላልሰማ ማውራት
3. ሴት ከጠላች በቅሎ ከበላች አመል አወጣች
4. በአደባባይ ወተት በቤት ውስጥ ጉጠት
5. ለተሾመ ይመሰክሩለታል ለተሻረ ይመሰክሩበታል

@amharic_proverb


#24 ✍️

1. የሽማግሌ ፍቅር እና የክረምት አበባ አንድ ነው
2. ሽታና ግማት ላልሰማ ማውራት
3. ሴት ከጠላች በቅሎ ከበላች አመል አወጣች
4. በአደባባይ ወተት በቤት ውስጥ ጉጠት
5. ለተሾመ ይመሰክሩለታል ለተሻረ ይመሰክሩበታል

@amharic_proverb


#23 ✍

1. የባሪያ ደግ የቁልቋል ዘንግ የለውም
2. ቆማጣን ቆማጣ ካላሉት ገብቶ ይፈተፍታል
3. ተመርቄያለሁ ብለህ ከተረገመ አትዋል
4. እንጨት አይሸከሙም ላመድ አሮጊት አያገቡም ላትወልድ
5. ጀምበር ሳለ እሩጥ አባት ሳለ አጊጥ

@Amharic_proverb

Показано 20 последних публикаций.