Ethiopian university️


Гео и язык канала: Эфиопия, Английский
Категория: Telegram


Welcome to Ethiopian University!
🌍📚 Your go-to channel for educational resources, study tips, and academic insights tailored for Ethiopian students. Join us to enhance your learning journey....
@ethioacadamic
ለጥቆማ
@Jesuschristbe
@educationbe

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Английский
Категория
Telegram
Статистика
Фильтр публикаций




ዛሬ በተጀመረው የ2017 ዓ.ም. የመጀመሪያው ዙር የመውጫ ፈተና ተንቀሳቃሽ ስልኮችን በተለያየ መንገድ ይዘው ለመግባት የሞከሩ በርካታ ተፈታኞች ወድያው ከፈተና ውጭ መደረጋቸውን ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


ተፈታኞች ከመሰል አስነዋሪ ድርጊቶች ራሳችሁን ጠብቁ ‼️


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news














የሐኪሞች የስራ አጥነት ቁጥር እየጨመረ ከመምጣቱ በተጨማሪ በተለያዩ በሽታዎች ተይዘው የህይወት ዋጋ እየከፈሉ ነዉ ተባለ፡፡

በህክምና የተመረቁ ስራ አጥ የህክምና ባለሙያዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር አስታዉቋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ሐኪሞች ተገቢውን ሕክምና በፍጥነት ባለማግኘታቸው የሕይወት ዋጋ እየከፈሉ ይገኛሉ ተብሏል፡፡

ማህበሩ ሀኪሞች ብዙ ጫናዎችን ተቋቁመው ስራ እየሰሩ ቢሆንም የሰሩበትን የትርፍ ሰዓት ክፍያ ሳይከፈላቸዉ የሚቆዩባቸዉ ክልሎች መኖራቸዉን አንስቷል፡፡

ክፍያ የሚጠይቁ ሐኪሞችም ለእስር የሚዳረጉበት ሁኔታዎች የታዩበት ዓመት ነበር ሲል ማህበሩ ገልጿል፡፡

እንደሕክምና ማህበር ከሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎች ጋር ምክክር ለማድረግ ቢሞከርም፤ አሁንም ከችግሩ ስፋት አንጻር ለብዙዎች ችግር ምላሽ መስጠት አልተቻለም ነዉ ያለዉ፡፡

ከዚህ ቀደም ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉት የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተግባር ይግዛዉ ፤ በአገራችን ያሉ የሀኪሞች ቁጥር ወደ 17ሺህ ነዉ ያሉን ሲሆን፤ ከዚህ መሃል ወደ 40 በመቶ የሚሆነዉ ወይም 1ሶስተኛዉ ብቻ የማህበሩ አባል መሆኑን አንስተዋል፡፡

የሙያ ማህበር መቅጠር አይችልም ፤ማድረግ የሚችለዉ ጉዳዩን ማሳወቅ ነዉ ያሉት ዶ/ር ተግባር፤ከጤና ሚኒስቴርም ሆነ ከክልል ጤና ቢሮዎች ጋር በጉዳዩ ላይ መነጋገራቸዉን በወቅቱ አንስተዉ ነበር፡፡

ዘንድሮ 61ኛውን ዓመታዊ የሕክምና ጉባኤና ዓለም አቀፍ የጤና አዉደ ርእይ ከየካቲት 14 – 15/2017ዓ.ም ለማካሄድ ማቀዱንም ማህበሩ አስታዉቋል፡፡
በጉባዔዉ በሃገር ውስጥ እና በውጭ ሃገር የሚኖሩ የህክምና ባለሙያዎች ያላቸውን እውቀት፣ የምርምር ግኝቶችን እና የህክምና ልምዶችን በማቅረብ የዓመቱን መሪ ቃል መነሻ በማድረግ የፓናል ውይይቶች እንደሚካሄዱም ለማወቅ ችለናል፡፡

ማህበሩ ከተመሰረተበት 1940 ዓ.ም ጀምሮ በህክምና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራት፣ ደህንነት እና በአጠቃላይ በህክምናው ዘርፍ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

#EthioFM
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news


በ2017 ዓ.ም አጋማሽ ላይ የሚሰጠውን የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና ለመውሰድ 176 ሺህ ተማሪዎች ተመዝግበዋል።

ፈተናውን በድጋሚ የሚወስዱትን ጨምሮ በጠቅላላው 176 ሺህ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን እንደሚወስዱ ይጠበቃል።

ፈተናው በኢትዮጵያ በሚገኙ በሁሉም የኒቨርሲቲዎች የሚሰጥ ሲሆን፤ ተጠሪነቱ ለትምህርት ሚኒስቴር ያልሆነው የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ውስጥም እንደሚሰጥ በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዬች መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ለአሐዱ ራዲዮ ተናግረዋል።

የግል ኮሌጅ ተማሪዎችም በመረጡትና በአቅራቢያቸው በሚገኝ የመንግስት ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ፈተናቸውን ይወስዳሉ ብለዋል።

@tikvahuniversity


#ExitExamSchedule

ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከጥር 26-30/2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡

የፈተናው ሙሉ መርሐግብር (የሚሰጡ ፈተናዎች ዝርዝር፣ የፈተና ቀንና ሰዓት፣ የመፈተኛ ማዕከላት እንዲሁም የተፈታኞች ዝርዝር) ከላይ ተያይዟል፡፡

እሑድ የካቲት 2/2017 ዓ.ም ጠዋት የኢኮኖሚክስ ትምህርት የመውጫ ፈተና በአምቦ እና በወለጋ ዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥም መርሐግብሩ ያሳያል፡፡

@tikvahuniversity




#ExitExamSchedule #AAU

ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከሰኞ ጥር 26/2017 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ይታወቃል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ለመፈተን የተመዘገባችሁ የፈተናው የመጀመሪያ ሁለት ቀናት መርሐግብር (ጥር 26 እና 27/2017 ዓ.ም) ከላይ ተያይዟል።

@tikvahuniversity


Management Exit Exam Full Day Schedule.xlsx
308.8Кб
Management Exit Exam Full Day Schedule; AAU
Tuesday February 04, 2025 (ጥር 27/2017 ዓ.ም)


Accounting Exit Exam Full Day Schedule.xlsx
301.5Кб
Accounting Exit Exam Full Day Schedule; AAU
Monday February 03, 2025 (ጥር 26/2017 ዓ.ም)


Next we will post exit exam all department's exam





Показано 18 последних публикаций.