#እየበረታ_ሔደ
#የሳምንቱ_ባርኮት
ሀልዎት_ቴሌግራም_ፋሚሊን_ለመቀላቀል! 👇
https://t.me/+aNnOeU8qkoA5ZTE8ሀልዎት_ቴሌግራም_ቻናልን_ለመቀላቀል👇
https://t.me/halwotchurch🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐
📖 ትንቢተ ሚክያስ 7: 7
እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር እመለከታለሁ፥ የመድኃኒቴንም አምላክ ተስፋ አደርጋለሁ፤ አምላኬም ይሰማኛል።
🖐 እግዚአብሔር ይስማችሁ፣ ከመቅደሱ ረድኤትን ይላክላችሁ፣ በጸሎት ቤቱ ደስ ያሰኛችሁ፣ አምላኬ ጣልቃ ይግባልኝ በምትሏቸው ሁሉ እግዚአብሔር ይድረስላችሁ፣ ፊቱን ያብራላችሁ፣ ቶሎም ይምጣላችሁ፣ እግዚአብሔር ፍርድን፤ ፍትህን በህይወታችሁ ያድርግላችሁ፣ በቤታችሁ፤ በኑሮ፤ በትዳር ህይወታችሁ ሁሉ የአምላክ ፍርድ፤ የአምላክ ጣልቃ ገብነት ይሁንላችሁ
🖐 ሌላ የላችሁምና፤ እግዚአብሔር የህይወታችሁ ብቸኛ ነውና እርሱን አሁንም ተስፋ በማድረግ ተባረኩ፣ አይኖቻችሁ እርሱን ብቻ በማየት ይባረኩ፣ እግዚአብሔርን ብቻ በመስማት ጆሮዎቻችሁ ይባረኩ፣ ደጁንም በመጥናት፤ በፊቱም በመቆየት ጉልበቶቻችሁ ይባረኩ፣ የእግዚአብሔር ደግነት በላያችሁ ላይ ይሁን፣
🖐 አምላኬ ዝም አለኝ እኮ፣ አምላኬ አልመለሰልኝም፤ አምላኬ ይሔ ጉዳይ ከእኔ ጋር እንዲቆይ እኮ ሆነ፤ አልመጣልኝም በምትሉት ጉዳይ ላይ ሁሉ የአምላክ ርህራሔ፤ የአምላክ መምጣትና የአምላክ መድረስ በቤትና በህይወታችሁ ይሁንላችሁ፣ ደግነቱን፤ ርህራሔውን ያብዛላችሁ አሁንም በጨለማችሁ ብርሀን ይሁንላችሁ፣ በጠላቶቻችሁ ላይ እግዚአብሔር መቅሰፍትና ማስፈራትን ይላክላችሁ፣ በወደቃችሁበት ላይ መነሳት ይሁንላችሁ፣ ፊቱን በመናፈቅ፤ እሱን በመጠባበቅ ባሉ ጉዳዮቻችሁ ሁሉ ላድ ደግሞ አምላካዊ መልስ በቤታችሁ ይሁን
🖐 የተባረኩ ቀኖችና ሳምንት በማሳለፍ ተባረኩ፣ እግዚአብሔር በነገር ሁሉ ይርዳችሁ፣ የአምላኬ ምህረትና ደግነት በእናንተ ላይ ትሁን፣ የከበደ ይቅለላችሁ፣ አምላክ ጥያቄዎቻችሁን ሁሉ ይመልስ፣ እሱ ስለናንተ ያውቃል፤ እሱ ስለናንተ ያስባልና በሚያስፈልጋችሁ ጊዜ ደግሞ ከአምላክ ዘንድ እርዳታ ይሁንላችሁ፣ ደጁን በመጥናት ተባረኩ፣ ፊቱ በመቆየት ተባረኩ፣ አይኖቻችሁ ወደሱ ብቻ በመመልከት ተባረኩ፣ ልባችሁ እርሱን ብቻ ተስፋ በማድረግ እግዚአብሔር በዚህ ይባርካችሁ፣ ደግነቱ ይብዛላችሁ🙏
🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐🖐
በኢትዮጵያ አማኑኤል ኅብረት ቤተ ክርስቲያን ሀልዎት አጥቢያ
አድራሻ፦ ወሎ ሰፈር ጎርጎሪዮስ አደባባይ ፊውቸር ታለንት ት/ት ቤት አጠገብ
☎️ +251118633493 📱+251 973 422024