የትኩረት ጉልበት!• ችግሩ እያለ፣ ትኩረታችንን ትክክለኛውን መፍትሄ መፈለግ ላይ ስናደርግ . . .
• ፍርሃቱ እያለ፣ ትኩረታችንን በጥንቃቄ ወደ ፊት በመራመድ አልፎ መሄድ ላይ ስናደርግ . . .
• የሰዎች ክፋት እያለ፣ ትኩረታችንን ስናስባቸው የሚያበረታቱን ጨዋ ወዳጆቻችን ላይ ስደርግ . . .
• የተለወጠብን ሰው እያለ፣ ትኩረታችንን አብሮነቱ የማይለዋወጠው ሰው ላይ ስናደርግ . . .
• ያልተሳካው ነገር እያለ፣ ትኩረታችንን የተሳካው ላይ እና ወደ ፊትም ሰርተን የምናሳካው ነገር ላይ ስደርግ . . .
• ስህተትና ስህተቱ ያስከተለው ጉዳት እያለ፣ ትኩረታችንን ከስህተቱ ያገኘነው የእድሜ ልክ ትምህርት ላይ ስናደርግ . . .
• በምርጫ ግራ መጋባቱ እያለ፣ ትኩረታችንን ምንም ምርጫ የሌለው ኑሮ ከሚኖሩ ሰዎች የመሻላችን ሁኔታ ላይ ስናደርግ . . .
ኃይላችንን እቆጥባለን፣ ነገን ለመጋፈጥ ጉልበት እናገኛለን፣ በሆነ ባልሆነው ግራ አንጋባም፣ ከልክ ካለፈ የሃሳብ ግልቢያ (overthinking) ረገብ እንላለን፡፡
የትኩረት ለውጥ እናድርግ!
@MarsilTvWorldWide